STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
40.7K subscribers
11K photos
272 videos
452 files
1.94K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
ዓለማችን በቴክኖሎጂ መጥቃለች። ሀገራችን ኢትዮጵያም ቴክኖሎጂ ከሚያስገኛቸው እንደ ኢኮኖሚ ያሉ ትሩፋቶች ተጠቃሚ ለመሆን፣ በዘርፉ የላቀ ዕውቀት ያላቸው ባለሙያዎችን ማፍራቷ ግድ ነው። ባለ ተሰጥኦ ታዳጊዎችና ወጣቶች ክህሎታቸውን እያዳበሩ፣ ሀገራቸውን በቴክኖሎጂ ከበለጸጉ ሀገራት ተርታ እንዲያሰልፉ፣ እንደ ቡራዩ የተሰጥዖ ማበልጸጊያ ትምህርት ቤት ያሉ የተሰጥዖ ማዕከላትን ማብዛት ይጠበቅብናል። የትምህርት ቤቱ ግንባታ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ በልዩ ልዩ መንገድ አስተዋጽዖ ያበረከቱ የአካባቢው ነዋሪዎች ምስጋና ይገባቸዋል።

[Abiy Ahmed Ali ]

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የጥሪ ማስታወቂያ

ከ2ኛ ዓመት ጀምሮ ላለችሁ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች በሙሉ
..................................................

ከ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ጋር በተያያዘ መደበኛ ትምህርታችሁ ተቋርጦ እንደነበር ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጅ የተቋረጠውን ትምህርት ለማስቀጠል ከ2ኛ ዓመት ጀምሮ ያላችሁ የህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታችሁ በቀን 17/02/2015 ዓ.ም እንድትመለሱ እናሳስባለን፡፡ ይህ የጥሪ ማስታወቂያ የ2ኛ እና 3ኛ ዓመት አኔስቴዢያ ተማሪዎችንም ይመለከታል፡፡

የዲላ ዩኒቨርሲቲ ህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመጠቀም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና አሰጣጥን ከአንድ ማዕከል እየተቆጣጠረ መሆኑን ገልጿል።

ኢንስቲትዩቱ የፈተና አሰጣጡን ሂደት ከአንድ ማዕከል መቆጣጠር የሚያስችሉ ለ24 ሰዓት ያለማቋረጥ የሚሰሩ ከ150 በላይ የደህንት ካሜራዎች እየተጠቀመ ይገኛል።

ካሜራዎቹ ዘመናዊ እና መብራት ቢጠፋም በራሳቸው ኃይል ያለማቋረጥ የሚሰሩ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ከፈተናው በተጨማሪ በኢንስቲትዩቱ ግቢ ውስጥ የሚካሄዱ እንቅስቃሴዎችን በመቆጣጠር ለፈተናው አሰጣጥ አስተማማኝ ደህንነት እንዲኖር መደረጉን የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር) ገልጸዋል።
ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#Update

የ12ኛ ክፍል " የተፈጥሮ ሳይንስ " ብሔራዊ ፈተና ዛሬ ጥቅምት 11 ቀን 2015 ዓ/ም በሚሰጠው የሥነ ዜጋና ሥነምግባር ትምህርት ፈተና ይጠናቀቃል።

የ2014 የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ ዩኒቨርሲቲዎች / የፌዴራል ተቋማት ውስጥ ከመስጠትም ባሻገር የተለያዩ ተቋማት ፈተናውን #በደህንነት_ካሜራ ጭምር ለመቆጣጠር ጥረት ሲያደርጉ ለመመለከት ተችሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ ላለፉት ዓመታት የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ስርዓትን እንደመከታተሉ ይሄ ፈተና ካለፉት ዓመታት ጋር ሲነፃፀር በተለይም በፈተና ስርቆት እና በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ #ቀድሞ ማሰራጨትን #በመከላከል በኩል እጅግ ከፍተኛ ለውጥ የታየበት ሆኖ አግኝቶታል።

ነገር ግን በዚህኛውም " የተፈጥሮ ሳይንስ " ፈተና ወቅትም ሆነ በባለፈው " የማህበራዊ ሳይንስ " ፈተና ወቅት በጥብቅ የተከለከለውን ስልክ / ሌላ የመገናኛ ዘዴ / ይዘው ወደ ክፍል በመግባት ፈተና በሚሰጥበት ሰዓት የፈተናውን ወረቀት ፎቶ በማንሳት በ " ቴሌግራም " ሲያሰራጩ የነበሩ ተፈታኞችን ተመልከተናል።

ይህንን ድርጊት ለመቆጣጠር ይመስላል ፈተና በሚሰጥባቸው ቀናት " ቴሌግራም " እንዲገደብ እየተደረገ የሚገኘው።

በፈተና ተቋማት ውስጥ ስለነበረው ጠንካራ ጎን፣ ክፍተት / ችግር ደግሞ የፈተናውን መጠናቀቅ ተከትሎ ከተፈታኞች ፣ ወላጆች ፣ ፈታኝ መምህራን አስተያየቶችን አሰባስበን እንክላችኃለን።

NB. ከብሔራዊ ፈተናው ጋር በተያያዘ እየተገደበ ያለው " ቴሌግራም " ከዛሬ ፈተና መጠናቀቅ በኃላ ሙሉ አገልግሎቱ ይመለሳል ተብሎ ይጠበቃል።
[TIKVAH]
ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተጠናቀቀ!

ፈተናውን ለወሰዳችሁ ቤተሰቦቻችን ሁሉ መልካም እድል😍

@NATIONALEXAMSRESULT
ላለፉት አራት ቀናት ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ሲሰጥ የቆየው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተጠናቋል።

ዛሬ ጠዋት የተሰጠውን የሥነ ዜጋና ሥነምግባር ትምህርት ፈተና መጠናቀቁን ተከትሎ ተማሪዎች ወደየቤተሰቦቻቸው መመለስ ጀምረዋል (በተለይ በቅርብ ርቀት የሚገኙ።)

ተማሪዎቹ በተዘጋጀላቸው ትራንስፖርት ወደየመጡበት እየተሸኙ መሆኑን ዩኒቨርሲቲዎች እያሳወቁ ነው። ምስል፦ የወለጋ ዩኒቨርሲቲ
ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
Photo
ጥቅምት 11/2015ዓም (ትምህርት ሚኒስቴር) በሁለት ዙር ሲሰጥ የነበረው የ2014 ዓም 12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና  ተጠናቋል ፦ ትምህርት ሚኒስቴር

ለመጀመሪያ ጊዜ በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ  በሁለት ዙር ሲሰጥ በነበረው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ  ፈተና ከ 900ሺህ በላይ ተማሪዎች በ130 የፈተና ጣቢያዎች  ተፈትነዋል።

ፈተናው  በመጀመሪያዉ ዙር የማህበራዊ ሳይንስ ፈተና ሂደት ካጋጠሙና  በመጀመሪያዉ ዙር ማጠቃለያ ከተገለጹ  ችግሮች ዉጪ በታቀደው መሰረት  በስኬት የተጠናቀቀ ሲሆን  የሁለተኛ  ዙር ተፈታኞችም ከዛሬ  ጀምሮ ወደ የአካባቢያቸው መመለስ ጀምረዋል።

ዩኒቨርስቲዎች ለፈተናው ውጤታማነት ያደረጉት ዝግጅት እና በፈተና አሰጣጥ  ሂደት ላይ የነበራቸው አስተዎፆ ከፍተኛ  የነበረ ሲሆን  ተፈታኞችም  የፈተና  ስርዓቱን  ባከበረ መልኩ  ፈተናቸውን  ሲወስዱ  ቆይተዋል።

ለዚህም  የትምህርት ሚኒስቴር  ለወላጆች፣ ተፈታኝ  ተማሪዎች  እና  ፈታኝ  መምህራን  ፣ጣቢያ  አስተባባሪዎች ፣ሱፐርቨይዘሮች ፣ የጸጥታ አካላት እና   በየደረጃው ለፈተናው ስኬታማነት  የበኩላቸውን ለተወጡ  አካላትም  ላቅ ያለ ምስጋናውን ያቀርባል።

የዘንድሮው  የፈተና  አሰጣጥ  ሂደት  የፈተና ስርቆት እና ኩረጃን  በማስቀረት  ሂደት  የነበረው አስተዎፆ  ውጤታማ  መሆኑ  የታየበት  እንደነበረም  ለማወቅ  ተችሏል።

በቀጣይም  የፈተና አሰጣጥ  ስርዓቱን  በማሻሻል የተሻለ እና በራሱ የሚተማመን    ትውልድን  ለመፍጠር በትኩረት  የሚሰራ  ይሆናል።

የፈተናዉን አጠቃላይ ሂደት በሚመለከት ዝርዝር መረጃዎችን በቀጣይ እንደሚገልፅ የትምህርት ሚኒስትር አሳውቋል፡፡

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot