መዝገበ ቅዱሳን
20.7K subscribers
1.92K photos
9 videos
6 files
25 links
የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው! መ/ሳ 1÷7
Bewust mesimer lemanegager
@Yesadkusitota
የሰማነውን እንናገራለን
ያየነውን እንመሰክራለን
Download Telegram
እንኳን ለአምላካችንና ለመድኀኒታችን፤ ለፈጣሪያችንና ለአዳኛችን መድኀኔ ዓለም ጥንተ ስቅለት ክብረ በዓል አደረሳችሁ፥ አደረሰን፡፡
#ጥንተ ስቀለት
#ክርስቶስ_የተሰቀለው መጋቢት ፳፯ ቀን #ከሆነ _እንደገና_በሌላ_ጊዜ_በዓለ_ስቅለትን_ማክበር_ለምን_አስፈለገ?
#ጥንተ_ትንሣኤ

#ጥንተ_ስቀለት
ጥንተ ስቅለቱ የመታሰቢያ በዓል በሚከበርበት በመጋቢት ፳፯ ቀን ሰማያዊ አምላክ ስለሰው ልጆች ፍቅር ሲል ልዩ ልዩ ጸዋትወ መከራዎችን የተቀበለበትና በሞቱ ሞትን ሽሮ የአዳምን ዘር ሁሉ ከሞት ሞት ያዳነበት፣ ለዓለሙ ሁሉ ፍቅሩን የገለጠበት፣ በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙምዓለምን ነፃ ያወጣበት፣ ሕማማተ መስቀልን በትዕግሥት ተቀብሎ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው #በገዛ_ፈቃዱ የለየበት የስቅለቱና የሞቱ መታሰቢያ የሚከበርበት ቀን በመሆኑ ጥንተ ስቅለት ተብሎ ይጠራል፡፡ በዓሉም በዓለ መድኃኔዓለም እየተባለ በየዓመቱ #በመድኃኔዓለም ስም በታነጹ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ታቦተ ሕጉ ይወጣል

👉#ክርስቶስ የተሰቀለው መጋቢት ፳፯ ቀን ከሆነ እንደገና በሌላ ጊዜ በዓለ ስቅለትን ማክበር ለምን አስፈለገ?
ክርስቶስ የተሰቀለው መጋቢት ፳፯ ቀን ከሆነ እንደገና በሌላ ጊዜ በዓለ ስቅለትን ማክበር ለምን አስፈለገ?
ክርስቶስ የተሰቀለው በዕለተ ዓርብ ሲሆን ከመቃብር የተነሣውም በዕለተ እሑድ በመሆኑ #ስቅለት ከዕለተ ዓርብ፣ #ትንሣኤም ከዕለተ እሑድ፣ #ዕርገት ደግሞ ከዕለተ ሐሙስ እንዳይወጡ፤ ሌሎቹም በዓላትና አጽዋማት በተወሰነላቸው ቀን እንዲውሉ ማድረግ ይቻል ዘንድ የቀድሞ አባቶችና ሊቃውንተቤተክርስቲያን ሰባት አዕዋዳት አዘጋጅተው እና ቀምረው ሁሉም ሥርዓቱን ጠብቆ ድርጊቱ በተፈጸመበት ቀን እንዲከበር የወሰኑ በመሆኑ ነው፡፡ በዚህም መሠረት ጥንተ ስቅለቱ መጋቢት ፳፯ ቀን በየዓመቱ እየታሰበ በዓለ ስቅለቱ ደግሞ ከሰሙነ ሕማማቱ ጋር በዓመት አንድ ጊዜ በዕለተ ዓርብ በጾምና በጸሎት እንዲሁም በአክፍሎትና በስግደት እንዲከበር በማድረግ ሕግና ሥርዓት ስለሠሩ በዚሁ መሠረት ይፈጻማል::

#ከዘጠኙ ዓበይት በዓላት አንዱ የሆነው የጌታችን #የጽንሰቱ_በዓል በታላቅ ድምቀት የሚከበርበት ቀን ከመሆኑ የተነሣ በዓሉን በዓል ተጭኖት ነው እንጂ ፫ኛው ቀን መጋቢት ፳፱ኝም
ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ የተነሣበት #ጥንተ_ትንሣኤ በመሆኑ እንደጥንተ ስቅለቱ ሁሉ ጥንተ ትንሣኤውም ከበዓለ ጽንሰቱ ጋር አብሮ የሚታሰብ መሆኑን ልንዘነጋው አይገባንም፡፡


#በኢትዮጵያ_በዋነኛነትና_በግንባር_ቀደምትነት_የስቅለት_በዓል_የሚከበርበት

#ታላቁ ገዳም #ዋልድባ (ዋሊ)፡፡
#142 ዓመታትን ያስቈጠረው ጥንታዊው የጮቢ ደብረ መድኀኒት መድኀኔ ዓለም፡፡ በ1868ዓ.ም. የተመሠረተ፡፡ በምዕራብ ሸዋ ዞን በጀልዱ ወረዳ በጮቢ የሚገኝ፡፡
በሃገራችን ከሚገኙ የመድኀኔዓለም ገዳማትና አድባራት ጥቂቶቹ፤

፤ ዋልድባ አበረንታት መድኀኔዓለም ገዳምና
ኤልሻማ ደብረ ማኅቶት መድኀኔዓለም ቤ.ክ.
፠ አንድ ላይ ያሉት፤
✤1. ዋልድባ አበረንታት መድኀኔዓለም ገዳም፤
✤2.ላሊበላ መድኀኔዓለም
✤3. ጎንደር መንበረ መንግሥት መድኀኔዓለም
✤4. መንዳባ አቡነ ያሳይ መድኀኔዓለም፤ ጣና
✤5. ሽረ እንዳሥላሴ መድኀኔዓለም ወመስቀል ክብራ
✤6. ቆላድባ መድኀኔዓለም፤ ጎንደር ከተማ አጠገብ
✤7.ቦሌ ደብረ ሳሌም መጥምቁ ዮሐንስ፤ (ቦሌ የመድኀኔዓለም ታቦት )
✤ 8.ድሬዳዋ መድኀኔዓለም
..
✤9.#ቀጨኔ_ደብረ_ሰላም_መድኀኔዓለም ✤ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለም ቤተ ክርስቲያን፤ ፤ የ108 ዓመታት ዕድሜ ያለው ጥንታዊ የኢያሱ ደብር፡፡ ‹‹በወርቅ ወበዕንቊ ሥርጉት ደብረ ሰላም፤ ወነገሥት ይትቀነዩ ለኪ››
ለዛቲ ቤት ሣረራ ኢያሱ ቀዲሙ ለዛቲ ቤት፤ ወፈጸመታ ንግሥት ዘውዲቱ፡፡ (ይህችን ደብረ ሰላምን በመጀመሪያ አቤቶ ኢያሱ /አልጋ ወራሽ ልጅ ኢያሱ/ (ክፍለ ያዕቆብ) በሐምሌ 26 ቀን 1903 ዓ.ም. መሠረታት፤ ንግሥት ዘውዲቱ አሁን ያለውን ሕንፃው ቤ.ክ ጥቅምት 27 ቀን 1913 ዓ.ም አስፈጸመች፡፡)
ስለ ታላቁ ደብር ብዙ ነገር ባወራን ደስ ባለን ነበር ….. የሰላም አምላክ የፍቅር ጌታ ያደረባት ደብረ ሰላም ብዙ ነገሮች አሏት፤ የብዙ ሊቃውንት መፍለቂያ፤ የላይ ቤት አቋቋም፣ የተክሌ ዝማሜና የሸዋና የራሱ የደብሩ ቀለም እንደ ወንዝ የሚፈስባት፤ ታሪካዊ ቅርሶችን የያዘ ቤተ መዘክር (Museum)ና ቤተ መጻሕፍት የሚገኙበት፤ ደብሩን አገልግለው ወደ ሌላ ደብር የሚዛወሩ ካህናት ኹሌም በዓይናቸው የደብሩ ፍቅር ውልብ የሚልባቸው፤ ምዕመናኑ በአጸዱና በግርማ ሞገሱ ኹሌም የሚደነቁበት፤ ስዕለት ሰሚ ታቦታት ያሉበት፤ 4ት የሚጠጉ ፈዋሽ ጠበሎች የሚገኙበት፡፡ ጽዶቹ ሳይቀሩ በ72 አርድዕት ቅዱሳን አምሳያ የተተከሉበት፤ በቀድሞ ዘመን መዐዛ ቅዳሴ የተሰኘው የአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ቅዳሴ በወርኃ ጽጌ የሚቀድስበት፤ 3 ጳጳሳትን ያፈራ፣ ……. ደብር ነው፡፡
✣ ለደብረ ሰላም ይደልዋ ስብሐት፤ እስመ በውስቴታ ኀደረ መድኀኔዓለም (በደብረ ሰላም በውስጧ መድኀኔዓለም ስላደረ ምስጋና ይገባታል፡፡
10 #መናገሻ_ጋራ_መድኀኔዓለም፤ ግማደ መስቀሉ ያረፈበት፤ ቀድሞ የቅዳሴ ቤቱን ታላቁ አባት አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ (ቀድሞ የልደታ ቤ.ክ) በአካል በመገኘት በመስቀሉ የባረከው፤ በድርሳነ ራጕኤል ላይ የተገለጸና ቅዱስ ራጕኤል የማይለየው፤ በአረማዊው ግራኝ ወረራ ጊዜ ቤተ ክርስቲያኑ ካህናቱን መነኮሳቱንና ምዕመናኑን እንደያዘ በምድር ውስጥ ገብቶ የተሰወረበት በሥጋ ዕረፍተ ሞት ያልተገቱ ሥውራን ግሩማን አበው የሚኖሩበት "ዛቲ ይእቲ አምባ ማርያም መካነ ክብሮሙ ወጸሎቶሙ ለቅዱሳን ወለነገሥታተ ኢትዮጵያ በሐ በልዋ ተሳለምዋ ጊሱ ሐቤሃ ኢትርሐቁ እምኔሐ" ብለው አበው ያወደሷት የጸሎት የአርምሞና የትኅርምት ቦታ፡፡
11. #ገዳመ_አባ_ጽጌ_ድንግል (መድኀኔዓለም ቤ.ክ)፤ ማኅሌተ ጽጌ የተደረሰበት ወሎ፤ ወግዲ፤ ወለቃ ወንዝ አጠገብ፤ የበረሃው ዕንቊ ገዳም፤ አባ ጽጌ ድንግል የፈለፈሉት ባለ 3 መቅደስ እጅግ ሰፊ ዋሻ ቤ.ክ፡፡
12. #ደብረ_ቀራንዮ_መድኀኔዓለም ቤ.ክ፥ አዲስ አበባ፤ በአዲስ አበባ ከተመሠረተ ከ1826 ዓ.ም ጀምሮ ፍልሰት ሳያጋጥመው በመቆየቱ፤ የመጀመሪያው የአዲስ አበባ ቤ.ክ፡፡ (ነገር ግን በመሃል ፍልሰት እያጋጠማቸው እንጂ በአዲስ አበባ ከ1600 ዓመታት በፊት ደብረ ኤረር፣ የካ ዋሻ ተክለሃይማኖትና /ኋላ የካ ሚካኤል/ በአብርሃ ወአጽብሃ ዘመን፤ እንዲሁም እንጦጦ ኪዳነ ምሕረት በአልአሜዳ ዘመነ መንግሥት መመሥረታቸውን ልብ ይሏል)
በዓለም አቀፍ ደረጃ በዋነኛነትና በግንባር ቀደምትነት የስቅለት በዓል የሚከበርባችው ፪ቱ ታላላቅ ገዳማት
፩ኛ. ኢየሩሳሌም ዴር ሡልጣን
፪ኛ. #ዋልድባ (ዋሊ)፡፡