ማኅበረ ቅዱሳን አዳማ ማዕከል ሕዝብ ግንኙነት
430 subscribers
1.09K photos
17 videos
1 file
84 links
Download Telegram
የደም ልገሳ በአዳማ ማዕከል

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ማኅበረ ቅዱሳን አዳማ ማዕከል የህዝብ ግንኙነትና ትብብር አገልግሎት ዋና ክፍል አስተባባሪነት ዛሬ ቀን 18/09/2016 ዓ.ም የማዕከሉን አባላት ጨምሮ ከሰ/ት /ቤት ከማኅበራት ከግቢ ጉባኤ እና አጋር አካላት ጋር በርካታ ኦርቶዶክሳውያን የተሳተፉበት የደም ልገሳ መርሐ ግብር ተከናውኗል።

መርሐ ግብሩ ከአዳማ ደም ባንክ ጋር በመተባበር  የተዘጋጀ ሲሆን 51 ዩኒት ደም ተለግሷል።በዕለቱ በደም ልገሳው ላይ የተሳተፉ ኦርቶዶክሳውያን ይህንን ነፍስ አድን በጎ ተግባር ወደፊትም በቋሚነት እንደሚሳተፉ ገልፀዋል።
እንኳን ለእናታችን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም አመታዊ ክብረ በዓል(ደብረ ምጥማቅ) በሰላም አደረሳቹ::🙏🙏🙏
እነሆ ጉባኤ ደብረ ምጥማቅ ዝግጅቱ ተጠናቆ ቀኑን በመጠባበቅ ላይ ይገኛል::
ታዲያ እርሶስ:-
፠ አባት እናት
፠ ወንድም እህት
፠ ወዳጅ ዘመድ
፠ ጓደኛ የስራ ባልደረባ
፠ ጉባኤው የሚመለከተውን ሰው ሁሉ በመጋበዝ መንፈሳዊ ግዴታዎን ይወጡ::

ሰናይ ቀን በቸር ያድርሰን::🙏🙏
አስቸኳይ የሥራ ማስታወቂያ

ማኅበረ ቅዱሳን የግቢ ጉባኤ ምሩቃንን ተጠቃሚ ለማድረግ ከተለያዩ ተቋማት ጋር ግንኙነት እያደረገ ይገኛል። በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት የምታሟሉ የግቢ ጉባኤ ምሩቃን በማኅበሩ ሕንጻ 2ኛ ወለል ላይ በሚገኘው የሕዝብ ግንኙነት እና ትብብር አገልግሎት ማስተባበሪያ ቢሮ በአካል በመቅረብ እና የትምህርት ማስረጃችሁን በመያዝ እንድታመለክቱ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

የትምህርት መስክ ፡- በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እና ተዘማጅ ዘርፍ ከታወቀ የትምህርት ተቋም በመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቀ/የተመረቀች
የሥራ ልምድ ፡- ዜሮ ዓመት
የሥራው አድራሻ፡- አዲስ አበባ
ብዛት ፡- 15
የማመልከቻ ቀን፡- ከግንቦት 27 ቀን እስከ ሰኔ 4 ቀን 2016 ዓ.ም በሥራ ሰዓት ብቻ
የ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መግለጫ እንደሚከተለው ይነበባል።

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ፡፡

በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በቅዱሳን አበው ሐዋርያት ትውፊት በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቁጥር 164 በተደነገገው መሠረት ምልዓተ ጉባኤው የርክበ ካህናት መደበኛ ስብሰባውን ከግንቦት 21 እስከ ግንቦት 28 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ በርካታ አጀንዳዎችን በመቅረጽ ውይይት ሲያካሄድ ሰንብቷል፡፡

ምልዓተ ጉባኤው ለቤተ ክርስቲያናችን አንድነት፣ ለሐዋርያዊ ተልእኮ መስፋፋት፣ ለመንፈሳዊ ዕድገትና ለምእመናን ደኅንነት ትኩረት በመስጠት ለቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንና ለሀገራችን ጠቃሚ የሆኑ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡

በዚሁ መሠረት፡-

1.በቅድስት ቤተ ክርስቲያንና በሀገራችን መንግሥት መካከል ሊኖር ስለሚገባው መልካም የሥራ ግንኙነት በቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት ከመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር የሚመካከር የብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ልዑክ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፤

2.በመላው ሀገራችን በተፈጠሩ ግጭቶች፣ አለመግባባቶችና የሰላም ዕጦት በርካታ የሰው ሕይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት እንደቀጠለ መሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስን በእጅጉ አሳዝኗል፡፡ ስለዚህ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሁሉም ባለድርሻ አካላት ከግጭትና ከጥፋት ድርጊት ተቆጥበው የተፈጠረውን አለመግባባትና ግጭት በውይይትና በምክክር እንዲፈቱ እና ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ ቅዱስ ሲኖዶስ በአጽንኦት ጥሪውን ያቀርባል፤