Natinael Mekonnen
7.91K subscribers
15.6K photos
1.06K videos
20 files
2.48K links
ይህ ቻናል ቴሌግራሜ hacked በተደረገበት ሳት ለግዝያዊነት የከፈትኩት ቻናል ነው ለችግር ጊዜ ይጠቅማል ተቀላቀሉ
በቀጥታ መረጃዎችን ለመስጠት ከፈለጉ @NatnaelMekonnen7 በማለት መረጃዎችን ይላኩልን
Facebook.com/natnaelmekonnen.et
Instagram.com/natnaelmekonnen21
Telegram https://t.me/NatinaelMekonnen21
Download Telegram
በአማራ ክልል ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ተወካዮችን ያሳተፈ የሰላም ኮንፍረንስ በባህር ዳር መካሄድ ጀምሯል

በአማራ ክልል ከሁሉም ዞኖችና ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ተወካዮች የተሳተፉበት የሰላም ኮንፍረንስ በባህርዳር ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

ለሁለት ቀናት የተሰናዳው ይኸው የሰላም ኮንፍረንስ እየተካሄደ የሚገኘው "ሰላም ለሁሉም፣ ሁሉም ለሰላም" በሚል መሪ ሃሳብ ነው።

በኮንፍረንሱ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ አገኘሁ ተሻገር፣ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ፣ የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፋንቱ ተስፋዬ፣ የጦር ሃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታ ማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎችና የህብረተሰብ ተወካዮች ተገኝተዋል።

ኮንፍረንሱ በቅርቡ በየአካባቢው የተካሄደው የሰላም ኮንፍረንስ ማጠቃለያ መሆኑም ተመላክቷል።

ኮንፍረንሱ በክልሉ እየተሻሻለ የመጣውን የሰላም ሁኔታ ዳር በማድረስ ወደ ተሟላ ልማት ለማስገባት ያለመ መሆኑም ተገልጿል።
አሚኮ
በመላዉ ኢትዮጲያ በቀጣዩ ዓመት 2.5 ሚሊዮን ኮንዶም በነጻ እንደሚከፋፈል ተነገረ

ከዚህ ቀደም ይሰሩ የነበሩ የኤች አይ ቪ መከላከል ስራዎች በጣም እየቀነሱ መሆናቸው እና ይሰጠው የነበረዉ ትኩረት በመቀነሱ በተለይም እድሜያቸው ከ15 እስከ 35 ዓመት ያሉት ለኤችአይቪ ኤድስ ይበልጥ ተጋላጭ እየሆኑ መሆኑን ተገልጿል፡፡ ባለፈው ዓመት ብቻ በተደረገ ጥናት የኤች አይ ቪ ታማሚ ከሆኑት ውስጥ 84 በመቶ ብቻ የሚሆኑት ራሳቸውን ያወቁ መሆናቸውን ተነግሯል።

ይህም ማለት በደማቸው ውስጥ ቫይረሱ የሚገኝ 16 በመቶ የሚሆኑ ሰዎች ታማሚ መሆናቸውን እና ራሳቸውን ያላወቁ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ የቫይረሱ ስርጭት ከመጠን ባለፈ እየጨመረ መጥቷል፡፡ ለዚኅም ትምህርት መስጠት እና በቂ የሆነ የኮንዶም አቅርቦት ሊኖር እንደሚገባ እንዲሁም በነጻ ሊሰጥ የሚችልበት ሁኔታ መፈጠር እንዳለበት ተጠቁሟል፡፡

ኤኤችኤፍ ባለፈው ዓመት 3.1 ሚሊዮን የሚሆኑ ላቭ ኮንዶም የተባለ የኮንዶም አይነት ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት በተለያዩ ከተማዎች የማዳረስ ስራ ሰርቷል፡፡ በተያዘው ዓመትም 2.5 ሚሊዮን ኮንዶም ከማሌዢያ ለማስገባት እንደታዘዘ እና ከታክስ ነጻ በሆነ መንገድ በማስገባት በነጻ ተደራሽ ለማድረግ ማቀዳቸውንም ዶክተር መንግስቱ ገ/ ሚካኤል ገልጸዋል
የእርዳታ እህል በመሸጥ ረሐብን ማባባስ የጨቋኞች ቋሚ ስልት ነው። ሁሉም ትግራዋይ ይታገለዋል።

የሕዝብን እርዳታ በመስረቅ መሸጥ ልማዱ እና አመሉ የሆነው የማፍያው ወያኔ ቡድን ምስኪን የትግራይ ክልል ነዋሪ ዜጎችን በረሐብ አለንጋ እየገረፈ ይገኛል።

ቀን በቀን ህፃናት በረሐብ እየረገፉ በአለበት የትግራይ ምድር ከሀገር ውስጥ እና ከአለምቀፍ ተቋማት የቀረበውን እርዳታ አረመኔው ወያኔ ግን እየሸጠ ጊዜያዊ ጥቅምን እያሳደደ ይገኛል።

ነባርና ቋሚ ባንዳዎቹ ባገኙት መንገዶች ሁሉ የእርዳታ እህልና ገንዘብ ወደ ራሳቸው ኪስ የማከማቸት የቆየ ልምድ አላቸው። ከውጪ የሚሰጠው እርዳታ በጥሬ ገንዘብ ካልሆነ እያሉ አሁንም ይከራከራሉ።

ወያኔ ትግራይ ህዝብ ላይ እከክ ነው የሆነው። እከክ ሲያኩት ያማል ሲተውት ይበላል ያሳክካል። ህዝቡ ሥራህ ልክ አይደለም እየበደልከን ነው ሲሉት ይገላቸዋል። ወያኔ የመጣ እርዳታን ሸጦ ህዝብን እያስራበ እንደሆነም ህዝቡ ያውቃል። ህዝብ ያለውን ግፉን ጭካኔውን እያየ እየተበደለ እያረረ ዝም የሚለው እስከኖረ ብቻ ነው ።
የዊክሊክስ መስራቹ ጁሊያን አሳንጀ ከእስር ተለቆ ከብሪታንያ ወጣ አሳንጀ አሜሪካ ካቀረበችበት 18 ክሶች አንዱን ለማመን የተስማማ ሲሆን በእስር ያሳለፋቸው አመታት ከግምት ውስጥ ገብተው በነጻ ይለቀቃል ተብሏል
የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ለሰባተኛ ጊዜ የስካይትራክስ የአፍሪካ ምርጥ አየር መንገድ ተብሎ ተመርጧል። አየር መንገዱ በተጨማሪም፣ የአፍሪካ ምርጥ የቢዝነስ ክፍል አየር መንገድ አሸናፊነትን ለስድስተኛ ተከታታይ ዓመት፣ የአፍሪካ ምርጥ የኢኮኖሚ ክፍል አየር መንገድ ተሸላሚነትን ለስድስተኛ ተከታታይ ዓመትና በአፍሪካ የኢኮኖሚ ክፍል ምርጥ የምግብ አገልግሎት ሰጪ የሚል ድል እንደተቀዳጀ ትናንት ማምሻውን አስታውቋል።
የካሳ ክፍያ እና የመሬት ግመታን በክልሎች በጀት እንዲሸፈን ስልጣን የሚሰጠዉ አዋጅ ፀደቀ

የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበት፣ ካሳ የሚከፈልበት እና ተነሺዎች መልሰው የሚቋቋሙበትን ሁኔታ ለመወሰን የወጣው የማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ በ 4 ተቋዉሞና በ 6 ድምፀ ታቅቦ በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል።

በማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 1161/2011 መሰረት በክልሎች ለሚከናወኑ የልማት ስራዎች የመሰረተ ልማቱን የሚገነባው የፌዴራል መንግስቱ የካሳ ክፍያውን እንዲፈፅም ያስገድዳል።

ዛሬ በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የፀደቁ አዋጅ ላይ ግን በፌዴራል መንግስት የሚከናወኑ የልማትና የማህበራዊ አገልግሎት ማስፋፊያ ስራዎች መሬት ከማስለቀቅ ጋር የተያያዙ ክፍያዎችን የክልልና የከተማ አስተዳደሮች እንዲፈፅሙ ስልጣን የሚሰጥ ነዉ።

ለካሳ የሚዉል ገንዘብ ፕሮጀክቶችን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ለክልሎች ከሚመደበው በጀት ላይ ጭማሪ ይደረግላቸዋል ። የዚህ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ በከፋዩና በገማቹ መካከል የነበረውን ያልተገባ ጥቅምና የተጋነነ ክፍያ መጠየቅን የሚያስቀር ይሆናል ተብሏል።
በአማራ ክልል የሰላም ጉዳይ የተካሄደው የሰላም ኮንፈረንስ ባለ 10 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቀቀ።

