STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
40.9K subscribers
11K photos
271 videos
452 files
1.93K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
#WachemoUniversity

ከአክሱም ዩኒቨርሲቲ በጊዚያዊነት ወደ ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ መምህራን ታህሳስ 11 እና 12/2014 ዓ.ም ሪፖርት እንዲያደርጉ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።

34 በአክሱም ዩኒቨርሲቲ ያስተምሩ የነበሩ መምህራን ወደ ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በትምህርት ማኒስቴር ጊዚያዊ ምደባ ተደርጎላቸዋል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#WachemoUniversity

በ2014 ዓ.ም በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደቡ ሬዝደንት ሀኪሞች ምዝገባ የካቲት 29 እና 30/2014 ዓ.ም እንደሚከናወን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ምዝገባው የሚደረገው በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የንግስት እሌኒ መሀመድ መታሰቢያ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል መሆኑ ተገልጿል።

ለቅጥር የሚያስፈልጉ፦

• 3×4 ፎቶግራፍ (4)፣
• የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒ፣
• የክሊራንስ ማረጋገጫ

ለትምህርት ምዝገባ (ሬጅስትራር) የሚያስፈልጉ፦

• የቅጥር ደብዳቤ፣
• ተጨማሪ 3×4 ፎቶግራፍ (4)፣
• ኦሪጅናል ዲግሪ ከሁለት ኮፒ ጋር፣
• ግሬድ ሪፖርት፣
• ኦፊሺያል ትራንስክሪፕት በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ፖስታ ሳጥን ቁጥር 667 ማስላክ

በሌላ ዩኒቨርሲቲ/ኮሌጅ ስፖንሰር የተደረጉ ሬዚደንቶች ቅጥር መፈጸም አይጠበቅባቸውም። የስፖንሰር ደብዳቤ እና ለትምህርት ምዝገባ የሚያስፈልጉ ሰነዶችን በመያዝ መመዝገብ ብቻ ይችላሉ።

ኦሬንቴሽን መጋቢት 01/2014 ዓ.ም ይሰጣል ተብሏል፡፡

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#WachemoUniversity

በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ግንቦት 09 እና 10/2014 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ወደ ተቋሙ ስትሄዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

• የ10ኛ እና 12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው
• ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው
• የ8ኛ ክፍል ሰርተፊኬት
• 3×4 ፎቶግራፍ (8)
• ብርድልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ልብስ
• የስፖርት ትጥቅ

በ Re-admission እና Withdrawal ወጥታችሁ የነበራችሁ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች ዳግም ቅበላ ግንቦት 11 እና 12/2014 ዓ.ም እንደሚከናወን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

ከተጠቀሱት ቀናት ውጪ የሚመጡ ተማሪዎችን የማያስተናግድ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።


ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#Update
#WachemoUniversity

ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች መግቢያ ግንቦት 09 እና 10/2014 ዓ.ም መሆኑን መግለጹ ይታወቃል።

የ1ኛ ዓመት ተማሪዎች #ዳግም_ቅበላ ግንቦት 11 እና 12/2014 ዓ.ም መሆኑንም ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች የተመደቡባቸውን ካምፓሶች ያሳወቀ ሲሆን በተገለጹት ቀናት በየካምፓሶቹ ሪፖርት አድርጉ ብሏል። (ዝርዝሩ ከላይ ተያይዟል።)

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#WachemoUniversity

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመስጠት የሚያስችላቸውን ዝግጅት እንዲያደርጉ የትምህርት ሚኒስቴር ማሳሰቡ ይታወሳል፡፡

የ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሁለት ዙር ከመስከረም 30/2015 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሰጥ ይታወቃል።

ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በተቋሙ የሚሰጠውን ፈተና አስመልክቶ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ሀብታሙ አበበ (ዶ/ር) ከሁሉም ምክትል ፕሬዝዳንቶች እንዲሁም ከኮሌጅ እና የትምህርት ቤት ዲኖች ጋር ውይይት አድርገዋል።

በዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ፣ በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የዱራሜ ካምፓስ እና በንግስት እሌኒ መሀመድ መታሰቢያ ኮምፕሬንስቪ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከ20 ሺህ በላይ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ ተገልጿል።

ሁሉም የኮሌጅ እና የትምህርት ቤት ዲኖች የትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው የፈተና አስፈፃሚዎች ምልመላ መነሻ መስፈርት መሰረት የፈታኝ መምህራን ምልመላ እንዲያደርጉ ፕሬዝዳንቱ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

ሚኒስቴሩ ከመስከረም 28 እስከ ጥቅምት 17/2015 ዓ.ም በሁሉም የዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ምንም አይነት መደበኛ ተማሪ እንዳይገኝ ማለቱ ይታወሳል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#WachemoUniversity ‼️

ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የ2015 ትምህርት ዘመን አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎችን መቀበል ጀምሯል።

በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስደው 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጡ ተማሪዎች በ15 የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች መመደባቸው ይታወቃል።

ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ከ1 ሺህ በላይ ተማሪዎች በትምህርት ሚኒስቴር ተመድበውለታል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#WachemoUniversity

በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስዳችሁ በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን እንድትከታተሉ ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ የሪሚዲያል ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሔደው ጥር 20 እና 21/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ወደ ተቋሙ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፡-

➢ የ8ኛ ክፍል ስርተፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➢ ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➢ የ12ኛ ክፍል ፈተና ሰርተፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➢ አንድ 2 x 2 እና ሁለት 3x4 ፎቶግራፍ፣
➢ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ።

የምዝገባ ቦታ፦

ስማችሁ ከ A-H የሚጀምር የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎችና እና ስማችሁ ከ A-M የሚጀምር የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ምዝገባችሁ በዋናው ካምፓስ የሚከናወን ሲሆን፤ ስማችሁ ከ I-Z የሚጀምር የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎችና እና ስማችሁ ከ N-Z የሚጀምር የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ምዝገባችሁን የምታደርጉት በዱራሜ ካምፓስ እንደሆነ ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot