የመጀመሪያ ኃጢያት እና የተሰጠው የአዳኙ ተስፋ (ዘፍጥረት 3 )
ውድ ልጆች: ባላችሁበት የጌታ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ:: በዛሬው ትምህርታችን የመጀመርያው ሀጥያት ምን እንደነበረ: ሀጥያት ወደዚህ ዓለም እንዴት እንደገባ: እግዚአብሔርም የመዳኛ መንገድን እንዴት እንዳዘጋጀ እናያለን።
በኤደን ገነት ውስጥ የሚያፈሩ ብዙ ዛፎች ነበሩ ክፉውንና መልካሙን የሚለየው የእውቀት ዛፍ በኤደን ገነት መካከል ተተክሎ ነበር ። እግዚአብሔር ስለዚህ ዛፍ አዳምንና ሔዋንን እንዲህ ሲል አዝዞአቸው ነበር: ‹‹በዚህ ገነት ውስጥ ካሉት ዛፎች ሁሉ የምታገኙትን ፍሬ መብላት ትችላላችሁ ነገር ገን በገነት መካከል ከተተከለው ከዚህ ዛፍ ፍሬ አትብሉ እነሆ እርሱን በበላችሁ ጊዜ ሞትን ትሞታላችሁ፡፡››
አንድ ቀን አዳምና ሔዋን በገነት ውስጥ እንዳሉ ዲያቢሎስ በእባብ ተመስሎ ወደ አዳምና ሔዋን መጣ። ከዚያም ‹‹እግዚአብሔር በገነት ውስጥ ካሉት ዛፍ ሁሉ ፍሬ እንዳትበሉ አዝዞአችኋልን?››አላቸው፡፡ ሔዋንም እንዲህ አለች፡- ‹‹በገነት ውስጥ ካሉት ዛፎች ከየትኛውም የሚገኘወን ፍሬ መብላት እንችላለን፡፡ ነገር ግን በገነት መካከል የሚገኘው ዛፍ ፍሬ እንዳንበላ እንዳንነካውም እግዚአብሔር ከልክሎናል: አለበለዚያ እንሞታለን፡፡››
ዳያቢሎስም ሲያታልላቸው ‹‹ይህ እውነት አይደለም አትሞቱም እኔን ስሙኝ : ከዚህ ዛፍ ፍሬ ከበላችሁ እንደ እግዚአብሔር ትሆናላችሁ መልካሙንና ክፉውንም ታውቃላችሁ›› አላቸው፡፡ ሔዋንም የዛፉን ፍሬ ተመለከተች ሲያዩት ያምራል: ስለሆነም አንዱን ፍሬ ቀጠፈችና በላች ሌላውንም ፍሬ ቀጥፋ ለአዳም ሰጠችው: እርሱም ደግሞ በላ፡፡ አዳምና ሔዋን ለእግዚአብሔር አልታዘዙም: ይህ የመጀመሪያው ኃጢአታቸው ነበር፡፡ ታላቅ ፍርሃት ፈሩ፡፡ እግዚአብሔር እንደሚቆጣ አወቁ ስለሆነም በገነት ውስጥ ከእግዚአብሔር ፊት ተሸሸጉ፡፡
አዳምና ሔዋን በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአትን አደረጉ፡፡ እግዚአብሔር ግን አሁንም በጣም ይወዳቸዋል፡፡ በሀጥአታቸው ምክንያት ለዘላለም እንዲቀጡ አልፈለገም፡፡ ስለሆነም የሚያስደንቅ ቃል ኪዳን ገባላቸው፡፡ እንዲህ አላቸው ‹‹ትክክለኛው ጊዜ ሲደርስ ልጄን ወደ ዓለም እልከዋለሁ: እርሱ ከሴት ይወለዳል ሰውም ይሆናል፡፡ እርሱ ኃጢአታችሁን ያስወግዳል›› አዳምና ሔዋን ይህን አስደናቂ ቃል ኪዳን ስሙ፡፡ ቃል ዲሳኑንም አመኑ። እግዚአብሔር እንደሚወዳቸው አዳኙም የእርሱን ኃጢአት ለማስወገድ እንደሚወለድ አወቁ፡፡ እግዚአብሔር ቃል ኪዳኑን ጠበቀ: ከብዙ ዓመታት በኋላ የእግዚአብሔር ልጅ በቤተልሄም ተወለደ ስሙም ኢየሱስ ተባለ: ኢየሱስም ሰው በሆነ ጊዜ ፍጽምና ያለውን ሕይወት ኖረ አንዳችም ስህተት አላደረገም፡፡ የህዝብ ሁሉ ኃጢያአት የሚያስተካክለውን ቅጣት በራሱ ላይ ወስዶ በመስቀል ላይ ሞተ፡፡ ለዚህ ነው ኢየሱስን የዓለም አዳኝ ነው የምንለው፡፡
እግዚአብሔር ሁሉንም አዳምና ሔዋንን ይወዳል ከገነት ውሰጥ እነሱን ማስወጣት ነበረበት እንደገና ከተከለከለው ዛፍ ፍሬ በልተው ኃጢያታቸው ጋር ለዘላለም እንዲኖሩ አልፈለገም፡፡ ስለሆነም እግዚአብሔር የእሳት ነበልባል የሆነ ሰይፍ የያዘ መልአክ ወደ ገነት ልኮ ከዚያ እንዲወጡ አደረገ፡፡ አዳምና ሔዋን ከዚያ ጊዜ ጀምሮ በረጅሙ የህይወት ዘመናቸው ኃጢያት በማድረግ ቀጠሉ ከዚያም በኋላ ሞቱ፡፡ እግዚአብሔር አዳኝ እንደሚልክላቸው የገባላቸውን ተስፋ አመኑ፡፡ ኢየሱስ ኃጢያት ወደሌለበት ከእርሱ ጋር እንዲኖሩ ወደ መንግሥተ ሰማያት ይወስዳቸዋል፡፡
#የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ጥቅስ : ሮሜ 5:14-21 (ከወላጆቻችሁ/ከታላላቆቻችሁ ጋር አጥኑ)።
ጥያቄ
1. አዳምና ሔዋንን እግዚአብሔርን ባለመታዘዝ ምን አደረጉ?
2. እግዚአብሔር ለእነርሱ የገባላቸው የተስፋ ቃል ምንድን ነበር? አዳኛቸው ማን ነው?
3. ከዚህ ክፍል ምን ተማራችሁ?
መልሳችሁን በሃሳብ መስጫ ቦታው ላይ ጻፉ! በተከታታይ የ5 ትምህርቶችን መልስ በትክክል ከመለሳችሁ የመጽሐፍ ሽልማት ይኖራችኋል።
መልካም እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!
http://www.mysundayschool.org
https://t.me/MYSundaySchool

MY Sunday School
Home | MY Sunday School
የአዳምና የሔዋን ልጆች (ዘፍጥረት 4)
===
አዳምና ሔዋን ብዙ ልጆች ነበሩአቸው። የመጀመሪያዎቹ ልጆቻቸው ቃየልና አቤል ይባላሉ፡፡ ቃየል ባደገ ጊዜ ገበሬ ሆነ: አቤል ባደገ ጊዜ ደግሞ አርብቶ አደር ሆነ። አንድ ቀን ቃየልና አቤል ለእግዚአብሔር ስጦታ ይዘው መጡ ያመጡትን ስጦታ በመሠዊያ ላይ አድርገው አቃጠሉት። አቤል ለእግዚአብሔር ፍጹምና ምርጥ የሆነ በግ አመጣ: ቃየል ግን ያመጣው ምርጥ የሆነውን ምርት አልነበረም። ለእግዚአብሔር ያቀረቡትን ስጦታ በዚህ ሁኔታ ነበር ያቀረቡት፡፡ እግዚአብሔር በአቤል ስጦታ ደስተኛ ሆነ: ነገር ግን በቃየል ስጦታ አልተደሰተም። ቃየል አልታዘዘመና በዚህ የተነሳ ቃየል ተናደደ : በቅናትም ተነሳስቶ አቤልንም ገደለው፡፡
እግዚአብሔር ቃየልም ‹‹ ወንድምህ የት ነው?›› ብሎ ጠየቀው።ፐቃየልም ‹‹አላውቅም እኔ የወንድሜ ጠባቂነኝን?›› ሲል መለሰ። እግዚአብሔር ‹ኃጢያትን አድርገሃል ወንድምህንም ገለኽዋል›› አለው:: ‹‹ አሁን በሜዳህ ያሉ ተክሎች በጥሩ ሁኔታ አይበቅሉልህም መኖሪያ ቤትም አይኖርህም: በሕይወት ዘመን ሁሉ ከአንድ ሥፍራ ወደ ሌላ ሥፍራ ትቅበዘበዛለህ፡፡›› አለው።
ቃየንም እንዲህ አለ ‹‹ይህ ቅጣት እጅግ ከባድ ነው ያገኘኝ ሁሉ ይገድለኛል፡፡›› ስለሆነም ያገኘው ሁሉ እንዳይገድለው እግዚአብሔር ለቃየን ምልክት አደረገለት፡፡ እግዚአብሔር ለአዳምና ለሔዋን ሌላ ልጅ ሰጣቸው፡፡ ስሙም ሴት ይባላል ሴት ከተወለደ በኋላ አዳም ሌላ 800 ዓመታት ያህል ኖረ፡፡ እጅግ ብዙ ወንዶችና ሴት ልጆችም ነበሩት፡፡ አዳም በሞተበት ጊዜ እድሜው 930 ዓመት ነበር፡፡
ልጆች:
👉አቤል በሙሉ ልቡ ጥሩ የሆነውን: ከሁሉ የተሻለውን ስጦታ ለእግዚአብሔር አቀረበ: እግዚአብሔርም ተቀበለው:: ስለዚህ ለእግዚአብሔር ስጦታ ስናቀርብ በሙሉ ልባችን የተሻለውን ማቅረብ ይኖርብናል::
👉ቃየል በቅናት ተነሳስቶ ወንድሙን ገደለው: ከዚህም የተነሳ ተረገመ: ተቅበዥባዥ ሆነ። ስለዚህ ልጆች ቅናት መጥፎ ነው: ወደ ክፉ እርምጃ ይወስዳል: በእርግማንም ያንከራትታልና ከሀጢአት ተጠበቁ:: መልካምንም አድርጉ!
#የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ጥቅስ : 2ቆሮንቶስ 9:6-8 (ከወላጆቻችሁ/ከታላላቆቻችሁ ጋር አጥኑ)።
ጥያቄ
1. እግዚአብሔር ያስደሰተው የማን ስጦታ ነው?
2. እግዚአብሔር ቃየን ወንድሙን አቤልን ስለ ገደለው ይቅርታ እንዲጠይቅና ይቅርም እንዲባል ፈልጎ ነበር፡፡ እግዚአብሔር ቃየንን ለመጠበቅ ምን አደረገ?