STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
40.7K subscribers
11K photos
272 videos
452 files
1.94K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
ችሎቶቻችን ይዛወሩ?

( ከአርስቴክት ዮሐንስ መኮንን የተወሰደ )

በኮቪድ-19 ምክንያት በጭንቀት ተውጠን ባሳለፍናቸው ሁለት ወራት ብቻ በሀገራችን ከ100 በላይ ሴቶች ተገደው መደፈራቸውን በሚዲያዎች ሰምተናል።

የፖለቲካ ሥልጣንን በኃይል አስገድደው በመቀማት መንግሥታዊ ሥርዓትን ለማፍረስ የሚሞክሩትን "አሸባሪዎች" የምንቀጣበትን ቆፍጠን ያለ ሕግ አበጅተን አደብ አስገዝተናል። ልጆቻችንን፣ እህቶቻችንን፣ ጓደኞቻችንን፣ ሚስቶቻችንን እና እናቶቻችንን አስገድዶ በመድፈር ቅስማችንን ሰብረው እንደማኅበረሰብ የሚያፈርሱንን ቅንዝረኛኞች አደብ ማስገዛት አቅቶናል

የሀገራችን ቅንዝረኞች ከአንድ ዓመት ጨቅላ እስከ 80 ዓመት መነኩሲት አስገድደው ደፍረው "በሰላም" ሲኖሩ በሌሎች ሀገሮች ቢሆን ምን እንደሚጠብቃቸው ታውቁ ይሆን ?

#ቻይና
የደፋሪውን ብልቱን በቢላ ይቆርጡታል ወይም በሞት ይቀጡታል።

#አፍጋኒስታን
ጭንቅላቱን በጥይት ያፈርሱለታል ወይንም በስቅላት ይቀጡታል!

#ግብጽ
በአደባባይ በገመድ አንጠልጥለው ይሰቅሉታል!

#ሳውዲ_አረቢያ
በአጭር ቀናት በሰይፍ አንገቱን ይቀንጠሱለታል!

#ሰሜኖን ኮሪያ
በአልሞ ተኳሾች በጉልበቱ አንበርክከው በጥይት ደብድበው የገድሉታል!

#ኢራን
በአደባባይ በገመድ አንጠልጥለው ይሰቅሉታል!

ጥቂቶቹን አነሳሁ እንጂ #በሕንድ#በኤሜሬቶች #በፓኪስታን ተመሳሳይ የሞት ቅጣታቸውን የሚጎነጯት ሲሆን በርካታ የዓለማችን ሀገሮች ደግሞ ቅንዝረኞች የእድሜ ልክ እሥራት ይከናነባሉ!

በእኛስ ሀገር? ከእነኚህ ጋር #ኢትዮጵያዊ ተብሎ መቆጠር በራሱ ይቀፋል። ካልሆነ የአስገድዶ መድፈር የፍርድ ችሎቶች ከላይ ወደዘረዘርኳቸው ሀገሮች ብናዛውራቸው ምን ይመስላችኋል ?

#SHARE
ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
@NATIONALEXAMSRESULT