STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
38.8K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.95K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
Audio
#ጎንደር_ዩኒቨርሲቲ

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሁከት ለመፍጠርና የመማር ማስተማሩን ሂደት ለማደናቀፍ ሲሞክሩ ተይዘው ከነበሩ 40 ተጠርጣሪዎች መካከል 21ዱ በምክርና በተግሳፅ ሲለቀቁ 19ኙ ተጨማሪ ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አስታወቀ።

(DW Radio )

https://t.me/joinchat/AAAAAFOUbJV0CPRu9x45bQ
#ጎንደር_ዩኒቨርሲቲ

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከክልል፣ ከዞን እና ከከተማ አስተዳደር የሚመለከታቸው አካላት፣ ከሀገር ሽማግሌዎች፣ ከሀይማኖት አባቶች፣ ከተለያዩ አደረጃጀት ተወካዮች፣ከተማሪ ተወካዮች እንዲሁም ከዩኒቨርሲቲው ካውንስል አባላት ጋር ሰፊ ውይይት አድርጊያለሁ ውይይቱን ተከትሎም ዛሬ ማለትም ታህሳስ 13/2012 ዓ.ም ትምህርት ተቋርጦባቸው በነበሩ ሁሉም ግቢዎች መደበኛ የመማር ማስተማር ስራው ተጀምሯል ሲል ገልጿል፡፡

(ጎንደር ዩኒቨርሲቲ)

@NATIONALEXAMSRESULT
https://t.me/joinchat/AAAAAFOUbJV0CPRu9x45bQ
Audio
#ጎንደር_ዩኒቨርሲቲ

ትምህርት አቋርጠው የነበሩ ከ7ሺህ በላይ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲው ያወጣውን ማስጠንቀቂያ ተቀብለው ወደ ትምህርት ገበታቸው መመለሳቸውን የጎንደር ዩኒቨርሲቲው አስታወቋል።

#ባህርዳር_ዩኒቨርሲቲ

ለመማር ፈቃደኛ አልሆኑም የተባሉ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ተማሪዎች ደግሞ ከዩኒቨርሲቲው ተሰናብተዋል። ተማሪዎቹ ግን የተሰናበትነው የተቀጡ ተማሪዎች ይመለሱ፣ በሌሎች ክልሎች ያሉ ተማሪዎች መብት ይጠበቅ በማለታችን ነው ይላሉ።

(DW)

@NATIONALEXAMSRESULT
https://t.me/joinchat/AAAAAFOUbJV0CPRu9x45bQ
ጎንደር_ዮንቨርሲቲ ዛሬ 22/2012 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ በተለያየ ደረጃ ተሳታፊ ሆነው በተገኙ ተማሪዎች፣ መምህራን፣ የአስተዳደር ሰራተኞች እና የጤና ባለሙያ ከቀላል የፅሁፍ ማሰጠንቀቂያ እስከ ሙሉ በሙሉ ከስራ እና ከትምህርት የማሰናበት እርምጃ ወስዷል፡፡

ከዚህም ውስጥ 52 ተማሪዎችን ያባረረ ሲሆን በዚህም 2 ተማሪዎች አንድ አመት ከትምህትር ገበታቸው እንዲታገዱ፣ 39 ተማሪዎች ለሁለት አመት ከትምህርት ገበታቸው እንዲታገዱ እንዲሁም 11 ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ከትምህርት ገበታቸው(ከዩኒቨርሲቲው) እንዲሰናበቱ ተወስኗል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ለ7 መምህራን ቀላል የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ፣ ለ3 መምህራን የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ፣ ለ3 መምህራን እና ለ8 የአስተዳደር ሰራተኞች እንዲሁም የጤና ባለሙያ ሙሉ በሙሉ ከስራ እንዲሰናበቱ ተወስኗል፡፡
@nationalexamsresult
Via #ጎንደር ዩኒቨርሲቲ
@nationalexamsresult
የዩኒቨርሲቲዎች መረጃ ለ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች

#የኔ_ዩኒቨርሲቲ _ይሄን_ይመስላል


#ጎንደር _ዩኒቨርሲቲ

መገኛ ፡ ፥ ከአዲስ አበባ በስተሰሜን 723 ኪ.ሜ ሰሜን ጎንደር ዞን ጎንደር ከተማ ውስጥ የምትገኝ ጥንታዊት ከተማ።

#የአየር ሁኔታ፡
ባብዛኛው ሞቃታማ አመሻሽ ላይ በጣም ነፋሻማ

#ስለከተማው ሁኔታ

በታሪክ የታጨቀች፣ ድንቅ ተፈጥሮ ያላት፣ የሐይማኖት ሀገር፣ህዝቦቿ ሰው ወዳድና አክባሪ ናቸው።

በውስጡ ያሉ ግቢዎች ፡

1. #አፄ ቴዎድሮስ ግቢ
የሚሰጣቸው department
-Natural & Computitional science
-geology
-Computer science ,Information Science
-Veternary medicine
-Buisness and Econimics ...etc

2. #ማራኪ ግቢ
የሚሰጣቸው departement
All social science fields like..
- School of Law
-social science & Humanities
-Theatrical and FineArts
-Journalism
-ግእዝ
-ሙዚቃ etc...
3. #አፄ ፋሲል ግቢ

all Engineering fields
-Civil engineering
-Mechanical engineering
-Hydraulic engineering
-Electrical engineering
-Biomedical engineering &
-Architecture

3. #ሕክምናና ጤና ሣይንስ ኮሌጅ
-Medicine
-HO
-Other health science(በውስጡ ብዙ ዲፓርትመንቶች እንዳሉ ሆኖ)

5. #ጠዳ ግቢ
የግብርና ካምፓስ ነው

የጤና ፊልዶች ላይ ፍላጎት ያላቹ ተማሪዎች #ጎንደር ዩኒቨርስቲ ቀዳሚ ተመራጭ ነን 😂 because we are popular in Haelth science Fields

WiFi ፦ Excellent

👉ማሳሰቢያ :
ከሎካሎች ጋር ያላችሁ ቀረቤታ በመከባበር ላይ የተመሰረተ ይሁን። እሳፈጣለው ሙድ እይዛለው እዛ አይሰራም ። (😂 የግል አስተያየት ነው)
በተረፈ ይመቻቹ M ነኝ 6ኛ አመት ሜዲሲን ተማሪ

የእርስዎን ዩኒቨርሲቲ መረጃ ደግሞ በ @MYUNIVERSITYINFOBOT ላይ በድምጽ ወይም በጽሑፍ ( ፎቶዎችም ብትልኩ ይደርሰናል) ይላኩልን።

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
የዩኒቨርሲቲዎች መረጃ ለ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች

#የኔ_ዩኒቨርሲቲ _ይሄን_ይመስላል

#ጎንደር_ዩኒቨርሲቲ

መገኛ፡ ጎንደር
በውስጡ ያሉ ግቢዎች፡
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በዋናነት አምስት ጊቢዎች አሉት

1, GC ግቢ <health science college>
2. Fasil ግቢ <Engineering science>
3. ቴዲ <all natural science> except eng. Science, health science, and agr. Science.
4. ማራኪ ግቢ< all social science>
5, ጤዳ ግቢ<agricultural science>

ማራኪ ቴዲ ቨተርነሪ እና ፋሲል ጊቢ የተያያዙ ጊቢዎች ሲሆኑ ጠዳ እና Health ጊቢ የተለየ ቦታ ነው ያሉት ፡፡

የአየሩ ሁኔታ፡ ጎንደር በሰሜን ኢትዮጵያ ስለምትገኝ በጣም ከፍታ ቦታ ላይ ነች። ይህም የጎንደርን አየር ቀን ቀን ፀሐያማ መሸት ሲል ደግሞ ብርዳማ እንዲሆን አድረጎታል ሶ ከቤታችሁ ስትመጡ ሹራብ ነገር ብትይዙ ይመረጣል።

