STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
38.9K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.95K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
Photo
ተማሪ ፅጌረዳ ግርማይን በስለት ወግቶ የገደለው ተማሪ በ22 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የውሳኔ ማሻሻያ አደረገ

👉የጋሞ አካባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከዚህ ቀደም ተከሳሹ በ17 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል

አርብ ጥቅምት 11 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ)

የደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የነበረችውን ተማሪ ፅጌረዳ ግርማይን በስለት ወግቶ የገደለው ተማሪ በ22 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ የውሳኔ ማሻሻያ አድርጓል።

የጋሞ ዞን ፍትህ መምሪያ ኃላፊ ሽመልሰ ጮራ እንደገለፁት፤ የወንጀሉ አድራጊ እና ተደራጊ ቀደም ሲል የአርባምንጭ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች እንደነበሩ አስታውሰዋል።

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ተከሳሽ ብሩክ በላይነህ "ያቀረብኩትን የፍቅር ጥያቄ አልተቀበለችም፣ ሌላ ፍቅረኛ ይዛ ውጪ ልትወጣ ነው።" በሚል ስሜት ተነሳስቶ የተማሪ ጽጌረዳ ግርማይን አካል ዘጠኝ ጊዜ በስለት ወጋግቶ የመግደል ወንጀል ፈፅሟል።

በቀድሞው አጠራር የጋሞ ዞን ዐቃቤ ህግ የመሠረተውን የወንጀል ክስ ተመልክቶ ግራና ቀኙን ሲያከራክር የቆየው የጋሞ አካባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀደም ሲል በቀን 19/10/2014 በዋለው ችሎት በተከሳሽ ላይ የ17 ዓመት ፅኑ እስራት ቅጣት መወሰኑም ይታወቃል።

የዞኑ ዐቃቤ ህግ በከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ቅር በመሰኘቱ ይግባኙን ለደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርቦ ሲከታተል መቆየቱን ሽመልስ ተናግረዋል።

የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በበኩሉ የጋሞ አካባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የበየነው የቅጣት ውሳኔ ከተፈፀመው ወንጀል አኳያ ተገቢነት ያለው ሆኖ ባለመገኘቱ፤ የሥር ፍርድ ቤቱን ውሳኔ አሻሽሎ ሰሞኑን በዋለው ችሎት በተከሳሽ ላይ የ22 ዓመት ፅኑ እሥራት የቅጣት ውሳኔ ማሰተላለፉን የጋሞ ዞን መ/ኮሚዩኒኬሽ አስታውቋል።
__
ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የሳይንስ ሙዚየሙ የፈጠራ ስራዎች በፍጥነት ወደ ቴክኖሎጂ እንዲቀየሩ ያደርጋል
***
(ኢ ፕ ድ)
በቅርቡ ተመርቆ ለዕይታ ክፍት የተደረገው የሳይንስ ሙዚየም በተለያዩ ደረጃዎች የሚፈጠሩ የፈጠራ ስራዎች በፍጥነት ወደ ቴክኖሎጂ እንዲቀየሩ ለማድረግ ከፍተኛ ሚና እንዳለው በፈጠራ ስራ ላይ የተሰማሩ ባለሙያዎች ተናገሩ።
ድሮን ፈጠራ ስራ ላይ የተሰማሩት የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ መምህር አማኑኤል ባልቻ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ሳይንስ ሙዚየም በፈጠራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች ስራ በፍጥነት ተቀባይነት አግኝቶ ወደ ቴክኖሎጂ እንዲቀየር ያደርጋል። ቴክኖሎጂን ያለፈጠራ እውን ማድረግ አይቻልም፣ ሀገር የምትፈልገውን ቴክኖሎጂ ለማስገኘት ፈጠራ ስራ አስፈላጊ ነው ብለዋል።
እንደ መምህር አማኑኤል ገለጻ፤ ዓለም በሰው አእምሮ የተፈጠሩ ነገሮችን በማበልጸግ የማህበረሰቡን ችግሮች መፍታት ወደሚያስችል ቴክኖሎጂ በማሸጋገር ላይ ትገኛለች። እንደ ሀገር የሚያስፈልጉንን ቴክኖሎጂዎች ለማሳደግም እሳቸው ከዘመኑ ቴክሎጂዎች አንዱ በሆነው የድሮን ቴክኖሎጂ ላይ ተሰማርተዋል። እስከ አሁን ድረስ በሰሩት የፈጠራ ስራ ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ ዘጠኝ ድሮኖች መፍጠራቸውንም ገልጸዋል።
በፈጠራ ስራቸው ከተሰሩ ድሮኖች በአብዛኛው በግብርና ዘርፉ የሚታዩ ችግሮችን ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=83974

ተማሪ ነክ መረጃዎን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የትምህርት ጥራት እና የሀገር ዕድገት ምን አገናኛቸው?
በፍፁም ሳልህ

ጥቅምት 11/2015 (ዋልታ) አሁንም መማር፣ መማር፣ መማር፤ የሚለው የቭላዲሚር ሌኒን ጥቅስ ጊዜም የማይሻር ጥቅስ ነው። የትኛውም ሥርዓት ቢሆን ይህንን ጥቅስ ደጋግሞ ማለቱ አይቀርም። ምክንያቱም ትምህርት የጥበብ መጀመሪያ ነውና። ይህ ጥቅስ በራሱ የትምህርት ፍልስፍና ነው።

የትምህርት ፍልስፍና ስንመለከት ዜጎች በራሳቸው የሚተማመኑ፣ ብቁና በምክንያታዊ ትንተና የሚያምኑ፣ በሙያቸው ብቃት ያላቸው፣ ሥራ ፈጣሪዎች፣ አዳዲስ ግኝቶችን አፍላቂዎች፣ ጠንካራ የሥነ ምግባርና ግብረገባዊ እሴቶችን የተላበሱ፣ ለሕግ ዘብ የቆሙ፣ በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪና ብቁ ዜጋ ሆነው አጠቃላይ ሰብእናቸው የተገነባ ዜጎችን በማፍራት ብዝኃነትን ላካተተው አገራዊ አንድነትና ሠላም ዘብ እንዲቆሙ ማድረግ ነው። ይህ ደግሞ በትምህርት ነው የሚገኘው።

አንዲት ሀገር ሁለንተናዊ እድገትን በማምጣት የሕዝቦቿን ኑሮ ማሳደግ የምትችለው በሚኖራት የሰው ኃይል እምቅ አቅም ነው፡፡ ዛሬ በሣይንስና ቴክኖሎጂ በልጽገው በአገራቸው ልማትን በማምጣት የሕዝባቸውን ተጠቃሚነት ያጎለበቱ አገራት ልምድ የሚያሳየን ይህንኑ ሐቅ ነው፡፡ ለዚህ ማሳያ በቅርብ ዓመታት ከነበሩበት የድህነት አረንቋ ወጥተው ከፍተኛ የሣይንስና ቴክኖሎጂ እድገት ደረጃ ላይ የደረሱ እንደ ደቡብ ኮሪያ፣ ቻይና፣ ሲንጋፖር፣ ቬትናም፣ ማሌዢያ፣ ወዘተ. ያሉ አገራት ተሞክሮን መጥቀስ ይቻላል፡፡

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
History of Ethiopia and the Horn ኮመን ኮርስ ስር እንዲካተት ተወሰነ

በትምህርትና ሥልጠና ፍኖተ ካርታ ጥናት ሰነድ መሰረት የትምህርት ፕሮግራሞች ዝቅተኛ የጊዜ እርዝማኔ ከሶስት ዓመት ወደ አራት ዓመት በተሻሻለባት ወቅት ለቅድመምረቃ ተማሪዎች የጋራ ኮርሶች ተለይተዉ እንዲሰጡ ምክረ ሃሳብ መቅረቡ ይታወቃል፡፡ በዚህ መሰረት የጥናት ሰነዱ ብስጥ ከተመላከቱ የጋራ ኮርሶች በተጨማሪ ከሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች በተውጣጡ በዘርፉ ልምድ ባላቸዉ ምሁራን 19 የጋራ ኮርሶች ተለይተዉና ሞጁሎች ተበጅተዉላቸዉ በየትምህርት ክፍሎቹ ተገምግመዉና ተተችተዉ በሰኔት ጸድቀዉ ስራ ላይ እንዲውሉ ተደርጓል፡፡ በዚህ መሰረት ዩኒቨርሲቲዎች የየኮርሶቹን የሞጁል ዝግጅት የሚመሩ የመስኩ ባለሙያዎችን በመምረጥ ሞጁሎቹ ተዘጋጅተው በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እየተተገበሩ ይገኛሉ፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ የታሪክ ኮርስም በሙያተኞች ተዘጋጅቶ በተለያዩ ዐውደ ጥናቶች እና የምክክር መድረኮች ላይ ቀርቦ የኢትዮጵያ የታሪክ ባለሙያዎች ማህበር ሰነዱን በመገምገም ግብዓት ሰጥቶበት እንዲዳብር ሆኗል፡፡

💢 ኮርሱን የሚሰጠው የመምህራን ቁጥርን ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ከተመራቂ ተማሪዎች በመጀመር እንደሆነም ተጠቁሟል።


ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ውድ የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ምንም አይነት የመግቢያ ቀን ስላላሳወቀ ከሀሰተኛ መረጃዎች እንድትጠነቀቁ ሲል የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት ያስጠነቅቃል የጥሪ ቀን በዚሁ የተማሪዎች ህብረት ቻናል የምንለቅ መሆኑን እንገልጻለን እስከዛዉ መልካም የእረፍት ጊዜን ተመኘሁ ።

#የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ሃይማኖት በዳዳ ህይወቷን እንድታጣ ያደረገው ግለሰብ በ25 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ተወሰነበት!

ዐቃቤ ህግ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የማስተርስ ተማሪ በነበረችው ሃይማኖት በዳዳ ላይ ከባድ የውንድና ወንጀል ፈጽሞ ህይወቷ እንዲያልፍ በማድረግ የ21 ዓመት እስራት ተፈርዶበት በነበረው ደግነት ወርቁ ላይ በተላለፈው የቅጣት ውሳሴ ላይ ቅር በመሰኘት ባቀረበው ይግባኝ መሰረት ቅጣቱ ተሻሽሏል፡፡

ተከሳሽ ግንቦት 17/2012 ዓ.ም በግምት 9፡00 ሰዓት ሲሆን በልደታ ክ/ከ/ወ 9 ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ግቢ ውስጥ የፋርማሲ ት/ቤት 4ኛ ፎቅ ቤተ ሙከራ ውስጥ የሙከራ ስራዋን እየሰራች የነበረች ሟች ሃይማኖት በዳዳን የምትሰራበት የምርምር ክፍል ውስጥ በመግባት በቢላዋ አንገቷን በማረድ እና ደረቷን በመውጋት ህይወቷ እንዲያልፍ ካደረገ በኋላ ስልክ እና ላፕቶፕ ጨምሮ ንብረቷን ይዞ በመሰወሩ ዐቃቤ ህግ የወንጀል ህግ አንቀጽ 671 ስር የተመለከተውን በመተላለፍ በፈጸመው ከባድ የውንብድና ወንጀል ክስ አቅርቦበት ወንጀሉን ስለመፈጸሙ በማስረጃ በማረጋገጡ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ወንጀል ችሎት ተከሳሽን ጥፋተኛ በማለት የቅጣት ማቅለያ እና ማክበጃ አስተያየቶችን በመቀበል ነበር ውሳኔውን ያስተላለፈው።

ይሁንና እንደ ዐቃቤ ህግ ቅሬታ በተከሳሽ በኩል ከቀረቡ የቅጣት ማቅለያ ሃሳቦች መካከል ተከሳሽ ወንጀል እስከፈጸመበት ጊዜ ድረስ የዘወትር ጸባዩ መልካም የነበረ መሆኑን እንዲሁም በ14 ቀን ኤች.አይ ቪን የሚያድን መድሓኒት አግኝቻለሁ በማለት ያቀረበው የቅጣት አስተያየት በልዩ የቅጣት ማቅለያ ምክንያትነት በመያዙ ተከሳሽ ማህበረሰቡን የሚጠቅም ልዩ የምርምር ስራ ስለመስራቱ በማስረጃ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ያቀረበው የድጋፍ ደብዳቤ ስለግኝቱ በማስረጃነት ተይዞ ቅጣቱ ከእርከን 37 ወደ እርከን 36 ዝቅ በማድረግ የ21 ዓመት እስራት ቅጣት መወሰኑ አግባብ አይደለም በማለት የተያዘው የቅጣት ማቅለያ ሃሳብ ተሰርዞ ተከሳሽ በቅጣት አወሳሰን መመሪያው መሰረት እርከን 37 ስር አስተማሪ ቅጣት ይጣልበት በማለት ይግባኝ አቅርቧል፡፡

በዚሁም መሰረት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተከሳሽ የኤች.አይ.ቪ መድሃኒት አግኝቷል በማለት በማስረጃ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ በቅጣት ማቅለያነት መያዙ አግባብ አይደለም በማለት የከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔን በማሻሻል ቅጣቱን ከእርከን 36 ወደ እርከን 37 ከፍ በማድረግ ተከሳሹ በ25 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ሲል ወስኖበታል።

[የኢፌዲሪ ፍትሕ ሚኒስቴር]
ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#Kotebe_University_of_Education

ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የ2015 ትምህርት ዘመን የሁሉም ፕሮግራሞች የመጀመሪያ ሴሚስተር ምዝገባ ጥቅምት 28 እና 29/2015 ዓ.ም እንደሚከናወን አሳውቋል።

የ2015 ትምህርት ዘመን የመጀመሪያ ሴሚስተር ትምህርት ጥቅምት 30/2015 ዓ.ም እንደሚጀምር ተገልጿል።

(ሙሉ መረጃው ከላይ ተያይዟል።)

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#የጥሪ_ማስታወቂያ
ለወልድያ ዩኒቨርሲቲ መምህራን እና አስተዳደር ሰራተኞች በሙሉ:

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የ2015 ዓ.ም ብሔራዊ የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና በስኬት ተጠናቋል – የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

የሀገራችን ዕድገት እና ብልጽግና የሚረጋገጠው የሥነ ምግባር እና የዕውቀት ጥራት ባለው የሰው ኃይል መሆኑ ይታወቃል። ፖሊሲና አሠራሯን በዚሁ ልክ ቀምራለች። ይኽ ጅምሯ በጥልቀት በተጠና የትምህርት ፍኖተ ካርታ ሥራ ተተግብሮ ታይቷል።

እጅግ አጓጊ በሆነው በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ዝግጅት እና ትግበራ ተራምዷል። የትምህርት መሪዎች፣ መምህራንና ወላጆች በታላቅ ቅንጅት በመሥራት ላይ ናቸው። የዚህ የለውጥ ሥራ አካል የሆነው ተማሪዎችን በሐቅ እና በሳይንሳዊ መንገድ የመመዘን ሥራ ታላቅ እመርታ አሳይቷል።

የዚሁ ለውጥ አካል የሆነው የ2015 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተናም የጥረቶቹ ተከታይ ሆኖ በታላቅ ስኬት ተጠናቅቋል። በቀደመው የማኅበራዊ ሳይንስ የፈተና አሰጣጥ ላይ የታዩ ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች ተገምግመው በተፈጥሮ ሳይንስ ፈተና ወቅት የተሠራው ሥራ እጅግ አመርቂ ሆኗል። የተፈጥሮ ሳይንስ የፈተና መርሃ ግብርም በመላ ሀገራችን በስኬት ተጠናቅቋል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
PADM Exit.docx
16.9 KB
PADM courses that are being selected for exit exams


ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#Telegram

ባለፉት ቀናት ከ2014 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ጋር በተያያዘ ሲገደብ የነበረው ቴሌግራም ዛሬ የ12ኛ ክፍል ፈተና መጠናቀቁን ተከትሎ ሙሉ አገልግሎት እንዲሰጥ ተደርጓል።

የ " ቴሌግራም " መገደብ ከፈተናው ጋር በተያያዘ የሀሰተኛ መረጃዎችን ስርጭት በመግታትና ተፈታኝ ተማሪዎች እና ወላጆች #እንዳይረበሹ በማድረግ በኩል ትልቅ የሆነ አስተዋጽኦ እንደነበረው መመልከት ተችሏል።

ባለፉት ዓመታት በነበሩ የብሄራዊ ፈተናዎች ላይ ከየትኛውም የማህበራዊ ሚዲያዎች በበለጠ በ " ቴሌግራም " በኩል ነበር የፈተና ወረቀቶች ከፈተና ቀን ቀደም ብሎ ሲሰራጭ የነበረው።

በአሁኑ የ2014 ዓ/ም ብሄራዊ ፈተና ተማሪዎችን ወደ ዩኒቨርሲቲ አስገብቶ ማስፈተኑ የፈተና ስርቆትን እና ቀድሞ ማሰራጨትን መከላከል ያስቻለ ሲሆን በአንዳንድ ተቋማት ስልክ ይዘው የገቡ ተማሪዎች ከፈተና ክፍል ሆነው የፈተና ወረቀት እያነሱ በቴሌግራም ግሩፖች እና ቻናሎች ላይ ሲያሰራጩ ነበር።

ነገር ግን በአብዛኛው ተማሪ ስልክ ይዞ እንዳይገባ በመደረጉ እና " ቴሌግራም " ም ሲገደብ ስለነበር ተፅእኖውን መቋቋም እንደተቻለ ይታመናል።

በቀጣዩ የ2015 ዓ/ም ብሄራዊ ፈተና ላይ መሰል ክፍተቶች እንዳይኖሩ ለማድረግ ከአሁኑ ፈተና ትምህርት በመውሰድ አንድም ተማሪ ስልክ ይዞ እንዳይገባ መፍትሄ ማበጀት ይገባል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot