መዝገበ ቅዱሳን
20.7K subscribers
1.92K photos
9 videos
6 files
24 links
የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው! መ/ሳ 1÷7
Bewust mesimer lemanegager
@Yesadkusitota
የሰማነውን እንናገራለን
ያየነውን እንመሰክራለን
Download Telegram
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

✞✞✞ እንኩዋን ለሐዋርያው "ቅዱስ እንድርያስ" እና "ለቅዱሳኑ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳቸሁ ✞✞✞

=>መሐሪ #እግዚአብሔር ኃጢአታችሁ በዛ : ሰውነታችሁ ከፋ ሳይል በአባታዊ ርሕራሔው ጠብቆ ይሔው ወርኀ ሐምሌን በሰላም አስፈጸመን:: አይመስለንም እንጂ በእነዚህ 30 ቀናት ሚሊየኖች አንቀላፍተዋል:: ሚሊየኖች በደዌ ዳኝነት ተይዘዋል:: በርካቶቹም ከሃይማኖታቸው ወጥተዋል::

+ታዲያ እኛ ይህ ሁሉ ያልደረሰብን በጐ ስለሆንን አይደለም:: ይልቁኑ ቸርነቱ በእኛ ላይ ስለበዛ ብቻ ነው እንጂ:: አሁንም በሰላም ከአዲሱ ዘመን እንዲያደርሰን ልንማጸነው ይገባል::

=>በዚህች ዕለት ደግሞ እነዚህን ቅዱሳን እናከብራለን:-

+*" ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ "*+

=>ቅዱሱ ሐዋርያ ተወልዶ ያደገው #በቤተ_ሳይዳ አካባቢ ሲሆን የሊቀ ሐዋርያት #ቅዱስ_ዼጥሮስ ትንሽ ወንድም ነው:: አባቱም #ዮና ይባላል:: ገና ከልጅነቱ ጀምሮ አሣ ማጥመድን ከትልቅ ወንድሙ ተምሯል:: እድሜው ከፍ ባለ ጊዜ ኦሪትን ተምሮ የመጥምቁ #ቅዱስ_ዮሐንስ ደቀ መዝሙር ሆኗል::

+ከእርሱም እያገለገለ ለ6 ወራት ተምሯል:: በወቅቱ ከወንጌላዊው (ወልደ ዘብዴዎስ) #ዮሐንስ ጋር ቅርብ ባልንጀራም ነበር:: ጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ በተጠመቀ ጊዜ ያን ድንቅ #ምሥጢረ_ሥላሴ ከተመለከቱትም አንዱ ነው::

+ጌታ ከጾም (ከገዳመ ቆረንቶስ) በተመለሰ ጊዜ እንድርያስ #መንፈስ_ቅዱስ አነሳስቶት ተከትሎታል:: መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ "ነዋ በግዑ ለእግዚአብሔር ዘያዐትት ኃጢአተ ዓለም - የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ እነሆ" ማለቱን ሰምቶ ቅዱስ እንድርያስ ጌታን ተከተለ::

+በዚህም የመጀመሪያው የክርስቶስ ደቀ መዝሙር ለመባል በቃ:: (ዮሐ. 1:47) ሊቁ #ማር_ገላውዴዎስም እመቤታችንን ሲያመሰግናት
"ለሐዋርያ #እንድርያስ ቀዳማዊ ማርያም ሃይማኖቱ::
ለመጀመሪያው ሐዋርያ ለእንድርያስ ሃይማኖቱ ማርያም አንቺ ነሽ::" ብሏል:: (#መልክዐ_ስዕል)

+ቅዱሱ ሐዋርያ ስሉጥ (ፈጣን) አገልጋይ እንደ ነበርም ወንጌል ይነግረናል:: (ዮሐ. 6:5) ለ3 ዓመታት ከ3 ወት ከጌታ እግር ሥር ተምሮ : በበዓለ ሃምሳ መንፈስ ቅዱስን ተቀበሎ : ምን ሃገረ ስብከቱ #ልዳ ብትሆን ብዙ አሕጉረ ዓለምን ሰብኩዋል::

+ይህች ቀን ሐዋርያው ከጌታ ጋር በመርከብ ውስጥ የተነጋገረባትና ቅዱስ ማትያስን ሰውን ከሚበሉ ሰዎች እጅ ያዳነባት ናት:: ቅዱስ እንድርያስ 30 ቀናት የሚፈጅ የባሕር ላይ ጉዞ ለማድረግ ከአርድእቱ ጋር ወደ ወደብ ቢሔድም መርከበኞች ሁሉ አናሳፍርም በማለታቸው የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወጣት መርከበኛ መስሎ ሐዋርያውንና አርድእቱን የሠላሳውን ቀን መንገድ በሰዓታት ልዩነት እንዲጨርሱ አድርጉዋል::

+ቅዱስ እንድርያስም ፍጡር (እንዲሁ ሰው) መስሎት ለጌታችን ስለ ጌታችን ሰብኮለታል:: መርቆታልም:: መርከበኛው ጌታችን መሆኑን ሲያውቅም ደንግጦ አልቅሷል::

"ሶበ አእመረ ኪያሁ ወጠየቀ አምሳሎ::
ዘተናገርኩ በድፍረት ምስሌከ ኩሎ::
ሥረይ ሊተ ጌጋይየ ወኅድግ ይቤሎ::" እንዲል::

+"ማረኝ?" ብሎታል:: ጌታችንም "አይዞህ እኔ ካንተ ጋር ነኝ" ብሎታል:: ቅዱሱ ሐዋርያ ለወንጌል አገልግሎት ተግቶ ያረፈው ታሕሳስ 4 ቀን ነው::

+*" ቅዱስ ዻውሎስ መናኒ "*+

=>ይህ ቅዱስ መላ ሕይወቱ ድንቅ ነው:: በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበረ ሲሆን የተባረከች ሚስት እና 2 ቡሩካን ልጆች የነበሩት አባት ነው:: #ቅዱስ_ዻውሎስ የነዳያን አባት : እጅግ ባለ ጸጋ : ቤተሰቡን የቀደሰና ባለ ሞገስ ሰውም ነው::

+ታዲያ ምጽዋት ወዳጅ ነውና ሲመጸውት : ሲመጸውት ሃብቱ አለቀ:: አሁንም መመጽወቱን አላቆመምና ቤቱ : ንብረቱ አልቆ ከነ ቤተሰቡ ነዳያን ሆኑ:: እርሱ ግን ያለ ምጽዋት ማደር አይችልምና አንድ ሃሳብ መጣለት:: ሚስቱንና ልጆቹን መሸጥ እንዳለበት ወሰነ::

+እነርሱ እንደ መሪያቸው ፍጹማን ናቸውና በደስታ ሃሳቡን ተቀበሉት:: መጀመሪያ ትልቁ ልጅ ተሸጠ:: ገንዘቡ ግን አሁንም በምጽዋት አለቀ:: ቀጥሎ ትንሹ ልጅ ተሸጠ:: አሁንም በምጽዋት አለቀ:: 3ኛ ደግ ሚስት ተሸጠችና እርሱም ተመጸወተ::

+በመጨረሻ ቅዱስ ዻውሎስ ራሱንም ሽጦ መጸወተና ይህ ድንቅ ሥራ ተጠናቀቀ:: ( ነገሩ ግራ እንዳያጋባን "ተሸጡ" ስንል ለአሕዛብ ወይም ለሌላ ሰው አይደለም:: 4ቱም የተሸጡት ለገዳማት ሲሆን ገዥዎቹ አበ ምኔቶቹ ናቸው:: ) ቅዱስ ዻውሎስ በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ መትቶ ምጽዋትንም : ገዳማዊ ሕይወትንም አትርፏል::

+በሁዋላ ወደ ተሸጠበት ገዳም ገብቶ እንዲህ ብሎ ጮኸ:- "ጌታ ሆይ! የሰጠኸኝን ሁሉ ላንተ መልሼ ይሔው መጥቻለሁ::" ጌታም ከሰማይ መለሰለት:- "ወዳጄ ሆይ! ባንተ ደስ ብሎኛል:: ተቀብዬሃለሁ" አለው:: 4ቱም #ቅዱሳን በንጹሕ ተጋድሎ ኑረው በዚህች ቀን ዐርፈው የማታልፈውን ርስት ወርሰዋል::

+*" ቅዱስ ሱርያል ሊቀ መላዕክት "*+

=>ከታላላቅ ሊቃናት አንዱ የሆነው #ቅዱስ_ሱርያል ክብሩ ብዙ ቢሆንም ብዙ ምዕመናን አያውቁትም:: የመላእክት መዓርግ ሲነገር #ሚካኤል : #ገብርኤል : #ሩፋኤል ብሎ ቀጥሎ የሚመጣው ሱርያል ነው::

+በ3ቱ ሰማያት ካሉት 9ኙ ዓለመ መላእክት የአንዱ (#የሥልጣናት) መሪ (አለቃ) ነው:: መልአኩ እጅግ ርሕሩሕ እና ተራዳኢ ነውና አንዘንጋው:: #ለኖኅ መርከብርን ያሳራው : ከጥፋት ውሃም ያዳነው ይህ ቅዱስ መልአክ ነው::

+በገድለ ሰማዕታትም ላይ እንደተጠቀሰው የሰማዕታት ረዳትና አዳኝም ነው:: #ቅዱስ_ሱርያል በሌላ ስሙ "#እሥራልዩ" ይባላል:: "የእሥራኤል ረዳት" እንደ ማለት:: ዛሬ ደግሞ የሊቀ መልአኩ ቅዳሴ ቤቱ ነው::

+*" ቅዱሳን መርቆሬዎስና ኤፍሬም "*+

=>እነዚህ ወጣቶች በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበሩ ሲሆን ከተወለዱባት #ገሊላ ወደ ግብጽ (#ገዳመ_አስቄጥስ) በምናኔ መጥተዋል:: ለ20 ዓመታትም በክህነት አገልግሎትና በተጋድሎ ኑረዋል::

+አንድ ቀን መናፍቃን (አርዮሳውያን) በወታደር ተከበው መጥተው በገዳሙ እንቀድሳለን አሉ:: የራሳቸውን መስዋዕት መንበሩ ላይም አኖሩ:: ከዛ ያሉ አበው አዘኑ:: ወጣቶቹ መርቆሬዎስና ኤፍሬም ግን ለአምላካቸው ቀኑ::

+ወደ ቤተ መቅደስ ገብተው መናፍቃኑን "በክርስቶስ አምላክነት የማያምን በዚህ መቅደስ ውስጥ አይሰዋም" ብለው በድፍረት የመናፍቃንን መስዋዕት ወደ ውጪ በተኑት:: በዚያች ሰዓት መናፍቃኑ 2ቱን ቅዱሳን ወደ መሬት ጥለው ደበደቧቸው:: ረገጧቸው:: የቅዱሳኑ አጥንቶችም ተሰባበሩ:: በመጨረሻ በስቃዩ ብዛት 2ቱም በአንድነት ዐረፉ::

=>የእነዚህ ሁሉ ቅዱሳን አምላክ ተረፈ ዘመኑን የንስሃ : የፍቅርና የአንድነት ያድርግልን:: ከወዳጆቹም በረከትን ያድለን::

=>ሐምሌ 30 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ
2.ቅዱስ ዻውሎስ መናኒ (ከቤተሰቡ ጋር)
3.ቅዱስ ሱርያል (እሥራልዩ) ሊቀ መላእክት
4.ቅዱሳን መርቆሬዎስና ኤፍሬም (ሰማዕታት)
5.ቅዱስ ጢሞቴዎስ ዘአልቦ ጥሪት (ፍልሠቱ)
6.እናታችን ማርያም ክብራ ኢትዮዽያዊት (የዐፄ ናዖድ ሚስት)

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ማርቆስ ዘአንበሳ (ሐዋርያ)
2.አባ ሣሉሲ ክቡር
3.ቅዱስ ጐርጐርዮስ ነባቤ መለኮት
4.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት
5.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት
ኅዳር 24 እንኳን ለ #የ24ቱ_ካህናተ_ሰማይ_በዓል እና በቆብ አያትና የልጅ ልጅ የኾኑት #አቡነ_ተክለሃይማኖትና_አቡነ_ሳሙኤል_ዘዋልድባ_ከካህናተ ሰማይ ጋር #የሥላሴን መንበር ላጠኑበት ዕለት በሰላም አደረሳቹህ ፡፡

#Share ያድርጉ

※እግዚአብሔር ከሠራዊተ #ሩፋኤል (ሊቃናት) #ሃያአራት ሊቃናት መርጦ በምንበረ ስብሐት በመጋረጃዋ ውስጥ ዙርያዋን ክንፍ ለክንፍ ገጥሞ አቁሟቸዋል፡፡ ሕዝ 1 ፥11-12
※ስማቸውን #ካህናተ_ሰማይ አላቸው የእሳትና የወርቅ ጽና አስያዛቸው ፤ የብርሃን አክለሊል ጳዝዮን ከሚባል የብርሃን ዘውድ ደፋላቸው የብርሃን ዘንግ ማኀተሙ መስቀል የሆነ አስያዛቸው ፤ የብርሃን ላንቃ ኀብሩ መብረቅ የመሰለ አለበሳቸው ፡፡ ‹‹በዙፋኑ ዙርያ ሀያአራት ዙፋኖች ነበሩ፤ በዙፋኖቹም ላይ ነጭ ልብስ ለብሰው በራሳቸውም የወርቅ አክሊል ደፍተው ሀያ አራት ሽማግሌዋች ተቀምጠው ነበር›› ዮሐ ራዕ 4፥-5

※እነዚህም በአንድ ላይ በአጠኑ ጊዜ ከማዕጠንታቸው የሚወጣው ጢስ መልኩ #መብረቅ ፤ ድምጹ ነጎድጓድ ፣ መዓዛው መልካም የሆነ ነው ፡፡ ‹‹ ሌላም መልአክ መጣና የወርቅ ጥና ይዞ በመሠዊያው አጠገብ ቆመ በዙፋኑም ፊት ባለው በወርቅ መሠዊያ ላይ ለቅዱሳን ሁሉ ጸሎት እንዲጨምርው ብዙ ዕጣን ተሰጠው ፤ የዕጣኑም ጢስ ከቅዱሳን ጸሎት ጋር ከመልአኩ እጅ በእግዚአብሔር ወጣ››ዮሐ ራዕ 8 ፥3-5

※የሚያጥኑት ምንድን ነው ቢሉ የጻድቃን ጸሎት ፤ የሰማዕታት ገድል ፣ የደጋግ ሰዎች ምግባር ነው ፡፡ በእናንተ እየጣጠነ ወደ እኔ ያርግ ( ይድርስ ) ብሏቸዋልና ፡፡ ያለ እነርሱም አቅራቢነት ጽድቅና ምጽዋት ወደ እግዚአብሔር አይቀርብም፡፡

※ኣቋቋማቸውም እንዲህ ነው ፤ ኪሩቤል በቀኝ እንደ ቀሳውስት ሱራፌል በግራ እንደ ዲያቆናት ከፍ ብለው ፤ካህናተ ሰማይ ዝቅ ብለው ክንፍ ለክንፍ ገጥመው ቁመው ይኖራሉ ፡፡
እንዲሁም ሌሎችም ቅዱሳን መንበረ ሥላሴን ያጠኑ አሉ፡፡ ለምሳሌም፤ በቆብ አያትና የልጅ ልጅ የኾኑት #አቡነ_ተክለሃይማኖትና_አቡነ_ሳሙኤል_ዘዋልድባ_ ከካህናተ ሰማይ ጋር የሥላሴን መንበር አጥነዋል ፨ አቡነ ዮሴፍ ዘጂፋት፣ አቡነ ዘርዐ ቡሩክ እንዲሁ አጥነዋል ፡፡
@petroswepawulos