በአማራ ክልል በባሕር ዳር ከተማ ከሰኔ 17 እስከ ሰኔ 18/2016 ዓ.ም ከሁሉም የክልሉ አካባቢዎች እና ከአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር የተውጣጡ ልዩ ልዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ያካሄዱት ክልላዊ የሰላም ኮንፈረንስ ባለ 10 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል።

ሙሉ መግለጫው ቀጥሎ ቀርቧል፦

በአማራ ክልል በባሕር ዳር ከተማ ከሰኔ 17 እስከ ሰኔ 18/2016 ዓ.ም ከሁሉም የክልላችን አካባቢዎች እና ከአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር የተውጣጣን ልዩ ልዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ያካሄድነውን ክልላዊ የሰላም ኮንፈረንስ አስመልክቶ የተዘጋጀ የአቋም መግለጫ፦

ኢትዮጵያ ሀገራችን ረጅም ታሪክ ያላት ሀገር፣ የበርካታ ባሕል እና ቋንቋ ባለቤት፣ የነፃነትና የአንድነት ተምሳሌት፣በገፀ ምድርና በከርሰ ምድር ሀብት የበለፀገች፣ የብዙ ብሄር ብሄረሰቦች መገኛና ድንቅ የባህል እሴቶች ባለቤት መሆኗ እንደተጠበቀ ሆኖ በሌላ በኩል ደግሞ ሀገራችን በተለያዩ ጊዜያቶች በርካታ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ችግሮች ሲፈትኗት ቆይተዋል፡፡ይሁን እንጂ እነዚህን በየጊዜው የገጠሟትን ፈተናዎች በህዝቦቿ ትብብርና አንድነት በከፍተኛ የድል አድራጊነት መንፈስ በመታገል እየተሻገረች እዚህ የደረሰች ሃገር መሆኗ ግልፅ ነዉ ፡፡

በመሆኑም የአማራ ሕዝብ፣ ከክልሉ ውጭ የሚኖሩ የክልሉ ተወላጆችን ጨምሮ ይህን የኢትዮጵያዊነት እሴት የተላበሱ ናቸው፡፡ በሀገረ መንግሥት ግንባታ ሂደትም ከሌሎች ወንድምና እህት ኢትጵያውያን ጋር በመሆን የራሱን አስተዋፅኦ ያበረከተ እና በርካታ ዋጋ የከፈለ ሕዝብ ነው፡፡

ስለሆነም የሕዝቦችን የአብሮነትና የአንድነት ገመድ ለመበጣጠስ የተለያዩ ግጭቶች በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች እያጋጠሙ ቆይተዋል፡፡ በአማራ ክልልም ገጥሞን የቆየው ችግር ለበርካታ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ምስቅልቅሎች ዳርጎን ቆይቷል፡፡

ሆኖም ግን በአሁኑ ወቅት በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች አንፃራዊ ሰላምና መረጋጋት የተፈጠረ ቢሆንም ወደ ቀድሞ ሰላሙና ወደ ዘላቂ ልማት ለመመለስ እንዲሁም ሕዝቡ የተረጋጋ ሕይወት እንዲመራ በማድረግ ረገድ በርካታ ቀሪ ሥራዎች እንደሚያስፈልጉን ይታወቃል፡፡

በመሆኑም ክልሉ ሰላማዊና የተረጋጋ፣ እንደቀድሞ ታሪኩ ለሀገር ሁለንተናዊ እድገትና አንድነት የድርሻውን እንድወጣ ለማስቻል ይህን የሰላም ኮንፍረንስ ያደረግን ሲሆን በውይይታችንም የተገኙ ግብአቶች ሕዝቡ በሰላም ለመኖር ያለውን መሻት በጉልህ የተረዳንበት እንዲሁም አሉን የምንላቸውን ጥያቄዎች በግልፅ ያቀረብንበት ነው፡፡

ጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊታችን የክልሉን ሰላም ወደነበረበት ለመመለስ ሲከፍል ለቆየው መስዋዕትነት በአማራ ሕዝብ ስም ታላቅ ክብር እየሰጠን የክልሉ ተወላጅ የሆኑ ጀኔራል መኮነኖች ለነበራችው የመሪነት ሚና ከፍተኛ ምስጋና እያቀረብን ለመላው የሀገር መከታ እና አለኝታ ለሆነው የሀገር መከላከያ ሠራዊታችን ያለንን አክብሮትና አድናቆት ለመግለፅ እንወዳለን፡፡

ሥለሆነም ከሰኔ 17/2016 ዓ.ም እስከ ሰኔ 18/2016 ዓ.ም ለተከታታይ ሁለት ቀናት በባሕር ዳር ከተማ ያደረግነውን ክልላዊ የሰላም ኮንፍረንስ አስመልክቶ ባለ 10 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት የጋራ ማድረጋችንን እናረጋግጣለን፡፡

በሰላምና በፀጥታ፣ በፖለቲካ፣ በማህበራዊ፣ በመልካም አስተዳደር፣ በማንነትናበራስ አስተዳደር ጉዳይ እንዲሁም ህገመንግሥትን ስለማሻሻል አስመልክቶ ያነሳናቸውን ጥያቄዎች በየፈርጃቸው ለፌደራል መንግሥትና ለክልሉ መንግስት እንዲቀርብልን ስምምነት ላይ ደርሰናል፡፡ ሁሉም ጥያቄዎች በአንድ ጊዜ እንደማይመለሱ ስለምናምን መንግስት የሕዝቡን ጥያቄ ለመፍታት ያለውን ቁርጠኝነት እንዲሁም በፍጥነት መመለስ ያለባቸውን ለመፍታት የሚኖረውን ዝግጁነት በጋራ እያየን እንዲሁም በሰላማዊ መንገድ እየተወያየን ጥያቄዎቹ እንዲፈቱልን መጠየቃችንን እንቀጥላለን፡፡

በክልሉ ውስጥ በርካታ የልማት ጥያቄዎች መኖራቸው ይታወቃል፡፡ እነዚህ የልማት ጥያቄዎች ያለ ሰላም ሊታሰቡ ስለማይችሉ ቅድሚያ በክልላችን ውስጥ ማንኛውም ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ የበኩላችንን ድርሻ ለመወጣት በውይይታችን የተስማማን መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ለሚድያ ተቋማትና ሙያተኞች እንዲሁም ለማኅበረሰብ አንቂዎች የክልሉ ሕዝብ በርካታ ሁለንተናዊ ችግሮች ተጋርጠውበት ቆይተዋል፡፡ በርካታ ምስቅልቅሎችም ደርሰውበታል፡፡ ስለሆነም ይህን ዘርፈ ብዙ ችግር ተገንዝባችሁ ሕዝቡን ወደ ሰላም የሚመልስና የክልሉ ሕዝብ ከሌሎች ወንድምና እህት ሕዝቦች ጋር በጋራ የገነባናት ሀገር ተከባብሮና በነፃነት ተዘዋውሮ እንዲሰራባት ለማስቻል የሚድያውን አየር በሰላም እንዲትሞሉልን በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን፡፡

የመንግሥት ባለስልጣናት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ምሁራን፣ የኪነጥበብ ባለሙያዎች፣ በውጭ የምትኖሩ ኢትዮጵያዊያን ዲያስፖራዎች፣ እንዲሁም መላ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ፤ በልልላችን ከተፈጠረው ቀውስ በመውጣት አስተማማኝና ዘላቂ ሰላም ለመገንባት በምናደርገው ጥረት ለክልላችን ሰላም ስትሉ ሁሉንም አይነት የሰላም ድጋፍ እንዲታደርጉ፣ ከመገፋፋትና ከመጠላለፍ በመውጣት ለክልሉ ሕዝብ ሰላማዊ እንቅስቃሴ በጋራ እንድትቆሙ እንጠይቃችኋለን፡፡

ታጥቃችሁ ጫካ የገባችሁ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን እንታገልለታለን የምትሉት ሕዝብ ያለበትን ችግርና የክልሉ ሕዝብ ኅልውና እንዴት እንደተፈተነ በግልፅ ታውቃላችሁ፡፡ ስለሆነም ጥያቄያችሁን በሰላማዊ መንገድ በውይይትና በድርድር እንዲታቀርቡ እንዲሁም የወገናችሁን ስቃይ ለመቀነስ እንዲቻል መገዳደል ይብቃን ብላችሁ ወደ ወገኖቻችሁ እንድትቀላቀሉ የሰላም ኮንፈረንሳችን ተሳታፊ በሙሉ ወገናዊ ጥሪ እያስተላለፍን መንግሥትም ሆደ ሰፊ በመሆን እነዚህ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ጋር በመወያየት እና በመደራደር ለሕዝባችን ሰላም ሲባል በይቅርታና በክብር እንዲቀበላቸው ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

የክልል መንግሥታት፣ እንዲሁም የዞንና የከተማ አስተዳደሮች በምታገለግሉት ሕዝብ ውስጥ የክልላችን ተወላጆች እናንተን የመንግሥት አስተዳደሮችን እና አብሮ ለዘመናት የኖረውን ወገኖቹን አምኖ እየኖረ መሆኑን በመገንዘብ ሕዝባችን ባይተዋርነትና ብቸኝነት እንዳይሰማው፣ ጥቃት እንዳይደርስበት፤ በክልላችን ለሚኖረው ሕዝብ የጥያቄ ምንጭ እንዳይሆን እንድሁም የሀገረ መንግሥት ግንባታ ሂደታችንን በአስተማማኝ ሁኔታ መሰረት እንድኖረዉ በጋራ እንዲንቀሳቀስ በሰላም ኮንፈረንሳችን ጥሪያችንን እያሰተላለፍን በአማራ ክልል ማንኛውም ዜጋ በብሔሩ ወይም በእምነቱ ወይም በሌሎች ምክንያቶች የማይገለልበት ክልል እንዲሆን እኛም እንደቀደመው ሁሉ እንደምንሠራ ቃል እንገባለን፡፡

በክልላችን ውስጥ የምትንቀሳቀሱ የፌደራልና የክልል የፀጥታ ኀይሎች በማንም ይጠንሰስ ማንም ይጀምረው በክልላችን ውስጥ እየሆነ ያለው ነገር ወንድም ወንድሙን እየገደለና ሕዝባችን የከፋ ችግር እየደረሰበት በመሆኑ ነው፡፡ በመሆኑም የጀመርነው የሰላም ጥረት እንዲሳካ የበኩላችሁን ጥረት እንድታደርጉና ከጫካ የሚመጡ ወንድሞቻችሁ ወንድም መሆናቸውን አውቃችሁ በፍፁም ሙያዊ ዲስፕሊንና ኢትዮጵያዊ ጨዋነት አቀባበል ታደርጉላቸው ዘንድ የከበረ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
በጫካ የሚገኙ ወንድሞቻችን በሰላማዊ መንገድ በውይይትና በድርድር ወደ ማኅበረሰቡ ከተቀላቀሉ በኃላ የሀገራችንን ሁለንተናዊ ችግር በዘላቂነት ይፈታል ተብሎ በታሰበውና ተስፋ በተጣለበት የሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ውስጥ በንቃት እንዲሳተፉ በማድረግ ያላቸውን ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ አቅርበው የሕዝቡን ችግር በትክክለኛው መንገድ እንዲፈታ በማድረግ ታሪካዊ ኀላፊነታቸውን እንዲወጡ ሁሉም አካል የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪያችንን እናሰተላልፋለን፡፡

በክልሉ ውስጥ ከተፈጠረው ችግር ጋር ተያይዞ ተጠርጥረው በህግ ቁጥጥር ስር የዋሉ ዜጎች ማለትም ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች፣ ምሁራን፣እንዲሁም ተፅዕኖ ፈጣሪ ዜጎች በክልሉ ውስጥ ለምንገነባው ዘላቂ ሰላም የበኩላቸውን እንዲወጡ ለማስቻል መንግሥት በይቅርታና በምህረት ነፃ እንዲወጡ በማድረግ ሚናቸውንና ድርሻቸውን እንዲወጡ እንጠይቃለን፡፡

በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የተደረገውን ደም አፋሳሽ ጦርነት በሰላማዊ መንገድ ለመቋጨት መንግሥት በሆደ ሰፊነት የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት ማድረጉ ይታወሳል፡፡ የፕሪቶሪያውን ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ የፊደራል መንግስትና የክልላችን መንግሥት ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ በሚገኙበት በዚህ ወቅት በህወሀት በኩል ገና ከጅምሩ ጀምሮ ስምምነቱን እንደ ጊዜ መግዣ በመጠቀም የማንነት እና የራስ አሥተዳደር ጥያቄ ባለባቸዉ አካባቢዎች ወረራ በመፈፀም ላይ ይገኛል ፡፡ በመሆኑም መንግስት የፕሪቶሪያውን ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊና ተፈፃሚ እንዲሆን በማድረግ ወራሪ ኀይሎች ከወረሩበት ቦታ በፍጥነት እንዲወጡ እንድሁም ጥያቄዎች በሰላማዊና በሕጋዊ መንገድ እልባት እንዲሰጣቸው ስንል የሰላም ኮንፈረንሳችን ይጠይቃል፡፡
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Breaking News : Kenya Defense Forces called in to assist police የኬንያ መከላከያ ሰራዊት ሰላምና የህግ ስርዓትን እንዲያስከብር ትዕዛዝ ተሰጠው።

የሀገሪቱ መንግሥት ለቀናት ከዘለቀው የፋይናንስ ህግ ተቃውሞ ጋር በተያያዘ የኬንያ መከላከያ ሰራዊት የህዝቡን ደህንነት፣ ሰላምና የህግ ስርዓት እንዲያስከብር አሰማርቷል።

በሌላ በኩል ፤ የኬንያው ፕሬዜዳንት መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በመግለጫቸው የዛሬውን ታቃውሞ ፤” እንደ ሀገር ክህደት / ከሃዲነት “ የሚቆጠር እንደሆነ ገልጸው ፤ የጸጥታ ኃይሎች የኬንያውያንን ደህንነት እንዲያስጠብቁ መመሪያ እንደሰጡ ተናግረዋል።

ተቃዋሚዎች የኬንያ ፓርላማን ሰብረው ስለገቡበት ክስተት ጉዳይም ምርመራ እንደሚደረግ አመልክተዋል።

የወንጀል ድርጊትና ወንጀለኞችን ህገ መንግስታዊ መብታቸውን ተጠቅመው የተቃውሞ ሰልፍ ከሚያደርጉት መለየት ይገባል ብለዋል።

ፕ/ት ሩቶ “ አደገኛ ወንጀለኞች “ ሲሉ የጠሯቸው አካላት ሊፈጸሙት የሚችልን ማንኛውም ሙከራ ከንቱ ሆኖ እንዲቀር የደህንነት አካላት እርምጃ እንዲወስዱ እንዳዘዙ ገልጸዋል።

ህዝቡንም “ ዛሬ ማታ ተኙ ! የናተ፣ የቤተሰቦቻችሁ እና የንብረቶቻችሁ ደህንነት ከምንም በላይ ቅድሚያ ሰጥተን እንጠብቃለን “ ብለዋል።

“ የተቃውሞው የፋይናስ ምንጮች ላይም ምርመራ ይደረጋል “ ሲሉ አክለዋል።

በኬንያ ዛሬ ማክሰኞ በነበረው ተቃውሞ እስካሁን በታወቀው ብቻ 10 ሰዎች ከጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተገድለዋል።
ፖለቲከኛው ጃዋር መሃመድ የመከላከያ ጄነራሎች ለድርድር ለመቀመጥ ለፋኖ ያደረጉትን ጥሪ፣ የፋኖ አመራርና የአማራ አክቲቪስቶች እንደበጎ እርምጃ እንዲመለከቱትና ለጥሪው ምላሽ ቢሰጡ ለሰላም አማራጭ ይሆናል ሲል በግል የማህበራዊ ሚዲያ የፌስቡክ ገፁ አስፍሯል።

መከላከያ ሰራዊት በሀገሪቱ የተፈጠሩ ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት በርካታ ጥረቶችን እያደረገ ያለ አንዱ የመንግሥት ተቋም ነው ብሏል።

መከላከያው እየተፈጠረ ያለውን ችግር በቅርበት የሚያውቅ በመሆኑ፣ ከፖለቲከኞች ቀድሞ ጥሪ ማቅረቡ መበረታታት አለበት ብሏል። ከኦነግ ሸኔ ጋርም ሰላም ለመፍጠር ለሁለት ጊዜ የተደራደረው መከላከያው ነው ብሏል።
ማርክ ሩት የኔቶ ዋና ጸሃፊ ተደርገው ተመረጡ


የኔዘርላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ሩት ጄንስ ስቶልትንበርግን ይተካሉ ተብለዋል


ኖርዌጂያዊው ጄንስ ስቶልትንበርግ የፊታችን ጥቅምት ስልጣናቸውን ለማርክ ሩት ያስረክባሉ ተብሏል

ተጨማሪ ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://bit.ly/3xCAevB
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ በዛሬ 37ኛ መደበኛ ስብሰባው ውሳኔዎችን አሳልፏል።ከውሳኔዎቹ መካከል በኢትዮጵያና በኩዌት መካከል በስራ ስምሪት ዘርፍ የተፈረመውን ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበ አዋጅ አንዱ ነው፡፡

ስምምነቱ በኩዌት በቤት ሰራተኝነት ተሰማርተው የሚገኙ እና በቀጣይም ከአሰሪዎች ጋር የሥራ ውል ውስጥየሚገቡ ኢትዮጵያውያን ሠራተኞች መብታቸውን ለማስጠበቅ የሚያስችል ሕጋዊ ማዕቀፍ እንዲኖር፣ በአገሪቱ የሚገኙ ዜጎቻችን ክብር፣ መብትና ጥቅም ለማስጠበቅ ትልቅ ጠቀሜታ ያለው እንዲሁም በሁለቱ መንግስታት መካከል የሁለትዮሽ ግንኙነትን ይበልጥ እንዲጠናከር የሚያግዝ ነው፡፡ ምክር ቤቱ በረቂቅ አዋጁ ላይ ከተወያየ በኋላ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትእንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
ህወሓት “በልዩ ሁኔታ” እንዲመዘገብ፤ የፍትሕ ሚኒስቴር ለምርጫ ቦርድ ጥያቄ አቀረበ!

ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) በፓለቲካ ፓርቲነት “በልዩ ሁኔታ” መመዝገብ እንዲችል ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጥያቄ ቀረበ። ምርጫ ቦርድ ጥያቄው ከፍትሕ ሚኒስቴር እንደቀረበለት ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አረጋግጧል።

◼️ብሔራዊው ምርጫ ቦርድ፤ ህወሓት “ኃይልን መሠረት ያደረገ የአመጻ ተግባር ላይ መሳተፉን” እንዳረጋገጠ በመጥቀስ የፖለቲካ ፓርቲውን “ህጋዊ ሰውነት” የሰረዘው በጥር 2013 ዓ.ም ነበር።

◼️ቦርዱ በወቅቱ ባስተላለፈው ውሳኔ፤ የህወሓት ኃላፊዎች “በፓርቲው ስም መንቀሳቀስ እንደማይችሉ” እገዳ መጣሉም ይታወሳል።

◼️የፍትሕ ሚኒስቴር ከሶስት ሳምንት በፊት በፓርላማ የጸደቀን አዋጅ መሰረት በማድረግ፤ ህወሓት “በልዩ ሁኔታ እንደ ፖለቲካ ፓርቲ ለመመዝገብ እንዲችል” ምርጫ ቦርድ “አስፈላጊውን ትብብር” እንዲያደርግ በደብዳቤ ጥያቄ አቅርቧል።

◼️ ከሁለት ቀን በፊት ሰኞ ሰኔ 17፤ 2016 ለምርጫ ቦርድ የተላከው ይህ ደብዳቤ፤ በግልባጭ ለሰላም ሚኒስቴር፣ ለብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት እንዲሁም ለትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር መላኩ ተገልጿል።

◼️ የፍትሕ ሚኒስትሩ ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞትዮስ ፊርማ ያረፈበት ይህ ደብዳቤ ለምርጫ ቦርድ መድረሱን የቦርዱ የኮሚዩኒኬሽን ክፍል ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አረጋግጧል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቀረበለትን ጥያቄ “በስራ ላይ ካሉ ህጎች አንጻር በመመርመር ውሳኔውን እንደሚያሳውቅ” የኮሚዩኒኬሽን ክፍሉ ገልጿል።

Via Ethiopia Insider
በሰሞኑ በአንዲት ልጅ መኪና የስርቆት ተጠርጣሪ ጉዳይ ላይ ሁሉም ነገር ላይ እኔ አውቃለሁ መረጃ አለኝ በማለት እየተጻፈ ነው:: ሁሉም ነገር ላይ ጥልቅ ማለት ጥሩ አይደለም በማለት ዝምታን መርጨ ነበር:: ነገሩ ሲበዛ አንድ ነገር ለማለት ወደድኩኝ

ሁሉም የመሰለውን ሳያጣራ ስለሚያወራ በጉዳዩ ላይ አንድ ሁለት ሶስት ነገር ልበልና የፍርድ ቤት ውሳኔዎቹን ከሰማን በኃላ እመለስበታለሁ::

በዕለቱ ጠዋት 12 ሰዓት ላይ ስልኬ ይጮኃል ለግዜው የደዋዩን (መረጃ) የሰጠኝን ስም ከመጥቀስ እቆጠብና ምድነው የተፈጠረው በማለት ስለ ጉዳዩ ልጁን ጠየኩት አንዲት ልጅ ከሚኖሩበት አፓርትመንት አንድ መኪና ይዛ እንደሄደች ይነግረኛል:: ልጅቷን ታውቃታለህ ወይ የኔ ጥያቄ ነው?! አላውቃትም ግን በአጋጣሚ ተዋውቀን ነው:: ከዛ ምን ተፈጠረ ከነበርንበት ክለብ ስንወጣ ሰላም ነበርን ቤት ስንደርስ አለመግባባቶች ስለነበሩ ወደ ቤት ጥያት ገባሁ:: ከደቂቃዎች በኃላ ግቢው ውስጥ ጩኸት ሰማሁና ምድነው ብዬ ስወጣ አብራህ የነበረችው ልጅ የጎረቤትህን መኪና ይዛ ሄደች በማለት እንደነገሩትና ልጁም እስር ቤት እንደሆነ ነገረኝ::

በሰዓቱ መኪና የተወሰደበት ጎረቤቱ በድንጋጤ እራሱን ስቶ ስለነበር ወደ ሆስፒታል መሄዱና ሰውየው እስኪነቃ እየተጠበቀ እንደሆነ እና ልጁም እዛው እንደታሰረ ተጨማሪ መረዳዎችን አገኘሁ:: ፖሊስ በደረሰው ክስ መሰረት ክትትል በሚያደርገበት ወቅት መኪናውን ይዛ የሄደችው ልጅ ጏደኛ ፖሊስ ቤት ያለው ልጅ ጋር ስልክ ደውላ መኪናውን ወስዳለች የተባለችው ልጅ ስልኳ እሱ ጋር እንደረሳች ትነግረዋለች በሰዓቱ ልጁ ፖሊስ ቤት ስለነበር ስልኩን እስፒከር ላይ በማድረግ ፖሊሶቹ የልጅቷ ጏደኛ የምትለውን ያደምጡ ነበር::

ልጁ ከፖሊስ ቤት ከፖሊስቹ ጋር በመሆን ስልክ ደዋይዋ ጏደኛዋ ቤት ይሄዱና መድረሳቸውን ለጏደኛዋ ይደውላል:: ጏደኛዋ የመኪናውን ቁልፍ በቤት በሰራተኛ ለቆሙት ሲቪል ፖሊሶችና ልጁ ትልካለች ልጅቷ በሰዓቱ ጏደኛዋ ቤት ተኝታ ስለነበር ፖሊሶች ገብተው ያዟት:: የሆነው ባጭሩ ይሄ ነው::

በዚህ የአንድ ቀን ውሎ ታሪክ ላይ ፖሊስ ምድነው ጥፋቱ? ምናልባት የተጠርጣሪን ምስል መለጠፉ ይሆን? ፖሊስ መኪናዬን ተሰረኩኝ ያለ ግለሰብ ክስ ሲመሰርት ስራውን አይስራ ክትትል አያድርግ ማለት ነው? ይህን ያልኩት አንዳኖች የሚጽፉትን ስላየሁ ነው:: የቀረውን ጉዳይ ፍርድ ቤት የሚለውን እንሰማለን:: እስካሁኑ ደቂቃ ድረስ ግን ልጅቷም ልጁም ከእስር አልተፈቱም መኪናዬ ጠፋብኝ ባሉት የግል ተበዳይ አቤቱታ መሰረት ልጅቷ ላይ ክስ ተመስርቷል::

ይኸው ነው!
ሰሳም ለወለጋ ህዝብ ሰላም ለኢትዮጵያ

Good News : “በዛሬው ዕለት በቄለም ወለጋ በመገኘት የ2016 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብራችንን በማስጀመሬ ታላቅ ደስታ ተሰምቶኛል”-ፕሬዝደንት ሽመልስ አብዲሳ

በዛሬው ዕለት በቄለም ወለጋ ዞን፣ ላሎ ቂሌ ወረዳ በመገኘት የ2016 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብራችንን በማስጀመሬ ታላቅ ደስታ ተሰምቶኛል ሲሉ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሸመልስ አብዲሳ ገለፁ።

ማንኛውም ዜጋ ያለምንም ማቅማማት በባለቤትነት እንዲሳተፍ ጥሪዬን እያቀረብኩ፥ ታላቁ ርዕያችን የሆነውን ኦሮሚያን መገንባት‼️ኢትዮጵያን ማፅናት‼️እና የአፍሪቃ ቀንድን ማረጋጋት‼️እውን በማድረግ ውስጥ የአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራም ሚና ከፍተኛ መሆኑን ላስታውስ እወዳለሁ ብለዋል።