STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
38.8K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.95K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ይገኛሉ ፦

#WolaitaSodoUniversity

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ እለተ ዛሬ 29 ቀን 2013 ዓ.ም በመደበኛ እና በተከታታይ የትምህርት መርሃ-ግብር በቅድመ ምረቃ እና በድህረ ምረቃ ያሰለጠናቸውን 5,310 ተማሪዎችን እያስመረቀ ይገኛል።

#WoldiaUniversity

የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ላለፋት ዓመታት በተለያዩ ትምህርት መስኮች ሲያሰለጥናቸው የቆዩ ተማሪዎቹን ዛሬ በሼህ ሙሃመድ ሁሴን አሊ ኣላሙዲን ስታዲየም እያስመረቀ ይገኛል።

በመደበኛው፣ በተከታታይ እና በክረምት መርሃግብር ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ 2785 የሚሆኑ እጩ ተመራቂ ተማሪዎችን ነው እያስመረቀ የሚገኘው።

ከጠቅላላ ተመራቂዎች ውስጥም 926 ሴቶች ናቸው።

#BahirdarUniversity

ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መድኮች ሲያስተምራቸው የቆያቸውን 5,117 ተማሪዎችን በፔዳ ካምፓስ በማስመረቅ ላይ ይገኛል።

4,203 የሚሆኑት የመጀመሪያ ዲግሪ (ቅድመ ምረቃ ፕሮግራም) የተማሩ ናችው። 759 በሁለተኛ ድግሪይ የተማሩ፣10 የፒኤችዲ ተመራቂዎች ይገኙበታል።

በሌላ በኩል በህክምና ስፔሻሊቲ የተመረቁ 40 የሚሆኑ ሰልጣኞች ዛሬ እየተመረቁ ነው።

ከአጠቃላይ ተመራቂዎቹ ውስጥ 1,623 የሚሆኑት ሴቶች ናቸው።

#DebarkUniversity

ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመጀመሪያ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 773 ተማሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ በማስመረቅ ላይ ይገኛል፡፡

#MizanTepiUniversity

ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ከ2 ሺህ በላይ ተማሪዎችን እያስመረቀ ይገኛል።

በሌላ በኩል፦

ሂልኮ የኮምፒዩተር ሳይንስ እና ቴክኖሎጅ ኮሌጅ ነገ ጥር 29/2013 ዓ/ም ተማሪዎቹን ያስመርቃል።

@NATIONALEXAMSRESULT
#DebarkUniversity

ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የ3ኛ እና 4ኛ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች የ2014 ዓ.ም የአንደኛ ሴሚስተር ምዝገባ መጋቢት 08 እና 09/2014 ዓ.ም እንደሚከናወን አስታውሷል።

ዩኒቨርሲቲው በተጠቀሱት ቀናት ብቻ የትራንስፖርት አገልግሎት ከጎንደር እስከ ደባርቅ እንደሚሰጥ አሳውቋል።

በመሆኑም ተማሪዎቹ ጎንደር ፒያሳ መስቀል አደባባይ በመገኘት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን እንደሚችሉ ገልጿል።


ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#DebarkUniversity

ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የ3ኛ እና 4ኛ ዓመት መደበኛ ተማሪዎቹን መቀበል ጀምሯል።

ተቋሙ የ3ኛ እና 4ኛ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች የ2014 ዓ.ም የአንደኛ ሴሚስተር ምዝገባ መጋቢት 08 እና 09/2014 ዓ.ም እንደሚከናወን በመግለጽ ጥሪ ማድረጉ ይታወሳል።

ዩኒቨርሲቲው ኮሚቴ በማቋቋም እና ከጎንደር እስከ ደባርቅ የትራንስፖርት አገልግሎት በማመቻቸት ተማሪዎቹን በመቀበል ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#DebarkUniversity

በ2014 ዓ/ም ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ከሰኔ 8-9 ቀን 2014 ዓ/ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#DebarkUniversity

ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 326 ተማሪዎች ነገ ያስመርቃል።

ተመራቂዎቹ በመደበኛ እና በቅዳሜና እሁድ መርሃ ግብሮች በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

ከተመራቂዎቹ 92 ተማሪዎች በመደበኛ መርሃ ግብር በኮምፒውተር ሳይንስ እና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የትምህርት መስኮች ትምህርታቸውን ተከታትለዋል።

ቀሪዎቹ 234 ተማሪዎች በቅዳሜና እሁድ መርሃ ግብር ትምህርታቸውን የተከታተሉ መሆናቸውን የዩኒቨርሲቲው የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር ሰውዓለም ሙሌ ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ገልጸዋል።

በ2010 ዓ.ም የመማር ማስተማር ሥራውን የጀመረው ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ፤ ሦሥተኛ ዙር መደበኛ ሰልጣኞቹን ነው ነገ የሚያስመርቀው።

ተማሪ ነክ መረጃዎች ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT
#DebarkUniversity

የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ቅድመ-ምረቃ መደበኛ ነባር ተማሪዎች የሆናችሁ የ2015 ዓ.ም የት/ዘመን የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀናት #ህዳር_1_እና_2፣ 2015 ዓ.ም መሆኑን እየገለፅን።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#DebarkUniversity

ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ በአስር የሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች ትምህርት መስጠት ሊጀምር ነው።

በቱሪዝምና ሆስፒታሊቲ አስተዳደር የሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም አዲስ ከሚጀመሩት አስር የማስተርስ ፕሮግራሞች ውስጥ አንዱ ነው።

ዩኒቨርሲቲው በተፈጥሮ እና ኮምፒዩቴሽናል ሳይንስ፣ በቢዝነስ እና ኢኮኖሚክስ እንዲሁም በግብርና እና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጆች ነው የማስተርስ ፕሮግራሞቹን የሚጀምረው።

አዲስ የሚከፈቱት የሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች፦

• MSc in Mathematics
• MSc in Chemistry
• MSc in Physics
• MSc in Biology
• MSc in Statistics

• MSc in Accounting and Finance
• MBA in Management
• MA in Tourism and Hospitality Management

• MSc in Soil Science
• MSc in Animal Production

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#DebarkUniversity

ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ በ2015 ዓ.ም በተቋሙ ለተመደቡ የአቅም ማሻሻያ (ሪሚዲያል) ፕሮግራም ተማሪዎች የትራንስፖርት አገልግሎት አዘጋጅቷል፡፡

ዩኒቨርሲቲው የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም ተማሪዎች መጋቢት 05 እና 06/2015 ዓ.ም ወደ ተቋሙ እንዲገቡ ጥሪ ማድረጉ ይታወቃል፡፡

በተጠቀሱት ቀናት ጎንደር ከተማ አዘዞ አይራ መገንጠያ እና መስቀል አደባባይ ላይ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ሰርቪሶች መዘጋጀታቸውን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#DebarkUniversity

ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡለትን የአቅም ማሻሻያ (ሪሚዲያል) ፕሮግራም ተማሪዎች መቀበል ጀምሯል፡፡

ዩኒቨርሲቲው የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም ተማሪዎች መጋቢት 05 እና 06/2015 ዓ.ም ወደ ተቋሙ እንዲገቡ ጥሪ ማድረጉ ይታወቃል፡፡

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#DebarkUniversity

ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ በ2015 የትምህርት ዘመን በተለያዩ የሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች ለመማር የተመዘገባችሁ አመልካቾች ትምህርት የሚጀምረው ነገ ሚያዝያ 29/2015 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል፡፡

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot