STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
38.8K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.95K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
ወራቤ ዩኒቨርሲቲ የቅድመ ምረቃ መደበኛ መርሃ ግብር የ2ኛ ዓመት (2013 ባች) የ2ኛ ሴሚስተር ምዝገባ ግንቦት 17 እና 18/2014 ዓ.ም እንደሚከናወን አሳውቋል።

የ2ኛ ዓመት 2ኛ ሴሚስተር ተማሪዎች ትምህርት ምዝገባ ግንቦት 19/2014 ዓ.ም እንደሚጀምር ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

(ዝርዝሩ ከላይ ተያይዟል። )

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#GambellaUniversity

በ2014 ዓ.ም በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ ግንቦት 29 እና 30/2014 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ወደ ተቋሙ ስትሄዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

• የ8ኛ፣ 10ኛ እና 12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው
• ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው
• 3×4 ጉርድ ፎቶግራፍ (6)
• አንሶላ እና የትራስ ልብስ
• የስፖርት ትጥቅ

ለተጨማሪ መረጃ የዩኒቨርሲቲውን ድረ-ገጽ www.gmu.edu.et ይመልከቱ።

ከተጠቀሱት ቀናት ውጪ የሚመጡ ተማሪዎችን የማያስተናግድ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#AddisAbabaEducationBureau
#MinistryOfEducation

"ተማሪዎች ዘንድሮ በያላችሁበት ክፍል ትደግማላቸሁ" በሚል የሚናፈሰው ወሬ ከእውነት የራቀ መሆኑን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።

ተማሪዎች የ2014 የትምህርት ዘመን የማጠቃለያ ፈተና ለመውሰድ እየተዘጋጁ መሆኑን የገለጸው ቢሮው፤ ኃላፊነት የጎደላቸው አካላት ሆን ብለው ተማሪዎችን ለማዘናጋት ዘንድሮ ከክፍል ወደ ክፍል መዘዋወር የለም የሚል ሀሰት መረጃ እያሰራጩ መሆኑን ገልጿል።

መረጃው ፍጹም ከእውነት የራቀ እንዲሁም ከዚህ ጋር የተያያዘ ከትምህርት ሚኒስቴር የወረደ አቅጣጫ የሌለ መሆኑን ቢሮው አረጋግጧል።

በተመሳሳይ "ሁሉም የአንደኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ባሉበት የትምህርት ደረጃ እንዲቀጥሉ ተወስኗል" በሚል የሚዘዋወረው መረጃ የተሳሳተ እና ከእውነት የራቀ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

የተቋሙን ስም እና አርማ በመጠቀም የተሳሳቱ እና የተዛቡ መረጃዎችን በመልቀቅ ውዥንብር እየፈጠሩ ያሉ የማህበራዊ ሚዲያዎችን ማየቱን ሚኒስቴሩ ጠቁሟል።

በመሆኑም ተማሪዎች የሚሰራጩት መረጃዎች የተሳሳቱ እና ከእውነት የራቁ መሆናቸውን አውቀው ትኩረታቸውን ትምህርታቸው ላይ ብቻ እንዲያደርጉ ሚኒስቴሩ ጠይቋል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
የትምህርት ማህበረሰቡ ይህንን በመረዳት ከተሳሳቱ መረጃዎች ራሳችሁን በማራቅ ሌሎች እንዳይሳሳቱ የማድረግ ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ ጥሪ እያቀረብን የትምህርት ሚኒስቴር ትክከለኛ የመረጃ ማሳረጫዎች የሚከተሉት መሆናቸውን እናሳውቃለን

ፌስቡክ-https://www.facebook.com/fdremoe

ቴሌግራም - https://t.me/ethio_moe

ሊንክድኢን- https://www.linkedin.com/company/ministry-of-education-ethiopia

ትዊተር- https://twitter.com/fdremoe?t=dFhfr8QytU_6LqQuVUIp2A&s=09

ከእነዚህ ውጭ ባሉ አድራሻዎች እኛን የሚመለከቱ አሳሳች መረጃዎች ስታገኙ እንድትጠቁሙንም በአክብሮት እንጠይቃለን።

ትምህርት ሚኒስቴር

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
በ47 ዓመቷ ዩኒቨርሲቲ የገባችው የ4 ልጆች እናት ❗️

ይህች እናት ተማሪ ይመኙሽ ምትኩ ትባላለች። ከ25 ዓመት በኋላ ወደ ትምህርት ገበታ በመመለስና ውጤት በማምጣት ወለጋ ዩንቨርስቲ ተመድባለች። ታዲያ ዛሬ በ47 ዓመት እድሜዋ ወደ ዩኒቨርሲቲው በማቅናት ምዝገባ ያካሄደቸው ይች አዲስ ተመዝጋቢ እናት የበርካቶችን ቀለብ ስባለች።

የአራት ልጆች እናት ስትሆን ከፍቃዷ ውጪ በቤተሰቦቿ ፍላጎት ትዳር እንድትይዝ በመደረጉ ትምህርቷን ለማቋረጥ ተገዳ እንደነበርም ተናግራለች።

በዩኒቨርሲቲ ቆይታዋ የጤና ትምህርት በማጥናት በሴቶች እና በህጻናት የጤና ችግሮች ዙሪያ የመስራት ፍላጎት እንዳላት አስታውቃለች።

በያዝነው ወር የ69 ዓመት የእድሜ ባለፀጋ እና የ11 ልጆች አባት የሆኑት ግለሰብ ጅማ ዩኒቨርሲቲን መቀላቀላቸው ይታወሳል።

© alain

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
Alert
ቃሊቲ ገላን 2ኛ ደረጃ ት/ቤት አለመረጋጋት አለ።

@NATIONALEXAMSRESULT
Alert
ቃሊቲ ገላን 2ኛ ደረጃ ት/ቤት አለመረጋጋት አለ። ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ፖሊሶች በቦታው እየሄዱ ይገኛሉ።

@NATIONALEXAMSRESULT
Alert
ቃሊቲ ገላን 2ኛ ደረጃ ት/ቤት አለመረጋጋት አለ።
መረጃ ለማግኘት እየጣርን ነው
@NATIONALEXAMSRESULT
Alert
ቃሊቲ ገላን 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በተማሪዎች መምህራን እና ፖሊሶች መካከል አለመረጋጋት አለ።

በጉዳዩ ላይ መረጃ ለማግኘት እየጣርን ነው።

@NATIONALEXAMSRESULT
"ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንዲራ ውጪ በት/ቤታችን ውስጥ አይሰቀል " የ2ኛ ደረጃ ተማሪዎች

አዲስ አበባ ቃሊቲ ገላን 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የተፈጠረው ምንድን ነው?

ባሳለፍነው ሳምንት የገላን 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የኦሮምያ ክልል ባንዲራ እንዲሰቀል እና የክልሉ መዝሙርም እንዲዘመር ይታዘዛል። ይሁንና ተማሪዎች ከኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር እና ባንዲራ ውጪ አንዘምርም አንሰቅልምም በሚል ቅሬታቸውን ያሰማሉ።

ከትናንት ወዲያ ሰኞ ዕለት ደግሞ ጠዋት ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር ከተዘመረ እና ብሔራዊ ባንዲራ ከተሰቀለ በኋላ የኦሮምያ ክልል ባንዲራ ሊሰቀል እና የክልሉ መዝሙር ሊዘመር ሲል ተማሪዎች ወደክፍል መግባት ይጀምራሉ። ይሁንና የትምህርት ቤቱ አስተዳደር እና አንዳንድ መምህራን በግዴታ ካልዘመራችሁ ባንዲራውንም
ካልሰቀላችሁ ብለው ተማሪዎችን ማስገደድ ሲጀምሩ ተማሪዎች ይህንን ሳይቀበሉ ቀርተው ወደ ክፍላቸው ይገባሉ። ትናንትናም እንዲሁ ይቀጥላል።

ዛሬ ጠዋት ግን የትምህርት ቤቱ አስተዳደር ቁጥራቸው ብዙ የሚሆኑ በከፊል የታጠቁ ፖሊሶችን በጊቢው ውስጥ እና አካባቢ በማሰማራት በግዴታ ሊያስዘምራቸው በመሞከሩ ተማሪዎች ቅሬታቸውን ማሰማት ይጀምራሉ። ኃይል በመጠቀም ለማስገደድ የሞከሩ መምህራንም ነበሩ።

የተማሪዎቹን ጩኸት የሰማው የአካባቢው ኅብረተሰብ እና ወላጆችም በመደናገጥ ወደ ትምህርት ቤቱ ያመራሉ። ተማሪዎችም በዚህ ሁኔታ መማር እንችልም ሲሉ ቅሬታቸውን ያሰሙ ሲሆን ሁኔታው ሳይባባስ ወደቤት ተበትነዋል።

ተጨማሪ መረጃ አጣርተን እናደርሳለን


ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
Photo
#Update

ከጠዋቱ ክስተት ጋር በተያያዘ የገላን 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ከመምህራንን ጋር ስብሰባ ተቀምጣል።

ተጨማሪ መረጃ አጣርተን እናደርሳለን


ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
ኢትዮ ቴሌኮም የ 1 ሰአት ገደብ የሌለው የሞባይል ኢንተርኔት ጥቅል አቅርቧል።

12 ብር ከፍላቹ ለ1 ሰአት የፈለጋቹትን ያለ ገደብ መጠቀም ትችላላችሁ ማለት ነዉ።

በቴሌብር - ማይ ኢቲዮቴሌ እና ኢትዮ ገበታላይ ነዉ ምታገኙት። በነዚህ አማራጮች ስትጠቀሙ 10% ቅናሽ ይኖረዋል 10 ብር ይሆናል።

አሪፍ አማራጭ ይመስለኛል ምን ታስባላቹ?
መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#ማስታወቂያ

የ2014 ዓ.ም የህግ ትምህርት መውጫ ፈተና (Exit Exam) ፈተናው የሚሰጥበት ቀናት ከሰኔ 21 - 24 ቀን 2014 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ አራት የስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 - 6፡00 ሰዓት ብቻ መሆኑን አውቃችሁ ተፈታኞች ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት እንድታደርጉ እናሳስባለን


ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
#ማስታወቂያ የ2014 ዓ.ም የህግ ትምህርት መውጫ ፈተና (Exit Exam) ፈተናው የሚሰጥበት ቀናት ከሰኔ 21 - 24 ቀን 2014 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ አራት የስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 - 6፡00 ሰዓት ብቻ መሆኑን አውቃችሁ ተፈታኞች ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት እንድታደርጉ እናሳስባለን ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን @NATIONALEXAMSRESULT
የቅድመ ዝግጅት ማስታወቂያ

የህግ ትምህርት መውጫ ፈተና ለመፈተን በዝግጅት ላይ ለምትገኙ ተፈታኞች (Exit Exam)

የህግ ትምህርት መውጫ ፈተና ቀደም ሲል በተገለፀው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ከግንቦት 29 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2014 ዓ.ም ለመስጠት የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በመሰራት ላይ እንገኛለን፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ የተፈታኞች ምዝገባ አንዱ እና ዋንኛው የቅድመ ፈተና አሰጣጥ ዝግጅት ተግባር ሲሆን ተፈታኞች ከታች የተዘረዘሩትን ነጥቦች ትኩረት በመስጠት ግንዛቤ እንዲጨብጡ እናሳስባለን፡፡
የምዝገባ ቀናት ማስታወቂያ - የተፈታኞች የምዝገባ ቀናት ከጥቂት ቀናት በኋላ ሲወሰን ለሁሉም አስፈታኝ ዩኒቨርሲቲዎች በደብዳቤ እና ለተፈታኞች “ አለ ” በሚለው የቴሌግራም ቻናል ይፋ ይደረጋል፡፡

የምዝገባ ቀናት ጊዜ ሰሌዳ ቆይታ - ከተፈታኞች ምዝገባ መጠናቀቅ በኋላ የፈተና ህትመት የሚካሄድበት ወቅት በመሆኑ እና ፈተናውን በጊዜ ሰሌዳው መሰረት ለመስጠት ያለው ጊዜ አነስተኛ በመሆኑ የተፈታኞች ምዝገባ ቀናት ቆይታ የተፈታኞች ምዝገባ መጀመሩ በደብዳቤ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ሰባት የስራ ቀናት ብቻ ይሆናል፡፡

