3.በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እየተከናወነ ባለው የኮሪደር ልማት ምክንያት ለፈረሱ የቤተ ክርስቲያናችን ይዞታዎች የከተማ አስተዳደሩ ምትክ ቦታ በመስጠትና ቤተ ክርስቲያናችን ወደ መልሶ ማልማት እንድትገባ ድጋፍ በማድረግ፤ በተለይም ክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አበቤ በፈረሰው የጽርሐ ምኒልክ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሕንፃ ምትክ በከተማ አስተዳደሩ ሙሉ ወጭ ተጨማሪ ምድር ቤትና የቦታ ስፋት ያለው B+G+4 ሕንፃ ገንብቶ ለማስረከብ ቃል በመግባትና የቤተ ክርስቲያናችን የበላይ ኃላፊ አባቶች በተገኙበት የመሠረት ድንጋይ እንዲጣል ማድርጋቸውን ቅዱስ ሲኖዶስ ከምስጋና ጋር የተቀበለው ሲሆን በተሰጠን ምትክ ቦታ ላይም የከተማው ፕላን በሚፈቅደው መሠረት የመልሶ ማልማት ሥራው እንዲከናወን ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
4.የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከተቋቋመበት አዋጅ መረዳት እንደሚቻለው ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ ሁኔታ ሀገራዊ ችግሮችን በምክክርና በውይይት ለመፍታት የተቋቋመ መሆኑን ተረድተናል፡፡ ይሁን እንጅ ሀገረ መንግሥትን ከመመሥረት ጀምሮ በአስታራቂነትና በሰላም ግንባታ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ለሆነችው እናት ቤተ ክርስቲያን እስከአሁን ድረስ በይፋ የቀረበ የተሳትፎ ጥሪ ሳይኖር ኮሚሽኑ የተሳታፊ ልየታንና አጀንዳ መረጣ አጠናቆ ወደ ምክክር ትግበራ እየገባ መሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስን ቅር አሰኝቷል፡፡ በመሆኑም የቤተ ክርስቲያኒቱ ተሳትፎና አጀንዳ የማቅረብ መብቷ እንዲረጋገጥ ከኮሚሽኑ ጋር በመነጋገር ጉዳዩን ተከታትሎ ለፍጻሜ የሚያበቃ ኮሚቴ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፡፡
5.የብፁዓን አባቶች የዝውውርና የአህጉረ ስብከት ሥያሜን አስምልክቶ የቀረቡ ጥያቄዎችን ምልዐተ ጉበኤው ተመልክቶ ተገቢውን ውሳኔ አሳልፏል፤
6.የሃይማኖት ጉዳዮች ረቂቅ አዋጅ ላይ ቅዱስ ሲኖዶስ በሰፊው ከተወያየ በኋላ በረቂቅ አዋጁ ሊሻሻሉ ይገባቸዋል ብሎ ያመነባቸውን የማሻሻያ ሐሳቦች በማዘጋጀት ለሚመለከተው መንግሥታዊ ተቋም እንዲላክና ረቂቅ አዋጁ ከመጽደቁ በፊት የተሰጡት የማሻሻያ ሐሳቦች በረቂቁ ስለመካተታቸው ክትትል የሚያደርግ ኮሚቴ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፡፡
7.በቅዱሳት መጻሕፍት ላይ ተመሥርቶ አባታዊ ምክርና ተግሣጽ ማስተላለፍ ከቀድሞ ጀምሮ የነበረ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ያለው መሆኑ ቢታወቅም በሀገራችን ኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተፈጠሩ አለመግባባቶች የተከሰቱትን ወቅታዊ ችግሮች አስመልክቶ እየተላለፉ ያሉ ቤተ ክርስቲያንን የማይወክሉ መልእክቶችን ቅዱስ ሲኖዶስ የማይቀበላቸውና በጥብቅ የሚቃወማቸው መሆኑን እየገለጸ ወደፊት እንዲህ ዓይነት ተመሳሳይ ድርጊት እንዳይፈጸም ለማድረግ ይቻል ዘንድ ወጥ የሆነ የመግለጫ አሰጣጥና የትምህርተ ወንጌል ተልእኮ ሕገ ደንብ ተዘጋጅቶ ለምልዐተ ጉበኤ እንዲቀርብ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤
8.ግብረ ሰዶማዊነትና የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ በሕገ ተፈጥሮም ሆነ በሰው ልጅ የሰብዓዊ አኗኗር ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው፣ ፈጣሬ ዓለማት እግዚአብሔር መለኮታዊ ፈቃዱ በተገለጠባቸው ቅዱሳት መጻሕፍት ፈጽሞ የተከለከለ፣ በቀኖናተ ቤተ ክርስቲያን፣ በፍትሕ መንፈሳዊና በፍትሐ ብሔር ድንጋጌዎች፣ በሥነ ልቦና ደንቦች የተወገዘ፣ ሥነ አእምሮዊ ሚዛንን የሚያዛባ፣ ግለሰባዊ ማንነትን፣ ቤተሰባዊ ሕይወትን፣ ማኅበራዊ ትሥሥርን የሚጎዳ ተግባር በመሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ እያወገዘ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻና የግብረ ሰዶማዊነትን ኃጢአት በተመለከተ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን አቋም በሚገልጽ መልኩ ራሱን ችሎ ዓለም አቀፋዊ ይዘቱን ባገናዘበ ሁኔታ ዝርዝር መግለጫ እንዲሰጥ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤
9.በደቡብ የሀገራችን ክፍል የቤተ ክርስቲያኒቱን አብነት ትምህርት ከማስፋፋትና ከፍ ያለ መዐርግ ከመስጠት አንፃር የጋሞና አካባቢው ዞኖች ሀገረ ስብከት የዝጊቲ ደብረ ሰላም አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን የአራቱ ጉባኤያት ማስመስከሪያ ትምህርት ቤት እንዲሆን በቀረበው ጥናት መሠረት ቅዱስ ሲኖዶስ ለምሥክር ጉባኤ ቤቱ ዕውቅና በመስጠት ወደ ትግበራ እንዲገባ ወስኗል፡፡
10.ከሀገራችን ውጭ ባሉ አህጉረ ሰብከት መደበኛ አገልግሎት ለመስጠት የሚላኩ አገልጋዮች በክፍሉ ሊቀጳጳስ ሲጠየቅ በሙያ ብቃታቸው፣ በምግባራቸውና በመንፈሳዊነታቸው የተመሰከረላቸው አገልጋዮች ከሁሉም አህጉረ ስብከት በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት አቅራቢነት በውድድር እየተለዩ በቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔ እንዲላኩ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
11.የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ዘመኑን የዋጀ እንዲሆን ቅዱስ ሲኖዶስ የዐሥር ዓመት መሪ ዕቅድ በማጽደቅ ወደ ትግበራ እንዲገባ መወሰኑ ይታወሳል፡፡ በዚሁም መሠረት ለአፈጻጸሙ ያመች ዘንድ በባለሙያዎች ተዘጋጅቶ የቀረበውን መዋቅራዊ አደረጃጀት በማጽደቅ በሕገ ቤተ ክርስቲያኑና በቃለ ዓዋዲው ተካቶ ሥራ ላይ እንዲውል ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
12.በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ተዘጋጅቶ የቀረበውን የ2017 ዓ.ም. ዓመታዊ በጀት በማጽደቅ በሥራ ላይ እንዲውል ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
በአጠቃላይ ቅዱስ ሲኖዶስ በመንፈስ ቅዱስ እየተመራ ላለፉት ተከታታይ ቀናት በመንፈሳዊ፣ ማኅበራዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በመወያየትና ተገቢውን ውሳኔ በማስተላለፍ መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው ዕለት በጸሎት አጠናቅቋል፡፡ መሐሪና ሁሉን ቻይ የሆነ እግዚአብሔር አምላካችን ለሀገራችን፣ ለሕዝባችን፣ ለዓለሙ ሁሉ ሰላሙን፣ ፍቅሩንና አንድነቱን ይስጥልን፡፡
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን
አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም
ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ግንቦት ፳፱ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም. ኢትዮጵያ አዲስ አበባ

Forwarded from Sun Printing
የአዳማ ማዕከል ጠቅላላ ጉባኤ ተጠናቀቀ
"የማህበረ ቅዱሳን አባላት ከሂደት ተኮር ( ብዙ የማይለካ) ተግባር ወደ ውጤት ተኮር (የሚለካ ተግባር) ላይ መሰማራት አለብን" የማህበረ ቅዱሳን ዋና ፀሐፊ መ/ር ዋስይሁን በላይ።
የማኅበረ ቅዱሳን አዳማ ማዕከል 26ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የተገኙት የማህበረ ቅዱሳን ዋና ፀሐፊ መ/ር ዋስይሁን የማህበረ ቅዱሳንን ተቋማዊ ለውጥ በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ለጉባኤው ታዳሚዎች ሰጥተዋል።
ሐምሌ 19/2016 ዓ.ም የተጀመረው የአዳማ ማዕከል 26ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ልዩ ልዩ የአገልግሎት አቅጣጫ እና ውሳኔዎችን በማሳለፍ የተጠናቀቀ ሲሆን ጉባኤው አባቶች ካህናት አባቶች፣ሊቃውንተ ቤ/ክ፣ የዋና ማዕከል ተወካዮች፣ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የማዕከሉ አባላት በተገኙበት ልዩ ልዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቋል።
በዕለቱ የቀረቡ ዋና ዋና መርሐ ግብራት
🌱የአዳማ ማዕከል የ2017 ዓ.ም እቅድ፤ የማኅበረ ቅዱሳን ተቋማዊ ለውጥ (በመ/ር ዋሲሁን በላይ)፤ የቤተክርስቲያን አሁናዊ ሁኔታ (በመ/ር ዳኜ ዘርፉ) ዋና ዋናዎቹ ሲሆኑ ከማዕከሉ ዋና ዋና አገልግሎቶች መረጃዎች፦
🌱127 በደረጃ አንድ ፤ 21 በደረጃ ሁለት ሰባኪያን በኦሮምኛ ቋንቋ ስልጠና ተሰጥቷል።
🌱በ8 ወረዳዎች 36 የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ተተግብሯል።
🌱50 የማፅናት ጉባኤያት ተከናውነዋል
🌱14 አዳድስ አማንያን እና 9 ከጠፉ ወገኖች ማስመለስ ተችሏል
🌱ለ3 የአብነት ት/ቤቶቸ ማስፊፊያ ተሰርቷል።
🌱1680 የግቢ ጉባኤ ተማሪዎችን አስመርቋል።
🌱ለ78 ገዳማውያን አባቶችና የአብነት ተማሪዎች እንድሁም ለ40 ነድያን ነፃ ህክምና ተሰጥቷል።
🌱21 የኦርቶዶክሳውያን ቤተሰብ የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጥቷል።
🌱1200 ምዕመናንን የተሳተፉበት መንፈሳዊ ቴአትር ተሰርቷል።

🌱እንዲሁም
የሚዲያ ቤተሰብን ለማደራጀት ተችሏል።
🌱ካሜራን ጨምሮ የቀረፃ ቁሳቁሶችን ግዥ ተፈፅሟል።
🌱ቦሩ ሜዳ በኦሮምኛ ቋንቋ ሁለት ጊዜ ተከናውኗል።
🌱6303 የአ/ጎ/ት/ቤት ተማሪዎችን በማስተማር ላይ ይገኛል።
የሚዲያ ቤተሰብን ለማደራጀት ተችሏል።
🌱ካሜራን ጨምሮ የቀረፃ ቁሳቁሶችን ግዥ ተፈፅሟል።
🌱ቦሩ ሜዳ በኦሮምኛ ቋንቋ ሁለት ጊዜ ተከናውኗል።
🌱6303 የአ/ጎ/ት/ቤት ተማሪዎችን በማስተማር ላይ ይገኛል።
ውድ የአዳማ ማዕከል አባላት እና የግቢ ጉባዔ ተማሪዎች፥
እድሜያቸው ከ15-35 አመት ውስጥ የሚገኙ ሴቶችን ከስር በተገለጹት በ9 ዘርፎች ላይ የሁለት ቀን ስልጠና ለመስጠት፤ እንዲሁም ዝግጁ ለሆኑ ደግሞ ወደgig ስራ ለማስገባት ዝግጅት እየተደረግ ነው። ስልጠናውን ለመውሰድ ፍላጎት ያላችሁ አባላት እና የግቢ ጉባዔ ተማሪዎች ፍላጎታችሁን በዚሁ ገጽ ላይ እንድታሳውቁን እንጠይቃለን።
ዘርፎቹ: The sectors are:
1. Accounting service providers,
2. Facilitation Skills,
3. Preparation of G+1 Building BOQ,
4.Pitch Trainers,
5. Coffee Harvesting, and
6. Sales.
7. Content Creation.
8. Call agents
9. Product photography
የሚፈለገው የትምህርት ደረጃ ለተወሰኑት ዲግሪ ሲሆን ለተራ ቁጥር 2, 4, &8 ድግሪ ሲሆን ለተራ ቁጥር 1, 3, 7, 6, 9ከ10 ጀምሮ ዲፕሎማ ፣ ድግሪ እና ከዛ በላይም ሊሆን ይችላል።
አዳማ ማዕከል ማኅበረ ቅዱሳን!

የ2017 ዓ.ም የደመራ በዓል በአዳማ ከተማ የምስራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ፣የሀገረ ስብከቱ ስራ አስኪያጅ እና የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም አባ ገዳዎች በተገኙበት ከህዝበ ክርስያኑ ጋር በድምቀት ተከበረ፡፡
የ2017 ዓ.ም የደመራ በዓል አከባበር በምስራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ መሪነት በተደረገ የፀሎት ስን ስረዓት ተከፈተ፡፡
በሊቃውንተ ቤተክርስቲያንና በሰንበት ትምህርት ቤት ዘማርያን ያሬዳዊ ዝማሬ ማቅረብ ከፀሎት ስነ ሥርዓቱ የተከተለ መርሐ ግብር ነበር፡፡
በማኀበረ ቅዱሳን አዳማ ማዕከል ዘማርያንና በወልዳ ዱከ ቡኦታ ዘማርያን መዝሙር ቀርቧል፡፡ ከዛ በማስከተል የአዳማ ደ/ገ/ቅ/ኪዳነምሕረት ቤ/ክ ሰ/ት/ቤት የባዓሉን ታሪካዊ ዳራ የሚያሳይ ትዕይንት የተከተለ ሲሆን ከዚያ በማስከተል የምስራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ስራ አስኪያጅ መላከ ምሕረት ቆሞስ አባ ገ/መድኅን ንጉሴ ጥልን በመስቀሉ ገደለ በሚል ርዕስ መስቀል የሰላምና የፍቅር ምልክት ነው በማለት የዕለቱን ትምህርተ ወንጌል ሰጥተዋል፡፡
ጲላጦስና ሄሮድስ ክርስቶስን ለመስቀል የመታረቃቸውን ምሳሌ በማንሳት መስቀል የእርቅ ምልክት ነው በይቅርታ መሻገር ያስፈልጋል፤ ይቅርታ ደግሞ የሰላም መሠረት ነው ሲሉ መልዕክታቸውን ያስተላለፉት የአዳማ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ሙላቱ ዲታ ናቸው፡፡
በመጨረሻም የምስራቅ ሸዋ ሀገረስብከት ሊቀጳጳስ ብፀዕ አቡነ ጎርጎርዮስ የመስቀልን በዓል ስናከብር የወደቁትን በማሰብ በሰላም ዕጦት የተፈናቀሉትን በመርዳት የታሰሩትን በመጎብኘት የመስቀሉን ምስጢር በህይወት መኖር እና በተግባር መተርጎም ይገባል በማለት መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን በአባታዊ ቡራኬና ፀሎት የዕለቱን መርሐ ግብር ከሳረጉ በኋላ ከሀገረ ስብከቱ የስራ ኃላፊዎች እና ከከተማ መስተዳደሩ ባለሥልጣት ጋር በመሆን ደመራውን ለኩሰው የእለቱ መርሐ ግብር ተጠናቋል፡፡