STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
40.7K subscribers
11K photos
272 videos
452 files
1.94K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
#Haramaya_University

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በ2014 የትምህርት ዘመን አዲስ የተመደቡ ተማሪዎችን መቀበል ጀምሯል።

ዩኒቨርሲቲው የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች መግቢያ ከግንቦት 12 እስከ 14/2014 ዓ.ም መሆኑን የገለጸ ቢሆንም ከትላንት ምሽት ጀምሮ አዲስ ገቢ ተማሪዎችን እየተቀበለ ይገኛል።

ዩኒቨርሲቲው አዲስ አበባ እና አዳማ ከተሞች ላይ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚያስተባብሩ ሰዎች መመደቡን በዩኒቨርሲቲው የፍሬሽማን ፕሮግራም ዳይሬክተር ጌታቸው ተሾመ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

ተማሪዎች የተመደቡትን ካምፓስ እና የመኝታ ክፍል በበይነ መረብ አማካኝነት እንዲያውቁ ዝግጅት መደረጉንም ተናግረዋል።

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ከ5 ሺህ 100 በላይ አዲስ ገቢ ተማሪዎች በትምህርት ሚኒስቴር ተመድበውለታል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#የጥሪ ማስታወቂያ
#GambellaUniversity

በ2014 ዓ.ም በጋምቤላ ዩኒቨርስቲ የተመደባችሁ የቅድመ ምረቃ መደበኛ መርሃ-ግብር ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሄደው #ከግንቦት_29 30/2014 ዓ.ም መሆኑን አውቃችሁ በተጠቀሰው ቀን በዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራር በአካል ቀርባችሁ እንድትመዘገቡ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

ውድ ተማሪዎቻችን ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትመጡ፡

1ኛ. የ8ኛ፣ 10ኛ እና 12ኛ ክፍል ክልላዊና ብሔራዊ ፈተና ውጤት ሰርተፊኬቶች ዋና እና የማይመለስ 1 ኮፒ፣

2ኛ. ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ዋና ትራንስክሪፕት ከማይመለስ 1 ኮፒ ጋር እንዲሁም ስድስት 3x4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣

3ኛ. አንሶላ፣ የትራስ ጨርቅና የስፖርት ትጥቅ ይዛችሁ መምጣት ይጠበቅባችኋል፡፡

#ማሳሰቢያ፡ከተጠቀሰው ቀን ቀድመውም ሆነ ዘግይተው የሚመጡ ተማሪዎችን የማናስተናግድ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ለበለጠ መረጃ የዩኒቨርሲቲውን ድረ-ገፅ WWW.gmu.edu.et ይጎብኙ፡፡

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
ተሸላሚ ሴት ተማሪዎች

በ2013 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ፈተናን በከፍተኛ ውጤት አጠናቀው ዩንቨርስቲዎችን ከተቀላቀሉ ሶስት ሴት ተማሪዎች ጋር የተደረገ ውይይት፦ ታዳጊዎቹ የተማሩት በኦሮሚያ ልማት ማህበር (ኦልማ) ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት አዳማ ቅርንጫፍ ሲሆን በክልል ደረጃ በሴቶች ዘርፍ ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገባቸውም ተሸላሚ ሆነዋል።

በክልል ደረጃ በሴቶች ዘርፍ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡት ሲፈን ፊጣ፣ ሎቲ ያደታ እና ሃዊ ጣሰው ለቃለ ምልልሱ ቀርበዋል፡፡ ሲፋን በሂሳብ ትምህርት ከ100 100 በማስመዝገብ ብዙም የማይስተዋለውን ከባዱን ፈተና በማሳካት መነጋገሪያ ሆናለች፡፡ ከሲፈን ጋር በዝግጅቱ የቀረቡ ሁለቱ ተማሪዎችም በሴቶች ዘርፍ እንደ ኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ ውጤት ለማስመዝገብ የበቁ ቀዳሚ ተማሪዎች በመሆን ሚያዚያ 29 ቀን 2014 ዓ.ም. የክልሉ ትምህርት ቢሮ ያዘጋጀውን የሜዳሊያ እና ገንዘብ ሽልማት ከክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ተቀብለዋል፡፡ 


ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2014 ዓ.ም የሁለተኛ ወሰነ ትምህርት የአካዳሚክ ካላንደር ማሻሻያ አድርጓል።

👉 የ8ኛ ክፍል ከተማ ዐቀፍ ፈተና ከሰኔ 27 እስከ 29/2014 ዓ.ም ድረስ ይሰጣል።

👉 የሁለተኛ መንፈቅ ዓመት ማጠቃለያ ፈተና ከሰኔ 20 እስከ 23/ 2014 ዓ.ም ድረስ ይሰጣል።

👉 የውጤት ማስረጃ የሚሰጥበት ቀን ሐምሌ 05/2014 ዓ.ም።

(ዝርዝር መረጃው ከላይ ተያይዟል።)

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#Update

በሰሜን ጎንደር ዞን በነበረው የጸጥታ ችግር ምክንያት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ያልወሰዱ እና ፈተናውን ወስደው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያላመጡ ተማሪዎች በሙሉ በቀጣይ ዓመት ፈተናውን እንደሚወስዱ ተገልጿል።

የዞኑ ትምህርት መምሪያ ተማሪዎቹ በቀጣይ ዓመት ለሚሰጠው ፈተና ከወዲሁ ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስቧል።

በዚህም የማጠናከሪያ ትምህርት ከግንቦት ወር ጀምሮ ለሁለት ወራት እንደሚሰጥ የዞኑ ትምህርት መምሪያ ገልጿል።

በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ያልወሰዱ እና ፈተናውን ወስደው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያላመጡ ተማሪዎች ከ2014 ዓ.ም ተፈታኞች ጋር በድጋሚ ፈተናውን እንዲፈተኑ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ መወሰኑ ይታወሳል።

(በሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት ወረዳ ስለጉዳዩ የጻፈው ደብዳቤ ከላይ ተያይዟል።)

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#Update
#Mizan_Tepi_University

በ2014 ዓ.ም ወደ ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ግንቦት 17 እና 18/2014 ዓ.ም እንደሆነ መገለጹ ይታወሳል።

አዲስ ገቢ ተማሪዎች የመመዝገቢያ ቦታ፦

👉 የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ~ ቴፒ ግቢ

👉 የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ~ ሚዛን ግቢ

ዩኒቨርሲቲው ሚዛን አማን እና ቴፒ ከተሞች ላይ ወደየካምፓሶቹ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ አውቶብሶች እንደተዘጋጁ ገልጿል።

ተጨማሪ መረጃ እና ድጋፍ ለማግኘት፦

ለሚዛን አማን
• 09-28-03-95-25
• 09-67-94-52-86
• 09-17-86-53-07
• 09-21-29-18-36

ለቴፒ
• 09-25-01-88-58
• 09-30-63-63-73

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#Wollo_University

ወሎ ዩኒቨርስቲ የአዲስ ገቢ ተማሪዎችን የመግቢያ ቀን አሳወቀ። በዚህም መሰረት 2014 በወሎ ዩኒቨርስቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ቀን #ግንቦት_21 እና 22 ,2014 ተብሏል።

📝Natural science --- ስማችሁ ከ A-K የሆናችሁ #ኮምቦልቻ ካምፓስ

📝Natural science --- ስማችሁ ከ L-Z የሆናችሁ #ደሴ ካምፓስ

📝All social science....Dessei Cumpas

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#WolloUniversity

ደሴ ግንቦት 14/2014 ወሎ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 823 ተማሪዎች እያስመረቀ ነው፡፡ ከተመራቂዎች መካከል 293ቱ ሴቶች ናቸው።

ዩኒቨርሲቲው በአሸባሪው ህወሓት ከወደመ በኋላ በቅንጅት መልሶ ተቋቁሞ መማር ማስተማር ስራውን ዳግም ጀምሮ ተማሪዎቹን ለዛሬው ምረቃ አብቅቷል።

ለዛሬ ምርቃ የደረሱ ተማሪዎች የሽብር ቡድኑ በፈጸመወ ወረራ ትምህርታቸው ቢስተጎጎልም ቅዳሜና እሁድ ጭምር አካክሰው ቆይታቸውን ያጠናቀቁ ናቸው፡፡

ከተመረቁት ውስጥ 106ቱ ሁለተኛ ዲግሪ ናቸው።

በምርቃን ስነ ስርዓቱ የተለያዩ ባድርሻ አካላት ተገኝተዋል
ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#Update
#WollegaUniversity

በ2014 ዓ.ም ወደ ወለጋ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ከግንቦት 15 እስከ 17/2014 ዓ.ም እንደሆነ መገለጹ ይታወቃል።

ዩኒቨርሲቲው ለአዲስ ገቢ ተማሪዎቹ የትራንስፖርት አገልግሎት ማዘጋጀቱን ገልጿል።

• መነሻ ከተማ፦ ደምቢ ዶሎ
መነሻ ሰዓት፦ ከጧቱ 12:00
ጉዞ ወደ ነቀምቴ፦ በ15/09/2014 ዓ.ም
አስተባባሪዎች፦
ለገሰ ግርማ ~ 0916640790
ዱሬሳ አለማየሁ ~ 0919521309

• መነሻ ከተማ፦ መንዲ
መነሻ ሰዓት፦ ከጧቱ 12:00
ጉዞ ወደ ነቀምቴ፦ በ15/09/2014 ዓ.ም
አስተባባሪዎች፦
መሀመድ ዑመር ~ 0912700614
ሚልኬሳ ታከለ ~ 0935063833

• መነሻ፦ አያና ከተማ
መነሻ ሰዓት፦ ከጧቱ 12:00
ጉዞ ወደ ነቀምቴ፦ በ15/09/2014 ዓ.ም
አስተባባሪዎች፦
ገመቹ ገለታ ~ 0930770690
ኒሞና ከበደ ~ 0918171173

• መነሻ፦ ሻምቡ ከተማ
መነሻ ሰዓት፦ ከጧቱ 12:00
ጉዞ ወደ ነቀምቴ፦ በ15/09/2014 ዓ.ም
አስተባባሪዎች፦
ሸሚን ኢብራሂም ~ 0917434355
አዳነች ደገፋ ~ 0964629049

• መነሻ፦ አዲስ አበባ (አስኮ)
መነሻ ሰዓት፦ ከጧቱ 12:00
ጉዞ ወደ ነቀምቴ፦
በ15/09/2014 ዓ.ም (2 አውቶቡሶች)
በ16/09/2014 ዓ.ም (1 አውቶቡስ)
አስተባባሪዎች ጀማል አደም ~ 0916700774
ደጋጋ ፈቀደ ~ 0917033569
ጃቤሳ አመንቴ ~ 0912290387
ቦንቱ ተመስገን ~ 0917675546
ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
የሐረማያ ዩኒቨርስቲ ከ5 ሺሕ በላይ አዲስ ተማሪዎች እየተቀበለ ነው

ግንቦት 14/2014 (ዋልታ) በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ ከ5 ሺሕ 1 መቶ በላይ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው እየገቡ ይገኛሉ።

ተማሪዎቹ ወደ ዩኒቨርሲቲው ሲደርሱም በአካባቢው ኅብረተሰብ፣ በዩኒቨርሲቲው አመራሮችና ነባር ተማሪዎች አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

በዩንቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት መንግስቱ ኡርጌ (ፕ/ር) እንዳሉት በዘንድሮው አመት በዩኒቨርሲቲ የተመደቡ 5 ሺሕ 180 አዲስ ተማሪዎች ወደ እየገቡ ነው።

ከኢትዮጵያውያን በተጨማሪ በኢትዮጵያ የትምህርት እድል ያገኙ የሶማሌ ላንድ፣ የደቡብ ሱዳን እና የጅቡቲ ዜጎች እንደሚገኙበት ገልፀዋል።

በተለይም የዩኒቨርሲቲው ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት ቀጣይ እንዲሆን ከአካባቢው ማኅበረሰብ እና የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ሲሰራ መቆየቱንና በቂ ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል።

ለሰላማዊ የመማር ማስተማር ሥራ ስጋት ሊሆኑ የሚችሉ ጉዳዮችንም ቀድሞ ከመከላከል አንፃር በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል።

ዩኒቨርሲቲውን የተቀላቀሉ አዲስ ተማሪዎችም በዩኒቨርስቲው ማኅበረሰብና በአካባቢው ነዋሪ በተደረገላቸው አቀባበል መደሰታቸውን ለዋልታ ተናግረዋል።

በሚኖራቸው ቆይታም ለዩኒቨርሲቲው ሰላማዊ የመማር ማስተማር የበኩላቸውን ለመወጣትና ትምህርታቸውን በአግባቡ ለመከታተል መዘጋጀታቸውን ጠቁመዋል።

የአካባቢው ማኅበረሰብም ወደ ዩኒቨርሲቲው የሚቀላቀሉ ተማሪዎች እንደ ቤተሰብ እንክብካቤ እንደሚያደርጉላቸው ገልፀዋል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ በጦርነቱ ጉዳት የደረሰባቸውን የትምህርት ተቋማት መልሶ ለመገንባት ዳያስፖራዉ እገዛ እንዲያደርግ ጥሪ አቀረቡ፡

የትምህርት ሚኒስቴር የጀመራቸውን ሪፎርም ስራዎችና በጦርነቱ ጉዳት የደረሰባቸውን የትምህርት ተቋማት መልሶ ለመገንባት በውጪ ሀገር ነዋሪ የሆነው ኢትዮጵያዊና ትዉልደ ኢትዮጵያዊ የበኩሉን ሚና እንዲጫወት ጥሪ አቀረበ ፡፡

በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራንና ተመራማሪዎች ጋር በተካሄደ ውይይት ላይ የትምህርት ሚንስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ እንደተናገሩት በሁሉም የትምህርት ርከን እየተካሄደ ያለው ሪፎርም ለመጪው የኢትዮጵያ ትውልድ የተሻለች ሀገር ለማስረከብ መሰረት የሚጥል ነው ብለዋል፡፡

የሕወሓት ቡድን በፈጸመው ወረራ ምክንያት የወደሙ አጅግ በርካታ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት በትምህርት ሚኒስቴር የግንባታ እቅዶች መቅረባቸውን የገለጹት ፕሮፌሰር ብርሀኑ እነዚህን የወደሙ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት በውጪ ሀገር ነዋሪ የሆነው ዳያስፖራ ተሳታፊ እንዲሆን ጥያቄ አቅርበዋል፡፡

በትምህርት ስርአቱ ላይ እየታየ ያለው የጥራት ፣ የብቃትና ሁለንተናዊ ክህሎት ያለው ዜጋን ከማፍራት አንጻር ያለው ችግር ስር የሰደደ ነው ያሉት ሚኒስትሩ የትምህርት ጥራትና ብቃት ላይ ስርነቀል የሆኑ ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

ከታችኛው የትምህርት ርከን እስከ ከፍተኛ ትምህርት ድረስ ያለው ችግር ሀገርን ለመገንባት መሰረታዊ ለውጥ የሚያስፈልገው መሆኑን የገለጹት ፕሮፌሰር ብርሀኑ ለዚህ ስኬታማነት በውጪ ሀገር ያለው ኢትዮጵያዊና ትዉልደ ኢትዮጵያዊ የከፍተኛ ትምህርት ባለሙያና ተመራማሪ የበኩሉን ሚና እንዲጫወት ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በተለይም ሁለተኛ ትውልድ የሆነው ዳያስፖራ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት መሰረታዊ ችግር ባለበት የእንግሊዝኛ ቋንቋ ማሻሻያ ፕሮግራም ላይ በመሳተፍና የእንግሊዝኛ ቋንቋን በማስተማር የትምህርት ስርአቱን የማስተማሪያ ቋንቋ ለመቀየር በሚደረገው ሀገራዊ ጥረት እገዛ እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡

የእንግሊዝኛ ቋንቋ ተናጋሪ ሀገራት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራንና ተመራማሪዎች ያላቸውን ትርፍ ጊዜ ጭምር በመጠቀም በከፍተኛ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፣ በከፍተኛ ትምህርት አመራር ፣ በጥናትና ምርምር ስራዎች ፣ ከሁለተኛ ዲግሪ በላይ እየተማሩ ያሉ ተማሪዎችን የማማከርና የማስተማር ዘርፍ ላይ ቢሰማሩ ለትምህርት ሪፎርሙ ስኬታማነት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ በማድረግ መጪው ትውልድ የተሻለች ኢትዮጵያን የሚገነባበት እድል ይፈጥራሉ ብለዋል፡፡


በለንደን የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ተፈሪ መለሰ በውይይቱ ላይ እንደተናገሩት በትምህርት ዘርፍ የተጀመረውን ሪፎርም ከግብ ለማድረስ በዩናይትድ ኪንግደም ነዋሪ የሆኑ ዳያስፖራ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራንና ተመራማሪዎች በአለም አቀፍ ደረጃ በሚቋቋመው የትምህርት ባለሙያዎች የዬኬ ቻፕተር ለሚያደርገው እንቅስቃሴ ኤምባሲው አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ማለታቸዉን ከኤምባሲዉ ያገኘነዉ መረጃ አመልቷል፡፡

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
The so called "ሀገር ተረካቢው ትውልድ"

ወደየት እየሄድን ነው?

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#Wollo_University

በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በወሎ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ግንቦት 21 እና 22/2014 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ግንቦት 23/2014 ዓ.ም ብቻ በቅጣት መመዝገብ ይቻላል።

ወደ ተቋሙ ስትሄዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

• ከ8 እስከ 12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች
ዋናውና ሁለት ኮፒ
• 3×4 ጉርድ ፎቶግራፍ (8)
• ብርድልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ልብስ
• የስፖርት ትጥቅ

ከተጠቀሱት ቀናት ውጪ የሚመጡ ተማሪዎችን የማያስተናግድ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።

(ለተጨማሪ መረጃ ከላይ የተያያዘውን ይመልከቱ።)

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT