STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
39.7K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.94K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
ስለ አዲሱ የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ

አዲሱ የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ በሚንስትሮች ምክር ቤት ፀድቆ መውጣቱ ይታወሳል::

ፖሊሲው ፍትሀዊ አካታችና ተደራሽ ትምህርትና ስልጠና ለመስጠት፣ በስራ ገበያው ላይ ብቁና ተፈላጊ የሰው ኃይል ለማፍራት እንዲሁም ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና የስራ ፈጠራን ለማስፋፋት የሚደረገውን ጥረት በከፍተኛ ደረጃ ያግዛል::

ፖሊሲው ካካተታቸውና ጉልህ ለውጥ ከተደረገባቸው ጉዳዮች አንዱ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፍ ነው::

የቴክኒክና ሙያ ስልጠና የሙያ ደረጃ የእሴት ሰንሰለት ትንተናን ተከትሎ፣ ኢንዱስትሪውን አካቶ ፣ ተቋማት ከአካባቢያቸው ነባራዊ ሁኔታ ጋር አስተሳስረው ተግባራዊ እንዲያደርጉ (Zoning and Differentiation) አስቻይ ሁኔታ መፈጠሩ እመርታ ነው::

ስልጠናው ከፍተኛ ልምድ ያላቸው የኢንዱስትሪ ሙያተኞችን አሰልጣኞችን የሙያ ማህበራትን የአሰሪ ማህበራትን በማሳተፍ 70% ተግባር ተኮር ሆኖ በኢንዱስትሪ እና ተቋማት ትብብር መሰጠቱ በዘርፉ ከፍተኛ ውጤት ለማስገኘት ያስችላል::

የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ቀደም ሲል እስከ ደረጃ 5 ብቻ ተወስኖ የነበረው የሙያ እርከን እስከ ደረጃ 8 (3ኛ ዲግሪ አቻ) ማደጉ ለመስኩ የተሰጠው ከፍተኛ ትኩረት ውጤት ነው::

ዜጎች እንደየ ፍላጎታቸውና አቅማቸው ከ 1ኛ እስከ 8ኛ የሙያ እርከን ደረጃ መሰልጠን የሚችሉበት ምህዳር መፈጠሩ እራሳቸውን ከፍ ባለ የስልጠና ደረጃ ለማብቃት ለሚሹ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል:: በዚህም በደረጃ 1-2 (ሰርትፍኬት አቻ)፣ ደረጃ 3-4 (አድቫንስድ ዲፕሎማ አቻ) ፣ ደረጃ 5-6 (የመጀመሪያ ዲግሪ አቻ)፣ ደረጃ 7 (ሁለተኛ ዲግሪ አቻ) እና ደረጃ 8 (የፒኤችዲ/3ኛ ዲግሪ አቻ) ድረስ መስልጠን የሚችሉ ይሆናል::

ከከፍተኛ ትምህርት ወደ ቴክኒክና ሙያ እንዲሁም ከቴክኒክና ሙያ ወደ ከፍተኛ ትምህርት የመግባት እድልን የፈጠረ በመሆኑ ዜጎች ፍላጎትን መሠረት ያደረገ ሙያና ክህሎት እንዲኖራቸው ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል::

የሙያና ቴክኖሎጂ ትምህርት ከቅድመ አንደኛ ጀምሮ ለህጻናት ከእድሜያቸው ጋር እየተመጣጠነ መሰጠቱ አእምሮአቸው የዳበረ እጃቸው የተፍታታ ዜጎችን ለማፍራት ጉልህ አስተዋጽኦ አለው::

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#WolloUniversity

በ2015 ዓ.ም ወሎ ዩኒቨርሲቲ ለአቅም ማሻሻያ ትምህርት (Remedial Program) የተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ የመግቢያ ጊዜ 👉መጋቢት 4 እና 5/2015 ዓ.ም መሆኑን ዩንቨርሲቲው አስውቋል።

፨ተጨማሪ መረጃ ከምስሉ ይመልከቱ ‼️

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#ማሳሰቢያ

የማካካሻ ትምህርት ለመውሰድ በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ፦

እንጅባራ የካቲት 27 እና 28/2015 ዓ.ም ያደረገው የተማሪዎች ቅበላ 50% እና ከዚያ በላይ ላመጡ በቀጥታ ወደ ዩኒቨርሲቲ ለሚገቡ ተማሪዎች ብቻ ነው።

የማካካሻ ትምህርት ለመውሰድ የተመደባችሁ ተማሪዎች በአሁኑ ጥሪ ያልተካተታችሁ መሆኑን አውቃችሁ ወደ ፊት በማስታወቂያ እስከሚገለጽ ድረስ ባላችሁበት ሆናችሁ በትዕግስት እንድትጠባበቁ ዩኒቨርሲቲው ያሳውቃል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የ2015 ዓ.ም በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ Remedial Program ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ

በ2015 ዓ.ም ት/ት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ማለፊያ ውጤት ላላመጣችሁ እና ለአቅም ማሻሻያ (Remedia Program) አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ አዲስ ተማሪዎች መግቢያ ቀን 👉 መጋቢት 11-12/07/2015 ዓ.ም መሆኑን አውቃችሁ በተጠቀሰው ቀን በአካል ቀርባችሁ ሪፖርት እንድታደርጉ እያሳሰብን በምዝገባ ወቅት የ12ኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተና የወሰዳችሁበትን ማስረጃዎቻችሁን እና የመኝታ አልባሳት አሟልታችሁ እንድትገኙ እናሳስባለን፡፡

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
በ2015 ዓ.ም የማካካሻ ትምህርት (Remedial) ለመውሰድ በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ፦

የማካካሻ ትምህርት(Remedial) ለመውሰድ በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች መጋቢት 4 እና 5/2015 ዓ.ም የምዝገባ ጊዜ እንዲሁም መጋቢት 6/2015 ዓ.ም ትምህርት የሚጀምርበት ጊዜ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ማሳሰቢያ፡-
ተማሪዎች ለምዝገባ ሲመጡ
 የ8ኛ ክፍል ካርድ፣ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክርቢት እና የ12ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ፤
 ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፤
 3*4 የሆነ 4 ጉርድ ፎቶግራፍ እና
 አጋዥ የትምህርት መጽሓፍትን ይዘው መምጣት የሚችሉ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን፡፡
ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣን ተማሪ ዩኒቨርሲቲው የማያስተናግድ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የአቅም ማሻሻያ/Remedial Program/ ፕሮግራም ለመከታተል ከትምህርት ሚኒስቴር ወልድያ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ 👉 ከየካቲት 30/2015 ዓ.ም እስከ መጋቢት 01/2015 መሆኑን አውቃችሁ በተጠቀሱት ቀናት በአካል ተገኝታችሁ ምዝገባ እንድታደርጉ ዩንቨርሲቲው አሳውቋል።

፨ዝርዝር መረጃ ከምስሉ ይመልከቱ ‼️

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
አዲሱ የትምህርትና ሥልጠና ፖሊሲ

በሚኒስትሮች ም/ቤት የጸወቀው አዲሱ የትምህርትና ሥልጠና ፖሊሲ መምህራን የሚቀጠሩበትን መስፈርትን ጨምሮ በርካታ ጉዳዮችን ያሻሽላል።

በትምህርት ሚኒስቴር እና በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የተዘጋጀው አዲሱ ፖሊሲ፤ ለ28 ዓመታት ሲተገበር የቆየውን የትምህርትና ሥልጠና ፖሊሲ የሚተካ ነው።

ፖሊሲው የመምህራን የሙያ ደረጃን፣ የተማሪዎችን የክፍል ዕርከኖችን፣ በሥርዓተ ትምህርት የሚካተቱ ቋንቋዎችን እንዲሁም በርካታ የትምህርት ሂደቶችንና አሰራሮችን የሚቀይር መሆኑ ተገልጿል።

ከተደረጉ በርካታ ማሻሻያዎች መካከል የመምህራን የትምህርት ዝግጁነትና ደረጃዎች አንደኛው ሲሆን የቅድመ-አንደኛ የትምህርት ደረጃ ተማሪዎችን ለማስተማር አነስተኛው የትምህርት ደረጃ "ሰርተፊኬት" እንዲሆን ያዛል።

ከአንደኛ እስከ ስድስተኛ ክፍል ያሉትን ተማሪዎች ለማስተማር ደግሞ ዝቅተኛው የትምህርት ዝግጅት "ዲፕሎማ" እንደሚሆን ረቂቅ ፖሊሲው አስቀምጧል።

ከ7ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ድረስ ለማስተማር አነስተኛው የመምህራን የትምህርት ዝግጅት የመጀመርያ ዲግሪ እንዲሆን በረቂቅ ፖሊሲው ተቀምጧል።

በተመሳሳይ እስከ 8ኛ ክፍል ለሚገኙ አመራሮች ዝቅተኛው የትምህርት ዝግጅት የመጀመርያ ዲግሪ ሲሆን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አመራሮች ቢያንስ ሁለተኛ ዲግሪ የትምህርት ዝግጅት እንዲኖራቸው ይጠበቃል።

በተመሳሳይ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተቋማት አመራሮች ከቴክኒክ ክህሎት ባሻገር ቢያንስ ሁለተኛ ዲግሪ እንዲኖራቸው ረቂቅ ፖሊሲው ያዛል። #ሪፖርተር

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
አዲሱ የትምህርትና ሥልጠና ፖሊሲ | ቋንቋዎች

አዲሱ የትምህርትና ሥልጠና ፖሊሲ የቀየረው ሌላው ጉዳይ ቋንቋ ሲሆን ተማሪዎች በትንሹ ሦሥት ቋንቋዎችን እንዲማሩ ይደነግጋል።

ተማሪዎች የአፍ መፍቻ ቋንቋን እንደ ማስተማሪያና እንደ የትምህርት ዓይነት ከታች ጀምሮ ሲማሩ ቆይተው፣ የሚኖሩባቸው ክልሎች በሚወስኑት መሠረት ቋንቋዎቹ መሰጠት የሚኖርባቸው የክፍል ደረጃ ይታወቃል።

እንግሊዘኛ ቋንቋ ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ እንደ ትምህርት ዓይነት ይሰጥና እንደ ማስተማርያ ቋንቋ ደግሞ በአስገዳጅነት ከዘጠነኛ ክፍል ጀምሮ ይሰጣል።

ተማሪዎችና ወላጆቻቸው መርጠው ከፌዴራል የሥራ ቋንቋዎች ውስጥ አንድ ተጨማሪ የአገር ውስጥ ቋንቋ ከሦሥተኛ ክፍል እስከ አስረኛ ክፍል እንዲማሩ የሚደረግ ሲሆን አንድ ሌላ ተጨማሪ የውጭ አገር ቋንቋ ደግሞ ከዘጠነኛ ክፍል ጀምሮ እንደ አማራጭ ትምህርት ይሰጣል፡፡

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
አዲሱ የትምህርትና ሥልጠና ፖሊሲ | የትምህርት ዕርከኖች

ረቂቅ ፖሊሲው የትምህርት ዕርከኖችን ቅድመ አንደኛ ደረጃ፣ አንደኛ ደረጃ፣ መካከለኛ ደረጃ እና ሁለተኛ ደረጃ በማለት በአራት ይከፋፍለዋል።

የአንደኛ ደረጃ ዕርከን ከአንደኛ እስከ ስድስተኛ ክፍልን ያጠቃልላል። መካከለኛ ደረጃ ሰባተኛ እና ስምንተኛ ክፍልን ያካትታል። ሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ከዘጠነኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉትን ይይዛል።

የከፍተኛ ትምህርትን በሚመለከት የቅድመ ምረቃ በትንሹ አራት ዓመታትን እንደሚፈጅ፣ ሁለተኛ ዲግሪ ደግሞ ሁለት ዓመታትን እንደሚፈጅ እና የሦሥተኛ ዶክትሬት ዲግሪ ደግሞ አራት ዓመታትን እንደሚፈጅ ፖሊሲው ይገልጻል።

የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስምንት ደረጃዎች የሚኖሩት ሲሆን አሠልጣኞች ከመጀመርያ ዲግሪ እስከ ሦሥተኛ ዲግሪ ድረስ የትምህርት ዝግጅት እንዲኖራቸው ይጠበቃል።

ለደረጃ አንድ እና ሁለት የመጀመርያ ዲግሪ፣ ከደረጃ ሦሥት እስከ ስድስት የሁለተኛ ዲግሪ እንዲሁም ለደረጃ ሰባት እና ስምንት ደግሞ ሦሥተኛ ዲግሪ እንደመስፈርት ተቀምጧል።

የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት፣ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት እና የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት (እስከ ስምንተኛ ክፍል ያለው ትምህርት) በግዴታና በነፃ እንደሚሰጥ ረቂቅ ፖሊሲው አስቀምጧል። #ሪፖርተር

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
"ከ760 ሺህ በላይ ሠልጣኞች ወደ ቴክኒክና ሙያ ተቋማት ይገባሉ፡፡"
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር

በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 760 ሺህ 832 ተማሪዎች ወደ ቴክኒክና ሙያ ተቋማት ገብተው እንደሚሰለጥኑ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አሳውቋል።

በአገር አቀፍ ደረጃ 608 ሺህ የሚሆኑት ሰልጣኞች ወደ ቴክኒክና ሙያ የሚገቡ ሲሆን 152 ሺህ ሰልጣኞች ከቴክኒክና ሙያ ውጪ ባሉ ማሰልጠኛ ተቋማት እንደሚሰለጥኑ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገልጸዋል፡፡

የዘንድሮው የቴክኒክና ሙያ ተቋማት የመቁረጫ ነጥብ የ2014 ዓ.ም 12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎችን ታሳቢ ተደርጎ የተሰራ በመሆኑ ለ2015 ዓ.ም ብቻ የሚያገለግል መሆኑን ሚኒስትሯ አመልክተዋል።

ተማሪዎቹ የመቁረጫ ነጥቡን እስካሟሉ ድረስ በመረጡት የሥልጠና መስክ በመንግሥት እና በግል ማሠልጠኛ ተቋማት ውስጥ መሠልጠን የሚችሉ መሆናቸውን አብራርተዋል።

በ2013 ዓ.ም እና በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ወስደው በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ሥርዓት ያልገቡ ተማሪዎች የሚስተናገዱት በ2014 ዓ.ም በነበረው የመቁረጫ ነጥብ መሰረት መሆኑን ገልጸዋል።

በቴክኒክና ሙያ ተቋማት የሚሰጠው ሥልጠና ወደ ደረጃ ስምንት ከፍ እንዲል መወሰኑን ሚኒስትሯ መናገራቸውን የኢፕድ ዘገባ ያሳያል፡፡

ደረጃ አምስት አድቫንስድ ዲፕሎማ፣ ደረጃ ስድስት የመጀመሪያ ዲግሪ፣ ደረጃ ሰባት ማስተርስ እና ደረጃ ስምንት ዶክትሬት (PHD) እኩሌታን የሚይዝ ነ
የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#MattuUniversity

በ2015 ዓ.ም በመቱ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የአቅም ማሻሻያ #ሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ የካቲት 30/2015 ዓ.ም እና መጋቢት 01/2015 መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

➧ ስማችሁ ከ”A-B” የሚጀምር የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በበደሌ ካምፓስ፤
➧ ስማችሁ ከ“A-B” የሚጀምር የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በበደሌ ካምፓስ፣
➧ ቀሪዎቻችሁ በዋናዉ ጊቢ በአካል በመቅረብ እንድትመዘገቡ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል፡፡

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሄዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➧ የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
➧ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➧ የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት፣
➧ አራት ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➧ የሌሊት አልባሳት፣
➧ የስፖርት ትጥቅ፡፡

ከተጠቀሱት ቀናት ውጪ የሚመጡ ተማሪዎችን የማያስተናግድ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሬሜዲያል ተማሪዎች ጥሪ ፦

በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የአቅም ማሻሻያ /Remedial Program/ ፕሮግራም ለመከታተል የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ / ምዝገባ ቀን ፦

👉 ወልድያ ዩኒቨርሲቲ - ምዝገባ ከየካቲት 30/2015 ዓ.ም እስከ መጋቢት 01/2015
👉 እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ - ምዝገባ መጋቢት 4 እና 5 ቀን 2015 ዓ/ም (መጋቢት 6 ትምህርት ይጀምራል)
👉 አሶሳ ዩኒቨርሲቲ - መግቢያ ቀን መጋቢት 11 እና 12 ቀን 2015 ዓ/ም
👉 ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ - ምዝገባ መጋቢት 1 እና 2 / 2015 ዓ/ም
👉 ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ - ምዝገባ መጋቢት 5 እና 6 ቀን 2015 ዓ/ም በቅጣት መጋቢት 7
👉 ወሎ ዩኒቨርሲቲ - መግቢያ ቀን መጋቢት 4 እና 5 ቀን 2015 ዓ/ም

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
በደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ በ20 ሚሊዮን ብር ወጪ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ተቀምጧል።

ለትምህርት ቤቱ የሚውለው ወጪ ሙሉ ለሙሉ የሚሸፈነው ሰዎች ለሰዎች በተሰኘው ግብረ ሰናይ ድርጅት መሆኑን የድርጅቱ የኢትዮጵያ ተጠሪ ይልማ ታዬ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

"ወጪው በደቡብ ክልል መንግስት እና ሰዎች ለሰዎች በተሰኘው ግብረ ሰናይ ድርጅት በጋራ እንደሚሸፈን" በመገናኛ ብዙሃን የተገለጸው ትክክል አለመሆኑን ገልጸዋል።

የትምህርት ቤቱ ግንባታ ሙሉ ወጪ በሰዎች ለሰዎች ድርጅት እንደሚሸፈን አረጋግጠዋል።

በዶ/ር ካርል ሄይንዝ በም የተቋቋመው ሰዎች ለሰዎች (Menschen für Menschen) ላለፉት 40 ዓመታት የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#BongaUniversity

በ2015 ዓ.ም በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የአቅም ማሻሻያ (ሪሚዲያል) ፕሮግራም ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ መጋቢት 1 እና 2/2015 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሄዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➧ የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
➧ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት፣
➧ የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
➧ አራት 3×4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➧ የሌሊት አልባሳት፣
➧ የስፖርት ትጥቅ፡፡

ከተጠቀሱት ቀናት ውጪ የሚመጡ ተማሪዎችን የማያስተናግድ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot