EECMY Children Ministry: MY Sunday School
957 subscribers
1.4K photos
15 videos
187 links
MY Sunday School is the official page of EECMY Children Ministry.

Wholistic Growth For Our Children!

Access Sunday School learning materials at www.mysundayschool.org
Download Telegram
ለልጆች እና ወጣቶች ቤተ መጻሕፍት 200 መጽሐፍቶችን ያበረከቱ አባት...አቶ አቤል ዶርቴት
===
አቶ አቤል ዶርቴት ይባላሉ። በአዲሱ ደቡብ ምዕራብ ክልል: ቤንች ሸኮ ዞን: ሚዛን ተፈሪ ከተማ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ይኖራሉ። ከመምህርነት ጀምረው በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ለአራት አስርት አመታት ህዝብን እና መንግስትን አገልግለዋል። በሚያመልኩበት እና በሚያገለግሉበት የመካነ አየሱስ ቤተ ክርስቲያንም በተለያየ የሃላፊነት ስፍራ አገልግለዋል: አሁንም እያገለገሉ ይገኛሉ።
በየ እያንዳንዱ ማህበረ ምዕመናን ቤተ መጻሕፍትን ማደራጀት እና ማስጀመር በሚል ራዕይ የጀመርነውን እንቅስቃሴ በመደገፍ በሚዛን ተፈሪ ቤቴል መካነ ኢየሱስ ማ/ም ለዚሁ አገልግሎት ድጋፍ እንዲውል ለሁለንተናዊ እድገት የሚረዱ 200 መጽሐፍቶችን አበርክተዋል። ጋሽ አቤል: ለዚህ መልካም ተግባርዎ ትውልድ ያመሰግንዎታል። በነዚህ መጽሐፍት ታንጸው እና አድገው ለቁም ነገር የበቁትን እንዲያዩ በሙሉ ጤንነት እና ረጅም እድሜ እግዚአብሔር ይባርኮት! ኑሩልን!

ልጆች እና ወጣቶቻችን በሁለንተናዊ እድገት ታንጸው እንዲያድጉ የልጆች እና የወጣቶች አገልግሎት ድፓርትመንት ሁለንተናዊ የልጆች እና ወጣቶች አገልግሎት ፓኬጅ አዘጋጅቶ እየሰራበት ይገኛል። ከፓኬጁ አንዱ አካዳሚክ ኤክሰለንሲ (Academic Excellency) ነው; ማለትም ልጆች እና ወጣቶች በእውቀት እና በመልካም ስነ ምግባር ታንጸው እንዲያድጉ መስራት ነው።

የወጣቱ ትልቁ ሀብት አዕምሮው ነው: አዕምሮ ደግሞ የሚገነባው እና የሚበለጽገው በእውቀት ነው: ከእውቀት ምንጮች ዋነኛው ደግሞ መጽሐፍ ነው። አንባቢ ትውልድ መሪ ነው (Readers are Leaders) እንደሚባለው ልጆች እና ወጣቶች መሪ ሆነው እንዲያድጉ ሁላችንም የድርሻችንን ልንወጣ ይገባል።

👉ውድ ወጣቶች: መሪዎች: (አገልጋዮች)...
በእያንዳንዱ ማ/ም ከትንሽ ጀምሮ (Mini Library) ቤተ መጽሐፍትን እንድታደራጁ እና ትውልዱን ወደ እውቀት ጎዳና በመምራት የድርሻችሁን እንድትወጡ አደራ እንላችኋለን። በሚዛን ተፈሪ መካነ ኢየሱስ ያለውን እንቅስቃሴ አይተን ደስ ብሎናል። ትምህርቱ: ስልጠናው: ጉብኝቱ ይቀጥላል።

#ቤተ_መጽሐፍትን በማ/ም ደረጃ ለማደራጀት:
👉በየ ማ/ም ካሉት መጠነኛ ክፍል (ቢሮ) መጠቀም ይቻላል (የግድ አዲስ ግንባታ አያስፈልግም)
👉መጽሐፍትን የማሰባሰብ እንቅስቃሴን በመጀመር ሰዎች መጽሐፍትን እንዲለግሱ ማድረግ ይቻላል።
👉የገቢ ማሰባሰቢያ በማድረግ ተጨማሪ አዳዲስ መጽሐፎችንም በየጊዜው አቅዶ መግዛት ይቻላል።
👉መጽሐፎቹ ለመንፈሳዊም እንዲሁም ለጠቅላላ እውቀት የሚረዱ ሳይንሳዊ መጽሐፎች: ለሁለንተናዊ አገልግሎት የሚረዱ እንዲሆኑ መስራት:
👉ኮሚቴ በማዋቀር አገልግሎቱ ፈጣን: ምቹ እና ለሁሉም ተደራሽ እንዲሆን ማድረግ ይቻላል።

#ቤተመጽሐፍቱ ተደራጅቶ ሲራ ሲጀምር:.
👉ልጆች ያነባሉ...
👉ወጣቶች ያነባሉ...
👉አገልጋዮች ያነባሉ...
👉መሪዎች ያነባሉ...
👉ምዕመኑ ያነባል...
👉አንባቢ ትውልድ ይፈጠራል; በዕውቀት ህይወቱን; ቤቱን:  ቤተሰቡን: አገልግሎቱን: ድርጅቱን: ሀገሩን ይመራል።

''መጻሕፍትን ያስተውሉ ዘንድ አእምሮአቸውን ከፈተላቸው፤...'' (ሉቃስ 24:45); የምታነቡትን እንድታስተውሉ አእምሮአችሁ በኢየሱስ ስም የተከፈተ ይሁን!
===
ይህ መልዕክት ለሌሎችም እንዲደርስ #Share/Forward በማድረግ ይተባበሩን።

የተለያዩ ትምህርቶችን ለማግኘት የሚከተለውን አድራሻችንን ይጠቀሙ👇!

http://www.mysundayschool.org
https://t.me/MYSundaySchool
https://t.me/eecmyyouthministry
ቤተመጻሕፍት ተመርቆ ተከፈተ
#አንባቢዎች_መሪዎች_ናቸው
====
''የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል'' እንደሚለው ቃሉ (2ጢሞቴዎስ 3:16): በቤተክርስቲያኒቱ የልጆች እና ወጣቶች ሁለንተናዊ አገልግሎት ፓኬጅ መሰረት: ልጆች እና ወጣቶች: እንዲሁም አገልጋዮች እና መሪወች አንባቢዎች እንዲሆኑ: አንብበው እንዲማሩ: ተምረው እንዲያስተምሩ: ታድሰው ትውልዱን እንድያድሱ በማሰብ በእያንዳንዱ ማ/ምዕመናን መጠነኛ ቤተመጻሕፍት (Mini Library) እንዲደራጅ ታስቦ እና ታቅዶ እየተሰራበት ይገኛል።
ይኼንንም ራዕይ ተቀብለው ከግብ በማድረስ በደቡብ ምዕራብ ቤቴል ሲኖዶስ የምትገኘዋ የሚዛን ተፈሪ ቤቴል መካነ ኢየሱስ ማ/ምዕመናን ቀዳሚ ሆናለች።በሲኖዶሱ በነበረው የልጆች እና ወጣቶች የመሪዎች ስልጠና ወቅት የተደራጀውን ቤተመጻሕፍት ለእግዚአብሔር ክብር እና ለሰው ልጆች ጥቅም እንዲሆን በጸሎት መርቀን ከፍተናል።
ይሄንን ራዕይ ተቀብለው በቀዳሚነት ስላስፈጸሙት
የሚዛን ተፈሪ ቤቴል መካነ ኢየሱስ ማ/ምዕመናን የልጆች እና የወጣቶች አገልግሎት አስተባባሪዎችን: የማ/ምዐሰመናኗን ሽማግሌዎች: ቄሶች እና በወንጌላውያንን: መጽሐፍትን በመለገስ አስተዋጽኦ ያደረጉትን ሁሉ የሥራው ሁሉ ባለቤት እግዚአብሔር አምላክ አብዝቶ ይባርካችሁ ለማለት እንወዳለን።

ከዚህ በመቀጠል በከተማ ደረጃም ትውልዱን ወደ ዕውቀት ጎዳና የሚመራ ቤተመጻሕፍት ለማደራጀት የድርሻችሁን እንደምትወጡ ተስፋ እናደርጋለን። እኛ የዓለም ብርሃን እና የምድር ጨው እንድንሆን ተጠርተናልና ብርሃናችን ለሰው ሁሉ እንዲበራ ወደ ትውልዱ ወጥተን በመልካም ምግባራችን ብርሃን በመሆን እና ለምድሪቱም ጨው በመሆን ለእግዚአብሔር ክብር እና ለሰው ልጆች ጥቅም እንዲሆን መስራት አለብን።

👉የወጣቱ ትልቁ ሀብት አዕምሮው ነው: አዕምሮ ደግሞ የሚገነባው እና የሚበለጽገው በእውቀት ነው: ከእውቀት ምንጮች ዋነኛው ደግሞ መጽሐፍ ነው። አንባቢ ትውልድ መሪ ነው (Readers are Leaders) እንደሚባለው ልጆች እና ወጣቶች መሪ ሆነው እንዲያድጉ ሁላችንም የድርሻችንን ልንወጣ ይገባል።

👉ውድ ወጣቶች: መሪዎች: (አገልጋዮች)... በዚህ አጋጣሚ ሌሎች ማ/ምዕመናናትም ይሄን መልካም ተሞክሮ በመውሰድ: ትውልዱን ወደ ዕውቀት ጎዳና ለመምራት የሚፈይደውን በእያንዳንዱ ማ/ምዕመናን መጠነኛ ቤተመጻሕፍት (Mini Library)
ማደራጀት አለብን ብለን የጀመርነውን ራዕይ ከግብ እንድታደርሱ በጌታ ፍቅር አደራ ልንላችሁ እንወዳለን።በሚዛን ተፈሪ ቤቴል መካነ ኢየሱስ ያለውን እንቅስቃሴ አይተን ደስ ብሎናል። ትምህርቱ: ስልጠናው: ጉብኝቱ ይቀጥላል።

#ቤተ_መጽሐፍትን በማ/ም ደረጃ ለማደራጀት:
👉በየ ማ/ም ካሉት መጠነኛ ክፍል (ቢሮ) መጠቀም ይቻላል (የግድ አዲስ ግንባታ አያስፈልግም)
👉መጽሐፍትን የማሰባሰብ እንቅስቃሴን በመጀመር ሰዎች መጽሐፍትን እንዲለግሱ ማድረግ ይቻላል።
👉የገቢ ማሰባሰቢያ በማድረግ ተጨማሪ አዳዲስ መጽሐፎችንም በየጊዜው አቅዶ መግዛት ይቻላል።
👉መጽሐፎቹ ለመንፈሳዊም እንዲሁም ለጠቅላላ እውቀት የሚረዱ ሳይንሳዊ መጽሐፎች: ለሁለንተናዊ አገልግሎት የሚረዱ እንዲሆኑ መስራት:
👉ኮሚቴ በማዋቀር አገልግሎቱ ፈጣን: ምቹ እና ለሁሉም ተደራሽ እንዲሆን ማድረግ ይቻላል።

#ቤተመጽሐፍቱ ተደራጅቶ ሲራ ሲጀምር:.
👉ልጆች ያነባሉ...
👉ወጣቶች ያነባሉ...
👉አገልጋዮች ያነባሉ...
👉መሪዎች ያነባሉ...
👉ምዕመኑ ያነባል...
👉አንባቢ ትውልድ ይፈጠራል; በዕውቀት ህይወቱን; ቤቱን: ቤተሰቡን: አገልግሎቱን: ድርጅቱን: ሀገሩን ይመራል።

''መጻሕፍትን ያስተውሉ ዘንድ አእምሮአቸውን ከፈተላቸው፤...'' (ሉቃስ 24:45); የምታነቡትን እንድታስተውሉ አእምሮአችሁ በኢየሱስ ስም የተከፈተ ይሁን!
===
ይህ መልዕክት ለሌሎችም እንዲደርስ #Share በማድረግ ይተባበሩን።

የተለያዩ ትምህርቶችን ለማግኘት የሚከተለውን አድራሻችንን ይጠቀሙ👇!

http://www.mysundayschool.org
https://t.me/MYSundaySchool
https://t.me/eecmyyouthministry