STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
40.8K subscribers
11K photos
271 videos
452 files
1.93K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
#ጥቆማ

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በቂ አመልካቾች ባሏቸው የትምህርት ክፍሎች በማታ እና በእረፍት ቀናት የመጀመርያ ዲግሪ አመልካቾች የ2016 ዓ.ም የመጀመርያ ሴሚስተር ምዝገባ ከህዳር 27 እስከ 29/2016 ዓ.ም ያከናውናል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
Are you facing difficulties in the following areas:
1: Masters Thesis writing
2: report writing
3:Data analsis
4: Methodology
5: Research Proposal
6: Assignments (Test/ Quizzes)
We do not only help in writing thesis but make sure your thesi is professionally written and well structured and plagiarism free

please text link below👇
@ResearcherETH
@ResearcherETH
@ResearcherETH
#SalaleUniversity

በ2016 ዓ.ም በሰላሌ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች እና በ2015 ዓ.ም በሰላሌ ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ትምህርታችሁን ስትከታተሉ ቆይታችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ታህሳስ 10 እና 11/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦ ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ጀነራል ታደሰ ብሩ ካምፓስ

ወደ ተቋሙ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፡-

➢ የ8ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ዋናውና አንድ ኮፒ፣
➢ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ዋናውና አንድ ኮፒ፣
➢ የ12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና አንድ ኮፒ፣
➢ ስምንት 3 x 4 ፎቶግራፍ፣
➢ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና ትራስ ልብስ፣
➢ የስፖርት ትጥቅ፡፡

ከላይ የተያያዘውን የተቋሙን ጥሪ ትክክለኛነት ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ከተቋሙ ከፍተኛ አመራር አረጋግጧል፡፡

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መስጫ ወረቀቶችን ደብቆ ፈተና ወደሚታረምበት አዳራሽ ሊገባ ነበር የተባለው ተከሳሽ ያቀረበው የክስ መቃወሚያ በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 5ኛ የሙስና ወንጀል ችሎት ውድቅ ተደረገ።

ችሎቱ የዐቃቤ ሕግ ምስክርን ለመስማት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

የክስ መቃወሚያው ውድቅ የተደረገበት ተከሳሽ ይድነቃቸው ተኮላ ይኼይስ፤ የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣዉን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 9 ንዑስ 2 ስር የተመለከተዉን ድንጋጌ ተላልፏል በሚል በፍትህ ሚኒስቴር የሙስና የወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ ክስ ያቀረበበት መሆኑ ይታወሳል።

በቀረበው ክስ ላይ ተከሳሹ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በሰኔ 29 ቀን 2015 ዓ.ም ባወጣው የስራ ማስታወቂያ ተመዝግቦ በፈተና አመቻችነትና ለእርማት ስራ በጊዜያዊነት መቀጠሩ ተጠቅሷል።

በተለይም ከነሀሴ 1 ቀን 2015 ዓ.ም እስከ ነሀሴ 8 ቀን 2015 ዓ.ም ባሉት ቀናት ውስጥ በብርሀንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ውስጥ የተቀመጡና ለእርማት የተዘጋጁ የ18 ተማሪዎች የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና መልስ መስጫ ወረቀቶችን ይዞ መውጣቱ በክሱ ዝርዝር ላይ ሰፍሯል።

ከዚህም በኋላ በነሀሴ 8 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 2 ሰዓት ከ30 አካባቢ በፈተና ወቅት የተፈታኝ ተማሪዎች የመልስ መስጫ ወረቀቶች ያልሆኑና የፈተና መልስ ተቀልሞባቸው (ተሞልቶባቸው) የተዘጋጁ 33 የመልስ መስጫ ወረቀቶችን ደብቆ ፈተና ወደሚታረምበት አዳራሽ ሊገባ ሲል በተደረገ ቁጥጥር በፍተሻ የተያዘ በመሆኑ በክስ ዝርዝሩ ላይ ተገልጿል።

በተጨማሪም በተከሳሹ መኖሪያ ቤት በተደረገ ብርበራ 44 የ2015 ዓ.ም ተፈታኝ ተማሪዎች የመልስ መስጫ ወረቀቶችና 10 ደግሞ ተመሳስለው የተዘጋጁ ሀሰተኛ የመልስ መስጫ ወረቀቶች የተገኙ መሆኑን ጠቅሶ ዐቃቤ ሕግ በክስ ዝርዝሩ ላይ አስፍሯል።

በዚህ መልኩ ተከሳሹ ሥልጣንን ያለአግባብ መገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል ተከሶ ክሱ በተረኛ ችሎት እንዲደርሰው ከተደረገና ክሱ በችሎት ከተነበበ በኋላ ክስ እንዲሻሻልለት የመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያ አቅርቦ ነበር

በከሳሽ ዐቃቤ ሕግ በኩል ደግሞ ክሱ ግልጽ መሆኑ ተጠቅሶ ሊሻሻል አይገባም የሚል መልስ ተሰጥቷል።

ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን መርምሮ ክሱ እንዲሻሻል የቀረበው ጥያቄ ህጋዊ መሰረት የለውም በማለት ውድቅ አድርጓታል።

ተከሳሹም በክሱ ላይ የተጠቀሰውን የወንጀል ድርጊት አለመፈጸሙን ጠቅሶ የዕምነት ክህደት ቃሉን በመስጠቱ ዐቃቤ ሕግ ምስክሮቹ እንዲሰሙለት ጠይቋል።

ፍርድ ቤቱም የዐቃቤ ሕግን ምስክሮች ለመጠባበቅ ለህዳር 28 ቀን 2016 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። #FBC

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
Are you facing difficulties in the following areas:
1: Masters Thesis writing
2: report writing
3:Data analsis
4: Methodology
5: Research Proposal
6: Assignments (Test/ Quizzes)
We do not only help in writing thesis but make sure your thesi is professionally written and well structured and plagiarism free

please text link below👇
@ResearcherETH
@ResearcherETH
@ResearcherETH
ዲላ ዩኒቨርሲቲ የ2016 ዓ.ም አዲስ ገቢ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ገለጸ፡፡

ዩኒቨርሲቲው በትምህርት ሚኒስትር የተመደቡለትን አዲስ ገቢ መደበኛ ተማሪዎች እንዲሁም በሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታቸውን በዲላ ዩኒቨርሲቲ ተከታትለው የማለፊያ ነጥብ ያስመዘገቡ ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጅት ማጠናቀቁን ገልጿል፡፡

ተቋሙ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት አምጥተው የተመደቡ 222 አዲስ ገቢ ተማሪዎች (162 በተፈጥሮ ሳይንስ እና 60 በማህበራዊ ሳይንስ) እንዲሁም በሪሚዲያል ፕሮግራም ውጤታቸውን አሻሽለው የተመደቡ 1,836 ተማሪዎች በድምሩ 2,058 ተማሪዎች የተመደቡለት መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ፍሬሽማን ፕሮግራም ዲን አስናቀ ይማም (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡

ዲላ ዩኒቨርሲቲ ለአዲስ ገቢ (Freshman Students) እና የሪሚዲያል ትምህርት ተከታትለው የማለፊያ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች ለህዳር 28 እና 29/ 2016 ዓ.ም ጥሪ ማድረጉ ይታወቃል፡፡


የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ከ134 ሚሊዬን ብር በላይ በሆነ ወጭ የተገነቡ 7 የትምህርት ተቋማት ግንባታቸው መጠናቀቁ ተገለጸ።

በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር በ2015 በጀት ዓመት ከ134 ሚሊዬን ብር በላይ በሆነ ወጭ የተገነቡ 7 የትምህርት ተቋማት ግንባታቸው መጠናቀቁን የትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ መንግስቱ አበበ ገልጸዋል።

3ቱ የትምህርት ተቋማቶች የበጀት ምንጫቸው በፌደራል የትምህርት ሚኒስትር መልሶ ማቋቋም ፕሮጀክት ሲሆን ለእያንዳንዳቸው 23 ሚሊዬን ብር ወጭ እንደጠየቁና እያንዳንዱ ፕሮጀክት 10 የመማሪያ ክፍል እንድሁም 2 መጸዳጃ ቤቶችን ያካተተ መሆኑን የትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ መንግስቱ አበበ አብራርተዋል።

2ቱ ተቋማት በክልሉ መልሶ ማቋቋም ፈንድ ጽ/ቤት የተገነቡ ሲሆን 4 መማሪያ ክፍል ፣1 የኢንፎርሜሽን ኮምዩኒኬሽን ቴክኖሎጅ እና 1 የፔዳጎጅካል ማዕከል እንዳላቸውና ለእያንዳንዱ ተቋም ከ13 ሚሊዬን ብር በላይ ወጭ መጠየቁን መምሪያ በኃላፊው አስረድተዋል።

10 የመማሪያ ክፍል እና 1የኢንፎርሜሽን ኮምዩኒኬሽን ቴክኖሎጅ ማዕከል ያለው 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በዱሮው አየር ማረፊያ በክልሉ ትምህርት ቢሮ መገንባቱን እና የቢራሮ 2ኛ ደረጃ ትምህርት በከተማ አስተዳደሩ በጀት ማጠናቀቅ መቻሉን ገልጸዋል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
Photo
የሪሚዲያል ፕሮግራም ምደባ ይፋ ሆኗል።

በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ብሔራዊ ፈተና ወስዳችሁ በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የሪሚዲያል ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የተቋም ምደባችሁን ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ማየት የምትችሉ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

ምደባችሁን ለማየት የቀረቡ አማራጮች፦

በድረ-ገፅ፦
https://placement.ethernet.edu.et

በቴሌግራም ቦት፦
https://t.me/moestudentbot

የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ #የማያስተናግድ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#MoE

የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በእንግሊዝኛ ቋንቋ መማራቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ (Letter of Proficiency) እንዲፃፍላቸው ለሚፈልጉ ትምህርት ሚኒስቴር አገልግሎቱን ይሰጣል።

ተገልጋዮች ወደ ትምህርት ሚኒስቴር ስትሔዱ ማሟላት የሚጠበቅባችሁ፦

1. 12ኛ ክፍል ማጠናቀቃችሁን የሚገልፅ ዋናው ሰርተፊኬትና የማይመለስ አንድ ኮፒ፣

2. በቀድሞው የትምህርት ፖሊሲ 10ኛ ክፍል ያጠናቀቁ ከሆነ፥ 10ኛ ክፍል ማጠናቀቃችሁን የሚገልፅ ዋናው ሰርተፊኬትና የማይመለስ አንድ ኮፒ፣

3. አመልካቾች ማንነታችሁን የሚገልፅ የታደሰ መታወቂያ /ፓስፖርት/ መንጃ ፈቃድ ከማይመለስ አንድ ኮፒ ጋር ማቅረብ እንደሚጠበቅባችሁ ሚኒስቴሩ ገልጿል።

አገልግሎቱ የሚሰጠው ሰኞ እና ሐሙስ በሥራ ሰዓት መሆኑ ተመላክቷል፡፡

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የኢትዮጵያ አየርመንገድ አቪዬሽን ዩንቨርስቲ ከ600 በላይ በተለያዩ መስኮች ያስለጠናቸውን ተማሪዎችን በማስመረቅ ላይ ይገኛል።

በዛሬው የምርቃት ፕሮግራም በአውሮፕላን አብራሪነት በአውሮፕላን ጥገና እና መስተንግዶ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎችን ነው እያስመረቀ የሚገኘው።