ተፈታኞች ለምዝገባ እና ለመፈተን ሲመጡ በተጨማሪ ግንዛቤ የሚያስፈልጋቸው ሁኔታዎች -
በሚማርበት ዩኒቨርሲቲ ፈተናውን ለመውሰድ የተፈቀደለት እና የተመዘገበ መሆን አለበት፣
ለምዝገባ የተወሰነውን ክፍያ በዩኒቨርሲቲው ባንክ ሂሳብ ቁጥር ብቻ ገቢ ያደረገ መሆን አለበት፣ ከዩኒቨርሲቲው ባንክ ሂሳብ ቁጥር ውጭ በሌላ ተቋም ገቢ በማድረግ ደረሰኝ ማቅረብ ወይም ከምዝገባ ጊዜ ሰሌዳ ውጪ ለዩኒቨርሲቲውም ገቢ በማድረግ ደረሰኝ ማቅረብ ተቀባይነት የለውም፣ ፈተና ላይ ለመቀመጥም አያስችልም፣
ለመፈተን የተመዘገበ ስለመሆኑ በዩኒቨርሲቲው በኩል ስሙ ለኢንስቲትዩቱ የተላከ መሆን አለበት፣ በምዝገባ ጊዜ ገደብ ውስጥ ብቻ ስሙ በዩኒቨርሲቲው መዝጋቢነት እና በኢንስቲትዩ ማረጋገጫ ያልተላለፈ ተመዝጋቢ ፈተና ላይ መቀመጥ አይችልም፣
ወደፊት በሚገለፀው የምዝገባ ጊዜ ሰሌዳ ብቻ የሚፈተንበትን ዩኒቨርሲቲ ምርጫ እንዲሁም በኤግዘምሽን ምክንያት የማይፈተናቸው ፈተናዎች ካሉ ማሳወቅ አለበት፣ ከምዘገባ ጊዜ ሰሌዳው ውጭ የሚቀርብ ኤግዘምሽን መረጃ እና የዩኒቨርሲቲ ለውጥ ተቀባይነት የለውም፣
በምዝገባ ወቅት የሚፈተንበትን ዩኒቨርሲቲ ምርጫ ሲመርጥ ከተማረበት ዩኒቨርሲቲ ርቆ የሚገኝ ከሆነ ህጋዊ ምክንያት (የመስሪያ ቤት መታወቂያ፣ የነዋሪነት መታወቂያ፣ አስገዳጅ የስራ ወይም የፀጥታ ሁኔታ መረጃ፣ የሆስፒታል መረጃ፣ ሌሎች) ማሳየት / ማቅረብ አለበት፣ ጉዳዩም ለኢንስቲትዩቱ በደብዳቤ መድረስ ይገባዋል፣ በፈተና አሰጣጥ ወቅት የተፈታኞች መረጃ ማጣራት ሲደረግ ስህተት ሆኖ ከተገኘ ፈተናው ይሰረዝበታል፣
ከተማረበት ዩኒቨርሲቲ ውጭ ተመዝግቦ የተገኘ ተፈታኝ ወይም ያላስተማረውን ተማሪ መዝግቦ መረጃ ያስተላለፈ ዩኒቨርሲቲ የምዝገባው መረጃ ውድቅ የሚደረግበት ሲሆን ኃላፊነቱን ተፈታኙ / ዩኒቨርሲቲው የሚወስድ ይሆናል፣ ፈተና ላይ ለመቀመጥም አያስችልም፣
በጊዜ ሰሌዳው መሰረት ዩኒቨርሲቲዎች የተመዝጋቢዎች ዝርዝር እና የተሰበሰበ ገንዘብ ገቢ ካላደረጉ ምንም ተፈታኝ እንዳልመዘገቡ ይቆጠራል / ኃላፊነት ይወስዳሉ፣
በፈተና አሰጣጥ ወቅት ማንነትን የሚገልጽ ህጋዊ መታወቂያ፣ እስክሪቢቶ እና የተፈቀዱ ማጣቀሻዎችን ብቻ ይዞ መገኘት ይገባል፣
በፈተና አሰጣጥ ወቅት ከተፈቀዱ ማጣቀሻዎች ውጪ ማንኛውንም ዓይነት ፅሑፍ ያለበት ወረቀትም ሆነ ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ፣ የእጅ ሰዓት፣ ተፈታኙ ከስራ መደቡ አንፃር ህጋዊ የሆነ ሆኖም በፈተና ጣቢያ የማይፈቀድ ነገር ይዞ መገኘት እንዲሁም ሌሎች በፈተና አሰጣጥ ወቅት የማይፈቀዱ ነገሮችን ይዞ መገኘት አይቻልም፣ በአራተኛው የፈተና ቀናት ማንነትን ከሚገልጽ ህጋዊ መታወቂያ እና ከእስክሪቢቶ በስተቀር ምንም ነገር ይዞ መምጣት አይፈቀድም፡፡ በቅድመ ፈተና ፍተሻ ወቅት በፈተና መስጫ ግቢ እና ክፍል ውስጥ ይህ ሆኖ ከተገኘ ሙሉ የፈተና ውጤት ይሰረዛል፣
በፈተና አሰጣጥ ወቅት ምንም ዓይነት ነገር መቀያየር እና መዋዋስ የማይቻል በመሆኑ ሁሉም ተፈታኝ በግሉ የሚጠቀምበትን ነገር ይዞ መገኘት ይገባዋል፣
የፈተና አሰጣጥ ከተጀመረ በኋላ በተለያየ ህጋዊም ሆነ ህጋዊ ባለሆነ ምክንያት ከሰላሳ ደቂቃ በኋላ አርፍዶ የሚመጣ ተፈታኝ ወደ ፈተና ግቢም ሆነ ክፍል ውስጥ መግባት አይፈቀድም፣ በመሆኑም ለፍተሻ ሂደት እና ለቅድመ ዝግጅት ሲባል ማንኛውም ተፈታኝ ፈተና ከሚሰጥበት ሰዓት አንድ ሰዓት ቀደም ብሎ ወደ ፈተና ጣቢያ ጊቢ እንዲደርስ ይመከራል፣
ውጤትን በተመለከተ ቅሬታ ካለ በዩኒቨርሲቲ በኩል በደብዳቤ ለኢንስቲትዩቱ የሚቀርብ ይሆናል፡፡

ኢንስቲትዩቱ - መልካም የቅድመ ዝግጅት ጊዜ!
ማስታወሻ - በቀጣይ ባሉት ቀናት እና ሳምንት ትኩረት የሚያስፈልጋቸው ማስታወቂያዎችን ይከታተሉ / ለሌሎች ያሳውቁ፡፡

#አለ_ህግ


ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#DillaUniversity

ዲላ ዩኒቨርሲቲ በ2014 ዓ.ም ለተመደቡለት አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች ጥሪ ለማድረግ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እያከናወነ መሆኑን አሳውቋል።

በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ለተማሪዎቹ ጥሪ እንደሚደረግ የዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራር ለ #ቲክቫህዩኒቨርሲቲ ገልጿል።

ዲላ ዩኒቨርሲቲ በ2014 የትምህርት ዘመን 5 ሺህ 780 አዲስ ገቢ ተማሪዎች በትምህርት ሚኒስቴር ተመድበውለታል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
12ኛ ክፍልን ከልጃቸው ጋር ተፈትነው ዩኒቨርስቲ የገቡት አርሶ አደሯ የአራት ልጆች እናት

"የአስረኛ ክፍል ተማሪ ሳለሁ ቤተሰቦቼ ከምወደው ትምህርት አቋርጠውኝ ለማላውቀው ሰው አስገድደው ዳሩኝ፤ ቢሆንም ትምህርት በጣም ስለምወድ ልጆቼን ካስተማርኩ በኋላ ወደ ትምህርቴ ተመልሼ ዩኒቨርስቲ የመግባት እድል አግኝቻለሁ" ይላሉ የ47 ዓመቷ ወ/ሮ ይመኙሽ ምትኩ።

ወ/ሮ ይመኙሽ ምትኩ የአራት ልጆች እናት ሲሆኑ፣ በዚህ ዓመት የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ወስደው ጥሩ ውጤት በማስመዝገብ ወለጋ ዩኒቨርስቲ ገብተዋል።

ከሦስተኛ ልጃቸው ጋር ከአስረኛ ክፍል ጀምሮ አንድ ክፍል የተማሩት ወ/ሮ ይመኙሽ፣ ወደ ቤት ሲመለሱም ሌሊት ከልጃቸው ጋር አብረው ቁጭ ብለው ያጠኑ እንደነበር ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ወ/ሮ ይመኙሽ የአስረኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተናን 3.7 ሲያመጡ፣ ልጃቸው ደቻሳ ደግሞ 3.9 በማምጣት ነበር ወደ መሰናዶ ትምህርት አብረው የገቡት።

ይህ የሆነው በ2011 ዓ.ም ሲሆን፣ የመሰናዶ ትምህርታቸውንም እናትና ልጅ በአንድ ክፍል ጎን ለጎን ተቀምጠው ነው የተከታተሉት።l
ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#JinkaUniversity

ጂንካ ዩኒቨርሲቲ ከትምህርት ሚኒስቴር የተመደባችሁ የ2014 ዓ.ም አዲስ ገቢ ተማሪዎችን ለመቀበል ከግንቦት 25-26/2014 ጥሪ ማስተላለፉ ይታወሳል። በመሆኑም የተማሪዎችንና የተማሪ ወላጆችን ድካምና እንግልት ለመቀነስ ሲባል እስከ ኮንሶና አርባምንጭ ከተሞች የነፃ የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት የዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት መወሰኑን ስናሳውቃችሁ በደስታ ነው።

በዚህም መሠረት በሁለቱም ማእከላት ማለትም በኮንሶና አርባምንጭ ከተሞች የሚያስተባብሩ ኮሚቴዎች የተዋቀሩ ሲሆን የአስተባባሪዎችን አድራሻ በዚሁ በዩኒቨርሲቲው የፌስቡክ ገፅና የቴሌግራም ቻናል t.me/JKUPIR ላይ የምናስቀምጥላችሁ ይሆናል። #ዩንቨርሲቲው

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT