መዝገበ ቅዱሳን
24.2K subscribers
1.97K photos
9 videos
6 files
26 links
የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው! መ/ሳ 1÷7
Bewust mesimer lemanegager
@Yesadkusitota
የሰማነውን እንናገራለን
ያየነውን እንመሰክራለን
Download Telegram
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

❖ መስከረም ፳፪ (22) ❖

✞✞✞ እንኩዋን ለአበው ሰማዕታት
#ቅዱስ_ዮልዮስና_ቅዱስ_ኮቶሎስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞

+"+ #ቅዱስ_ዮልዮስ_ሰማዕት +"+

=>ከሁሉ አስቀደሞ ስለ ሰማዕታት ዜና ሲሰማ ለዚህ
ቅዱስ አንክሮ (አድናቆት): ክብርና የጸጋ ውዳሴ
ይገባዋል:: ምክንያቱም ገድለ ሰማዕታትን የጻፈልን እርሱ
ነውና:: ነገር ግን መጻፍ ሲባል: ነገሮች እንዲህ እንደ
እኛው ዘመን ቀላል እንዳይመስሏችሁ:: ቅዱሱ ዜና
ሰማዕታትን ለማዘጋጀት ሃብቱን: ንብረቱን: ቤተሰቦቹንና
ሕይወቱንም ሰውቷል::

+ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:- በመጨረሻው ዘመነ
ሰማዕታት (በ3ኛው መቶ ክ/ዘ) ዓለም በደመ ሰማዕታት
ስትሞላ የሰማዕታቱን ዜና የሚጽፍ: ሥጋቸውን እንኩዋ
የሚቀብር አልተገኘም:: "ወኃጥኡ ዘይቀብሮሙ-
የሚቀብራቸውም አጡ" እንዳለ ቅዱስ ዳዊት:: (መዝ. 78:3)

+#እግዚአብሔር ግን ስለ ወዳጆቹ #ሰማዕታት ይህንን
ቅዱስ አስነሳ:: ቅዱስ ዮልዮስ በዘመኑ ደግ ክርስቲያን:
ትዳርና ልጆች ያሉት: እጅግ ባለ ጸጋና 300 አገልጋዮች
ያሉት: ምጽዋትንም የሚወድ ሰው ነበር::

+በወቅቱ ክርስቲያኖች በየመንገዱ ወድቀው መታየታቸው
ዕረፍት ቢነሳው ከቤተሰቦቹ ጋር መክሮ መልካም ግን
ደግሞ ከባድ ውሳኔን አስተላለፈ:: ውሳኔውንም ታጥቆ
ይተገብረው ጀመር:: ነገሩ እንዲህ ነው:-

1.የታሠሩ ክርስቲያኖችን ቁስላቸውን እያጠበ
ያጐርሳቸዋል::

2.ቀን ቀን አገልጋዮቹን አስከትሎ የሰማዕታቱን ሥጋ
እየሰበሰበ: ሽቱ ቀብቶ ይገንዛቸዋል:: አንዳንዶቹን ወደ
ቤተሰቦቻቸው ሲልክ ሌሎቹን ራሱ ይቀብራቸዋል::

3.ሌሊት ሌሊት በ300ው አገልጋዮቹ እየታገዘ
የሰማዕታቱን ዜና: ቀለም በጥብጦ: ብራና ዳምጦ:
ብዕር ቀርጾ: ሲጽፍና ሲጠርዝ ያድራል:: በተረፈችው
ጥቂት ሰዓት ደግሞ ይጸልያል:: ቅዱስ ዮልዮስ በእውነት ድንቅ ሰው ነው:: በምን እንመስለዋለን! እርሱን
የፈጠረውን ጌታ "ዕጹብ ዕጹብ" ብለን ከማድነቅ በቀር::

+ሰማዕታቱም ስለ ደግነቱ የሚመልሱለት ቢያጡ ዝም
ብለው ይመርቁት ነበር:: ምርቃናቸውም "ለሰማዕትነት
ያብቃህ" የሚል ነው:: በእርግጥ ይህ ለዘመኑ ሰዎች
ምርቃት ላይመስለን ይችል ይሆናል:: እርሱ ግን ይህንን
ሲሰማ ሐሴትን ያደርግ: እጅም ይነሳቸው ነበር:: በዘመኑ
ትልቁ ምርቃት ይሔው ነበርና::

+እንዲህ: እንዲህ እያለ ዘመነ ሰማዕታት ሊፈጸም ወራት
ቀሩት:: በዚህ ጊዜ ለሰማዕትነት ከመነሳሳቱ የተነሳ
ጌታችንን ተማጸነ:: ጌታችንም ተገልጾለት "ሒድና ሰማዕት
ሁን: ፈቅጄልሃለሁ" አለው:: እርሱም ደስ እያለው ዜና
ሰማዕታቱን ለሁነኛ ሰው ሰጥቶ: ሃብት ንብረቱን ለነዳያን
አካፈለ::

+ቀጥሎም ቤተሰቦቹንና አገልጋዮቹን ጨምሮ 500
ሰዎችን አስከትሎ ወደ ሃገረ #ገምኑዲ ሔደ:: በመኮንኑ
ፊት የክርስቶስን አምላክነት ቢመሰክር ፈጽመው
አሰቃዩት:: በማግስቱም ወታደሮቹ ለጣዖት ካልሰገድክ
ሲሉት "ቆዩማ ላሳያችሁ" ብሎ በጸሎቱ ጣዖታትን ከነ
ካህናቶቻቸው ምድር ተከፍታ እንድትውጣቸው አደረገ::

+በዚህ ተአምር የደነገጠው መኮንኑ #አርማንዮስ ከነ
ሠራዊቱ በክርስቶስ አመነ:: ክብሩንም ትቶ ቅዱስ
ዮልዮስን ተከተለው:: ቀጥሎም ጉዞ ወደ ሃገረ #አትሪብ
ሆነ:: በዚያም ብዙ መከራን ተቀብሎ ጣዖታቱን
አወደማቸው::

+እዚህም የአትሪብ መኮንን ደንግጦ ከነ ሠራዊቱ አምኖ
ቅዱሱን ተከተለው:: በመጨረሻ ግን ሰማዕትነት
እንዳይቀርበት ስለሰጋ ቅዱስ ዮልዮስ ተአምራት
ማድረጉን ተወ:: በፍጻሜውም የ3ኛው ሃገር መኮንን
ቅዱስ ዮልዮስ ከቤተሰቡና ከ1,500 ያህል ተከታዮቹ
ጋር: 2ቱን የሃገረ ገዥዎች ጨምሮ አንገታቸውን
አሰይፏቸዋል:: ቅዱሱም የክብር ክብርን አግኝቷል::

+"+ #ቅዱስ_ኮቶሎስ_ሰማዕት +"+

=>ይህ ቅዱስ በቀደመ ሕይወቱ አረማዊ ሲሆን
የክርስቶስን ስም ሰምቶ አያውቅም:: በ4ኛው መቶ ክ/ዘ
በፋርስ (አሁን #ኢራን) ሳቦር የሚባል ክፉ ንጉሥ ነግሦ
ክርስቲያኖችን ያሰቃይ ነበር:: እርሱ የሚያመልከው
ፀሐይና እሳት ነውና::

+የዚህ ንጉሥ ልጆቹ 'ልዑል ኮቶሎስና ልዕልት አክሱ'
ይባላሉ:: በቤተ መንግስት ውስጥ ስላደጉ የሚያመልኩት
የአባታቸውን ጣዖት ነበር:: በፋርስ መንግስት ውስጥ
ከነበሩ የጦር አለቀቆችና ሃገረ ገዥዎች አንዱ #ጣጦስ ይባላል::

+ይህ ሰው እጅግ ብሩህ የሆነ ክርስቲያን ነበርና ዘወትር
ከንጹሕ አገልግሎቱ ተሰነካክሎ አያውቅም:: ትንሽ ቆይቶ
ግን ክርስቲያን መሆኑን ሳቦር ስለ ሰማ ሠራዊት
ይልክበታል:: "ሒዱና ጣጦስን መርምሩት: ክርስቲያን
ከሆነና አማልክትን እንቢ ካለ በእሳት አቃጥላችሁ
ግደሉት" አላቸው::

+በአጋጣሚ የንጉሡ ልጅ ኮቶሎስና ጣጦስ በጣም
የሚዋደዱ ባልንጀሮች ነበሩና ሊያስጥለው ወዶ ሔደ::
ኮቶሎስ ቅዱስ ጣጦስ ታስሮ በእሳት ሊቃጠል ሲል
ደረሰ:: ወዲያውም ወደ እሳቱ ውስጥ ጨመሩት:: እነርሱ
ፈጥኖ አመድ ይሆናል ብለው ጠብቀው ነበር:: ግን
አልሆነም::

+ቅዱስ ጣጦስ በእሳት መካከል ቁሞ አላቃጠለውም::
እንዲያውም በትእምርተ መስቀል ቢያማትብበት እሳቱ
ብትንትን ብሎ ጠፋ:: ኮቶሎስ ተገርሞ ቅዱሱን
ባልንጀራውን "ወንድሜ! ሥራይ (መተት) መቼ ተማርክ
ደግሞ?" ሲል ጠየቀው::

+እርሱ እስከዚያች ሰዓት ኃይለ እግዚአብሔርን
አልተረዳምና:: ቅዱስ ጣጦስ ግን "ወንድሜ! አትሳሳት:
እኛ ክርስቲያኖች መተትን አናውቅም:: በፈጣሪያችን
በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ግን ሁሉን ማድረግ እንችላለን"
ሲል መለሰለት::

+ኮቶሎስ ተገርሞ "አሁን እኔ በክርስቶስ ባምን እንዳንተ
ማድረግ እችላለሁ?" ቢለው ቅዱሱ "አዎ ትችላለህ!" አለው:: ወዲያውም "እሳት
አንድዱልኝ" አለና እጣቱን በመስቀል ምልክት አስተካክሎ
ወደ እሳቱ ቢያመለክት እሳቱ 12 ክንድ ርቆ ተበትኖ
ጠፋ::

+በዚያችው ሰዓት ቅዱስ ኮቶሎሰ በክርስቶስ አመነ::
ክብሩንና የአባቱን ቤተ መንግስት አቃሎ ወደ እስር ቤት
ገባ:: አባቱ ሳቦር ይህን ሲሰማ ተቆጥቶ "ምከሪው"
ብሎ እህቱን አክሱን ላከበት::

+ቅዱስ ኮቶሎስ ልትመክረው የመጣችውን እህቱን
አሳምኖ የክርስቶስ ወታደር አደረጋት:: አስቀድሞ
#ቅዱስ_ጣጦስ: አስከትሎም #ቅድስት_አክሱ ተገደሉ::
በፍጻሜው ግን ቅዱስ ኮቶሎስን እግሩን አስረው
በየመንገዱ ጐተቱት:: በጐዳናም አካሉ እየተቆራረጠ
አለቀ:: ክርስቲያኖች በድብቅ መጥተው የ3ቱንም ሥጋ በክብር አኑረዋል::

=>አምላከ ቅዱሳን ሰማዕታትን ባጸናበት ጽናት ሁላችንም
ያጽናን:: በረከታቸውንም ያብዛልን::

=>መስከረም 22 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን
በዓላት=
1.ቅዱስ ዮልዮስ ሰማዕት
2."1,500" ሰማዕታት (የቅዱስ ዮልዮስ ማሕበር)
3.ቅዱስ ኮቶሎስ ሰማዕት
4.ቅድስት አክሱ ሰማዕት
5.ቅዱስ ጣጦስ ሰማዕት
6.ቅዱስ ባላን ሰማዕት

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዑራኤል ሊቀ መላእክት
2.ቅዱስ ሉቃስ ወንጌላዊ
3.ቅዱስ ደቅስዮስ (የእመቤታችን ወዳጅ)
4.አባ እንጦንስ አበ መነኮሳት
5.አባ ዻውሊ የዋህ

=>+"+ ሰውን ከአባቱ: ሴት ልጅንም ከእናቷ . . .
እለያይ ዘንድ መጥቻለሁና:: ለሰውም ቤተሰዎቹ ጠላቶች
ይሆኑበታል:: ከእኔ ይልቅ አባቱን ወይም እናቱን የሚወድ
ለእኔ ሊሆን አይገባውም:: ከእኔ ይልቅም ወንድ ልጁን
ወይም ሴት ልጁን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም::
መስቀሉን የማይዝ በሁዋላየም የማይከተለኝ ለእኔ ሊሆን
አይገባውም:: +"+ (ማቴ. 10:35)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
@petroswepawuos
#ጥቅምት_25

ጥቅምት ሃያ አምስት በዚህች ቀን #ቅዱስ_አቡነ_አቢብ (አባ ቡላ) አረፈ፣ የመላእክት አምሳል የሆነ #አባ_እብሎይ አረፈ፣ የከበረ #ቅዱስ_ዮልዮስ_ሰማዕት ቤተ ክርስቲያኑ የከበረችበት ነው።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_አቡነ_አቢብ (አባ ቡላ)

ጥቅምት ሃያ አምስት በዚህች ቀን ታላቅና ክብር የሆነ አቢብ የተባለ መስተጋድል አባ ቡላ አረፈ።

የዚህም ቅዱስ የአባቱ ስም አብርሃም የእናቱም ስም ሐሪክ ነው እነርሱም ከሮሜ አገር ሉፊ ከሚባል አውራጃ ናቸው በዘመናቸውም ከሀዲው ንጉሥ መክስምያኖስ በክርስቲያን ወገኖች ላይ መከራ ስለ አመጣ ስደት ሁኖ ነበርና እነርሱም በስደት ብዙ ዘመን ኖሩ።

ልጅንም በአጡ ጊዜ የተባረከ ልጅን ይሰጣቸው ዘንድ በጾም በጸሎት ተወስነው ወደ እግዚአብሔር ለመኑ የእግዚአብሔርም መልአክ በሕልም ተገለጠላቸውና ፍሬ የመላበትን ዘለላ ሰጣቸው።

ይህም ቅዱስ በተፀነሰ ጊዜ በቤታቸው አጠገብ ታላቅ ዛፍ በቀለ በቅጠሉም ላይ በሮማይስጥ ቋንቋ ቡላ የእግዚአብሔር አገልጋይ በጽዮንም አድሮ የሚኖር የያዕቆብ ፈጣሪ ያከበረው የሚል ጽሑፍ ነበረበት።

በተወለደም ጊዜ ክርስትና ሳያስነሡ ዓመት ሙሉ አኖሩት እመቤታችን ማርያምም ለሮሜ ሊቀ ጳጳሳት ለሰለባስትርዮስ ተገልጣ ወደ አብርሃም ቤት ሒዶ ሕፃኑን እንዲአጠምቀው አዘዘችው እርሱም ሒዶ የክርስትና ጥምቀትን አጠመቀው ስሙንም ቡላ ብሎ ሰየመው እናትና አባቱም ሳይነግሩት ቡላ ስለ ሰየመው አደነቁ ዕፁብ ዕፁብ አሉ።

ከዚህም በኋላ ሊቀ ጳጳሳቱ በጸለየ ጊዜ የቊርባን ኅብስትና ወይን የተመላ ጽዋ ከሰማይ ወረደ እርሱም ቀድሶ ሥጋውንና ደሙን ከሕፃኑ ጋር አቀበላቸው በዚያንም ጊዜ ሕፃኑ የአንድ ዓመት ልጅ ሲሆን በባሕርይ በህልውና በመለኮት ከወልድ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ የሆነ አብ በግብር በአካል በሰም ልዩ ነው በባሕርይ በህልውና በመለኮት ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ የሆነ ወልድ በግብር በአካል በስም ልዩ ነው በባሕርይ በህልውና በመለኮት በአብ ከወልድ ጋር አንድ የሆነ መንፈስ ቅዱስ በግብር በአካል በስም ልዩ ነው ብሎ ተናገረ።

ከጥቂት ዘመንም በኋላ አባትና እናቱ ኅዳር ሰባት ቀን ሙተው ሕፃኑ ብቻውን ቀረ።

ሕፃኑም ዐሥር ዓመት በሆነው ጊዜ ለጣዖት መስገድን የሚያዝ ከሀዲ መኰንን መጣ ቅዱስ ቡላም በሰማ ጊዜ ወደ መኰንኑ ሒዶ የረከሱ አማልክቶቹን ረገመ መኰንኑም በአካል ታናሽነቱን አይቶ እጅግ አደነቀ በዚያንም ጊዜ በችንካር እንዲቸነክሩት ሥጋውንም እንዲሠነጣጥቁት ቆዳውንም ከዐጥንቱ እንዲገፉ እጆቹንና እግሮቹንም በመጋዝ እንዲቆርጡ ጀርባውንም እንዲገርፉ በሾተሎችና በጦሮች መካከል አድርገው ከመንኰርኵር ውስጥ እንዲጨምሩት ዳግመኛም በመንገድ ላይ እንዲጐትቱት አዘዘ የመላእክት አለቃ ሚካኤልም መጥቶ አዳነው ያለ ጉዳትም ጤነኛ አደረገው።

ከዚህም በኋላ ወደ ሌላ መኰንን ሒዶ እርሱንና የረከሱ ጣዖቶቹን ረገመ መኰንኑም ተቆጥቶ በሚያዝያ ወር ዐሥራ ስምንት ቀን ራሱን በሰይፍ ቆረጠው ቅዱስ ሚካኤልም ከሰማይ ወርዶ ከሙታን ለይቶ አስነሣው ወደ አንድ ገዳምም ወስዶ የምንኲስና ልብስንና አስኬማን በመስቀልም ምልክት አለበሰው። እንዲህም አለው ከቅዱሳን ጻድቃን አንድነት ትሆን ዘንድ እግዚአብሔር አዝዞሃል።

ያን ጊዜም ቅዱስ አባ ቡላ ከደረቅ ተራራ ላይ ወጣ ያለ ማቋረጥም በውስጧ እየተጋደለ ኖረ። የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መከራውንና ስቅለቱን በአሰበ ጊዜ ከረጅም ዕንጨት ላይ በመውጣት ራሱን ወደታች ሁል ጊዜ ይወረውር ነበር።

በአንዲትም ቀን ከዛፍ ላይ በተወረወረ ጊዜ ሰይጣን ሊገድለው ስለ በረታበት ሞተ ያን ጊዜም ክብር ይግባውና መድኃኑታችን ከሞት አነሣውና እንዲህ አለው ከእንግዲህ ስምህ ቡላ አይሁን አቢብ ይባል እንጂ የብዙዎች አባት ትሆናለህና።

እርሱም የክርስቶስን ፍቅር እጅግ ጨመረ ፊቱንም እየጸፋ ሥጋውን በየጥቂቱ እየቆረጠ ጀርባውንም ሰባት መቶ ጊዜ እየገረፈ ኖረ ጌታችንም ይፈውሰው ነበር በየእሑድም ቀን ከቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያም እንደተወለደ በሌሎች ቀኖችም እንደተያዘና ከአይሁድ መከራ እንደ ተቀበለ ሁኖ ይገለጽለት ነበር።

ስለዚህም ሳይበላ ሳይጠጣ አርባ ሁለት ዓመት ኖረ ዳግመኛም ናላው ፈስሶ እስቲአልቅ ዐሥራ ሁለት ወር በራሱ ተተክሎ ኖረ። በአንዲትም ቀን የጌታችንን መከራ በአሰበ ጊዜ ሰይፉን በአንጻሩ ተከለ ከዕንጨት ላይም ወጥቶ በላዩ ወድቆ ሞተ ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያምም ከአእላፍ መላእክት ጋር መጥታ የእኔና የልጄ ወዳጅ ሰላምታ ይድረስህ አለችው ። ከበድኑም ቃል ወጥቶ የሰማይና የምድር ንግሥት እመቤቴ ሰላምታ ይገባሻል አላት እርሷም በከበሩ እጆቿ ዳሥሣ ከሞት አስነሣቸው።

ዕድሜውንም ፈጽሞ ከዚህ ዓለም የሚወጣበት ጊዜ ሲደርስ ክብር ይግባውና ጌታችን ክርስቶስ በእጁ ልዩ የሆኑ አክሊሎችን የሚያበሩ ልብሶችንም ይዞ ተገለጠለት ወዳጄ አቢብ ሆይ በማያልቅ ተድላ ደስታ ደስ አሰኝህ ዘንድ ወደእኔ ና ስምህን ለሚጠራ መታሰቢያህን ለሚያደርግ እኔ ኃጢአቱን አስተሠርይለት ዘንደ በራሴ ማልኩልህ ወይም ለተራቆተ የሚያለብሰውን ለተራበም የሚያጠግበውን ለተጠማ የሚያጠጣውን የገድልህን መጽሐፍም የሚጽፈውን ወይም የሚያነበውንና የሚሰማውን በጸሎትህም የሚታመኑትን ሁሉ እስከ ዐሥር ትውልድ እምራቸዋለሁ ይህንም ብሎ አፉን ሳመው በደረቱም ላይ አድርጎ ወደአየር አወጣው የመላእክትንም ምስጋና በሰማች ጊዜ ነፍሱ ከሥጋው ተለየች ወደ ሰማያዊት ኢየሩሳሌም ገባች።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_አባ_እብሎይ

ዳግመኛም በዚህችም ቀን ደግሞ አክሚም ከሚባል አገር የመላእክት አምሳል የሆነ አባ እብሎይ አረፈ። የዚህም ቅዱስ የአባቱ ስም አሞኒ የእናቱ ስም ሙስያ ነው ሁለቱም በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን የሆኑ በሕጉ ጸንተው የሚኖሩ ድኆችንና መጻተኞችን የሚወዱ የሚረዱ ናቸው።

ነገር ግን ልጅ አልነበራቸውም ሙስያም ዕንጨት የያዘ ብርሃናዊ ሰው በቤቷ ውስጥ ሲተክለውና ወዲያውኑ ለምልሞ አብቦ ሲያፈራ ያ ብርሃናዊው ሰውም ከዚህ ፍሬ የሚበላ ሁሉ ለዘላለም ይኖራል ሲላት እርሷም ከፍሬው ወስዳ ስትበላና በአፏ ውስጥ ጣፋጭ ሲሆንላት በልቧም ፍሬ ይሆንልኝ ይሆን ስትል ራእይን አየች።

ከእንቅልፏም በነቃች ጊዜ ራእይን እንዳየች ለባሏ ነገረችው እርሱም እርሷ እንዳየችው ያለ ማየቱን ነገራት እግዚአብሔርንም አብዝተው አመሰገኑት ትሩፋትንና ተጋድሎን በመጨመር በየሁለት ቀን የሚጾሙ ሆኑ ምግባቸውም እንጀራና ጨው ነው።

ይህን ቅዱስ እብሎይን በፀነሰችው ጊዜ እናቱ በገድል ወንዶችን እስከምታሸንፍ ድረስ በየሌሊቱ ሁሉ አንድ ሽህ ስግደትን ትሰግዳለች ሕፃኑን እስከ ወለደችው ድረስ ዘጠኝ ወር ያህል እንዲህ ስትጋደል ኖረች።

በወለዱትም ጊዜ እብሎይ ብለው ሰየሙት በጐለመሰም ጊዜ የምንኩስናን ልብስ ሊለብስ ወደደ ምክንያትም እስቲያገኝ እንዲህ ኖረ አቢብ የሚባል ወዳጅ ነበረውና እርሱ በሌሊት ወሰደው ከላዕላይ ግብጽ በሚገኙ ገዳማት በአንዱ ገዳም ውስጥ መነኰሰ በገድልም በመጠመድ ታላቅ ተጋድሎን ተጋደለ።
ከጥቂት ወራትም በኋላ በጥቅምት ወር ሃያ አምስት ቀን አባ አቢብ አረፈ ያን ጊዜ አባ እብሎይ አብሎግ ወደሚባል ገዳም ሔደ ወደርሱም ብዙ ሰዎች ተሰበሰቡ እርሱም በበጎ አምልኮ እግዚአብሔርን መፍራትን የሚያስተምራቸው ሆነ።

ቅዱስ አቢብም በአረፈበት ቀን መታሰቢያውን ሲያደርጉ ይህ ቅዱስ አባ አብሎይ ወንድሞች ሆይ በአባ አቢብ ስም ዛሬ ጸሎትን የሚጸልየውን ኃጢአቱን እግዚአብሔር ያስተሰርይለታል በዕረፍትህ መታሰቢያ ቀን የአባ አቢብ ፈጣሪ ሆይ ኃጢአቴን ሁሉ ተውልኝ ብሎ አንዲት ጸሎትን የሚጸልየውን ሁሉ እኔ ኃጡአቱን እተውለታለሁ ሲል ቃል ኪዳን ሰጥቶታልና አላቸው።

በዚያችም ሰዓት ከመነኰሳት አንዱ አረፈ እነርሱም ሊገንዙት በዚያ ቁመው ሳሉ አባ እብሎይ ስለ ተናገረው ቃል ከመነኰሳት አንዱ ተጠራጠረ በዚያንም ጊዜ ያ የሞተው ተነሥቶ ይናገር ዘንድ ጀመረ አባ እብሎይ ስለተናገረው ቃል ለምን ትጠራጠራላችሁ ለአባታችን አቢብ በመታሰቢያው ቀን በዚህ ቃል ኪዳን እግዚአብሔር ሰጥቶናልና አላቸው ። ይህንንም ብሎ ተመልሶ አረፈ መነኰሳቱም አደነቁ ምስጉን እግዚአብሔርንም አመሰገኑት።

ይህ አባ እብሎይም ብዙ ዘመናት ኖረ ልጆቹ መነኰሳትም በዙ ብዙ ገዳማትም ተሠሩለት። የኖረበትም ዘመኑ በታላቁ አባ መቃርስ ዘመን ነው የአባ እብሎይንም የትሩፋቱን ዜና አባ መቃርስ በሰማ ጊዜ እጅግ ደስ ተሰኘበት እርሱን እያጽናና እያረጋጋ መነኰሳት ልጆቹንም እግዚአብሔር የሚወደውን በመሥራት ያጸናቸው ዘንድ መልእክትን ጻፈለት።

ይህንንም በአስቄጥስ ገዳም ሁኖ አባ መቃርስ ሲጽፍ አባ እብሎይ በላዕላይ ግብጽ ሳለ በመንፈስ ቅዱስ አውቆ በዙሪያው ያሉትን መነኰሳት እንዲህ አላቸው። እነሆ ማጽናናትን የተመላች መልእክትን አባ መቃርስ ጻፈልን። ከዚህም በኋላ ከአባ መቃርስ ዘንድ የተላኩትን መነኰሳት ሁሉ ወጥተው በደስታ ተቀብለው አስገቧቸው መልእክቱንም በመነኮሳቱ ሁሉ ፊት አነበቡ በታላቅ ደስታም ደስ አላቸው።

ይህም አባ እብሎይ ወደ አባ አሞንዮስ የሔደ ከእርሱ ዘንድም የምትኖረውን ስሟ የዋሂት የተባለችውን የተቀደሰች ሴት ያየ ነው። ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ከዚህ ዓለም ድካም ሊአሳርፈው ወዶ በየካቲት ወር በአምስተኛው ቀን አረፈ እኛ ግን የአባ እብሎይን ዜና ከወዳጁ ከአባ አቢብ ጋር ጻፍን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ዮልዮስ_ሰማዕት

በዚህችም ቀን ዳግመኛ አቅፋሐስ ከሚባል አገር ሰማዕት ለሆነ ለቅዱስ ዮልዮስ ቤተ ክርስቲያኑ የከበረችበት ነው።

ይህም ቅዱስ ዮልዮስ በሀገረ ጥዋ በሰማዕትነት በአረፈ ጊዜ በገድሉ እንደተጻፈ ዲዮቅልጥያኖስ ከጠፋ በኋላ ጻድቅ ሰው ቈስጠንጢኖስ ሳይጠመቅ ነገሠላቸው በጥቂት ወራትም የክርስትና ጥምቀትን ተጠመቀ የቤተ ክርስቲያንም ሥልጣን ከፍ ከፍ አለ ከሀድያን ነገሥታት ለገደሏቸው ንጹሐን ሰማዕታት በስማቸው አብያተ ክርስቲያናት ታነፁ።

ስለ ቅዱሳን ሰማዕታትም ስለ ሥጋቸው እንዲአስብ ገንዞ በመሸከም ወደ አገራቸው እንዲአደርሳቸው ከአገልጋዮቹም ጋር ገድላቸውን እንዲጽፍ እግዚአብሔር እንደአቆመውና እንደጠበቀው ከዚህም እርሱ ራሱ በሰማዕትነት እንዴት እንደ ሞተ የቅዱስ ዮልዮስን ዜና ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ በሰማ ጊዜ ስለበጎ ተጋድሎው ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ቅዱስ ዮልዮስን አመሰገነው ።

ስለዚህም ለቅዱስ ዮልዮስ ያማረች ቤተ ክርስቲያን በግብጽ አገር ሠርተው ሥጋውን በውስጧ ያኖሩ ዘንድ ንጉሡ ወደ ግብጽ አገር ብዙ ገንዘብ ላከ በዚያንም ጊዜ ንጉሡ እንዳዘዘ አነፁለት ። የቅዱስ ዮልዮስንም ሥጋ አፍልሰው በውስጧ አኖሩት ሊቀ ጳጳሳት አባ እለእስክንድሮስም ከኤጲስቆጶሳቱ ጋር አከበራት እንደዛሬዪቱም ቀን በዓል አከበረባት ከሥጋውም ታላላቅ የሆኑ ድንቆች ተአምራት ተገለጡ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አባ_ሕጻን_ሞዐ_ዘደብረ_ሊባኖስ

በዚህችም ቀን የደብረ ሊባኖሱ አባ ሕፃን ሞዐ ቃልኪዳን የተቀበሉበት ነው። በአባታቸው አርከሌድስ እናታቸው ትቤ ጽዮን ይባላሉ፡፡ የተወለዱት ጥር 25 ነው፡፡ አቡነ ሕፃን ሞዐ እና ከእነ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ጋር የሥጋ ዝምድና አላቸው፡፡ ይኸውም አባታቸው አርከሌድስና ጸጋ ዘአብ ወንድማማቾቸ ናቸው፡፡ አርከሌድስና ጸጋ ዘአብ ሌሎች ሌሎች አራት ወንድሞች አሏቸው፡፡

እነርሱም እንድርያስ፣ ዘርዐ አብርሃም፣ ቀሲስ ዮናስ እና ቀሲስ ዮሐንስ ናቸው፡፡ አርከሌድስ ሕፃን ሞዐን ይወልዳል፣ ጸጋ ዘአብ ተክለ ሃይማኖትን ይወልዳል፣ እንድርያስ ሳሙኤል ዘወገግን፣ ዘርዐ አብርሃም ታላቁ አኖሬዎዮስን፣ ቀሲስ ዮናስ ገላውዲዮስንና የፈጠጋሩን ማትያስን፣ እና ቀሲስ ዮሐንስ ዜናማርቆስን ይወልዳሉ፡፡ እነዚህ የከበሩ ቅዱሳን አባቶቻችን በእናታቸውም ወገን ቢሆን እንዲሁ በዝምድና የተቆራኙ ናቸው፡፡ አቡነ ሕፃን ሞዐ በሌላኛው ስማቸው ሕፃን ዘደብረ በግዕ ተብለውም ይጠራሉ፡፡ ይኸውም የደብረ በግዕን ገዳም የመሠረቱት እርሳቸው ስለሆኑ ነው፡፡

ከ47ቱ የሀገራችን ቀደምት ቅዱሳን ውስጥ አንዱ ናቸው፡፡ በመንዝና በተጉለት የሚገኙ ታላላቅ ገዳማትን አብዛኞቹን የመሠረቷቸው አቡነ ሕፃን ሞዐ ናቸው፡፡ ጻድቁ በክፉዎች ወሬና ሴራ ምክንያት ከበሬ ጋር ተጠምደው ሰማዕትነት የተቀበሉ አባት ናቸው፡፡ ከበሬ ጋር ሲታረሱ ውለው በእጅጉ ከደከማቸው በኋላ በኃይል የተነፈሱባት ምድሪቱ ዛሬም ድረስ ልክ እንደሰው የሚሞቅ ትንፋሽ ታወጣለች፡፡ ያም በጻድቁ እስትንፋስ አምሳል ከመሬት ውስጥ የሚወጣው እስትንፋስ ለአስም በሽታ መድኃኒት ሆኖ ብዙዎችን እየፈወ ነው፡፡

ገዳማቸው ከደብረ ብርሃን ከተማ በእግር የ2 ሰዓት መንገድ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ይኸውም ከወንይዬ ተክለ ሃይማኖት ገዳም አጠገብ ነው፡፡ ጻድቁ ጥር 25 ቀን ልደታቸው፣ ጥቅምት 25 ቃል ኪዳን የተቀበሉበት ዕለት ሲሆን ሐምሌ 25 ደግሞ ዕረፍታቸው ነው፡፡

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን ።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ጥቅምት እና #ከገደላት_አንደበት)
#ጥቅምት_25

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ጥቅምት ሃያ አምስት በዚህች ቀን #ቅዱስ_አቡነ_አቢብ (አባ ቡላ) አረፈ፣ የመላእክት አምሳል የሆነ #አባ_እብሎይ አረፈ፣ የከበረ #ቅዱስ_ዮልዮስ_ሰማዕት ቤተ ክርስቲያኑ የከበረችበት ነው፣ የደብረ ሊባኖሱ #አባ_ሕፃን_ሞዐ ቃልኪዳን የተቀበሉበት ነው።

††† እንኩዋን ለአበው ሰማዕታት #ቅዱስ_ዮልዮስና_ቅዱስ_ኮቶሎስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ †††

†††

††† #ቅዱስ_ዮልዮስ_ሰማዕት †††

=>ከሁሉ አስቀደሞ ስለ ሰማዕታት ዜና ሲሰማ ለዚህ ቅዱስ አንክሮ (አድናቆት): ክብርና የጸጋ ውዳሴ ይገባዋል:: ምክንያቱም ገድለ ሰማዕታትን የጻፈልን እርሱ ነውና:: ነገር ግን መጻፍ ሲባል: ነገሮች እንዲህ እንደ እኛው ዘመን ቀላል እንዳይመስሏችሁ:: ቅዱሱ ዜና ሰማዕታትን ለማዘጋጀት ሃብቱን: ንብረቱን: ቤተሰቦቹንና ሕይወቱንም ሰውቷል::

+ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:- በመጨረሻው ዘመነ ሰማዕታት (በ3ኛው መቶ ክ/ዘ) ዓለም በደመ ሰማዕታት ስትሞላ የሰማዕታቱን ዜና የሚጽፍ: ሥጋቸውን እንኩዋ የሚቀብር አልተገኘም:: "ወኃጥኡ ዘይቀብሮሙ-የሚቀብራቸውም አጡ" እንዳለ ቅዱስ ዳዊት:: (መዝ. 78:3)

+#እግዚአብሔር ግን ስለ ወዳጆቹ #ሰማዕታት ይህንን ቅዱስ አስነሳ:: ቅዱስ ዮልዮስ በዘመኑ ደግ ክርስቲያን: ትዳርና ልጆች ያሉት: እጅግ ባለ ጸጋና 300 አገልጋዮች ያሉት: ምጽዋትንም የሚወድ ሰው ነበር::

+በወቅቱ ክርስቲያኖች በየመንገዱ ወድቀው መታየታቸው ዕረፍት ቢነሳው ከቤተሰቦቹ ጋር መክሮ መልካም ግን ደግሞ ከባድ ውሳኔን አስተላለፈ:: ውሳኔውንም ታጥቆ ይተገብረው ጀመር:: ነገሩ እንዲህ ነው:-

1.የታሠሩ ክርስቲያኖችን ቁስላቸውን እያጠበ ያጐርሳቸዋል::

2.ቀን ቀን አገልጋዮቹን አስከትሎ የሰማዕታቱን ሥጋ እየሰበሰበ: ሽቱ ቀብቶ ይገንዛቸዋል:: አንዳንዶቹን ወደ ቤተሰቦቻቸው ሲልክ ሌሎቹን ራሱ ይቀብራቸዋል::

3.ሌሊት ሌሊት በ300ው አገልጋዮቹ እየታገዘ የሰማዕታቱን ዜና: ቀለም በጥብጦ: ብራና ዳምጦ: ብዕር ቀርጾ: ሲጽፍና ሲጠርዝ ያድራል:: በተረፈችው ጥቂት ሰዓት ደግሞ ይጸልያል:: ቅዱስ ዮልዮስ በእውነት ድንቅ ሰው ነው:: በምን እንመስለዋለን! እርሱን የፈጠረውን ጌታ "ዕጹብ ዕጹብ" ብለን ከማድነቅ በቀር::

+ሰማዕታቱም ስለ ደግነቱ የሚመልሱለት ቢያጡ ዝም ብለው ይመርቁት ነበር:: ምርቃናቸውም "ለሰማዕትነት ያብቃህ" የሚል ነው:: በእርግጥ ይህ ለዘመኑ ሰዎች ምርቃት ላይመስለን ይችል ይሆናል:: እርሱ ግን ይህንን ሲሰማ ሐሴትን ያደርግ: እጅም ይነሳቸው ነበር:: በዘመኑ ትልቁ ምርቃት ይሔው ነበርና::

+እንዲህ: እንዲህ እያለ ዘመነ ሰማዕታት ሊፈጸም ወራት ቀሩት:: በዚህ ጊዜ ለሰማዕትነት ከመነሳሳቱ የተነሳ ጌታችንን ተማጸነ:: ጌታችንም ተገልጾለት "ሒድና ሰማዕት ሁን: ፈቅጄልሃለሁ" አለው:: እርሱም ደስ እያለው ዜና ሰማዕታቱን ለሁነኛ ሰው ሰጥቶ: ሃብት ንብረቱን ለነዳያን አካፈለ::

+ቀጥሎም ቤተሰቦቹንና አገልጋዮቹን ጨምሮ 500 ሰዎችን አስከትሎ ወደ ሃገረ #ገምኑዲ ሔደ:: በመኮንኑ ፊት የክርስቶስን አምላክነት ቢመሰክር ፈጽመው አሰቃዩት:: በማግስቱም ወታደሮቹ ለጣዖት ካልሰገድክ ሲሉት "ቆዩማ ላሳያችሁ" ብሎ በጸሎቱ ጣዖታትን ከነ ካህናቶቻቸው ምድር ተከፍታ እንድትውጣቸው አደረገ::

+በዚህ ተአምር የደነገጠው መኮንኑ #አርማንዮስ ከነ ሠራዊቱ በክርስቶስ አመነ:: ክብሩንም ትቶ ቅዱስ ዮልዮስን ተከተለው:: ቀጥሎም ጉዞ ወደ ሃገረ #አትሪብ ሆነ:: በዚያም ብዙ መከራን ተቀብሎ ጣዖታቱን አወደማቸው::

+እዚህም የአትሪብ መኮንን ደንግጦ ከነ ሠራዊቱ አምኖ ቅዱሱን ተከተለው:: በመጨረሻ ግን ሰማዕትነት እንዳይቀርበት ስለሰጋ ቅዱስ ዮልዮስ ተአምራት ማድረጉን ተወ:: በፍጻሜውም የ3ኛው ሃገር መኮንን ቅዱስ ዮልዮስ ከቤተሰቡና ከ1,500 ያህል ተከታዮቹ ጋር: 2ቱን የሃገረ ገዥዎች ጨምሮ አንገታቸውን አሰይፏቸዋል:: ቅዱሱም የክብር ክብርን አግኝቷል::

+"+ #ቅዱስ_ኮቶሎስ_ሰማዕት +"+

=>ይህ ቅዱስ በቀደመ ሕይወቱ አረማዊ ሲሆን የክርስቶስን ስም ሰምቶ አያውቅም:: በ4ኛው መቶ ክ/ዘ በፋርስ (አሁን #ኢራን) ሳቦር የሚባል ክፉ ንጉሥ ነግሦ ክርስቲያኖችን ያሰቃይ ነበር:: እርሱ የሚያመልከው ፀሐይና እሳት ነውና::

+የዚህ ንጉሥ ልጆቹ 'ልዑል ኮቶሎስና ልዕልት አክሱ' ይባላሉ:: በቤተ መንግስት ውስጥ ስላደጉ የሚያመልኩት የአባታቸውን ጣዖት ነበር:: በፋርስ መንግስት ውስጥ ከነበሩ የጦር አለቀቆችና ሃገረ ገዥዎች አንዱ #ጣጦስ ይባላል::

+ይህ ሰው እጅግ ብሩህ የሆነ ክርስቲያን ነበርና ዘወትር ከንጹሕ አገልግሎቱ ተሰነካክሎ አያውቅም:: ትንሽ ቆይቶ ግን ክርስቲያን መሆኑን ሳቦር ስለ ሰማ ሠራዊት ይልክበታል:: "ሒዱና ጣጦስን መርምሩት: ክርስቲያን ከሆነና አማልክትን እንቢ ካለ በእሳት አቃጥላችሁ ግደሉት" አላቸው::

+በአጋጣሚ የንጉሡ ልጅ ኮቶሎስና ጣጦስ በጣም የሚዋደዱ ባልንጀሮች ነበሩና ሊያስጥለው ወዶ ሔደ:: ኮቶሎስ ቅዱስ ጣጦስ ታስሮ በእሳት ሊቃጠል ሲል ደረሰ:: ወዲያውም ወደ እሳቱ ውስጥ ጨመሩት:: እነርሱ ፈጥኖ አመድ ይሆናል ብለው ጠብቀው ነበር:: ግን አልሆነም::

+ቅዱስ ጣጦስ በእሳት መካከል ቁሞ አላቃጠለውም:: እንዲያውም በትእምርተ መስቀል ቢያማትብበት እሳቱ ብትንትን ብሎ ጠፋ:: ኮቶሎስ ተገርሞ ቅዱሱን ባልንጀራውን "ወንድሜ! ሥራይ (መተት) መቼ ተማርክ ደግሞ?" ሲል ጠየቀው::

+እርሱ እስከዚያች ሰዓት ኃይለ እግዚአብሔርን አልተረዳምና:: ቅዱስ ጣጦስ ግን "ወንድሜ! አትሳሳት: እኛ ክርስቲያኖች መተትን አናውቅም:: በፈጣሪያችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ግን ሁሉን ማድረግ እንችላለን" ሲል መለሰለት::

+ኮቶሎስ ተገርሞ "አሁን እኔ በክርስቶስ ባምን እንዳንተ ማድረግ እችላለሁ?" ቢለው ቅዱሱ "አዎ ትችላለህ!" አለው:: ወዲያውም "እሳት አንድዱልኝ" አለና እጣቱን በመስቀል ምልክት አስተካክሎ ወደ እሳቱ ቢያመለክት እሳቱ 12 ክንድ ርቆ ተበትኖ ጠፋ::

+በዚያችው ሰዓት ቅዱስ ኮቶሎሰ በክርስቶስ አመነ:: ክብሩንና የአባቱን ቤተ መንግስት አቃሎ ወደ እስር ቤት ገባ:: አባቱ ሳቦር ይህን ሲሰማ ተቆጥቶ "ምከሪው" ብሎ እህቱን አክሱን ላከበት::

+ቅዱስ ኮቶሎስ ልትመክረው የመጣችውን እህቱን አሳምኖ የክርስቶስ ወታደር አደረጋት:: አስቀድሞ #ቅዱስ_ጣጦስ: አስከትሎም #ቅድስት_አክሱ ተገደሉ:: በፍጻሜው ግን ቅዱስ ኮቶሎስን እግሩን አስረው በየመንገዱ ጐተቱት:: በጐዳናም አካሉ እየተቆራረጠ አለቀ:: ክርስቲያኖች በድብቅ መጥተው የ3ቱንም ሥጋ በክብር አኑረዋል::

=>አምላከ ቅዱሳን ሰማዕታትን ባጸናበት ጽናት ሁላችንም ያጽናን:: በረከታቸውንም ያብዛልን::

=>መስከረም 22 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ዮልዮስ ሰማዕት
2."1,500" ሰማዕታት (የቅዱስ ዮልዮስ ማሕበር)
3.ቅዱስ ኮቶሎስ ሰማዕት
4.ቅድስት አክሱ ሰማዕት
5.ቅዱስ ጣጦስ ሰማዕት
6.ቅዱስ ባላን ሰማዕት

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዑራኤል ሊቀ መላእክት
2.ቅዱስ ሉቃስ ወንጌላዊ
3.ቅዱስ ደቅስዮስ (የእመቤታችን ወዳጅ)
4.አባ እንጦንስ አበ መነኮሳት
5.አባ ዻውሊ የዋህ

=>+"+ ሰውን ከአባቱ: ሴት ልጅንም ከእናቷ . . . እለያይ ዘንድ መጥቻለሁና:: ለሰውም ቤተሰዎቹ ጠላቶች ይሆኑበታል:: ከእኔ ይልቅ አባቱን ወይም እናቱን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም:: ከእኔ ይልቅም ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም:: መስቀሉን የማይዝ በሁዋላየም የማይከተለኝ ለእኔ ሊሆን አይገባውም:: +"+ (ማቴ. 10:35)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
@petroswepawulos
@petroswepawulos
@petroswepawulos