በምርቃት ስነስርዓቱ የኢትዮጵያ አየርመንገድ ዋና ስር አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰውን ጨምሮ የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩንቨርስቲ ፕሬዚዳንት አቶ ካሴ ይማም የተማሪዎች ወላጆች በተገኙበት በኢትዮጵያ አየርመንገድ ውስጥ ፕሮግራሙ እየተካሄደ ይገኛል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Freshman 2016 Notes AMU.pdf
287.2 KB
የአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ አንደኛ ዓመት ተማሪዎች ይህን ፋይል አንብቡት


💥Students who want to be transferred from Natural Science to Social Science can submit their
written application to the main or campus registrar offices. The application should be short but
must contain the applicant’s full name, ID number and signature.

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
አዲግራት ዩኒቨርስቲ በትምህርት ሚኒስቴር የተመደቡለትን 832 አዲስ ተማሪዎች መቀበሉን አስታወቀ።

ዩኒቨርስቲው በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ከ1 ሺሕ 500 በላይ ተማሪዎች ታህሳስ 6 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚያስመረቅም ተመላክቷል።

የዩኒቨርስቲው የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር ዮሐንስ ከበደ እንዳሉት ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎቹን የተቀበለው የመመገቢያ፣ የመማሪያ፣ የመኝታ እና ሌሎች ለመማር ማስተማር ሥራው አስፈላጊ የሆኑ የዝግጅት ሥራዎችን ካጠናቀቀ በኋላ መሆኑን ተናግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪ የዩኒቨርስቲውን ቅጥር ግቢ በማስዋብና በማፅዳት ተማሪዎቹን መቀበሉን ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።

ዩኒቨርስቲው ትምህርታቸውን በተለያዩ ምክንያቶች አቋርጠው ከነበሩ ከ5 ሺሕ በላይ ተማሪዎች መካከል ዳግም ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ 1 ሺሕ 500 ተማሪዎችን የፊታችን ቅዳሜ እንደሚያስመርቅም ዮሐንስ አመልክተዋል።

የመቀሌ እና የአክሱም ዩኒቨርስቲዎች በተያዘው የትምህርት ዘመን የሚያስተምሯቸውን ከ2 ሺሕ በላይ ተማሪዎች ባለፈው ሳምንት መቀበላቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
"ከ51ሺ ትምህርት ቤቶች መካከል የጥራት መስፈርቶችን ያሟሉት 6ቱ ብቻ ናቸው" - የትምህርት ሚኒስቴር

የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አሁን ላይ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ስር ካሉ 51 ሺህ ትምህርት ቤቶች መካከል የተቀመጡ የጥራት ደረጃዎችን ያሟሉት 6 ትምህርት ቤቶች ብቻ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡

አብዛኛው ትምህርት ቤቶች ምቹ የመማሪያ ቦታ የሌላቸው፤ የትምህርት መማሪያ ቁሳቁስ እና ብቁ የመምህራን እጥረት እንዳለባቸውም አመላክተዋል ፡፡

መንግስት አሁን ላይ ይህንኑ ችግር ለመቅረፍ አዲስ ስርዓተ ትምህርት ከማዘጋጀት ጀምሮ የመምህራንን አቅም ማሻሻል እንዲሁም የመንግስት ትምህርት ቤቶች ከግል የትምህርት ተቋማት ጋር የሰፋ ልዩነት እንዳይኖራቸው በትኩረት እየሰራበት እንዳለም ጠቁመዋል፡፡

እያንዳንዱ የግል የትምህርት ቤቶች 10 አቅም የሌላቸው ተማሪዎችን ተቀብለው በነፃ በማስተማር ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ የሚያስችል አሰራር እየተዘረጋ ስለመሆኑም ሚኒስትሩ አስታውቀዋል፡፡

በተጨማሪም አለምአቀፍ ትምህርት ቤቶችም ለአቅም ደካማ ተማሪዎች ነፃ የትምህርት እድል እንዲሰጡ እንደሚደረግም ነው የተናገሩት፡፡

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot