ሙድ እንያዝ በእኛ
260K subscribers
2.09K photos
154 videos
13 files
205 links
★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °
Download Telegram
"#ደስተኛ_ለመሆን የሚረዱ አስርቱ የሕይወት መርሆዎች!"😂🤣😄
❀︵‿♡ ~♡︵❀
🔻#እራስህን_ከሌላ_ሰው_ጋር_አታፎካክር!"
:
☞ሁላችንም እንደ አሻራችን ሁሉ ባህሪያችን እና ፍላጎታችንም በጣም ይለያያል። #ደስታን ከሚያጠፉ ምክንያቶች አንደኛው እራስን ከሰው ጋር ማፎካከር ነው። አሳ🐬 ደስታዋን እንደ ወፍ🦅 በሰማይ ልፈልግ ብትል፤ወፍ ደግሞ እንደ አሳ በውሃ ውስጥ ልፈልግ ብትል፤ ሁለቱም ሳይደሰቱ ይቀራሉ።
🔐ስለዚህ ደስታህን በራስህ መለኪያ ለካው። አንተ በሌሎች ስትቀና ሌሎችም ባንተ እንደሚቀኑ እወቅ።
:
🔺#አትኩሮትህን በሌለህ ነገር ላይ ሳይሆን ባለህ ነገር ላይ አድርገው!"
:
#የጎደለህ_ምንድን_ነው?
#ያለህስ_ምንድን_ነው
ብታመዛዝነው የቱ ይበልጣል? ብዙዏቻችን ሃሳብ እና አትኩሮቶቻችን በሌለን ነገር ላይ ስለሆነ፤ ያለንን ነገር ሳንጠቀምበት እንቀራለን።
#ደስተኛ ለመሆን ሁሉም ነገር ሊኖርህ አይገባም። በደንብ ካስተዋልከው አሁን ያለህ ነገር ደስተኛ ለመሆን በቂ ነው። ምክንያቱም አንተ ያለህን የሚመኙ ምስኪኖች ብዙ ናቸውና።
:
🔻 #እራስህን_ሁን!
:
☞በዚህ ምድር ላይ ሌላውን ለመምሰል እንደመሞከር ከበድ ነገር ምን አለ? ሌላውን ለመምሰል ስትሞክር፤ የምትጣላው ከሰው ጋር ሳይሆን ከገዛ እራስህ ጋር ነው።
#እናም እራስህን አታስቀይመው፤ እውነተኛ ወዳጆችህ አንተን ባንተነትህ ይቀበሉሃል… ከምንም በላይ እራስህን በመሆን ከራስህ ጋር ሰላም ፍጠር፤
:
🔺 #ሁሉን_ለማስደሰት_አትሞክር!
:
☞አንድ ነገር ስታደርግ ሰዎች ደስ እንዲላቸው ብለህ ሳይሆን ትክክለኛ እና አንተ ያመንክበት ነገር ስለሆነ ይሁን።
በዚህ ምድር ላይ ምንም አይነትጻዲቅ ሰው ብትሆን እንኳን ሁሉንም ሰዎች ማስደሰት አትችልም።
#ስለዚህ የምታደርጋቸው ነገሮች ከህሊናህ ጋር እስከተስማሙ ድረስ በቂ ነው።
ለሰው ሳይሆን ለህሊናህ ኑር።
:
🔻 #የውሸት_ደስታን_አትፈልግ!
:
☞በውሸት ደስታና በእውነተኛ ደስታ መካከል ትልቅ ልዩነት አለ። የውሸት ደስታ፤ ጊዜያዊ በሆኑና ከውጪ በምናገኛቸው ነገሮች የሚመጣ ነው።
ሃዘናችንን ለጊዜው የሚጋርድ ጊዜያዊ ማስታገሻ፤ እውነተኛ ደስታ ግን ሃሳባችን፤ አላማችን፤ ምግባራችን ሲጣመር የሚፈጠር ስሜት ነው። ሃዝን እና መከራችንን ሳንደብቅ የምንጽናናበት ደስታ፤
:
🔺"ማንን እንደምታገኝ አታውቅምና ለሁሉም ሰው #ቅን_ሁን!"
:
☞ከመንገደኛው አንስቶ እስከ ቅርብ ወዳቻችን ድረስ፤ ሰዎች በኛ ላይ ትልቅ አስተዋጽዎ አላቸው።
#በህይወትህ የምታሰፍራቸው ነጥቦች ሁሉ በኋላ ላይ ተያይዘው መስመር መስራታቸው አይቀርም። የተናቀው ድንጋይ የማዕዘን ራስ ይሆናል ተብሏልና ሰዎችን አትናቅ። በየትኛውም አጋጣሚ ለምታገኛቸው ሰዎች ትክክለኛውን ነገር አድርግ፤
:
🔻"#መለወጥ_የማትቻለውን ነገሮችን ተቀበላቸው!"
:
☞ብዙሰዎች ጭንቀት ውስጥ የሚገቡት መለወጥ የማይችሏቸውን ነገሮች ለመለወጥ ስለሚጥሩ ነው። ምንም እንኳን በህይወታችን ውስጥ አብዛኛው ነገሮች ላይ ስልጣን ቢኖረንም፤ መለወጥ የማችላቸው ነገሮች አሉ። ከአቅምህ በላይ በሆኑ ነገሮች እራስህን አታስጨንቅ።
ከአቅምህ በላይ የሆነውን ነገር ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ስጠው።
:
🔺 #የራስህ_እውነተኛ_ወዳጅ_ሁን!
:
☞ምንም እንኳን ሰዎች በአንተ ቢያምኑብህም እና ቢመኩብህም ፤ አንተ በገዛ እራስህ ካላመንክ ህይወትህ ምንም ዋጋ የለውም።
ከሰዎች ፍቅር በላይ የራስህ ፍቅር ወሳኝ ነው። የሚገርመው ሰዎች እራሱ ሊወዱህ የሚችሉት አንተ በመጀመሪያ እራስህን መውደድ ስትችል ነው። እራስህን በደንብ ተንከባከበው። ሲያጠፋ ይቅር በለው፤ ሲደክም አበርታው፤ ሲሳካለት አሞካሸው።
ላንተ ካንተ የቀረበ ማን አለህና?

🔻"#መልካም_አስብ_መልካም_ተናገር!"
:
☞በመጀመሪያ ሰው ያስተሳሰቡ ውጤት መሆኑን እመን፤ አሁን የምንኖረው ህይወት ያመለካከታችን እና ያስተሳሰባቸን ውጤት ነው። ይህን ካወቅክ አስተሳሰብህን በጥንቃቄ አጢነው። ደስተኛ ለመሆን የተመረጠ አስተሳሰብ ሊኖርህ ይገባል።

🔺"#ለምን_እንደምትኖር_እወቅ!"
:
☞ህይወት ማለት የተሰጠህን ሃላፊነት ለመጨረስ የተሰጠችህ ጊዜ ናት። ሃላፊነትህ ምንድንነው? በህይወትህ ማድረግ የምፈልገው ነገር ምንድን ነው? መልሱ ካወቅክ ለህይወት ያለህ አመለካከት ይለወጣል።
#ፈጣሪ_ማስተዋሉን_ያብዛልን!
❀︵‿♡ ~♡︵❀
@Teke_Man ነኝ Join @Mudenyaz
የምትወዳት ልጅ መለያየት ሳትፈልግ አዝናብህ ስትለይ ዝም አትበል። ተሟሙተህ የራስህ አድርጋት። ከልብህ ከወደድካት ለሷ ካንተ በላይ የሚያስፈልጋት የለም። ሴት ልጅ አበባ ናት። በፍቅር የሚንከባከባትን እንጂ እየመጣ የሚቀጥፋትን አትፈልግም!!
#ስለዚህ ወንድሜ ሴት ልጅ ምልክቱን ስታሳይህ አንተም ከወደድካት አይንህን እንዳታሽ፤ ሄደህ አናግራት!! ፍርሃትና ኩራት የስንቱን ፍቅር ኦና እንዳስቀረ ብታይ ዛሬዉኑ ዉሳኔህን ታስተካክላለህ።

#መልካም_የፍቅር_ቀን!! 😊😁
💚💛❤️
ከዝንቅ መዝናኛ የተወሰደ Join @Mudenyaz