ጎንደር ከአድስ አበባ በ 727km ርቀት ላይ ትገኛለች። ከአድስ ጎንደር በ ሀገር አቋራጭ ባስ ማለትም selam bus, habasha bus, zemen bus,golden bus እና በTata፨ bus ከተጓዝን በአንድ ቀን እንደርሳለን።
ወይም ደግሞ ከመናሀርያ ወደ ባህርዳር ተጉዘን ከዛም ባህርዳር አድረን ወደ ጎንደር መምጣት እንችላለን ነገር ግን የመጀመሪያውን ምርጫ ብትጠቀሙ ይሻላል፤ ወጪ እንዳይበዛባችሁም ከእንግልት ለመዳንም ከላይ የተዘረዘሩትን ባሶች ብትጠቀሙ አሪፍ ነው።
በplane መምጣት ለምትፈልጉ ደግሞ የኢትዮጵያ አየር መንገድን በመጠቀም በደቂቃዎች ውስጥ ጎንደር አየር ማረፊያ መድረስ ይችላሉ። it takes only 41 min. ዋጋው የናንተን ትኬት መቁረጫ ቀን ይወስነዋል። ቅድሚያ ለሚጓዙ ተጓዦች ከ1600 ጀምሮ ካልሆነ ግን 2300 ETH BIRR ድረስ ኢትዮ አየር መንገድ ያስከፍላል
ማስጠንቀቂያ ከመናኸሪያ ወደ ግቢ በምትሄዱበት ወቅትና ግቢ ከገባቹህ በኋላ ወደ ከተማ ምናምን ስትወጡ ንብረቶቻችሁን በንቃት መጠበቅ ይኖርባቹሃል ምክንያቱም ከተማው ላይ አዲስ ተማሪዎችንና የግቢ ተማሪዎችን የሚሰርቁ የተደራጁ ሌቦች አሉ ።

የትኛውም ግቢ ለምትገቡ ተማሪዎች አደራ ማለት የምወደው የንብረታችሁን ነገር በጣም መጥፎ መጥፎ የዝርፊያ ወንጀሎች ተበራክተዋልና ።

#ወባ ቢንቢ ምናምን ሚባል ነገር የሌለው ማኛ ግቢ ነው

ትምሮ በጎንደር
Gondar University
Health science college በሀገራችን ቀደምት ከመሆኑ የተነሳ በሀገርቱ ካሉ universityዎች አሪፍ የሚባል የትምህርት አሠጣጥ አለው ፤በhealth science college ውስጥ ያሉ Departmentችን በ www.uog.edu.et በመግባት ማየት yichlal።
Engineering science
የተከፈተው በቅርብ ጊዜ ቢሆንም እንኳ በሀገራችን ካሉ ዩኒቨርሲቲዎች የመጀመርያውን ደረጃ የሚይዝ campus ነው።
በ ውስጡ 8 የተለያዩ departments አሉ
1. Electrical and computer Engineering
2. Biomedical Engineering 🆕
3. Chemical Engineering
4. Mechanical Engineering
5. Civil Engineering
6. Construction management Engineering (cotem)
7. Industrial Engineering
8. Hydraulics Engineering
ሲሆኑ ምናልባት nxt year የሚጨመሩ departments ይኖራል የሚል ተስፋ አለ።
በተጨማሪም ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በ iot ማለትም በ Engineering science ለተከታታይ 3 አመት ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ዪኒቨርሲቲዎች 1ኛ በመውጣት ሃትሪክ ሰርቷል።
ዩንቨርሲቲው በጤናው ዘርፍ የካበተ ልምድ እና ዝና ያለው ሲሆን ደግሞ ለtechnology(engineering and CS) more ትኩረት እየሰጠ ይገኛል።

first semester engineering courses
1.Applied one( maths guide book ካላቹህ እንዳትረሱ)
2.mechanics
3.Drawing(drawing material እንዳትረሱ)
4.Communicative( English)
5.Civics
6. Engineering profession

About ምግብ ቤቶች
ለነን ካፌ ተማሪዎች ፋሲል ግቢ ውስጥ ወደ 4 ላውንጆች አlu ፤ከአራቱ ላውንቾች ውስጥ አንዱ አሪፍ ሚባልው 560ብር ወርሃዊ ኮንትራት ነው ምሳ እና እራት (no ቁርስ coz non cafe ቁርስ የበሶ ኮንትራት...)
Fasil Launge
1. በየአይነት 10 birr(wowwww)
2. ሹሮ 10 birr
3. የፍስክ ምግብ ከ15-25 birr(wowwww)
መምህራን launge
1. የፆም ከ 15-35birr
2. የፍስክ ከ 20-50
Mami launge
እዚህ ምግብ ቤት ዋጋው ከመምህራን ጋር ተመሳሳይ ሲሆን ምግባቸው ግን 1ኛ ነw

coffee house lounge
እዚህም ምግባቸው አሪፍ ነዉ። ዋጋቸውም ከላይ እንደጠቀስኩት ተመሳሳይ ነዉ።
ከላይ የጠቀስኳቸው lounቾች ባጠቃላይ ፋስል ግቢ ውስጥ ያሉ ናቸው።

የእርስዎን ዩኒቨርሲቲ መረጃ ደግሞ በ @MYUNIVERSITYINFOBOT ላይ በድምጽ ወይም በጽሑፍ ( ፎቶዎችም ብትልኩ ይደርሰናል) ይላኩልን።

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ነው።

#ጎንደር_ዩኒቨርሲቲ

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ 6 ሺህ 574 ተማሪዎችን ዛሬ እያስመረቀ ይገኛል፡፡

በ87 የመጀመሪያ እንዲሁም በ67 የድህረ ምረቃ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ነው የሚያስመርቀው፡፡

በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ የውኃ መስኖ እና ኢነርጅ ሚኒስትር ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ተገኝተዋል፡፡

#ደብረታቦር_ዩኒቨርሲቲ

የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በተለያየ የትምህርት መስክ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎቹን እያስመረቀ ይገኛል።

ዩኒቨርሲቲው ለስምንተኛው ዙር ነው ተማሪዎቹን እያስመረቀ የሚገኘው።

#ቦንጋ_ዩኒቨርሲቲ

የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ 2ኛ Batch ተማሪዎች በዛሬው ዕለት እያስመረቀ ይገኛል።

#ደብረብርሃን_ዩኒቨርሲቲ

የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በ13ኛ ዙር በተለያዩ መርሃ ግብሮች ያስተማራቸውን በ2ኛ ዲግሪ 231 ተማሪዎችን እና በ3ኛ ዲግሪ አንድ ተማሪ እያስመረቀ ነው።

#ኮተቤ_ሜትርፓሊታን_ዩኒቨርሲቲ

የኮተቤ ሜትርፖሊታን በተለያየ የትምህርት ክፍሎች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመርቋል።

ዩንቨርሲቲው በዛሬው እለት ያስመረቃቸው በመጀመሪያና ሁለተኛ ድግሪ ወንድ 448 ሴት 135 በድምሩ 583 ተማሪዎች ናቸው።

#ቅድስተ_ማርያም_ዩኒቨርሲቲ

የቅድስተ ማርያም ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች በድህረ ምረቃ ያሰለጠናቸውን 636 ተማሪዎችን በኦሮሞ ባህል ማዕከል አስመርቋል።

አጠቃላይ ከተመረቁት ውስጥ 322 ወንዶች 314 ደግሞ ሴቶች ናቸው።

#ሀራምቤ_ዩኒቨርሲቲ
ሀራምቤ ዩኒቨርሲቲ በተለያየ ትምህርት መስክ ያሰለጠናቸውን 3683 ተማሪዎችን እያስመረቀ ነዉ።
ዩኒቨርሲቲው ለ18ኛ ዙር ነው ተማሪዎችን እስመረቀ የሚገኘው።

[ኢፕድ፣ ዋልታ፣ አሚኮ፣ የዩኒቨርሲቲዎች ገፅ]

መረጃዎችን ለማግኘት
@NATIONALEXAMSRESULT
#ጎንደር_ዩኒቨርሲቲ

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በ2015 ዓ.ም የተመደቡ አዲስ ገቢ የቅድመ ምረቃ መደበኛ እና የአቅም ማሻሻያ (ሪሚዲያል) ፕሮግራም ተማሪዎች መቀበል ጀምሯል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ከዛሬ መጋቢት 11/2015 ዓ.ም ጀምሮ ተማሪዎቹን በመቀበል ላይ ይገኛል፡፡

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot