STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
38.8K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.95K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
በግብፅ ከዛሬ ጀምሮ የትምህርት ተቋማት ተዘግተዋል!

ፕሬዘዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጥር ሲባል ትምህርት ቤቶች፣ ዩኒቨርሲቲዎች ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ሳምንታት እንዲዘጉ አዘዋል።

የግብፅ የወጣቶች እና የስፖርት ሚኒስቴር ደግሞ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ በሀገሪቱ የሚደረጉ ሁሉንም ስፖርታዊ ውድድሮችን ሰርዟል። በአሁን ሰዓት በግብፅ 110 የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ይገኛሉ።

#ግብጽ_አውሎ_ነፋስም_እየመታት_መሆኑ_ይታወቃል❗️


ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
@NATIONALEXAMSRESULT
ችሎቶቻችን ይዛወሩ?

( ከአርስቴክት ዮሐንስ መኮንን የተወሰደ )

በኮቪድ-19 ምክንያት በጭንቀት ተውጠን ባሳለፍናቸው ሁለት ወራት ብቻ በሀገራችን ከ100 በላይ ሴቶች ተገደው መደፈራቸውን በሚዲያዎች ሰምተናል።

የፖለቲካ ሥልጣንን በኃይል አስገድደው በመቀማት መንግሥታዊ ሥርዓትን ለማፍረስ የሚሞክሩትን "አሸባሪዎች" የምንቀጣበትን ቆፍጠን ያለ ሕግ አበጅተን አደብ አስገዝተናል። ልጆቻችንን፣ እህቶቻችንን፣ ጓደኞቻችንን፣ ሚስቶቻችንን እና እናቶቻችንን አስገድዶ በመድፈር ቅስማችንን ሰብረው እንደማኅበረሰብ የሚያፈርሱንን ቅንዝረኛኞች አደብ ማስገዛት አቅቶናል

የሀገራችን ቅንዝረኞች ከአንድ ዓመት ጨቅላ እስከ 80 ዓመት መነኩሲት አስገድደው ደፍረው "በሰላም" ሲኖሩ በሌሎች ሀገሮች ቢሆን ምን እንደሚጠብቃቸው ታውቁ ይሆን ?

#ቻይና
የደፋሪውን ብልቱን በቢላ ይቆርጡታል ወይም በሞት ይቀጡታል።

#አፍጋኒስታን
ጭንቅላቱን በጥይት ያፈርሱለታል ወይንም በስቅላት ይቀጡታል!

#ግብጽ
በአደባባይ በገመድ አንጠልጥለው ይሰቅሉታል!

#ሳውዲ_አረቢያ
በአጭር ቀናት በሰይፍ አንገቱን ይቀንጠሱለታል!

#ሰሜኖን ኮሪያ
በአልሞ ተኳሾች በጉልበቱ አንበርክከው በጥይት ደብድበው የገድሉታል!

#ኢራን
በአደባባይ በገመድ አንጠልጥለው ይሰቅሉታል!

ጥቂቶቹን አነሳሁ እንጂ #በሕንድ#በኤሜሬቶች #በፓኪስታን ተመሳሳይ የሞት ቅጣታቸውን የሚጎነጯት ሲሆን በርካታ የዓለማችን ሀገሮች ደግሞ ቅንዝረኞች የእድሜ ልክ እሥራት ይከናነባሉ!

በእኛስ ሀገር? ከእነኚህ ጋር #ኢትዮጵያዊ ተብሎ መቆጠር በራሱ ይቀፋል። ካልሆነ የአስገድዶ መድፈር የፍርድ ችሎቶች ከላይ ወደዘረዘርኳቸው ሀገሮች ብናዛውራቸው ምን ይመስላችኋል ?

#SHARE
ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
@NATIONALEXAMSRESULT
#ግብጽ|በግብጹ ፕሬዘዳንት አልሲሲ ላይ የተነሳው ቁጣ በመላው ግብፅ ተቀጣጥሏል ተባለ❗️

የግብፅ ፕሬዝዳንት አብደል ፈታህ አልሲሲ በግብፅ አለመረጋጋትና ትርምስ ለመፍጠር ጥረት የሚያደርጉ ሁሉ ከድርጊታቸው ቢታቀቡ ይሻላቸዋል ሲሉ ማስጠንቀቃቸውን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

ተቃዋሚዎች አልሲሲ ስልጣን እንዲለቁ ይፈልጋሉ፤ እንደ ዋና ምክያት የሚያነሱት ደግሞ ሙሰኝነታቸውን ነው፡፡

ሲሲ ለአመታት ከጦር ሀይሉ ጋር በመሆን ለፕሬዝዳንቱ ቤተሰብ እና ጓደኞች ይሆኑ ዘንድ ከተገነቡ ቅንጡ ቤቶችና ከሌሎች በርካታ የግንባታ ፕሮጀክቶች ጋር በተያያዘ የሙስና ወንጀል ፈፅመዋል እያሉ ነው፡፡

ተቃውሞው ቁጣቸው እየጨመረ በሚመጣ አመፀኞች ተቀጣጥሏል፡፡በተለይ በገጠርና ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው አካባቢዎች በርትቷል፡፡ ህገ ወጥ ግንባታዎች ይቁሙ የመሰሉ መፈክሮች እየተሰሙ ነው፡፡

እየወጡ እንዳሉ ዘገባዎች በመላው ግብፅ 40 መንደሮች ላይ የተቀሰቀሰው አመፅ የፖሊስ የሀይል እርምጃ ሊገታው አልቻለም፡፡

ኤል ሲሲ ለአመፅ የተጠሩትን ጥሪዎች ግብፃውያን ባለመስማታችሁ አመሰግናለሁ ብለዋል፡፡

በህዝቡ እየተነሱ ያሉ ጥያቄዎችን የሪፎርሙ አካል አድርጎ መንግስት እንደሚተገብራቸውም ገልፀዋል፡፡

በስደት ላይ በሚገኘው በግብፃዊው የንግድ ሰው ሞሀመድ አሊ በተደረገው ጥሪ ተቃዋሚዎች በአልሲሲ መንግስት ላይ በማመፅ ጎዳናዎችን እንደ አውሮፓውያኑ ከ መስከረም 20 ጀምሮ እያጥለቀለቁ ነው፡፡

ፖሊስ አመፆቹን ለመበተን አስለቃሽ ጭሶችን ተጠቅሟል፡፡ እንደ ሚድል ኢስት ሞኒተር ዘገባ የግብፅ የፀጥታ ሀይሎች 400 ሰዎችን ሲያስሩ 3 ሰዎች ደግሞ ተገድሏል፡፡

አመጹ ከተጀመረ ጀምሮ የተያዙ እድሜያቸው ያልደረሰ 60 ህፃናትም ከእስር እንዲፈቱ እየተጠየቀ ነው፡፡

ህፃናቱ ከ 10 እስከ 15 ዕድሜ ሲሆኑ ሁሉም አመፁ በብዛት ከሚደረግበት ላይኛው ግብፅ ናቸው፡፡

አብዛኞቹ አመፆች በመንደሮችና በገጠራማ አካባቢዎች እየተደረጉ ያሉት ካይሮንና አሌክሳንድርያን በመሰሉ ከተሞች የፀጥታ ሀይሉ ጥብቅ ጥበቃ እያደረገ ስለሆነ ነው፡፡

ባለፈው አመት መስከረም መጨረሻ ላይ ስደት ላይ ያለው ሞሀመድ አሊ ስፋት ያለው አመፅ በጠራ ወቅት በሺዎች የሚቆጠሩ ግብፃውያን በተለያዩ ትላልቅ የግብፅ ከተማ ጎዳናዎች በመውጣት የሲሲ መንግስት ስልጣኑን እንዲለቅ ጠይቀው ነበር፡፡

በስፔን በስደት ላይ የሚገኘው ሞሀመድ አሊ ፤ ሲሲ በአሁኑም አመት በአገዛዙ ላይ ግብፃውያን እንዲያምፁ ጥሪ በማድረጉ ግብፅ በአመፅ ታምሳለች፡፡

በጥሪው ሰልፈኞች በተለያዩ ግዛቶች በመውጣት ያለፉትን አመታት አመፆችንም አስታውሰዋል፡፡

አል ሲሲ በሀምሌ 2013 ነበር በወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት የሀገሪቱን የመጀመርያ በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጡትን ሞሀመድ ሙርሲን አስወግደው ስልጣን ላይ የወጡት፡፡

ምንጭ:- ኢትዮ ኤፍ ኤም

ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT