STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
38.8K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.95K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
#SalaleUniversity

ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ በ2014 ዓ.ም በመደበኛ መርሃ ግብር በመጀመሪያ ዲግሪ የተመደቡ ተማሪዎችን
መቀበል ጀምሯል።

የአዲስ ገቢ ተማሪዎች ምዝገባ ግንቦት 08 እና 09/2014 ዓ.ም እንደሚከናወን ዩኒቨርሲቲው መግለጹ ይታወሳል።

ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ በ2014 ዓ.ም ከ4 ሺህ በላይ አዲስ ገቢ ተማሪዎች በትምህርት ሚኒስቴር ተመድበውለታል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#Hawassa_University

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የ2014 ዓ.ም አዲስ ገቢ ተማሪዎቹን መቀበል ጀምሯል፡፡

ዩኒቨርሲቲው የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች መግቢያ ግንቦት 08 እና 09/2014 ዓ.ም መሆኑን መግለጹ ይታወሳል።

ዩኒቨርሲቲው 5 ሺህ 200 አዲስ ገቢ ተማሪዎች በትምህርት ሚኒስቴር ተመድበውለታል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#KebriDehariUniversity

በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ወደ ቀብሪደሃር ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ የመግቢያ እና የምዝገባ ቀን ከግንቦት 18-20/2014 ዓ.ም መሆኑን እየገለፅን፤ በዩንቨርሲቲዉ ሬስትራር ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ ሪፖርት እንድታደርጉ እናስታዉቃለን።

፨ወደ ዩንቨርሲቲው ስትመጡ
1. የ8ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሰርተፍኬት ዋናውንና ኮፒዉ
2. የ10ኛ እና 12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሰርተፍኬት ዋናውንና ኮፒ
3. ከ9 እስከ 12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውንና ኮፒ
4. 3x4 የሆነ ጉርድ ፎቶ ግራፍ (ብዛት=10)
5. አንሶላ፣የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ ይዛችሁ እንድትመጡ እናሳስባለን፡፡


ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች አቀባበል እየተደረገ ነው

ግንቦት 9/2014 (ዋልታ) የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ለ10ኛ ጊዜ በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በትምህርት ሚኒስቴር ለተመደቡ ከ4 ሺሕ 500 በላይ አዲስ ገቢ ተማሪዎችን በዛሬው ዕለት አቀባበል እያደረገ ነው፡፡

በአቀባበል ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት፣ ምክትል ፕሬዝዳንቶችና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች አደረጃጀት እንዲሁም የከተማው ማኅበረሰብ ተወካዮች ተገኝተዋል።

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ሀብታሙ አበበ (ዶ/ር) ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት በማስተላለፍ ዩኒቨርሲቲው በቅርብ ጊዜ ተመስርቶ የመማር ማስተማሩን ሥራ የጀመረ ዩኒቨርሲቲ ቢሆንም በርካታ ሀገር ዐቀፍና ክልላዊ ድሎችን የተጎናፀፈ ተቋም መሆኑን ገልጸዋል።

በተጨማሪም ሰላም ወዳድ ማኅበረሰብ የሚገኝበትና የሰላም አምባሳደር የሆነ ግቢ እንደሆነ መናገራቸውን ከዩኚቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡


ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#Oda_Bultum_University

ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ የ2014 ዓ.ም አዲስ ገቢ ተማሪዎቹን ተቀብሏል፡፡

ዩኒቨርሲቲው የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች መግቢያ ግንቦት 08 እና 09/2014 ዓ.ም መሆኑን መግለጹ ይታወሳል።

ዩኒቨርሲቲው 3 ሺህ 500 አዲስ ገቢ ተማሪዎች በትምህርት ሚኒስቴር ተመድበውለታል።


ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#Jinka_University

በ2014 ዓ/ም በጂንካ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ተማሪዎች የመግቢያ ቀን ግንቦት 25-26 /2014 ዓ/ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የምዝገባ ሂደቱንና ሌሎች ተጨማሪ መረጀዎችን በዩኒቨርሲቲው ድረገፅ www.jku.edu.et እና በፌስቡክ ገፅ
https://www.facebook.com/178538809733160/posts/1039175540336145/ ላይ ስለሚለቀቅ በዛ መከታተል ትችላላችሁ።


ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#Update

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የነበረችው ፅጌሬዳ ግርማይን በመግደል የተከሰሰው ተማሪ ለውሳኔ ለግንቦት 19/2014 ዓ.ም ተቀጥሯል።

ተከሳሹ የመከላከያ ምስክሮች በማቅረብ ራሱን ሲከላከል ቆይቷል።

ፍርድ ቤት የቀረቡ ምስክሮች "ሟች እና ተከሳሾች ጓደኛሞች እንደነበሩ እንደሚያውቁና ከዚያ ውጪ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ" ገልጸዋል።

በሕግ ጥላ ስር በሚገኘው ተከሳሽ ብሩክ በላይነህ ላይ የፍርድ ማቅለያ እና ማክበጃ መቅረቡን የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሕግ አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ መርኪያ መንገሻ ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተናግረዋል።

ተከሳሹ በአርባ ምንጭ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዳዩን እየተከታተለ ይገኛል።

ፍርድ ቤቱ ቤቱ ውሳኔ ለመስጠት ተለወጫ ቀጠሮ ለግንቦት 19/2014 ዓ.ም ሰጥቷል።

ጥር 23/2014 ዓ.ም የተገደለችው የ20 ዓመቷ ተማሪ ፅጌሬዳ ግርማይ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሆቴልና ቱሪዝም ማኔጅመንት የ2ኛ ዓመት ተማሪ ነበረች፡፡

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#Fake_News_Alert

በ2015 ዓ.ም የአንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ባሉበት የትምህርት ደረጃ እንዲቀጥሉ የትምህርት ሚኒስትሩ ተናገሩ በሚል በማኅበራዊ የትስስር ገጾች የሚዘዋወረው መረጃ #ሐሰት መሆኑን እንገልጻለን።

ቲክቫህ እንደዚህ አይነት ዘገባ አለመስራቱንም ልናረጋግጥ እንወዳለን።

ሀሰተኛ፣ ነተዛቡ እና ያልተረጋገጡ መረጃ ከሚያሰራጩ የማኅበራዊ ሚዲያ አካውንቶች ራስዎን ይጠብቁ፡፡

ትክክለኛው የትምህርት ሚኒስቴር አድራሻ፦

https://www.facebook.com/fdremoe

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#Ethiopian_Civil_Service_University

የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በ2ኛ ዲግሪ ፕሮግራም በመደበኛ፣ በክረምት፣ በማታ እና በቅዳሜና እሁድ መእሃ ግብሮች ለመማር የተመዘገባችሁ አመልካቾች የመግቢያ ፈተና ግንቦት 20 እና 21/2014 ዓ.ም እንደሚሰጥ አሳውቋል።

(የትምህርት ክፍሎች እና ፈተናው የሚሰጥበት ቀን ዝርዝር ከላይ ተያይዟል።)

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT