Natinael Mekonnen
7.77K subscribers
16.4K photos
1.1K videos
20 files
2.52K links
ይህ ቻናል ቴሌግራሜ hacked በተደረገበት ሳት ለግዝያዊነት የከፈትኩት ቻናል ነው ለችግር ጊዜ ይጠቅማል ተቀላቀሉ
በቀጥታ መረጃዎችን ለመስጠት ከፈለጉ @NatnaelMekonnen7 በማለት መረጃዎችን ይላኩልን
Facebook.com/natnaelmekonnen.et
Instagram.com/natnaelmekonnen21
Telegram https://t.me/NatinaelMekonnen21
Download Telegram
በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን በሀሞሮ ወረዳ ላይ ለበርካታ ዓመታት የህዝብን ሰላም ሲያውኩ የነበሩ የሽኔ አባላት ለምዕራብ ዕዝ ክፍለጦር እጅ መስጠታቸው ተገለፀ።

በጃን ኢፓ ሲመራ የነበረውና ሰላሳ አምስት የሰው ሀይል ያለው ቡድን ሙሉ ለሙሉ ከሰላሳ አራት የነፍስ ወከፍ መሳሪያ ጋር እራሱ አመራሩን ጃን ኢፓን ጨምሮ በቀጠናው ለሚገኘው መከላከያ ሰራዊት እጅ ሠጥተዋል።

የክፍለጦሩ ምክትል አዛዥ ሻለቃ ወልዳይ አስፋው በአካባቢው ለብዙ ዓመታት ከህዝቡ ጋርና ከሽብር ቡድኑ ጋር ባደረግነው ውይይት ከጦርነት ይልቅ ሰላምን አማራጭ አድርገው በፈቃደኝነት ከፍተኛ አመራሩን ጃል ኢፓን ጨምሮ ሰላሳ አምስት ታጣቂዎች ከነ ሙሉ ትጥቃቸው እጅ እንዲሠጡ አድርገናል ብለዋል።

በጦርነት የሚገኝ ትርፍ የለም ያሉት ሻለቃ ወልዳይ አስፋው ቀጣይም በድርድርና በሰላማዊ ውይይት የሚያምኑትን ታጣቂዎች እየመከርን ወደ ሰላም እንዲመጡ የማድረግ ስራዎችን ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር በመሆን አጠናክረን እንቀጥልበታለን ብለዋል።

የሀሞሮ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ቀጤሳ ሽፈራው መከላከያ ሰራዊቱ በየጊዜው በሽብር ቡድኑ ላይ በሚወስደው እርምጃ ከፍተኛ ድል እያስመዘገበ መሆኑን ተናግረው ዛሬም አብዛኛው የሽብር ቡድኑ የሰላምን አማራጭ እንዲጠቀም ያደረገው ሠራዊቱ በመሆኑ ትልቅ ክብር ይገበዋል ሲሉ ተናግረዋል።

የሽብር ቡድኑ ከፍተኛ አመራር ጃን ኢፖ አሁን እያደረግን ባለው የትግል አቅጣጫ ለኦሮሞ ህዝብም ሆነ ለኢትዮጵያ የማይጠቅምና እርስ በእርስ ደም የሚያፋስስ በመሆኑ የእስካሁኑ ይበቃል በማለትና በተሰጠን የሰላም አማራጭ መጠቀምን በመምረጥ በእኔ የሚመራውን ሙሉ ቡድን ይዤ ለመከላከያ ሰራዊቱ እጅ ሰጥቻለው ሲል አስረድቷል።
„በኢትዮጵያ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለማስቀረት እንደ ሰጎን አንገትን በአሸዋ ስውጥ መደበቅ ሳይሆን፤ የችግሩን መንስኤ መጋፈጥና በሰከነ መንገድ መፍታት ይገባል“

አረጋዊ በርሔ (ዶ/ር) በታሪካዊው ራስ መኮንን አዳራሽ በተካሄደው 4ኛው ልዩ ሴሚናር ላይ ከተናገሩት የተወሰደ፡፡
ዩቲዩበሮቹ በቁጥጥር ስር ዋሉ...🇪🇹👌

ለማህበረሰቡ ወግና ባህል ፍፁም ተቃራኒ የሆነ ሐሰተኛ እና አፀያፊ የፈጠራ ታሪክ እያሰራጩ ህዝብን የሚያደናግሩ ዩቲዩበሮችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ሃሰተኛ መረጃ እና ከማህበረሰቡ መልካም ባህልና ወግ የተቃረኑ አፀያፊ የፈጠራ ታሪኮችን በማህበራዊ ሚዲያ እያሰራጩ በህዝብ ላይ ውዥንብር እና መደናገርን የሚፈጥሩ ግለሰቦች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል፡፡

ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ አላማ ከመጠቀም ይልቅ ገንዘብ ለማግኘት ሲሉ ብቻ ከእውነት የራቁ መሰረተ ቢስ የፈጠራ አፀያፊ ወሬዎችን እየፈበረኩ በማሰራጨት የህዝብን ደህንነት ስጋት ላይ የሚጥሉ ዩቲዩበሮችን በቁጥጥር ስር ማዋል መጀመሩን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 አማረ እና ቤተሰቦቹ በተባለ ህንፃ ላይ ቢሮ ተከራይተው የተለያዩ የዩቲዩብ ገፆችን በመክፈት የማህበረሰቡን ሥነ ልቦና የሚጎዱ የፈጠራ ታሪክ በማሰራጨት የተጠረጠሩ ስድስት ግለሰቦች በህዝብ ጥቆማ እና ፖሊስ ባደረገው ክትትል ተይዘው በየካ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ምርመራ እየተጣራ ይገኛል፡፡
በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል መቅደስ መብራት መኮንን የተባለችው ግለሰብ ሮሄ፣ ልዩነት፣ ጣዕም፣ አዲስ አለም፣ ዘይቤ፣ ህይወት፣ እይታ፣ እና ዩኒት ህይወት የተባሉ የዩቲዩብ ገፆችን በመክፈት በስራ አስኪያጅነት ስትመራ የነበረች ናት ተብሏል፡፡

ብሩክ ወርቅነህ ጌታሰው የተባለ ግለሰብ ደግሞ ገፆቹን በምክትል ስራ አስኪያጅነት እና በአስተባባሪነት ሲመራ የነበረ ሲሆን ናትናኤል አበራ በቀለ፣ እየሩሳሌም አስማረ ምህረት እና ምህረት ያሲን ቲጋ የተባሉት ግለሰቦች ደግሞ በፕሮግራም አቅራቢነት እንዲሁም ናትናኤል ዮሃንስ አሸነፍ በካሜራ ባለሙያነት ሲሰሩ የነበሩ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
በአምስት የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እጅግ ዘመናዊ የሆነ የመልቲ ሚዲያ ስቱዲዮ ግንባታ ተከናውኗል፡፡

መልቲ ሚዲያ ስቱዲዮ

ስቱዲዮቹ በትምህርት ሚኒስቴር፣ ማስተርካርድ ፋውንዴሽን፣ አሪዞና ስቴት ዩኒቨርሲቲ እና ሻያሾኔ ኩባንያ ትብብር በተተገበረ e-SHE የተባለ ፕሮግራም አማካኝነት የተገነቡ ናቸው።

ስቱዲዮቹ በ'ሪሶርስ ማዕከልነት' የሚያገለግሉ ሲሆን የዲጂታል ትምህርትን ለማጠናከር ትልቅ ፋይዳ ይኖራቸዋል።

ስቱዲዮቹ በየትኞቹ ዩኒቨርሲቲዎች ይገኛሉ?

ስቱዲዮቹ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ጅማ ዩኒቨርሲቲ፣ ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ፣ ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ እና ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ መቋቋማቸው ተገልጿል።

እነዚህ ስቱዲዮች የከፍተኛ ትምህርት ሽግግርን በአምስቱ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም በቅርብ ርቀት በሚገኙ አስር ክላስተር ዩኒቨርሲቲዎች ለማምጣት እንደሚያስችሉ ይጠበቃል።

የስቱዲዮቹ ሌሎች ጠቀሜታዎች

መምህራን ስቱዲዮቹን በመጠቀም ለe-learning የሚጠቀሟቸውን ኮርሶች ማዘጋጀት ይችላሉ። እነዚህ ዩኒቨርሲቲዎች የተዘጋጁትን ኮርሶች ለመደበኛ እና የርቀት ትምህርት ፕሮግራሞች መጠቀም ይችላሉ።

ስለ e-SHE ፕሮግራም

e-SHE 'ኢ-ለርኒግ ከፍተኛ ትምህርትን ለማጎልበት' የአምስት ዓመት ፕሮጀክት ሲሆን በኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የዲጂታል ትምህርትን ተቋማዊ ለማድረግና ለማጎልበት ግብ ያደረገ ነው።

በፕሮጀክቱ የአምስት ዓመት ቆይታ 35 ሺህ መምህራን እና 800 ሺህ ተማሪዎች የዲጂታል ትምህርት አቅም ግንባታ ስልጠናዎችን እንደሚወስዱ ይጠበቃል።
“ስለ አማራ መብት እንቆረቆራለን በሚል ጫካ የገባችሁ ወንድሞች ከክልላችሁ መንግስት ጋር አብራችሁ እንድትሰሩ ጥሪ አቀርባለሁ”፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በባህርዳር የተገነባው የዓባይ ድልድይ ምረቃ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር፤ ስለ አማራ መብት እንቆረቆራለን በሚል ጫካ የገባችሁ ወንድሞች ከክልላችሁ መንግስት ጋር አብራችሁ እንድትሰሩ ጥሪ አቀርባለሁ ብለዋል፡፡

ስለ አማራ ዲሞክራሲ የሚታገል ማንኛውም ግለሰብ እና ቡድን ሰክኖ በማሰብ ሕዝቡን እና ክልሉን መጥቀም በሚችሉ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን እንዲያደርግ አሳስበዋል፡፡

ስለ አማራ መብት፣ ልማት እና ዲሞክራሲ እንቆረቆራለን በሚል ጫካ የገባችሁ ወንድሞች ለዚህ ግዜው ባለመሆኑ ከክልላችሁ መንግስት ጋር አብራችሁ ልትሰሩ ይገባል፤ ሞት ይበቃል ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ብልጽግና በኢትዮጵያ ልክ የሚሰራ፣ ዓለም የደረሰበትን ቴክኖሎጂ የሚመጥን ስራ የሚሰራና በቃሉ የሚገኝ ፓርቲ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በተደጋጋሚ ለኢትዮጵያ ብልጽግናን እንመኛለን ስንል በንግግር ያልተገነዘቡን ሰዎች በዚህ ድልድይ ብልጽግና ማለት ምን ማለት እንደሆነ እንዲረዱ እፈልጋለሁ ብለዋል።

የብልጽግና ራዕይና ተልእኮ ያሳከውን ድልድይ ላይ ቆሜ ይህ ንግግር በማድረጌ ደስታ ይሰማኛል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

የዓባይ ወንዝ ድልድይ በሀገሪቱ ግዙፍ ከሚባሉ ፕሮጀክቶች አንዱ መሆኑን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ኢትዮጵያ የሚገባትን፣ የአማራ ሕዝብ የሚገባውን፣ ለባሕር ዳርም ውበት የሚመጥን ታላቁን ሥራ በጋራ ለማስመረቅ በቅተናል ሲሉም ተናግረዋል።

በሕዝቦች መካከል በተፈጠሩ አልባሌ ትርክቶች ምክንያት እየላላ ያለውን ትስስር ሊያጠናክር የሚችል የትርክት ድልድይ መገንባት እንደሚያስፈልግም ገልፀዋል፡፡

እንደመንግስት ሁለት ድልድይ ለመገንባት እንፈልጋለን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የመጀመሪያው ልማትን የሚያሳልጥ ድልድይ ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ ህዝብን የሚለያይ ግድግዳ በማፍረስ የአንድነት ድልድይ መገንባት ነው ብለዋል፡፡

ይህ ሁለት ዓይነት ድልድይ ኢትዮጵያን በርቀት ያሻግራል ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያን የሚመጥን ድልድይ በውቧ ባህር ዳር ከተማ ማስቀመጥ ለቻሉ ባለሙያዎች እና መሪዎች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምስጋና አቅርበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዓባይ ድልድይ ምረቃ ላይ ለእናቶች ቀን የእንኳን አደረሳችሁ መልእክትም አስተለልፈዋል፡፡

ዛሬ የተመረቀው የዓባይ ድልድይ የ380 ሜትር ርዝመት እና 43 ሜትር ስፋት ያለው በሁለቱም የመንገድ ክፍል ባለሶስት መስመር የተሽከርካሪ መንገድን ብሎም በጎን የብስክሌት መጋለቢያ መስመር የተሰናዳለት ግዙፍ ድልድይ መሆኑ ተገልጿል።
በሳምንቱ መጨረሻ በአማራ ክልል ከነበረን ቆይታ ተመልሰን ከከፍተኛ የፌደራል የሥራ ኃላፊዎች ጋር በጎንደር የሚገኙ ሶስት እጅግ አስፈላጊ ፕሮጀክቶችን የሥራ አፈፃፀም በመገምገም የሚጠናቀቁበትን መንገድ አስቀምጠናል። የፕሮጀክቶቹ ስራዎች የመገጭን ግድብ ማጠናቀቅ፣ የጎንደር ከተማን የውሃ አቅርቦት ማሻሻል እና የአዘዞ ጎንደር 11 ኪሎ ሜትር መንገድ ሥራ መፈፀም ናቸው። በዛሬ ጠዋቱ ግምገማ በመመስረት ስራዎቹ በፍጥነት እንዲጠናቀቁ የፕሮጀክቶቹ አስተዳደር ማሻሻያ እንዲደረግ መመሪያ ሰጥቻለሁ።