STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
38.9K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.95K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
Wollo university

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የመደበኛ እና ተከታታይ ትምህርት ፕሮግራም የቅድመ-ምረቃ እንዲሁም የድህረ-ምረቃ ተማሪዎች የ2015 ዓ.ም አመታዊ የትምህርት የጊዜ ሰሌዳ (Academic Calendar) ከዚህ በታች የተገለፀ ሲሆን በፕሮግራሙ መሰረት ተገቢውን ዝግጅት ከወዲሁ እንድታደርጉ እያሳወቅን የመደበኛ ተማሪዎች ትምህርት የሚጀመረው ጥቅምት 30/2015 ዓ.ም ሲሆን የመመዝገቢያ ጊዜ ጥቅምት 28 እና 29/2015 ዓ.ም መሆኑን አውቃችሁ በየኮሌጃችሁ ሬጅስትራር በአካል በመገኘት እንድትመዘገቡ በጥብቅ እናሳስባለን።


የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት
━━━━━━━━━━━━━━━━━
ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የ2014ዓም 12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች የሁለተኛ ቀን ፈተና በሰላም ተጠናቋል ።

ጥቅምት 09/2015 ዓም.፣ (ትምህርት ሚኒስቴር ) የ2014ዓም 12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች የሁለተኛ ቀን ፈተና በሰላም የተጠናቀቀ ሲሆን በነገው እለትም የሚቀጥል ይሆናል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
"አማራ ክልል ላይ ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ፈተናቸውን አቋርጠው እንዲወጡ የሚያደርጉ አካላት የአማራ ጠላቶች ናቸው" ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር)

ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 08/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ርዕሰ መስተዳደሩ ይሄን ያሉት የ2014 ዓ.ም የወጣቶች የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማጠቃለያና የእውቅና አሰጣጥ መርሃግብር ላይ ነው።

መንግስት የትምህርት ሥርዓቱን ጥራት ለማሻሻል እና በፈተና ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለመሙላት አዲስ የአፈታተን ስርዓት መንደፉ የሚደገፍ መኾኑን ነው የተናገሩት።

ኾኖም ግን በመጀመሪያው ዙር የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች በተለየ ሁኔታ አማራ ክልል ላይ 12ሺህ በላይ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተናቸውን አቋርጠው መውጣታቸው የሚያሳዝን ነው ብለዋል።

ተማሪወች ልዩ ተልዕኮ ባላቸው የአማራ ጠላቶች መጠቀሚያ ሁነዋል ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳደሩ።
የክልሉ ወጣት ራሱን በራሱ እንዲያጠፋ ፣የተሳሰሰተ አቅጣጫ እንዲይዝ፣የወጣቶችን ስነልቦና የሚሰልቡ በተለያየ መገናኛ አውታሮች የሚሰብኩ አካላት አሉ ነው ያሉት።

ለራሱም፣ ለወላጅም፣ ለሀገር የሚያኮራ ዜጋ ለመፍጠር የሚደረገውን ተግባር የሚያከሽፉ የአማራ ጠላቶች ናቸው ብለዋል።

ራሱን እያጠፋ፣ ራሱን እያከሰረ መልማትና ማደግ የለምና ይሄን ማህበራዊ ቀውስ የፈጠረው ማነው የሚለውን ወጣቱ መመርመር እንደሚገባውም አሳስበዋል።

ወጣቶች ለመኖር እንዳይጓጉ፣ ለሕዝባቸው ፣ ለሀገራቸው እውቀታቸውንና ክህሎታቸውን እንዳይጠቀሙ የሚያደርጉ አካላት የአማራ ጠላት መኾናቸውን መረዳት ይገባል ብለዋል።

ችግር አለ ከተባለ ኀላፊነትን እየተወጡ መጠየቅ እንጂ ራስን አስቀድሞ ለኪሳራ ዳርጎ ሌላውን ተጠያቂ ማድረግ አይቻልም ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳደሩ።

መምህራን ወላጆች፣ ወጣቶችና ማንኛውም ሰው እሄን ነገር መመርመር ፣እኩይ ዓላማ አንግበው ለጥፋት የሚዳርጉ አካላትን ለህግ ማቅረብ ይገባልም ብለዋል።

በየትኛውም መመዘኛ በአማራ ክልል ተማሪዎች ተፈትነው ማለፍ ባህል ኾኖ እያለ በጠላት ማደናገሪያዎችን ተማሪዎች ፈተናቸውን አቋርጠው መውጣት እንዳሳዘናቸው ነው የተናገሩት። በዚህ ጉዳይ መንግስት ተገቢውን ምርመራ እንደሚያደርግና እርምጃ እንደሚወስድም ገልጸዋል።

አሚኮ

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ማተብ ታፈረ በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ እየተፈተኑ የሚገኙ የሁለተኛው ዙር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች የፈተና አሰጣጥ ሁኔታን ጎበኙ።
***
በጉብኝታቸውም የፈተና አሰጣጥ ሁኔታው በተረጋጋ መንፈስ ሕግና ሥርዓቱን ጠብቆ እየተሰጠ እንደሚገኝ መገምገማቸውን ገልጸዋል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የ2015 ዓ.ም ምዝገባ ከዚህ በታች በተጠቀሱት ቀናት በሁሉም ካምፓሶች የሚከናወን መሆኑ ተገልጿል።

ሀ. ለሁለተኛ ዲግሪ እና ሶስተኛ ዲግሪ ተማሪዎች

1. ሁለተኛ ዓመትና ከዚያ በላይ ለሆኑ መደበኛ እና የእረፍት ቀናት የድህረምረቃ (ሁለተኛ እና ሶስተኛ ዲግሪ) ተማሪዎች የመመዝገቢያ ጊዜ ጥቅምት 21-22/2015 ዓ.ም፡፡

2. ለአዲስ ገቢ አንደኛ ዓመት መደበኛ እና የእረፍት ቀናት የድህረምረቃ (ሁለተኛ እና ሶስተኛ ዲግሪ) ተማሪዎች የመመዝገቢያ ጊዜ ጥቅምት 23-24/2015 ዓ.ም፡፡

ለ. ለመጀመርያ ዲግሪ ተማሪዎች

1. የማታና የእረፍት ቀናት የመጀመርያ ዲግሪ ተማሪዎች የመመዝገቢያ ጊዜ ጥቅምት 25-27/2015 ዓ.ም

2. ነባር የመጀመርያ ዲግሪ ተማሪዎች የመመዝገቢያ ጊዜ ጥቅምት 28-29/ 2015 ዓ.ም

 የአንደኛ ዓመት መደበኛ (Freshman) ፕሮግራም ተማሪዎች በመልሶ ቅበላ መግባት የሚችሉ ተማሪዎች ምዝገባ የሚከናወነው ከ2015 ዓ.ም አዲስ ገቢ ተማሪዎች ጋር መሆኑን ተገልጿል።

ማሳሰቢያ : ከተጠቀሰው ቀን አስቀድሞ አሊያም ዘግይቶ የሚመጣ ተመዝጋቢን ዩንቨርስቲው አስያተናግድም።

(የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራርና አልሙኒ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት)


ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
በ11 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ተወሰነ።

የአማራ ብሔር ተወላጅ የሆኑ የደንቢዶሎ ዩንቨርስቲ ተማርዎችን በማገት ለኦነግ ሸኔ አሳልፈው ሰተዋል ተብለው የተከሰሱ አምስት ተከሳሾች በ11 አመት ጽኑ ዕስራት እንዲቀጡ ውሳኔ ተሰጠ።

የቅጣት ውሳኔውን የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የፀረሽብርና ህገመንግስታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።

የቅጣት ውሳኔ የተወሰነባቸው ተከሳሾች ከሊፋ አብዱረሀማን :ዮሴፍ ጃረታ:ጋዲሳ ገለቱ: ነብዩ በባከር :እና ናስር መሀመድ ይባላሉ።

ተከሳሾቹ የኦነግ ሸኔ የፖለቲካ ርዕዮተ አለም አላማን ለማራመድ ህብረተሰቡን ለማሸበርና መንግስትን ለማስገደድ በማሰብ የደንቢዶሎ ዩንቨርስቲ ተማሪዎችን ለማገት ከኦነግ ሸኔ አመራሮችና ከአባላት ጋር በመሆን ከህዳር 22 ቀን 2012 ዓ/ም ጀምሮ ስምምነት መፈጸማቸውን ጠቅሶ ዓቃቢህግ ባቀረበው ክስ አመላክቶ ነበር።

በዚህም ክስ ላይ ረሱቅ አብደላ የተባለው 16ኛ ተከሳሽ በሚያሽከረክረውና ሀምዲ አረብሴ በረዳትነት በሚሰራበት ኮድ 3 ታርጋ ቁ._34629 ኦሮ በቀይ ዶልፊን መኪና በህዳር 24 ቀን 2012 ዓ/ም የአማራ ብሔር ተወላጆች የሆኑት ተማሪ ሞንሙን በላይ :ተማሪ ጤናለም ሙላቴ: ተማሪ ሳምራዊት ቀሬ: ተማሪ አስቤ አያሌው እና የአካባቢው ኗሪ የሆነችው ተማሪ ትግስት መሳይን እንዲሁም በውል ያልተለዩ ሌሎች ሴቶችንም በደንቢዶሎ ዩንቨርስቲ ተከስቶ የነበረውን የተማሪዎች ግጭት በመፍራት በመሸሽ ላይ እንዳሉ በተጠቀሰው ተሽከርካሪ ተሳፍረው እንደነበር ዓቃቢህግ ዘርዝሯል።

በስምምነታቸው መሰረት ተማሪዎቹ የተሳፈሩበትን መኪና 1ኛ ተከሳሽ ከሊፋ አብዱራሀማን : አብዲ ኢብራሂም: ናስር መሀመድ: ዮሴፍ ጀረታ : አወሉ ጅብሪል :ነብዩ ባቤሰር :ጋዲሳ ገለቱ የተባሉ ተከሳሾች ካልተያዙ ከሌሎች ግብረአበሮቻቸው ጋር በመሆን ዱላና የጦር መሳሪያ በመያዝ መኪናውን በማስቆም አማረኛ ቋንቋ ብቻ ተናጋሪ ተማሪዎችን በመለየት ከመኪናው አሶርደው ወስደው በጫካ ውስጥ ማገታቸውን ዓቃቢህግ በክሱ ገልጿል።

የመኪናው ሹፌርና ረዳትም ጉዳዩን ለጸጥታ አካል ሳያሳውቁ መቅረታቸውን በክሱ አመላክቷል።

ተከሳሾቹንም በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ በሐምሌ 10 ቀን 2012 ዓ/ም በ1996 ዓ/ም የወጣውን ወንጀል ህግ አንቀጽ 32 1ሀ እና አንቀጽ 35:38 እንዲሁም የፀረሽብር አዋጅ ቁጥር 652/2001አንቀጽ 3/3 ድንጋጌን በመተላለፍ ክስ ቀርቦባቸው ነበር።

ተከሳሾቹ ወንጀሉን አለመፈጸማቸውን የዕምነት ክህደት ቃላቸውን መስጠታቸውን ተከትሎ ዓቃቢህግ ወንጀሉ መፈጸማቸውን ያስረዳልኛል ያለውን የሰነድና የሰው ምስክር አቅርቦ ማሰማቱን መዘገባችን ይታወሳል።

ፍርድ ቤቱ የቀረበውን ማስረጃ መርምሮ በተከሰሱበት አንቀጽ 1ኛ ከሊፋ አብዱረሀማን :ዮሴፍ ጃረታ:ጋዲሳ ገለቱ: ነብዩ በባከር :እናናስር መሀመድ የተባሉ 5 ቱ ተከሳሾች በመጋቢት 9 ቀን 2014 ዓ/ም በነበረ ቀጠሮ እንዲከላከሉ ብይን ሰቶ ነበር።

አብረዋቸው ተከሰው የነበሩ ሌሎች 3 ተከሳሾችን ማለትም ጌታቸው ዮናስ :አብደሳ ፋፋ እና ተፈሪ ኒካ የተባሉትን ደግሞ በተከሰሱበት ክስ ወንጀሉን ስለመፈጸማቸው በቂ ማስረጃ አልቀረበባቸውም ሲል በነጻ ማሰናበቱ ይታወሳል።

እንዲከላከሉ ብይን የተሰጠባቸው የአምስት ተከሳሾችን በተለያዩ ቀናቶች የመከላከያ ማስረጃ አቅርበው አሰምተዋል።

ተከሳሾቹ ቀደም ሲል የተከሰሱበት የፀረሽብር አዋጅ ቁጥር 652/2001አንቀጽ 3/3 ድንጋጌ ተቀይሮ በተሻሻለው በፀረ ሽብር አዋጅ ቁጥር 1176/2012 አንቀጽ 3 ንዑስ ቁ 1/ሀ መሰረት በነሃሴ 19 ቀን 2014 ዓ/ም በነበረ ቀጠሮ መከላከል አለመቻላቸው ተገልጾ በአንድ ዳኛ የሀሳብ ልዩነት በሁለት ዳኞች አብላጫ ድምጽ የጥፋተኝነት ፍርድ ተላልፎባቸዋል።

ይሁንና አንዳኛው ዳኛ 5 ኛ6 ኛ እና 8ኛ ተከሳሾች ባቀረቡት የመከላከያ ማስረጃ የተከላከሉ መሆኑን ጠቅሶ ጥፋተኛ ሊባሉ አይገባም ሲል የሀሳብ ልዩነት እንዳለው ለችሎቱ ገልጾ ነበር።

ተከሳሾቹ በቅጣት ማቅለያነት ያቀረቡት 4 የቅጣት ማቅለያ አስተያየት ማለትም የወንጀል ሪከርድ እንሌለባቸው :የቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆናቸውን: ከበጎ በአድራጎትና በማህበራዊ እንቅስቃሴ ያበረከቱትን አስተዋጾ በማቅለያ ተይዞላቸዋል።

በከሳሽ ዓቃቢህግ በኩል ወንጀሉ በቡድን እና በጭካኔ የተሞላ ድረሰጊት የተፈጸመ ነው ሲል ያቀረበውን የቅጣት ማክበጃን ፍርድ ቤቱ ይዞለታል።

በዚህም መሰረት ተከሳሾቹ ጥፋተኛ በተባሉበት አንቀጽ እጃቸው ከተያዘበት ጊዜ ጀምሮ የሚታሰብ በ11 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ተወስኗል።

ተከሳሾቹ ከመንግስት የተከላካይ ጠበቃ ተመድቦላቸው የህግ ድጋፍ እየተደረገላቸው ጉዳያቸውን ሲከታተሉ ቆይተዋል።

ከቅጣት ውሳኔ በኋላ ተከሳሾቹ እየሳቁ ከችሎት ሲወጡ ተስተውሏል።

Via Tarik Adugna

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ የአስክሬን ሽያጭ ይካሄዳል በሚል በተሰራጨው መረጃ ዙሪያ ክስ ሊመሰርት እንደሚችል አስታወቀ

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የኮሙኒኬሽን ክፍል ዳይሬክተር አቶ ነዋይ ፀጋዬ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት የኮሌጁን  የፎረንሲክ  ሕክምና ምንነት እና አገልግሎት አሰጣጥ በወጉና በአግባቡ ሳይረዱ የተሳሳተ እና ተገቢ ያልሆነ መረጃ ለሕዝብ አሰራጭተዋል ሲሉ ገልፀዋል።

ይህንን ዘገባ ያሰራጨው የመገናኛ ብዙሃን በይሆናል እና በዘፈቀደ የራሳቸውን ያልተገባ ምልከታ ጨምረው አካተዋል ይህም የተሳሳተ ግንዛቤ እንዲወስዱ አድርጓል ሲሉ አክለዋል። የምርመራ ጋዜጠኝነት መስራት ከፈለጉ የተደራጀ መረጃ ከሚመለከታቸው ባለሙያዎችና ኃላፊዎች ማግኘት ይችሉ ነበረ ግን አላደረጉም ሲሉ አክለዋል።

አቶ ነዋይም አያይዘው በሰሩት የዩ -ቲዩብ ቪዲዮ እንደተረዳነው ስለፎረንሲክ ምርመራና ተያያዥ ጉዳዮች ለሕዝብ ለማሰተማር( ለማስረዳት) በቂ እውቀት መረጃ ሳይኖራቸው በስማ በለው የተሳሳተ እና ያልታረመ መረጃቸውን ለቀዋል ለዚህም ይጠየቃሉ ብለዋል። የሕክምና ትምህርት አሰጣጥና  በመስኩ የሚደረገውን የአገልግሎት አሰጣጥ  በእጅጉ ይጎዳዋል፡፡

ይህ ካለበቂ መረጃ እና ቅድመ ዝግጅት ያልተሰራ ዘገባ ከዩቲየብ ቻናሉ እንዲወርድ እና የይቅርታ  ማሰተባበያ እንዲሰጡ በአጽንኦት እየጠይቃለን በማለት ይህ የማይደረግ ከሆነ በሐሰት ዘገባ አቅደው በመስራታቸው ወደ ሕግ  የምናቀርብ መሆኑን እንገልጻለን ሲሉ አቶ ነዋይ ተናግረዋል።


#ዳጉ_ጆርናል

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የሳይንስ ሙዚየም ለታዳጊዎች ያለው አበርክቶ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሳይንስ ሙዚየም በታዳጊዎች አዕምሮ ውስጥ የሳይንስና ቴክኖሎጂን ፅንሰሃሳብ ከማስረፁም በላይ ነገ መሆን የሚፈልጉትን ትክክለኛ መሰረት ይዘው እንዲያድጉ መንገድ እንደሚከፍት ይነገራል፡፡

የሳይንስ ሙዚየም መስከረም ወር ላይ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በመዲናዋ በይፋ መከፈቱ የሚታወስ ሲሆን÷ሙዚየሙ ኢትዮጵያ በአስገራሚ ፍጥነት በማደግ ላይ ካለው ቴክኖሎጂ ጋር ለመጣመር ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይም ነው ተብሎለታል ።

የሙዚየሙን በይፋ መከፈት ተከትሎም ለተከታታይ ሳምንታት ለእይታና ለህዝብ ክፍት ሲሆን÷ በዚኅም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ሙዚየሙን በመጎብኘት ላይ ይገኛሉ፡፡

ሙዚየሙን ሲጎበኙ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያነጋገራቸው ታዳጊዎች ሙዚየሙን በመጎብኘታቸው መደሰታቸውን እና እኔም ሀገርን የሚያስጠራ ስራ በሳይንሱ እና በቴክኖሎጂው ዘርፍ አበረክታለሁ የሚል መነቃቃትን እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል፡፡

እንዲሁም ከዚህ በላይ እንድንሰራ ያደርገናል፤ መሆን ለምንፈልገው ነገር እገዛ ያደርግልናል፤ ለነገ እራሳችንን ለማዘጋጀት ይጠቅመናል ሲሉም አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

ሙዚየሙን ያልጎበኙ ታዳጊዎችም መጥተው እንዲጎበኙና በርካታ ነገሮችን እንዲመለከቱ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ትንተና፡- እየጨመረ ባለው የትምህርት ዋጋ ወላጆች ፈተና ውስጥ ባሉበት ወቅት፣ ጦርነትና የተፈጥሮ አደጋዎች በኢትዮጵያ 13 ሚሊዮን ተማሪዎችን ከትምህርት ቤት ውጪ አድርገዋል

   በምህረት ገ/ክርስቶስ እና በአሰፋ ሞላ

የዘንድሮው የትምህርት መሳሪያ የዋጋ ንረት ምክንያት በአዲስ አበባ እና በአንዳንድ የሀገሪቱ ክፍሎች የመማሪያ ቁሳቁስ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ጭማሪ ተደርጎበት ሲሽጥ ሰንብቷል፡፡ ይህም የወላጆችን የመግዛት አቅም ፈትኗል፡፡

በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ በሀገሪቱ በተከሰቱ ጦርነቶች፣ ድርቅና ጎርፍ ሳቢያ 13 በሚሊዮን የሚሆኑ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ተፈናቅለዋል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ በተለያዩ የሃገሪትዋ ክፍል ወደ ትምህርት ቤት ገበታቸው ያለተመለሱ ህጻናት በትክክለኛው አድሜያቻው ወደ ትምህርት ገበታቸው ባለመመለሳቸው በራሳቸውና በሃገር ላይ ከፍተኛ የሆነ ጉዳቶች አንደሚኖረው በተለያዩ ዘርፍ ሚገኙ ሙሁራን ሲናገሩ ይስተዋላል።

ሙሉ ዘገባው ከዚህ በታች ቀርቧል

https://amharic.addisstandard.com/%e1%89%b5%e1%8a%95%e1%89%b0%e1%8a%93%e1%8d%a1-%e1%8a%a5%e1%8b%a8%e1%8c%a8%e1%88%98%e1%88%a8-%e1%89%a3%e1%88%88%e1%8b%8d-%e1%8b%a8%e1%89%b5%e1%88%9d%e1%88%85%e1%88%ad%e1%89%b5-%e1%8b%8b%e1%8c%8b/
[Adiss standard ]

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቡራዩ ከተማ የተገነባውን የልዩ ተሰጥዖ ማበልፅጊያ ኢንስቲትዩት መርቀው ከፈቱ!!!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በቡራዩ ከተማ የተገነባው የልዩ ተሰጥአ ማበልፅጊያ ኢንስቲትዩት መርቀው ከፍተዋል፡፡

ኢንስቲትዩቱ የኢትዮጵያ ባለተሰጥኦዎችን ካሉበት ለይቶ በማውጣት ተሰጥኦዋቸው ባለበት ደረጃ በልጽጎ ያለጊዜ ገደብ ወደ ምርትና አገልግሎት እንዲቀየርና ሀገር እንዲጠቅሙ ማስቻል መሆኑ ተገልጿል፡፡ፕሮጀክቱ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መሰረቱ የተጣለ ሲሆን ከ708 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት መሆኑ ተገልጿል፡፡

የፕሮጀክቱ ባለቤት የፌዴራል መንግስት ቢሆንም የከተማ አስተዳደሩ ቁልፍ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ፕሮጀክቱ ከትምህርት፤ ከሰው ሃይል ልማት፤ከስራ እድል ፈጠራ እንዲሁም ለሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢኖቬሽን ልማት ምርምር ስርዓት አኳያ መሰረት ይጥላል ተብሎ ይታመናል፡፡

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot