STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
40.7K subscribers
11K photos
272 videos
452 files
1.94K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ነው።

#ጎንደር_ዩኒቨርሲቲ

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ 6 ሺህ 574 ተማሪዎችን ዛሬ እያስመረቀ ይገኛል፡፡

በ87 የመጀመሪያ እንዲሁም በ67 የድህረ ምረቃ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ነው የሚያስመርቀው፡፡

በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ የውኃ መስኖ እና ኢነርጅ ሚኒስትር ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ተገኝተዋል፡፡

#ደብረታቦር_ዩኒቨርሲቲ

የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በተለያየ የትምህርት መስክ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎቹን እያስመረቀ ይገኛል።

ዩኒቨርሲቲው ለስምንተኛው ዙር ነው ተማሪዎቹን እያስመረቀ የሚገኘው።

#ቦንጋ_ዩኒቨርሲቲ

የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ 2ኛ Batch ተማሪዎች በዛሬው ዕለት እያስመረቀ ይገኛል።

#ደብረብርሃን_ዩኒቨርሲቲ

የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በ13ኛ ዙር በተለያዩ መርሃ ግብሮች ያስተማራቸውን በ2ኛ ዲግሪ 231 ተማሪዎችን እና በ3ኛ ዲግሪ አንድ ተማሪ እያስመረቀ ነው።

#ኮተቤ_ሜትርፓሊታን_ዩኒቨርሲቲ

የኮተቤ ሜትርፖሊታን በተለያየ የትምህርት ክፍሎች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመርቋል።

ዩንቨርሲቲው በዛሬው እለት ያስመረቃቸው በመጀመሪያና ሁለተኛ ድግሪ ወንድ 448 ሴት 135 በድምሩ 583 ተማሪዎች ናቸው።

#ቅድስተ_ማርያም_ዩኒቨርሲቲ

የቅድስተ ማርያም ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች በድህረ ምረቃ ያሰለጠናቸውን 636 ተማሪዎችን በኦሮሞ ባህል ማዕከል አስመርቋል።

አጠቃላይ ከተመረቁት ውስጥ 322 ወንዶች 314 ደግሞ ሴቶች ናቸው።

#ሀራምቤ_ዩኒቨርሲቲ
ሀራምቤ ዩኒቨርሲቲ በተለያየ ትምህርት መስክ ያሰለጠናቸውን 3683 ተማሪዎችን እያስመረቀ ነዉ።
ዩኒቨርሲቲው ለ18ኛ ዙር ነው ተማሪዎችን እስመረቀ የሚገኘው።

[ኢፕድ፣ ዋልታ፣ አሚኮ፣ የዩኒቨርሲቲዎች ገፅ]

መረጃዎችን ለማግኘት
@NATIONALEXAMSRESULT
የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ጥሪ ፦

በ2014 ዓ/ም የመጀመሪያ ዓመት አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ሚያዚያ 29 እና 30 / 2014 ዓ/ም ሲሆን ተማሪዎች በአካል ተገኝታችሁ ምዝገባ እንድታከናውኑ ጥሪ ቀርቧል።

#ደብረብርሃን_ዩኒቨርሲቲ #Tewabe


ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
Fake news Alert‼️
#ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ
ደብረብርሃን ዩንቨርስቲ በሪሚዳል ፕሮግራም የተመደቡ ተማሪዎችን የካቲት 29-30 ጥሪ አድርጓል በሚል የዩንቨርስቲውን ሎጎ እና ማህተም በማመሳሰል የውሸት መረጃ እያሰራጩ ተመልክቻለሁ። በመሆኑም ዩኒቨርሲቲው እስካሁን ጥሪ ያላደረገ በመሆኑ የተመደባችሁ ተማሪዎች በትዕግሥት እንድጠብቁ ከዩኒቨርስቲው ያገኘሁት መረጃ ይጠቁማል።
ከውሸት መረጃ እንጠንቀቅ።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot