STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
40.9K subscribers
11K photos
271 videos
452 files
1.93K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
#MekelleUniversity

መቐለ ዩኒቨርሲቲን ወደ ቀድሞ ልኽቀቱ ለመመለስ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ገለጸ፡፡

ዩኒቨርሲቲው ከወራት በኋላ በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ ባወጣው መልዕክት፤ የተቋሙን ልኽቀት ለመመለስ የሁሉንም የትብብር ድጋፍ ጠይቋል፡፡

ባለፉት ሁለት አስቸጋሪ ዓመታት በሀሳብ እና ድጋፍ ከዩኒቨርሲቲው ጋር አብረው ለነበሩ ዓለም አቀፍ አጋሮች፣ የዩኒቨርሲቲው የቀድሞ ተማሪዎች እና የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ አስተዳደሩ ምስጋና አቅርቧል፡፡

ተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
Photo
#MekelleUniversity

ትግራይ ያሉ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ ቀደመው የመማር ማስተማር ስራቸው ለመመለስ ከፍተኛ ርብርብ እያደረጉ ይገኛሉ።

ከነዚህም ውስጥ የኣክሱምና ራያ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ተመድበው መማር ያልቻሉ ተማሪዎች በአጭር ቀናት ውስጥ በስልክ እየደወሉ እንዲመዘገቡ ጥሪ አቅርበዋል።

ለማስታወሻ ፦ https://t.me/tikvahethiopia/77964

የመቐለ ዩኒቨርሲቲ በተመሳሳይ ለሁሉም በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ላልተመደቡ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ጥሪ አቅርቧል።

ዩኒቨርስቲው በጦርነቱ ምክንያት ትምህርት ያቋረጡ የመጀመርያ ዲግሪ ተማሪዎች ቀጥሎ የተቀመጡትን መረጃዎች ከሚያዝያ 16-20/2015 ዓ.ም. ባሉት የስራ ሰዓታት ብቻ ከታች በተቀመጡት ስልክ ቁጥሮች በመጠቀም መረጃዎች እንዲያቀብሉ ጠይቋል።

ተፈላጊ መረጃዎቹ ምንድናቸው ?

👉 ሙሉ ስም
👉 የመታወቅያ ቁጥር
👉 ትምህርት ክፍል
👉 የስንተኛ ኣመት ተማሪ መሆንዎ

እነዚህን መረጃዎች የመላኪያ ስልክ ቁጥሮች ፦

1. EiTM - 0984026089 / 0984026059
2. MIT - 0984026727
3. CHS - 0984023986
4. CVS - 0984024072
5. CLG - 0984023987
6. CSSL - 0984023985
7. CBE - 0984024069
8. IPHC - 0984025512
9. CDAaNR - 0984025593
10. CNCS - 0984025582
11. Other Universities - 0984025589

መቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የፅሁፍ መልእክቱን ሲልኩ #በእንግሊዘኛ እንዲልኩ አሳስቧል።

ዩኒቨርሲቲው በሌሎች የሀገራችን ዩኒቨርሲቲዎች ሲማሩ የነበሩና በጦርነቱ ምክንያት ያቋረጡ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች ከላት የተጠየቁትን መረጃዎች ፤ከዛ በተጨማሪ ሲማሩበት የነበረውን የዩኒቨርሲቲ ስም በማከል መረጃ እንዲያሳውቁ ጥሪውን አቅርቧል።

በሌላ በኩል ፥ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የድህረ ምረቃ ተማሪዎቹን በቅርብ ጊዜ እንደሚጠራ ገልጿል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#MekelleUniversity

መቐለ ዩኒቨርሲቲ በ2013 ዓ.ም በጦርነት ምክንያት ትምህርታቸውን አቋርጠውና በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች መቀጠል ያልቻሉ ተማሪዎቹ ለመቀበል ዝግጅት ማጠናቀቁን አሳውቋል።

በዚህም ተመራቂ ያልሆኑ ተማሪዎች ጥቅምት 05 እና 06/2016 ዓ.ም ትምህርታችሁን ስትከታተሉ በነበራችሁበት ግቢ እንድትገኙ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል፡፡

በ2013 ዓ.ም በአንደኛ ዓመት ተመድባችሁ በጦርነቱ ምክንያት ትምህርት ያልጀመራችሁ እንዲሁም አዲስ ገቢ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች የትምህርት ሚኒስቴር በሚያስቀምጠው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ጥሪ እንደሚደረገ ተገልጿል፡፡

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#MekelleUniversity

በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን በመቐለ ዩኒቨርሲቲ እንድትከታተሉ የተመደባችሁ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ጊዜ ከጥር 13 እስከ 15/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የምዝገባ ቦታ፦
የማኅበረሰብ ሳይንስ ተማሪዎች በዓዲ ሐቂ ግቢ፤ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በዋናው ግቢ (አርዲ)

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

የ8ኛ፣ 10ኛ እና 12ኛ ክፍል ሰርትፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ትራንስክርፕት ዋናውና ኮፒው፣
አራት 4x4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot