Natinael Mekonnen
7.77K subscribers
16.4K photos
1.1K videos
20 files
2.52K links
ይህ ቻናል ቴሌግራሜ hacked በተደረገበት ሳት ለግዝያዊነት የከፈትኩት ቻናል ነው ለችግር ጊዜ ይጠቅማል ተቀላቀሉ
በቀጥታ መረጃዎችን ለመስጠት ከፈለጉ @NatnaelMekonnen7 በማለት መረጃዎችን ይላኩልን
Facebook.com/natnaelmekonnen.et
Instagram.com/natnaelmekonnen21
Telegram https://t.me/NatinaelMekonnen21
Download Telegram
" ከቅርብ ጊዜ ወዲህ #ጅቦቹ ሰው መተናኮስ ፤ በቀን መታየትና #ሰብሰብ ብሎ መሄድ ጀምረዋል " - ነዋሪዎች

" በኛ ቀበሌ ብቻ 3 ህጸናት በጅቦች ተበልተዋል። 2ቱ ሲሞቱ አንዷ ተርፋለች " - አቶ ማርቆስ ቡታ

ከሰሞኑን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ውስጥ የተራቡ ጅቦች እያደረሱ ስላለው ጥቃት የሚመለከቱ መረጃዎችን ማጋራታችን ይታወሳል።

በተለይ በስልጤ ዞን እና በሀላባ ዙሪያ በተፈጸሙ የጅብ ጥቃቶች ምክኒያት የሰው ህይወት መጥፋትና የአካል ጉዳት መድረሱን መግለጻችን አይዘነጋም።

በወቅቱ " የጅብ መንጋ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ  ተከስቷል " የሚለውን ዜና የሰሙ የሲዳማ ክልል፣ የሀዋሳ ከተማ ዙሪያ ነዋሪዎች " ችግሩ እኛም ጋር አለ እንዲያዉም ከህጻናት ባለፈ አዋቂዎችንም አሳስቦናል " በማለት መልዕክቶቻቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አድረሰዋል።

ጉዳዩን በተመለከተ የቲክቫህ ኢትዮጵያ የሀዋሳ አባል በሀዋሳ ዙሪያ ቡሽሎ ፣ ፊንጭ ውሀና ገመጦ... ወዘተ ቀበሌዎች ያሉ ማህበረሰቦችና የጸጥታ አካላትን አነጋግሯል።

የአካባቢው ነዋሪዎች በጊዜ ወደ ቤታቸው መግባት መጀመራቸውን በመጥቀስ ህጻናት ልጆቸውም ፍርሀት እንዳደረባቸዉ ገልጸዋል።

በተለያየ ጊዜ በ5 ሰዎች ላይ የጅብ ጥቃት ደርሶ እንደነበር እና 2 ህጻናት እንደሞቱ 1 ህጻን እንዲሁም 4 አዋቂዎች ደግሞ እንደተጎዱ አስረድተዋል። የሚመለከተው አካል አንዳች መፍትሄ እንዲሰጣቸውም ጠይቀዋል።

በአካባቢው ለረዥም ጊዜያት ጅቦች እንደነበሩ የሚገልጹት ነዋሪዎቹ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ሰው መተናኮስ ፤ በቀን መታየትና #ሰብሰብ ብሎ መሄድ መጀመራቸው እንዳስገረማቸው ገልጸዋል።

ጉዳዩን በተመለከተ ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡት የቡሽሎ ቀበሌ ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ማርቆስ ቡታ ፤ " በእኛ ቀበሌ ብቻ 3 ህጻናት በጅቦች ተበልተዋል " ሲሉ ተናግረዋል።

2ቱ መሞታቸውን ፤ አንዷ ህጻን በወቅቱ በተደረገ ርብርብ ተርፋ በተደረገላት ህክምና መዳኗን ገልጸዋል።

በአጎራባች ቀበሌያት ውስጥ በ2 አዋቂ ሰዎች ላይ አሰቃቂ አደጋ ቢደርስም ለመትረፍ እንደቻሉ የጠቀሱት አቶ ማርቆስ ችግሩ አሳሳቢ በመሆን የጸጥታ አካላት እየተነጋገረበት ነው ብለዋል።

ማህበረሰቡ በጊዜ በመግባት የሚሰጠዉን የጥንቃቄ መልእክት በአግባቡ እንዲተገብርም ጠይቀዋል።