መዝገበ ቅዱሳን
20.7K subscribers
1.92K photos
9 videos
6 files
24 links
የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው! መ/ሳ 1÷7
Bewust mesimer lemanegager
@Yesadkusitota
የሰማነውን እንናገራለን
ያየነውን እንመሰክራለን
Download Telegram
=>+*"*+ እንኩዋን ከዘመነ #ቅዱስ_ሉቃስ ወደ ዘመነ #ቅዱስ_ዮሐንስ በሰላም አሸጋገራችሁ:: ለቅዱሳኑም በዓል እንኩዋን አደረሳችሁ +*"*+

=>#በእግዚአብሔር ቸርነት #ሉቃስ አለፈ: #ዮሐንስ ተተካ:: ይህች ዕለት እጅግ ክብርትና ልዕልት ናት::
¤አዲስ ዓመት:
¤አዲስ ሕይወት:
¤አዲስ ተስፋ:
¤አዲስ በረከትን እናገኝ ዘንድ እርሱ በቸርነቱ ከዚህች ዕለት አድርሶናልና:: ለእርሱ ምን ይከፈለዋል? "ተመስገን!" ከማለት በቀር::

¤ይህቺ ዕለት ብዙ ስያሜዎች ቢኖሯትም እነዚህን እንጠቅሳለን:-

1."ቅዱስ ዮሐንስ" (#መጥምቁ_ዮሐንስ ርዕሰ ቅዱሳን ስለሆነ በእርሱ ተሰይማለች)

2."#ርዕሰ_ዐውደ_ዓመት" (የዐውደ ዓመቶች ራስ)

3."#እንቁጣጣሽ" (ንግስተ ሳባንና ንጉሥ ሰሎሞንን አንድ ያደረገች ዕለት)

4."#ዕለተ_ማዕዶት" (መሸጋገሪያ)

5."#ጥንተ_ዕለታት" (የዕለታት መጀመሪያ)

6."#ዕለተ_ብርሃን" (የአዲሱን ዓመት ብርሃን የምናይባት)

¤ከምንም በላይ ግን ይህች ዕለት የአዝማነ መንግስተ ሰማያት ምሳሌ ናት:: አሮጌው ዓመት የዚህ ዓለም ምሳሌ ሲሆን አዲሱ ደግሞ የሰማያዊው ሕይወት ምሳሌ ነው:: #ዻጉሜን ደግሞ የዘመነ ምጽዓት ምሳሌ ናት:: በእነዚህና በሌሎች ምክንያቶች ዕለቷ ክብርት ናት::

<< ምንተ ንግበር / ምን እናድርግ? >>

=>እግዚአብሔር ከእኛ ብዙና ከባድ ነገሮችን አይፈልግም:: ደግሞም አይጠብቅም:: እርሱ ቸር ነውና በአዲሱ ዓመት ከእኛ:-

1.እንፋቀር ዘንድ
2.ንስሃ እንገባ ዘንድ እና
3.የቀናውን ጐዳና እንድንመርጥ ብቻ ይፈልጋል::

¤በተሠማራንበት ሥራ ሁሉ: ባለንበትም ሃገር ሁሉ እግዚአብሔርን እናክብር: ድንግል እመቤታችንን እናፍቅር: ቅዱሳንን እናስብ ዘንድ ልንተጋ ይገባል::
¤ለዚህም ደግሞ የሥላሴ ቸርነት: የእመ ብርሃን አማላጅነት: የቅዱሳኑ ሁሉ ጸጋ በረከት ይደርብን::

<< ዘመኑን የፍቅር: የሰላምና የበረከት ያድርግልን:: >>

+*" #ቅዱስ_በርተሎሜዎስ_ሐዋርያ "*+

=>#ወንጌል ላይ እንደ ተጠቀሰው ከ12ቱ ቅዱሳን #ሐዋርያት አንዱ ቅዱስ በርተሎሜዎስ ነው:: (ማቴ. 10:3) ነገር ግን ዜና ሕይወቱ በስፋት ሲተረክ አንሰማም:: ቅዱሱ ሐዋርያ እንደ ሌሎቹ ወንድሞቹ ዓለምን በወንጌል ትምሕርት አብርቷል:: በትውፊት ትምሕርት መሠረት '#በርተሎሜዎስ' የሚለውን ስም ያወጣለት ጌታችን ሲሆን ትርጉሙም 'ተክሎችን የሚያጠጣ' ማለት ነው::

¤ከሐዋርያትም ጌታ አስቀድሞ የስም ቅያሪ ያደረገለት ለእርሱ እንደ ሆነ ይታመናል:: በርተሎሜዎስ የግብርና ሥራውን ትቶ: የጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ደቀ መዝሙር ሆኖ: ከዋለበት እየዋለ: ካደረበትም እያደረ ምሥጢረ ወንጌልን ተምሯል::

¤ጸጋ መንፈስ ቅዱስን ከተቀበለ በሁዋላም ከሐዋርያት ጋር ዓለምን በዕጣ ተካፍሏል:: ሃገረ ስብከቱም '#እልዋህ' እና '#አርማንያ' ናቸው:: የአርማንያ መንበርም የእርሱ ነው:: ቅዱሱ ገድሉ እንደሚለው አሕዛብን በስብከቱና በሚያስደነግጡ ተአምራቱ አሳምኗል::

¤ከቅዱስ #ዼጥሮስ: ከቅዱስ #እንድርያስ: #ከክርስቶፎሮስና ከሌሎቹም ሰባክያን ጋር ዓለምን ዙሯል:: ሙታንን አስነስቶ: ድውያንን ፈውሶ: አጋንንትን አውጥቶ: ብዙወችን ወደ ሕይወት መልሷል:: የደረቁ እንጨቶችም በእጁ ላይ እንዳሉ ለምልመው: አብበው ያፈሩ ነበር::

¤ቅዱስ በርተሎሜዎስ እያስተማረ ወደ ኢትዮዽያም ደርሶ እንደ ነበር ይነገራል:: በመጨረሻም 'ለሚስቶቻችን ንጽሕናን አስተምረሃል' በሚል ተከሶ: ንጉሥ አግሪዻ በሰቅ (ጸጉር) ጠቅልሎ: አሸዋ ሞልቶ: ባሕር ውስጥ ጥሎታል:: በዚያውም ዐርፏል::

+*" #ቅዱስ_ሚልኪ_ቁልዝማዊ "*+

=>ይህቺ ሃገረ ቁልዝም ግብጽ ውስጥ የምትገኝ ስትሆን ብዙ ቅዱሳንን አፍርታለች:: በተለይ የአባ እንጦንስና የልጆቹ ማረፊያ ከመሆኗ ባሻገር ቅዱስ አባ ሚልኪም ወጥቶባታል:: ቅዱሱ የዘመነ ጻድቃን ፍሬ: የስለት ልጅም ነው:: ጥሩ ክርስቲያኖች የነበሩት ወላጆቹ እጅግ ባለጸጐችም ነበሩ::

¤በስለት መንታ ልጆችን (ሚልኪና ስፍናን) ወልደው: በሥርዓት አሳድገዋል:: ቅዱስ ሚልኪ በሕጻንነት ወራቱ ስቆና ከሕጻናት ጋር ተጫውቶ አያውቅም:: ብሉያትና ሐዲሳትን ጠንቆቆ ካጠና በሁዋላ እድሜው 19 ሲደርስ ወላጆቹ "እንዳርህ" አሉት:: የልቡን እያወቀ "እሺ" አላቸው::

¤ቀጥሎም "ባልንጀሮቼን ልጋብዝበት" ብሎ: 1,000 ወቄት ወርቅ ተቀብሎ: በፈረስ ተቀምጦ ሔደ:: መንገድ ላይ መቶውን ለተከተሉት: 9 መቶውን ወቄት ለነዳያን: ፈረሱን ደግሞ ለአንድ ደሃ ሰጥቶ: ጡር (ጢር) ወደ ሚባል በርሃ ገሰገሰ::

¤መጥፋቱ በቤተሰብ ሲሰማ ታላቅ ሐዘንና ለቅሶ ተደረገ:: እናቱም ዐይኗ ተሰወረ:: እርሱ ግን #አባ_አውጊን ከሚባል ባሕታዊ ሒዶ ደቀ መዝሙሩ ሆነ:: ለ3 ዓመታትም ተፈትኖ መነኮሰ::

¤ከዚያም በጠባቡ ጐዳና ገብቶ በጾም: በጸሎት: በትሩፋት ከፍ ከፍ አለ:: ከቅድስናው ብዛት የተነሳ አጋንንት ገና ከርቀት ሲያዩት ይሸሹት ነበር:: የነካቸውም ሁሉ ይፈወሱለት ነበር:: በእርሱ ጸሎትም በፋርስና በሮም ሰላም ሆነ::

¤አንድ ቀን የዳዊትን መዝሙር እየዘመረ ሲሔድ የአገረ ገዥውን ልጅ ዘንዶ በልቶት ሲለቀስ ደረሰ:: ጸሎት አድርጐ ዘንዶውን ጠራውና "እንደ ነበረ አድርገህ ትፋው" ሲል አዘዘው:: ዘንዶውም ተፋው: ሰይጣኑም ሸሽቶ አመለጠ::

¤ሃገረ ገዥው ደስ ቢለው 300 ቤቶች ያሉት ገዳም ለማር #ቅዱስ_ሚልኪ አነጸለት:: በዚያም 300 መነኮሳት ተሰብስበው ትልቅ ገዳም ሆነ:: #ማር_ሚልኪ ሁሉን ካሰናዳ በሁዋላ "ከዚህ አልወጣም" ብሎ በዓቱን ዘጋ:: ሰይጣን ግን "አስወጣሃለሁ" ብሎ ፎክሮ ሒዶ በንጉሡ ልጅ አደረባትና አሳበዳት::

¤"ከሚልኪ በቀር የሚያሰወጣኝ የለም" አለ:: ንጉሡ ወታደሮቹን ጠርቶ "ሒዳችሁ: አባ ሚልኪን ይዛችሁ ብትመጡ ሽልማት: ካልሆነ ግን ሞት ይጠብቃችሁአል" አላቸው:: እነርሱም በጭንቅ አግኝተው "እንሒድ" አሉት:: "በሮም ከተማ በር ላይ እንገናኝ" አላቸው::

¤ልክ በዓመቱ እነርሱ ሮም ሲደርሱ ማር ሚልኪ ደመና ጠቅሶ ከተፍ አለ:: ልጅቱንም አቅርቦ ሰይጣንን "እየታየህ ውጣ" አለው:: ወደል ጐረምሳ ሆኖ ወጣ:: ወስዶም አሰረው:: ከቀናት በሁዋላ ሕዝቡና ንጉሡ እያዩ ማር ሚልኪ ደመና ላይ ተቀምጦ: ሰይጣኑን የድንጋይ ገንዳ አሸክሞ እየነዳ ወሰደው::

¤ሕዝቡም ደስ ብሏቸው በታላቅ ዝማሬና እልልታ ሸኙት:: ሰይጣኑንም ለዘለዓለም አሰረው:: ቅዱስ ሚልኪ በገዳሙ ለዓመታት ከተጋደለ በሁዋላ በዚህች ቀን ቅዱሳን #አባ_እንጦንስ: #መቃርስ: #ሲኖዳ እና ሌሎችም መጥተው: በክብር ተቀብለውት ዐርፏል:: አበው "#ትሩፈ_ምግባር" ይሉታል::

+"+ #ቅዱስ_ራጉኤል_ሊቀ_መላእክት +"+

=>ከዘጠኙ ሊቃነ መላእክት አንዱ ሲሆን በብርሃናት ላይ ተሹሟል:: ለሃገራችን ልዩ ፍቅር ያለው መልአኩ ከሔኖክ ጀምሮ የብዙ ቅዱሳን ረዳት ነው:: ዛሬ በዓለ ሲመቱ ነው::

+"+ #ቅዱስ_ኢዮብ_ጻድቅ +"+

=>ታላቁ ጻድቅ: የትእግስትም አባቷ ቅዱስ ኢዮብ በጭንቅ ደዌ ለብዙ ዘመናት በመከራ ከኖረ በሁዋላ በዚህች ቀን በፈሳሽ ውሃ (በዮርዳኖስ) ታጥቦ ሰውነቱ ታድሷል:: ክብርም ተመልሶለታል:: በፈሳሽ ውሃ የምንጠመቅበት አንዱ ምክንያትም ይሔው ነው::

=>የበርተሎሜዎስ አምላክ ፍቅሩን:
¤የሚልኪ አምላክ ትሩፋቱን:
¤የራጉኤል አምላክ ረድኤቱን:
¤የኢዮብ አምላክ ትእግስቱን ያሳድርብን::

=>መስከረም 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ርዕሰ ዓውደ ዓመት
2.ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ
3.ቅዱስ /ማር/ ሚ