STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
39.8K subscribers
11K photos
272 videos
452 files
1.94K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
ለአዲስ አበባ ከንቲባ እና የቀበሌ ካድሬዎች ስልክ መግዣ 140,000 ( አንድ መቶ አርባ ሺህ ብር) ተመድቧል።

ስንት ሰው ነበር በረሃብ ያለቀው?
የሀገራችንን መጨረሻ ያሳምርልን😔

@NATIONALEXAMSRESULT
የተማሪ ሊዲያ አበራ ጉዳይ ...

በደቡብ ክልል ሀላባ ቁሊቶ ከተማ በሚገኘው የሀለባ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ10ኛ ክፍል ተማሪዋ #ሊዲያ_አበራ የካቲት 22 ቀን 2015 ዓ/ም ከትምህርት ቤቷ ተወስዳ ከታሰረች በኋላ ጉዳዩ የማኅበራዊ ሚዲያ መነጋገሪያ ሆኗል።

ሊዲያ ከታሰራች በኋላ ለ5 ቀናት ፍርድ ቤት ሳትቀርብ መቆየቷን እና በእስር ቤት ውስጥ የሰብአዊ መብት ጥሰት እንደተፈጸመባት አባቷ አቶ አበራ ሻሞሮ እንዲሁም ጠበቃዋ አቶ አበባየሁ ጌታ እንዳገለፁለት ቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት በድረገፁ አስነብቧል።

በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የሕግ እና ፖሊስ ሥራ ክፍል ዳይሬክተር ወ/ሮ ታሪኳ ጌታቸው የ14 ዓመቷ ተማሪን ጉዳይ ኮሚሽኑ እየተከታተለ መሆኑን ገልፀዋል።

የሊዲያ እስር ምክንያት ምንድን ነው ?

በሀላባ ቁሊቶ 30 ዓመታት የኖሩት አቶ አበራ ሻሞሮ፣ ሁለት ሴት ልጆች የሃላባ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የ10ኛ እና 11ኛ ክፍል ተማሪዎች ናቸው።

ሊዲያ የካቲት 22/2015 ዓ.ም. በመደበኛ ትምህርቷ ላይ ተገኝታ ነበር።

በዚያን ዕለት ሊዲያ በምትማርበት ክፍል ውስጥ አንዲት ተማሪ መውደቋ የነገሮች ሁሉ መነሻ ነው።

👉 ጉዳዩን በተመለከት ሰሜ አይጠቀስ ያሉ የሀላባ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህር የሰጡት ቃል ፦

" ተማሪዋ የወደቀችው ሊዲያ መተት አሰርታባት ነው በሚል በተፈጠረ ግርግር የትምህርት ቤቱ ሥራ በጊዜያዊነት ተስተጓግሎ ነበር።

ከጥቂት ጊዜ በኋላም ፖሊሶች ወደ ትምህርት ቤቱ መጡ።

ያለምንም መጥሪያ...ፖሊሶች መጥተው ከነዩኒፎርሟ፣ ከነደብተሯ እያለቀሰች” ከትምህርት ቤት ወሰዷል።

ይህ በጣም አሳሳቢ እና የሚያሳዝን ነው። "

👉 የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ ወንድሙ መርጋም የሰጡት ቃል ፦

" በዚያን ዕለት ሌላም ተማሪ መውደቋ ለሊዲያ እስር ምክንያት ሆኗል። ሆኖም ታዳጊዋ ላይ ቀደም ብሎ ተማሪዎች እና ወላጆቻቸው አቤቱታ ያቀርቡባት ነበር።

ከእሷ ጋር አብረን ምግብ በልተናል የሚሉ 8 ተማሪዎች ወላጆች ቅሬታ አቅርበዋል፤ ትምህርት ቤቱ እርምጃ ይውሰድ የሚል ጫናም እየበረታ መጥቶ ነበር።

በዚህ ሳቢያ ትምህርት ቤቱ የቅሬታ አቅራቢ ተማሪዎች ወላጆች ጉዳዩን ወደ ፖሊስ ጣቢያ እንዲወስዱ አድርጓል።

በትምህርት ቤት ውስጥ ከእሷ [ሊዲያ] ጋራ ግንኙነት ነበረን፣ ምግብ በልተናል ያሉ 8 ተማሪዎች ወድቀዋል ፤ ይሄ ነገር ከእሷ ጋር ግንኙነት አለው? ወይስ የለውም ? የሚለውን ለማጣራት ነው ክስ ተመስርቶ በዚያው እየታየ ያለው።

በዕለቱ ተማሪዎች ስለተረበሹ እና እርምጃ መውሰድ ስላለብን...ለፖሊስ ልጅቷን በአፋጣኝ ይዛችሁ ብትሄዱ የተሻለ ይሆናል ያልነው። "

ሆኖም ይህ በሊዲያ ላይ የቀረበው ቅሬታ በእህቷ ላይ አልተሰማም ተብሏል።

👉 የሊዲያ ጠበቃ አቶ አበባየሁ ጌታ ፦

" ሊዲያ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ከተወሰደች በኋላ ከሕግ ውጪ ለ5 ቀናት ፍርድ ቤት ሳትቀርብ ታስራ ቆይታለች።

ከአምስት (5) ቀናት በኋላ ሃላባ መጀመሪያ ፍርድ ቤት ካለ ጠበቃ ጋር ቀርባ የ14 ቀናት ቀጥሮ ለምርመራ ከተሰጠ በኋላ ወደ ሃላባ ቁሊቶ ማረሚያ ቤት ተወስዳለች።

ይህ ድርጊት ከሕግ ጋር የሚጻረር ነው። ለአካለ መጠን ያልደረሰ ሰው በወንጀል ሲጠረጠር ከቤተሰቦቹ ጋር ቆይቶ ለምርመራ ሲፈልግ እንደሚጠራ በሕግ ተደንግጓል።

በተጠረጠረችበት ወንጀል #ጥፋተኛ ሆና ብትገኝ እንኳን የማረሚያ ቤት እስር እንደማይፈረድባት የወንጀል ሕጉ ያስቀምጣል።

በተሰጠው የጊዜ ቀጠሮ ላይ ለሃላባ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ተጠይቋል። ይግባኙም የታዳጊዋ አያያዝ እንዲሁም ለቀናት በእስር ላይ እንድትቆይ መደረጉ ተገቢ አይደለም የሚል ነው።

የሊዲያ ከሳሾች ጉዳት ደርሶብናል ያሉት ተማሪዎች ወላጆች ሲሆኑ ልጆቻችንን ላይ ባደረገችባቸው መተት/ድግምት አፍዝዛ ጉዳት አድርሳባቸዋለች የሚል ማመልከቻ አቅርበው ነው የተከሰሰችው።

ክሱ ተሰራ በተባለው መተት / ድግምት ተጎድተው ሕክምና ላይ የሚገኙ ተማሪዎች አሉ ይላል።

ሊዲያም ባለፈው አርብ አግኝተናት አናግረናት ነበር። በወቅቱም ንቅሳት ካለብሽ እናይሻለን በሚል እርቃኗን እንደፈተሿት ተናግራለች።

ሊዲያ እስሩ በተፈጸመባቸው የመጀመሪያዎቹ ቀናት ታለቅስ ነበር። አሁን መምህራን፣ የትምህርት ቤት ጓደኞቿ እና ሌሎች ሰዎች እየጠየቋት በመሆኑ በጥሩ ሞራል ላይ ትገኛለች።

በኢትዮጵያ ሕግ ድግምት ፣ ጥንቆላ፣ እኔ አውቅልሃለሁ ባይነት፣ መንፈስ መጥራት እና መሰል ወንጀሎች የሚዳኙበት ድንጋጌ አለ።

ሆኖም እነዚህ ወንጀሎች ጥቅምን ለማግኘት በማሰብ እና የሌላን ሰው ገንዘብ ለማግኘት የሚፈጸም እንጂ የግል ጥቅም ምን እንደሆነ በማታውቅ ታዳጊ ልጅ፣ ገንዘብ ያለበትን እጠቁማቸኋለሁ ባላለችበት ሁኔታ. . . [ሕጉ] ይህንን ሁኔታ ሊቀበለው አይችለም።

ሰዎችን ለማፍዘዝ የተለያዩ ዱቄት መሰል ምርቶችን ማምረት፣ መሸጥ እና ማሰተላለፍ ወንጀል ነው ሊዲያ ግን ይህንን ሁሉ አላደረገችም።

በማኅበራዊ ሚዲያዎች ለሕይወቷ የሚያሰጉ ዛቻዎች እና ማስፈራሪያዎች እየተዘዋወሩ ነው። በደረሰባት የሥነ ልቦና ጫና ምክንያት ከሥነ ልቦና ጫናው ተላቃ ትምህርቷን ትቀጥላለች ማለት ይከብዳል። "

👉 የሊዲያ አባት አቶ አበራ ሻሞሮ ፦

" ... የልጄ እስር የተወረወረ ዱብ ዕዳ ነው። ልጆቼ በትምህርታቸው ከአጠቃላይ ተማሪ ተሸላሚ ናቸው። እያጠኑ የሚያድሩ ናቸው።

የተቀረውን የትምህርት ጊዜ ሌላ አካባቢ እንዲጨርሱ እየሞከርኩ ነው።

ልጄም በማረሚያ ቤት ባነጋገርኩበት ወቅት መቼ ነው ከዚህ የምወጣው? ብላ ጠይዋኛለች። "

👉 ጉዳዩን በተመለከተ የሀላባ ዞን የቁሊቶ ከተማ አሰተዳደር ሰላም እና ፀጥታ ጽህፈት ቤት ከቀናት በፊት በፌስቡክ ገጹ ይህን ብሏል ፦

" ... በከተማችን በሙሰሊም ሴት ተማሪዎች ላይ ድግምት አሲራለች ተብላ በታሰረች ተማሪ ሊዲያ አበራ በተያያዥ ጉዳይ በአቶ ናስር በሀላባ በዚህም ጉዳይ መሰል ተያያዥነት ያላቸው ግለሰቦችም ጭምር ተይዘው በምርመራ ሂደት በማረሚያ መኖራቸው ይታወቃል።

በታሰሩበት ኬዝ እንዳንድ አክቲቪስቶች ጉዳዩን ወደ ሓይማኖታዊ ለማስመሰል በማጦዝ የሚሞክሩ እንዳላችሁ በማሕበራዊ ሚዲያ እየታየ ያለው ሁኔታ በፖሊስ እና በምርመራ ባለሙያዎች ሂደቱ እየተጣራና ማንም በተጠረጠረበት ወንጀል ታሰሮ አንደሚጣራ የሚታወቅ  ስለሆነ ሁሉም ማህበረሰብ በትዕግስት እንዲጠብቅ ስንል እናሳስባችኋለን።

#ይህንን_ተላልፎ የሚገኝ ማንኛውንም  አካል በህግ የምንጠይቅ መሆኑን እናውቃለን። "

የመረጃ ምንጭ ፦ ቢቢሲ የአማርኛው አገልግሎት / የሀላባ ዞን የቁሊቶ ከተማ አሰተዳደር ሰላም እና ፀጥታ ጽህፈት ቤት ናቸው።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#DillaUniversity

በ2015 ዓ.ም በዲላ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የአቅም ማሻሻያ (ሪሚዲያል) ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ መጋቢት 14 እና 15/2015 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የምዝገባ ቦታ፡-

➧ የማህበራዊ ሳይንስ መስክ ተማሪዎች በሐሴዴላ ግቢ
➧ የተፈጥሮ ሳይንስ መስክ ተማሪዎች በኦዳያአ ግቢ

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሄዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➧ የ8ኛ ክፍል ውጤት ዋናውና ኮፒው፣
➧ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➧ አራት 3×4 ፎቶግራፍ፣
➧ የሌሊት አልባሳት፣
➧ የስፖርት ትጥቅ፡፡

ትምህርት የሚጀመረው ➧ መጋቢት 18/2015 ዓ.ም

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#DebarkUniversity

ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡለትን የአቅም ማሻሻያ (ሪሚዲያል) ፕሮግራም ተማሪዎች መቀበል ጀምሯል፡፡

ዩኒቨርሲቲው የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም ተማሪዎች መጋቢት 05 እና 06/2015 ዓ.ም ወደ ተቋሙ እንዲገቡ ጥሪ ማድረጉ ይታወቃል፡፡

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ከ3 ሺህ በላይ የሪሚዲያል ተማሪዎች ይቀበላል።

ዩኒቨርሲቲው ሚዛን አማን ከተማ እና ቴፒ ከተማ በሚገኙት ሁለት ካምፓሶች ተማሪዎቹን መጋቢት 08 እና 09/2015 ዓ.ም እንደሚቀበል ተገልጿል።

የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ሚዛን-አማን ከተማ በሚገኘው ዋናው ግቢ እንዲሁም የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ቴፒ ከተማ በሚገኘው ቴፒ ግቢ በመገኘት ሪፖርት አድርጉ ተብሏል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#DambiDolloUniversity

በ2015 ዓ.ም በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ተማሪዎች የመግኒያ ጊዜ መጋቢት 19 እና 20/2015 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሄዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➧ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ፣
➧ ከ8-12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና 2 ኮፒ፣
➧ ስምንት 3×4 ፎቶግራፍ፣
➧ የሌሊት አልባሳት፣
➧ ማጣቀሻ መጻሕፍት፡፡

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#ተራዝሟል

በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የአቅም ማሻሻያ (ሪሚዲያል) ፕሮግራም ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜን #በቀናት ተራዝሟል፡፡

የምዝገባ ጊዜ መጋቢት 11 እና 12/2015 ዓ.ም ይከናወናል ተብሎ የነበረ ቢሆንም ባልተገለፀ ምክንያት ወደ መጋቢት 15 እና 16/2015 ዓ.ም መራዘሙን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ቀን 6/7/2015 ዓ.ም

#ማስታወቂያ!

በ2014 ዓ.ም በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሀገራቀፍ ፈተና የላቀ ውጤት አምጥታችሁ የውጪ ሀገር የትምህርት እድል /Scholarship / ለተሰጣችሁ ተማሪዎች

በ2014 ዓ.ም በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሀገራቀፍ ፈተና የላቀ ውጤት አምጥታችሁ የውጪ ሀገር የትምህርት እድል/Scholarship / የተሰጣችሁ 273 ተማሪዎች የውጪ ሀገር ትምህርቱ የሚጀመረዉ ከመስከረም 2016 ዓ.ም ጀምሮ በመሆኑ ቀደም ሲል ወደተመደባችሁባቸው ዩኒቨርስቲዎች እንድትገቡ እናሳስባለን፡፡

ለውጪ ሀገር ትምህርታችሁ የሚያግዝ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርትና ሌሎች የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ከተመደባችሁባቸው ዩኒቨርስቲዎች ጋር በመነጋገር የሚፈጸም ይሆናል፡፡

ማስታወሻ፤- በዚህ ጉዳይ በተናጠል ወደ ትምህርት ሚኒስቴር የሚመጣ ተማሪ የማናስተናግድ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር!

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
"ጅል ሰው በንግግሩ ይታወቃል ብልህ ሰው ደግሞ በዝምታው" ፓይታጎረስ

እንግዲህ ምን እንንላለ? ዝም!😔
ፍጻሜያችንን ያሳምርልን

@NATIONALEXAMSRESULT
#MoE

በ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው የRemedial ፕሮግራም ለመከታተል #መቅደላአምባ_ዩኒቨርስቲ የተመደቡ ተማሪዎች የተደረገ ማስተካከያ ስላለ ምደባቸውን እንደገና ገብተው እንዲያሁ ትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
#MoE በ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው የRemedial ፕሮግራም ለመከታተል #መቅደላአምባ_ዩኒቨርስቲ የተመደቡ ተማሪዎች የተደረገ ማስተካከያ ስላለ ምደባቸውን እንደገና ገብተው እንዲያሁ ትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል። የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን @NATIONALEXAMSRESULT Click here for advertisement…
#Update

መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ተመድበው የነበሩና በትምህርት ሚኒስቴር ወደ ወልድያ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ የአቅም ማሻሻያ ሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የመግቢያ ጥሪ ተደርጓል።

በዚህም በ2015 የትምህርት ዘመን ወደ ወልድያ ዩኒቨርሲቲ በድጋሜ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ መጋቢት 07 እና 08 /2015 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሄዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➧ የ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
➧ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➧ አራት 3×4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➧ የሌሊት አልባሳት፣
➧ የስፖርት ትጥቅ፣

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
Education and Training Policy Yekatit 2015 Final.pdf
7.2 MB
#ቢያስፈልግዎ

አዲሱ የትምህርትና ሥልጠና ፖሊሲ

አዲሱ ፖሊሲ በሚኒስትሮች ም/ቤት ከፀደቀበት ከየካቲት 20/2015 ዓ.ም ጀምሮ በሥራ ላይ ውሏል፡፡

ፖሊሲው በትምህርት ሚኒስቴር እና በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የተዘጋጀ ሲሆን ለ28 ዓመታት ሲተገበር የቆየውን የትምህርትና ሥልጠና ፖሊሲ የሚተካ ነው።

ፖሊሲው የመምህራን የሙያ ደረጃ፣ የተማሪዎችን የክፍል ዕርከኖች እንዲሁም በሥርዓተ ትምህርት የሚካተቱ ቋንቋዎችን ቀይሯል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
Chemistry Course Content.pdf
754.9 KB
#For Remedial Students Natural Science Courses.

Please share it for remedial students.


የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
Geography Remedial Module for Grade 12 students.pdf
447.2 KB
#For Remedial Students Social Science Courses.

Please share it for remedial students.


የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot