This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በዩኒቨርሲቲዎች የተፈጠረውን ግጭት በማነሳሳት የተጠረጠሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው።
#FBC
@NATIONALEXAMSRESULT
https://t.me/joinchat/AAAAAFOUbJV0CPRu9x45bQ

ቁጥሩ በአንድ ጨምሯል የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ በኢትዮጵያ
በኢትዮጵያ ስድስተኛው የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ መገኘቱን የጤና ሚኒስትር ዶተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።
የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በአዲስ አበባ ውስጥም ከሄስፒታሎች፤ ከሆቴሎች ግንኙነትን ዘርግቶ በጋራ እየሰራ መሆኑ ይታወቃል።
በመሆኑም በዛሬው ዕለት ከዱባይ ወደ ኢትዮጵያ የመጣች የ 59 ዓመት እንግሊዛዊ ዜግነት ያላት ዲፕሎማት ስትሆን በ መጋቢት 7/2012 ከሆቴል በተደረገ ጥቆማ ግለሰቧ በምትገኝበት እራሷን አግልላ እንድትቆይ በማድረግ በተደረገላት የላብቶሪ ምርመራ ናሙና ውጤት የኮሮና ቫይረስ መያዟ ተረጋገግጧል።
#FBC
ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን

1441ኛው የረመዳን ፆም አርብ ይጀመራል!
በህዝበ ሙስሊሙ ዘንድ ታላቅ ቦታ ያለው የረመዳን ፆም የፊታችን አርብ እንደሚጀመር የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዬች ጠቅላይ ምክር ቤት አስታውቋል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዬች ጠቅላይ ምክር ቤት የህዝብ ግንኙነት ሃላፈ ዑስማን አደም ለኤፍ ቢ ሲ እንደተናገሩት ጨረቃ ዛሬ ረቡዕ ባለመታየቷ ፆሙ የሚጀመረው አርብ መሆኑን ገልፀዋል።
ወሩን በፆም እና ሀይማኖታዊ የፀሎት ስነስርአቶች የሚያሳልፉት ሙስሊሞች ራሳቸውንና ወገኖቻቸውን ከኮቪድ-19 ወርርሽኝ በመጠበቅ በቤት ውስጥና በመተሳሰብ እንዲያሳልፉ ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጅ ኡመር ኢድሪስ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል።
ፆሙ አርብ የሚጀምር በመሆኑ ሀሙስ ምሽት የተራዊህ ሰላት የሚጀመር ይሆናል።
ምንጭ፦ #FBC
#SHARE
ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን

የኦፌኮ የቀድሞ አመራረ አቶ ደጀኔ ጣፋ፣ አቶ መስተዋርድ ተማም እና የአቶ ጃዋር መሀመድ የኮምፒውተር ኢንጂነሪንግ ባለሙያ አቶ ሚሻ አደም ላይ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ ተመሰረተ።
ክሱ በሁለት የተከፈለ ሲሆን፥ 1ኛ ተከሳሽ አቶ ደጀኔ ጣፋ እና አቶ መስተዋርድ ተማም ላይ ሲሆን፥ ሁለተኛው በአቶ ሚሻ አደም ላይ ነው ።
የአቃቤ ህግ ክስ እንደሚያመለክተው በ1996 ዓመተ ምህረት የወጣውን የኢፌዴሪ የወንጀል ህግ 238/2 ስር የተመለከተውን በመተላለፍ ካልተያዙ ግብረ አበሮቻቸው ጋር በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን በሀይል፣ በዛቻ እና ህግወጥ በሆነ በማንኛውም መንገድ በህግመንግስት የተቋቋመን ስርዓት ለማፍረስ በማሰብ ”ከሰኔ 2012 ዓመተ ምህረት በኋላ የመንግስት የስልጣን ዘመኑ የሚያበቃ በመሆኑ መንግስት ሆኖ መቀጠል ስለማይችል‘ በማለት የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም ግፊት ሲያደርጉ እንደነበር አቃቤ ህግ በክሱ ጠቅሷል።
”በሀገሪቱ የሚገኙ የሚኒሊክና ተመሳሳይ ሀውልቶች መፍረስ አለባቸው፣ የኦሮሞ ቄሮዎች የሌሎች ብሄሮችን ንብረት ማቃጠል አለባቸው‘ በሚል በሰኔ 23 ቀን 2012 ዓመተ ምህረት የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ አስቀድመው የሰጡትን እና በተመሳሳይ መግዘብ ተጠርጣሪ የሆኑት አቶ ጃዋር መሀመድ ከጥዋቱ 1 ሰዓት ሲሆን፥ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስምንት ጳውሎስ ሆስፒታል አካባቢ የሟች አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ አስክሬንን ለመሸኘት ለተሰበሰበ በርካታ ህዝብ ”ከአሁን በኋላ ብቻችንን አናለቅስም፣ የነፍጠኛ ልጆች ከዚህ በፊት እንደጨረሱን ሁሉ አሁንም እየጨረሱን ነው፣ አሁኑኑ ወደ ሚኒሊክ ሃውልት ሂዱና አፍርሱ፣ አንድ ነፍጠኛ ከመጣ እንዳታልፉት እርምጃ ውሰዱባቸው፣ ከዚያ ወደ አራት ኪሎ ቤተ መንግስት በመሄድ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ያለውን ስርዓት መገርሰስ አለብን‘ በማለት የተሰጣቸውን ተልዕኮ ለማሳካት አንደኛ ተከሳሽ አቶ ደጀኔ ጣፋ በተመሳሳይ መዝገብ ተጠርጣሪ ከሆኑት አቶ በቀለ ገርባ ጋር ወጣቶችን በማደራጀት ቡራዩ ከተማ ኬላ አስክሬኑ እንዳያልፍና ”አስክሬኑን ወደ አዲስ አበባ እንዲመለስ ማድረግ አለብን‘ የሚል ትእዛዝ በስልክ ተቀብሎ በዚሁ ስፍራ ከግብረ አበሮቻቸው ጋር በመሆን መሳሪያ የያዙ በርካታ ወጣቶችን በማስተባበር መንገድ በመዝጋት አስክሬኑን ወደ አዲስ አበባ መመለሳቸው በክሱ ተመልክቷል።
በሰኔ 22 ቀን ደግሞ ከሌሊቱ 5 ሰዓት ከ10 ላይ በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን ደምበል በተባለ ቦታ ካልተያዘ ግብረ አበሩ ጋር መንገድ እንዲዘጋ በማድረግ መንግስትን ከስልጣን ለማስወገድ የመጨረሻ ትግል እንዲያደርጉ አቶ ደጀኔ ተእዛዝ መስጠታቸው በክሱ ተጠቅሷል።
በሰኔ 23 በምእራብ ወለጋ ነጆ ወረዳ ያልተያዘ ግብረ አበሩ የየአካባቢውን የመንግስት መዋቅር እንዲያፈርሱ ትእዛዝ ያስተላለፉ መሆኑንም ነው ያመለከተው።
ሁለተኛ ተከሳሽ መስተዋርድ ተማም ደግሞ ከጃዋር መሀመድ የተሰጠውን ተልዕኮ ተቀብሎ ቡራዩ ከተማ ኬላ ላይ አስገድዶ አስክሬኑን ወደ አዲስ አበባ በመመለስ የኦሮሞ የባህል ማዕከል መግቢያ በር ጥሶ ሲገባ መያዙን የጠቀሰው በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን የደምበል አስተዳደር ፅህፈት ቤት እና የማህበረሰብ ፖሊስ ቢሮን በአጠቃላይ ግምታቸው ከ700 ሺህ ብር የሚበልጥ ንብረት በማውደም እንዲሁም የግል ምግብ ቤትና የመጠጥ ንግድ ተቋማት ላይ ከ824 ሺህ ብር በላይ የሚያወጣ ንብረት የአምስት ግለሰቦች ምግብ ቤትና የዘይት ማምረቻ ፋብሪካን ጨምሮ 3 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር የሚያወጣ ንብረት የተቃጠለ መሆኑን እና 5 ሚሊየን ብር የሚያወጡ ተሽከርካሪዎች የተቃጠሉ መሆናቸውን የጠቀሰው አቃቤ ህግ በዚህ ወንጀል ተግባር ምክንያት በተነሳ ግጭት በቡራዩ የሁለት ሰዎች እና በአዲስ አበባ የስድስት ሰዎች ህይወት ያለፈና በህዝብ ደህንነት ወይም ኑሮ ላይ ከፍተኛ ቀውስ የደረሰ በመሆኑ ተከሳሾች በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን በህግመንግስቱና በህግመንግስታዊ ስርዓቱ ላይ የሚፈፀም ወንጀል ክስ ቀርቦባቸዋል።
ተከሳሾቹ ክሱ የደረሳቸው ሲሆን፥ ክሱን ተመልክቶ ለመከራከርና ዋስትና እንዲፈቀድላቸው ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል።
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ የፀረ ሽብር ጉዳዮች ወንጀል ችሎት የተገኘው አቃቤ ሀግ ክሱ ከ15 ዓመት በላይ የሚያስቀጣ መሆኑን ተከትሎ በስነ ስርዓት ህጉ መሰረት ዋስትና ያስከለክላቸዋል ሲል ተቃውሞ ተከራክሯል።
ጉዳዩን የተከታተለው ፍርድ ቤቱም መርምሮ የዋስትና ክርክሩ ላይ ብይን ለመስጠት ለነገ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
አቶ ሚሻ አደምም በቴሌኮም ማጭበርበር ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸዋል።
የቴሌኮም ማጭበርበር አዋጅ ቁጥር 761/204 አንቀፅ 9/1 ስር የተመለከተውን በመተላለፍ በግለሰብ እጅ መያዝ የሌለበትና የማይፈቀደውን አቶ ጃዋር መሀመድ ከኢትዮቴሌኮም ፍቃድ ሳይኖራቸው የሳታላይት መሳሪያ ከአሜሪካ ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ጃፓን ኤምባሲ አካባቢ በአቶ ጃዋር መሀመድ መኖሪያ ቤት በመትከል በሞባይል ስልክ፣ በታብሌትና ኮምፒውተር የረዥም ርቀት ግኑኝነት በማድረግ የግል የዳታ እና የቪዲዮ ከአምሰት እስከ 25 ኪሎ ሜትር ርቀት ሲስተም ውስጥ ያሉ ተጠቃሚዎች የኢንተርኔት አገልግሎትን ተደራሽ በማድረግ፣ በቤታቸው ውስጥ የግል ኔትወርክ ሲስተም እንዲኖር በማድረግ እና የቪዲዮ ዳታ ግኑኝነት እንዲኖር በማድረግ በሀምሌ 4 ቀን 2012 በመኖሪያ ቤታቸው ነቅለው ከደበቁበት በክትትል በቁጥጥር ስር ውሏል ብሏል።
ካለፍቃድ የቴሌኮም መሰረተ ልማት መዘርጋት ወንጀል ክስ ቀርቦበታል።
ተከሳሹ በዋስትና እንዲፈታ የጠየቀ ሲሆን፥ አቃቤ ህግ ክሱ ከ20 ዓመት በላይ የሚያስቀጣ በመሆኑ እንዲሁም ተከሳሹ ከሀገር ሊያመልጥ ሲል በቁጥጥር ስር የዋለ መሆኑን ጠቅሶ ዋስትናን ተቃውሟል። ክርክሩን የተከታተለው ፍርድ ቤቱ ብይን ለመስጠት ለነገ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
Via #FBC

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ጥራት ምክር ቤት በይፋ ተመሰረተ።
የትምህርትና ስልጠና ፕሮግራሞች የሀገሪቱን ፍላጎትና ገበያ ማዕከል ያደረጉ እንዲሆኑ ምክር ቤቱ ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል ተብሏል።
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ሳሙኤል ኡርቃቶ (ዶ/ር) ምክር ቤቱ የከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና ጥራትና አግባብነትን ለማስጠበቅ ከማስቻል ባለፈ የሀገሪቱ የትምህርትና ስልጠና ፕሮግራሞች በዓለም ዐቀፍ ደረጃ እንዲመዘኑ ያግዛል ብለዋል፡፡
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከምክር ቤቱ ጋር በጋራ በመሆን በሚያቀርቡት ጥናት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ከምደባ ወደ ቅበላ ይሸጋገራሉ ተብሏል።
ምክር ቤቱ የሁሉም የሙያ መስኮች ማህበራት ውክልና ያለውና የኢንዱስትሪ ማህበራትንና ተቀራራቢ ሲቪክ ማህበራትን አካቶ የተደራጀ ነው።
Via #FBC
#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ
ለተጨማሪ ተማሪ ነክ ለሆኑ የተጣሩ መረጃዎች እና ዜናዎች የቴሌግራም ቻናላችንን ተቀላቀሉን

የወሎ ዩኒቨርሲቲ ከ10 ሺህ በላይ መደበኛ ቅድመ ምረቃ ተማሪዎቹን መጋቢት 12 እና 13 እንደሚቀበል አስታወቀ፡፡
የዩኒቨርሲቲው የህዝብ ግንኙነት ክፍል ሀላፊ ዶ/ር ብርሀን አሰፍ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተቋሙ ለመማር ማስተማር አገልግሎት የሚያስፈልጉ ዝግጅቶችን በማጠናቀቅ ለተማሪዎች ጥሪ ማድረጉን ገልጸዋል።
ዩኒቨርሲቲው ከ1ኛ እሰከ 3ኛ ድግሪ ድረስ ያሉ ተማሪዎችን እንደሚቀበል የተገለጸ ሲሆን÷ በኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የሚማሩ ተማሪዎችን ጨምሮ ከ10 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ለመቀበል መዘጋጀቱ ተገልጿል።
ሁሉም የቅድመ ምረቃ ተማሪዎችም በተጠቀሰው ቀን በዩኒቨርሲቲው በመገኘት ምዝገባ ማካሄድ እንዳለባቸው አሳስቧል።
#FBC
ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን

በአማራ ክልል በህውዓት ወረራ ምክንያት የወደሙ ከ1 ሺህ በላይ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት የሚያስችል መርሐ ግብር በደሴ ከተማ እየተካሄደ ነው።
የመልሶ ግንባታ መርሐ ግብሩ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ፣ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋን ጨምሮ የፌደራል እና የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት ነው የተጀመረው፡፡
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ወንድወሰን አቢ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት ÷ በክልሉ ውድመት ከደረሰባቸው የትምህርት ተቋማት መካከል 170 ያህሉ በትምህርት ሚኒስቴር የሚገነቡ ናቸው፡፡
ከእነዚህ ተቋማት ውስጥ ሰባት ትምህርት ቤቶች በመጀመሪያው ዙር የመሠረት ድንጋይ ተቀምጦላቸው በቅርብ ጊዜ ግንባታቸው የሚጠናቀቁ መሆናቸውን አመላክተዋል፡፡
በአማራ ክልል በትምህርት ተቋማት ላይ ብቻ የደረሰው ጠቅላላ የጉዳት መጠን ከ5 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት ሲሆን÷ በደሴ ከተማ እና በደቡብ ወሎ ዞን በትምህርት ተቋማት ላይ የደረሰው የወድመት መጠን ደግሞ 1 ቢሊየን 729 ሚሊየን ብር ይገመታል ተብሏል፡
#FBC
ተማሪ ነክ መረጃ እንዘግባለን

የዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝነት ማረጋገጥ የትምህርት ጥራትን ከማስጠበቁም በላይ በተቋማቱ የሚነሱ ልዩ ልዩ የጥቅማ ጥቅም ጥያቄዎችን ለመመለስ ያስችላል ሲል ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል፡፡
የትምህርት ሚኒስትር ዴዔታ ሳሙዔል ክፍሌ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት÷ ነጻ ያልሆኑ የትምህርት ተቋማት በነጻነት መስራት ፣ እውቀታቸውን ማካፈል እና የሚጠበቅባቸውን ተግባር መፈጸም አይችሉም፡፡
ለዚህም የትምህርት ሚኒስቴር ዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝ እንዲሆኑ በማድረግ በሃገር ግንባታው ላይ የራሳቸውን ሚና መወጣት እንዲችሉ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
በዚህ ረገድም ራስ ገዝነቱ ተቋማዊነታነታቸውን የሚያላብስ በመሆኑ ምን ዓይነት ሰው በምን ዓይነት ክፍያ እንቅጠር ከሚለው ጀምሮ በሃብት አስተዳደር ላይም ጥቅሙ ከፍተኛ ነው ብለዋል።
ተጠያቂነት ያለው በመሆኑ የህግ ማዕቀፍ ተዘጋጅቶለት ክትትል እንደሚደረግበት የተገለፀው ራስ ገዝነቱ÷ ዩኒቨርሲቲዎች የምዘና እና ስርዓተ ትምህርታቸውንም በነጻነት በማዘጋጀት በሃገር ግንባታው ላይ የራሳቸውን ሚና እንዲጫወቱ ያደርጋል ነው የተባለው፡፡ #FBC
የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot

Audio
#ይደመጥ
- የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ጉዳይ እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ስጋት
- የተማሪዎች ምረቃ እና የመውጫ ፈተና መያያዝ
- የሬሜዲያ ፈተና ተፈታኞች ጉዳይ
- የትምህርት ጥራት እና ፈተና
እነዚህን እና ሌሎች ጉዳዮች የተዳሰሰበት " ፋና ቴሌቪዥን " ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማህበር ፕሬዝዳንት ዶ/ር አረጋ ይርዳው ጋር ያደረገው ቃለ ምልልስ ከላይ በድምፅ ፋይል ተያይዟል።
ፋይሉ 13 MB ነው።
Credit - #FBC

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መስጫ ወረቀቶችን ደብቆ ፈተና ወደሚታረምበት አዳራሽ ሊገባ ነበር የተባለው ተከሳሽ ያቀረበው የክስ መቃወሚያ በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 5ኛ የሙስና ወንጀል ችሎት ውድቅ ተደረገ።
ችሎቱ የዐቃቤ ሕግ ምስክርን ለመስማት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
የክስ መቃወሚያው ውድቅ የተደረገበት ተከሳሽ ይድነቃቸው ተኮላ ይኼይስ፤ የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣዉን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 9 ንዑስ 2 ስር የተመለከተዉን ድንጋጌ ተላልፏል በሚል በፍትህ ሚኒስቴር የሙስና የወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ ክስ ያቀረበበት መሆኑ ይታወሳል።
በቀረበው ክስ ላይ ተከሳሹ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በሰኔ 29 ቀን 2015 ዓ.ም ባወጣው የስራ ማስታወቂያ ተመዝግቦ በፈተና አመቻችነትና ለእርማት ስራ በጊዜያዊነት መቀጠሩ ተጠቅሷል።
በተለይም ከነሀሴ 1 ቀን 2015 ዓ.ም እስከ ነሀሴ 8 ቀን 2015 ዓ.ም ባሉት ቀናት ውስጥ በብርሀንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ውስጥ የተቀመጡና ለእርማት የተዘጋጁ የ18 ተማሪዎች የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና መልስ መስጫ ወረቀቶችን ይዞ መውጣቱ በክሱ ዝርዝር ላይ ሰፍሯል።
ከዚህም በኋላ በነሀሴ 8 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 2 ሰዓት ከ30 አካባቢ በፈተና ወቅት የተፈታኝ ተማሪዎች የመልስ መስጫ ወረቀቶች ያልሆኑና የፈተና መልስ ተቀልሞባቸው (ተሞልቶባቸው) የተዘጋጁ 33 የመልስ መስጫ ወረቀቶችን ደብቆ ፈተና ወደሚታረምበት አዳራሽ ሊገባ ሲል በተደረገ ቁጥጥር በፍተሻ የተያዘ በመሆኑ በክስ ዝርዝሩ ላይ ተገልጿል።
በተጨማሪም በተከሳሹ መኖሪያ ቤት በተደረገ ብርበራ 44 የ2015 ዓ.ም ተፈታኝ ተማሪዎች የመልስ መስጫ ወረቀቶችና 10 ደግሞ ተመሳስለው የተዘጋጁ ሀሰተኛ የመልስ መስጫ ወረቀቶች የተገኙ መሆኑን ጠቅሶ ዐቃቤ ሕግ በክስ ዝርዝሩ ላይ አስፍሯል።
በዚህ መልኩ ተከሳሹ ሥልጣንን ያለአግባብ መገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል ተከሶ ክሱ በተረኛ ችሎት እንዲደርሰው ከተደረገና ክሱ በችሎት ከተነበበ በኋላ ክስ እንዲሻሻልለት የመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያ አቅርቦ ነበር
በከሳሽ ዐቃቤ ሕግ በኩል ደግሞ ክሱ ግልጽ መሆኑ ተጠቅሶ ሊሻሻል አይገባም የሚል መልስ ተሰጥቷል።
ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን መርምሮ ክሱ እንዲሻሻል የቀረበው ጥያቄ ህጋዊ መሰረት የለውም በማለት ውድቅ አድርጓታል።
ተከሳሹም በክሱ ላይ የተጠቀሰውን የወንጀል ድርጊት አለመፈጸሙን ጠቅሶ የዕምነት ክህደት ቃሉን በመስጠቱ ዐቃቤ ሕግ ምስክሮቹ እንዲሰሙለት ጠይቋል።
ፍርድ ቤቱም የዐቃቤ ሕግን ምስክሮች ለመጠባበቅ ለህዳር 28 ቀን 2016 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። #FBC