STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
40.8K subscribers
11K photos
271 videos
452 files
1.93K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
#Update

ዛሬ እና ነገ የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ወደ መፈተኛ ማእከላት / ዩኒቨርሲቲዎች ይገባሉ።

ይህ ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ጥብቅ በሆነ ህግ መሰጠት ከመጀመሩ ጋር በተያያዘ ፈተናቸውን ጨርሰው የወጡት " የማህበራዊ ሳይንስ " ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው የተመለከቱትን እና በቀጣዩ " የተፈጥሮ ሳይንስ " ፈተና ወቅት ሊስተካከለ ይገባል ያሏቸውን ጉዳዮች በዝርዝር አቅርበዋል።

ፈታኝ መምህራንም ሀሳባቸውን አጋርተዋል።

#ከማህበራዊ_ሳይንስ_ተፈታኞች

- በባለፈው ፈተና ወቅት በአንዳንድ ተቋማት ውስጥ በምግብ አቅርቦት ጉዳይ ክፈትቶች የነበሩ ሲሆን ተማሪዎች በጊዜ ምግብ እንዲያገኙ እንዲሁም በግቢ ውስጥ ያሉት የአገልግሎት ሰጪዎች በተመጣጣኝ ዋጋ ሊያቀርቡ ይገባል። " የውሃ " አቅርቦትም ችግሮች የነበሩባቸው ተቋማት ነበሩ የሚገቡት ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያቸው እንደመሆኑን ለአምስት ቀን እንኳን ተማሪ ለማስተናገድ የሚሆን ውሃ ማቅረብ ይገባል። 

- አንዳንድ ተቋማት ውስጥ ስርዓት የጎደላቸው ተፈታኝ ተማሪዎች በሌሎች ተማሪዎች ላይ ጫና ለማሳደር ሲሞክሩ ታይቷል ፤ በየዶርሙ እየዞሩ ምግብ አምጡ፣ ብር አምጡ ሲሉ የነበሩም ተማሪዎች የነበሩ ሲሆን በቀጣዩ የፈተና ወቅት እንዲህ አይነት ባህሪ ያላቸው ተፈታኞች ካጋጠሙ የሚመለከተው አካል ለሌሎች አስተማሪ የሆነ እርምጃ መውሰድ ያስፈልገዋል።

- በባለፈው ፈተና ወቅት በአንዳንድ ተቋማት ውስጥ ሌሎች ተማሪዎችን የሚረብሹ፣ የሚጮሁ ፣ በየዶርሙ እየሄዱ ተማሪ በተኛበት ሲያንኳኩ የነበሩ ተማሪዎች ነበሩ ፤ በተጨማሪ የግል ትምህርት ቤት ተማሪዎች " ፈተና ደርሷቸዋል " በሚል የተሳሳተ መረጃ ተማሪዎች ላይ ጫና ለማሳደር እና ለማስፈራራት የሞከሩ ነበሩና በዚህኛው ፈተና ሁሉም ተማሪ በቂ ገለፃ እና ከመሰል ድርጊቶች እንዲቆጠቡ ማስገንዘብ ይገባል።

- ተፈታኝ ተማሪዎች ፤ ስለታም ነገሮች እና የተከለከሉ የሚጬሱ ነገሮችን ለምሳሌ እንደ ሲጋራ እንዳያስገቡ ፍተሻ ላይ የሚመደቡ የፀጥታ ኃይሎች ያለመሰልቸት ፍተሻ ማድረግ ይገባቸዋል። በግቢ ውስጥ ተማሪዎች ሲረብሹ ቢገኙ ደግሞ አጥፊዎችን ለይቶ ማስወጣት ይገባል እንጂ ሁሉም ተማሪዎች ላይ በጅምላ እምርጃ መውሰድ አይገባም።

- አንዳንድ ስነ ስርዓት የሌላቸው ተፈታኝ ተማሪዎች " ሴት ተማሪዎችን ለመተንኮስ " የሞከሩም ታይተዋልና የፀጥታ ኃይሎች ተማሪዎች ሳይጨነቁ እና ምንም ሳይፈሩ ፈተናቸውን እንዲወስዱ ማድረግ አለባቸው ፤ የላላ ቁጥጥር በተማሪዎች ውጤት ላይ የሚያደርሰው ተፅእኖ ከባድ ነው።

- ከተማሪዎች ማደሪያ/ዶርም ጋር በተያያዘ ትክክለኛና ወጥ የሆነ አሰራር መዘርጋት ይኖርበታል። በአንዳንድ ተቋማት ተማሪዎች በተመደቡበት ሳይሆን እንደፈለጉ እየገቡ፣ ሌሎችን ተፈታኝ ተማሪዎች እየረበሹ የመኝታ ክፍል ለመያዝ ሲጥሩ ነበር። አንዳንድ ተማሪዎች " ተመድበንበታል " ብለው የሄዱበት ማደሪያ / ዶርም በሌሎች ተይዞ እንዳገኙ ገልፀዋል፤ በማደሪያ ክፍል ችግር የተንገላቱ ብዙ ናቸው። በቀጣይ ፈተና ወቅት ይህ ከማደሪያ ክፍል ጋር የተያያዘ ችግር መስተካከል ይኖርበታል።

- ምሽት ላይ የተማሪዎችን ደህንነት የማስጠበቅ ስራ መጠናከር አለበት፣ የሚረብሹ፣ የሚጮሁ ተማሪዎችን መቆጣጠር ይገባል። ከዚህ ባለፈ ከፍተሻ መሰላቸት ጋር በተያያዘ ሊሆን ይችላል ያልተፈቀዱ ነገሮች አልፈው ሲገቡ ታይተዋል ፤ ስልክም ደብቀው ይዘው የገቡም ነበሩና ጥብቅ የሆነ ፍተሻ እና ቁጥጥር ያስፈልጋል።

ማጠቃለያ ፦ የ2014 ተፈታኞቹ እንደመጀመሪያ ጊዜ የዩኒቨርሲቲ ቆያታቸውና በእንደህ አይነት መንገድ ለፈተና መቀመጣቸው አዲስ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በርከታ እክሎች የነበሩ ቢሆን በቀጣይ ላለው ፈተና እንዲስተካከል ጠቁመዋል።

#ከፈታኝ_መምህራን

- አንዳንድ ፈታኞች " ኩረጃን በሚያበረታታ " ድርጊት ሲፈፅሙ ነበር ፤ ይህ የትውልድ ጉዳይ ለመሆኑን ያለመሰላቸት የፈተናውን ሂደት መከታተል አለባቸው።

- ተማሪዎች ስልክ ይዘው ግቢ እንዳይገቡ የተደረገው ከውጭ በመደዋወል በሀሰተኛ ወሬ እንዳይረበሹ በማሰብ ነበር ነገር ግን አንድ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ፈታኝ በፈተነበት ተቋም ፀጥታ ለማስከበር የተሰማሩ አካላት ለተማሪዎች ስልክ ሲሰጡ ተመልክቷል። የፀጥታ ኃይሎች ግቢ ውስጥ ሬድዮ ብቻ ቢጠቀሙ እና ሞባይል ባይፈቀድ መልካም መሆኑን ጠቁሟል።

- አንድ የቤተሰባችን አባል የሆነ ፈተና ፈታኝ ተማሪዎች ለቀው ከወጡበት በአንዱ ተቋም እያስፈተነ የነበረ ሲሆን በፈተና ስርዓቱ ያጋጠሙ ችግሮችን በዝርዝር ገልጾልናል፡ ሱፐርቫይዘሮች እና የጣቢያ ኃላፊዎች ስራቸውን በቁርጠኝነት ሊሰሩ እንደሚገባ እና በፈተና ክፍል ለሚስተዋሉ ችግሮች ፈጣን መፍትሄ ሊሰጡ ይገባል ብሏል።

- በፈተና ወቅት ለተፈታኞ የተሰጠው " የፈተና ሰዓት " በአግባቡ መቆጣጠር የሚገባ ሲሆን ቢቻል ቢቻል ፈተናው " ሙሉ በሙሉ " እስኪያልቅ የፈተናውን ወረቀት ይዘው እንዳይወጡ መከታተል ቢቻል ጥሩ ነው።

- "በቂ ዝግጅት"  ያላደረጉ ተማሪዎች የኩረጃ መንገዱ ሁሉ ስለተዘጋባቸው የፈተናው ስርዓት እንዲረበሽ እና ፈተናው እንዲሰረዝ ለማድረግ ሲጥሩ ነበር። እነዚህ ተማሪዎች ዓለማቸውን ለማስፈፀም ሌላ አካባቢ " ፈተና ተሰረቋል " የሚል እና ሌሎችንም ያልተረጋገጡ ወሬዎችን ነው የሚያስወሩት።

በተጨማሪ ፦

• በአንዳንድ ተቋማት ውስጥ ተማሪዎች ፈታኞችን በግልፅ " እንድንኮራረጅ ካላስደረጋችሁን " ሲሉ ነበር ፤

• ፈታኝ የሚያክብሩ እንዳሉ ሁሉ ፈታኞችንና የፈተናውን ህግ የማያከብሩ ነበሩ፣

• አንዳንድ ተማሪዎች ለፈተና መምጣታቸውን በማወቅ መዘጋጀት ሲገባቸው በግቢ ውስጥ ጥንድ ጥንድ ሆነው ሲዟዟሩ/ሲዝናኑ ነበር ፣

• አንዳንድ ተማሪዎች " ፈተናውን አናልፍም " በሚል የጥያቄ ወረቀቱን ሳይከፍቱት የመልስ ወረቀቱን ዝም ብለው ሲሞሉ ነበር ፣

• ተማሪዎች " በጭንቀት " ብቻ ለህመም ስለሚጋለጡ ትምህርት ሚኒስቴር / ዩኒቨርሲቲዎች በተማሪዎች ስነልቦና ላይ ከፍተኛ ስራ ሊሰሩ ይገባል። ተማሪዎቹ ለፈተና ሊገቡ ሲሉ ፈተናውን በራሳቸው አቅም መስራት እንደሚችሉ ተስፋ ሊሰጣቸው ይገባል።

ማጠቃለያ ፦ ክፍተቶች በቶሎ ቢታረሙና መስተካከል የሚገባቸው ጉዳዮች በፍጥነት ቢስተከከሉ ቀጣዩን ፈተና ካለፈው በመማር ስኬታማ ማድረግ ይቻላል።

#ለተፈጥሮ_ሳይንስ_ተማሪዎች

ማህበራዊ ሚዲያ ላይ በሚናፈስ ምንም ያልተረጋገጠ እና ሀሰተኛ ወሬዎች ሳትረባሹ ቀደም ብለው ወደ ግቢ ገብተው ብሔራዊ ፈተናውን ከወሰዱት " የማህበራዊ ሳይንስ " ተፈታኝ ጓደኞቻችሁ ግቢውን ለመላመድ ይረዳቹ ዘንድ በቂ መረጃ በመጠየቅ ፣ የፈተና ህጎችን ሁሉ በማክበር ፈተናችሁን በስኬት ታጠናቅቁ ዘንድ እንመኛለን። መልካሙ ሁሉ ይግጠማችሁ ፤ መልካም ፈተና !

#ለማህበራዊ_ሚዲያ_ተጠቃሚዎች

ዩኒቨርሲቲ ገብተው ፈተና የወሰዱት / በቀጣይ ቀናት የሚወስዱት ታዳጊዎች ለፈተና ስርዓቱ ብቻ ሳይሆን ለዩኒቨርሲቲ ዓለም አዲስ በመሆናቸው መደገፍ ፣ ማበረታታት  እና በራሳቸውን እንዲተማመኑ ማድረግ ፣ እንጂ በሀሰተኛ እና ባልተረጋገጠ ወሬ እንዲረበሹ እና ይህን ገና ብዙ የሚሰሩበትን እድሜ የፖለቲካ ቁማር መጫወቻ ማደርግ ፣ ተስፋቸው እንደጨለመ አድርጎ ወሬ መንዛት የአይገባም።

tikvah ethiopia

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#MettuUniversity


በ2016 ዓ.ም በሬሚድያል ትምህርት መረሃ ግብር በትምህርት ሚኒስቴር ወደ መቱ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ (Remedial Students) ተማሪዎች፤ የምዝገባ ጊዜ ጥር 20-21/2016ዓ.ም መሆኑን አዉቃችሁ በአካል በመቅረብ እንድትመዘገቡ ዩንቨርሲቲው አሳስቧል።

ማሳሰቢያ፤
 የስማችሁ ቀዳሚ ፊደል A- B #ለተፈጥሮ ሳይንስ ስትሪም እና ለማህበራዊ ሳይንስ ስትሪም የሚጀምር ተማሪዎች ፤ ምዝገባችሁ የሚሆነው በበደሌ ካምፓስ መሆኑን እናሳስባለን፡፡


📌ተማሪዎች ለምዝገባ ስትሄዱ
ብርድ ልብስ፤ አንሶላና ትራስ ጨርቅ፤ የስፖርት ልብስ
ከ8-12ተኛ ክፍል ያሉ የት\ት ማስረጃዎች ኦረጂናልና ኮፒ ኢንድሁም
አራት(4) ጉርድ ፎቶ ግራፍ ይዛችሁ ረፖርት እንድታደርጉ ዩንቨርሲቲው ጨምሮ አሳስቧል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot