መዝገበ ቅዱሳን
20.7K subscribers
1.92K photos
9 videos
6 files
24 links
የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው! መ/ሳ 1÷7
Bewust mesimer lemanegager
@Yesadkusitota
የሰማነውን እንናገራለን
ያየነውን እንመሰክራለን
Download Telegram
#ሐምሌ_14

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም

ሐምሌ ዐሥራ አራት በዚች ቀን የጌታ ክርስቶስ ጭፍራ #ቅዱስ_አብሮኮሮንዮስ በሰማዕትነት አረፈ፣ የታላቁ #አባ_መቃርስ እና #የሰማዕቱ_አሞንዮስ መታሰቢያቸው ሆነ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_አብሮኮሮንዮስ

ሐምሌ ዐሥራ አራት በዚች ቀን የጌታ ክርስቶስ ጭፍራ ቅዱስ አብሮኮሮንዮስ በሰማዕትነት አረፈ። የዚህም ቅዱስ ትውልዱ ከኢየሩሳሌም ነው የአባቱ ስም ክርስቶፎሮስ ነው ትርጓሜውም ክርስቶሰን የለበሰ ማለት ነው። ክርስቲያንም ነበረ የእናቱም ስም ቴዎዶስያ ነው እርሷ ግን ጣዖታትን ታመልክ ነበረች።

አባቱም በአረፈ ጊዜ እናቱ ወሰደችው ከእርሱም ጋራ ብዙ ገንዘብ ይዛ ወደ አንጾኪያ ከተማ ሔደች ልጅዋንም በእስክንድርያ ከተማ ገዥ አድርጎ ይሾመው ዘንድ ለዲዮቅልጥያኖስ እጅ መንሻ ሰጠችው እርሱም ሾመው የሹመት ደብዳቤውንም ጽፎ ክርስቲያኖችን እንዲአሠቃይ አዘዘው።

ከአንጾኪያም ከተማ ወጥቶ ጥቂት እንደተጓዘ ወደእርሱ የሚያስፈራ ቃል ከሰማይ መጣ በስሙም ጠርቶ እንዲህ አለው ከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ እንዳዘዘህ ብታደርግ አንተ በክፉ አሟሟት ትሞታለህ።

እርሱም ራስህን ትገልጥልኝ ዘንድ ጌታዬ ሆይ እለምንሃለሁ አለው ወዲያውኑም የብርሃን መስቀል ታየው ዳግመኛም በኢየሩሳሌም የተሰቀልኩ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ እኔ ነኝ የሚለውን ቃል ሰማ።

ይህንንም ቃል በሰማ ጊዜ እጅግ ፈራ ተመልሶም ከአንጥረኛ ዘንድ የወርቅ መስቀል አሠራ ከዚህም በኋላ ወደ እስክንድርያ ከተማ ተጓዘ በጉዞውም ውስጥ ሊገድሉት ዐመፀኞች አረማውያን ተነሡበት እርሱም በእነርሱ ላይ በርትቶ ክብር ይግባውና በጌታ ክርስቶስ መስቀል ድል አደረጋቸው።

እናቱም በጦርነት ላይ ለረዱህና ላዳኑህ አማልክት መሥዋዕትን ሠዋ አለችው እርሱም እንዲህ አላት እኔስ አዳኝ በሆነ በመስቀሉ ኃይል ላዳነኝ ክብር ይግባውና ለእግዚአብሔር እሠዋለሁ።

ይህንንም በሰማች ጊዜ ልጅዋ አብሮኮሮንዮስ ክርስቲያን እንደሆነ ወደ ዐመፀኛው ዲዮቅልጥያኖስ ልካ ነገረችው። ዲዮቅልጥያኖስም ጭፍራ ልኮ ወደ ቂሣርያ ከተማ አስወሰደው የቂሣርያውንም ገዥ ስለ ርሱ እንዲመረምርና እንዲአሠቃየው አዘዘው።

ከዚህም በኋላ ወደ መኰንኑ በአቀረቡት ጊዜ በፊቱ ቁሞ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ ለመሞት እስቲደርስም ጽኑዕ ግርፋትን ገረፈው ከዚህም በኋላ አሠረው። በዚያችም ሌሊት ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በታላቅ ብርሃን ውስጥ ታየው ከእርሱም ጋራ ብርሃናውያን መላእክት ነበሩ ከማሠሪያውም ፈታውና በመለኮታዊ እጁ ዳሰሰው ከቍስሎቹም ሁሉ አዳነው።

በማግሥቱም መኰንኑ ስለ ቅዱሱ ዜና ሙቶ እንደሆነ ወይም አልሞተ እንደሆነ ጠየቀ ለእርሱ የሞተ መስሎት ነበረና። ቅዱሱም በመጣ ጊዜ ጤነኛ ሁኖ አየውና መኰንኑ አደነቀ በዚያ የነበሩ ሕዝቡም አይተው እጅግ አደነቁ እንዲህም እያሉ ጮኹ እኛ በግልጥ ክርስቲያን ነን በቅዱስ አብሮኮሮንዮስ አምላክ እናምናለን። ከእነርሱም ጋራ ሁለት መኳንንትና ዐሥራ ሁለት ሴቶች እናቱ ቴዎዶስያም ነበሩ መኰንኑም ራሶቻቸውን በሰይፍ እንዲቆርጧቸው አዘዘ። እነርሱም ቆረጡአቸው። በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ሐምሌ ስድስት ቀን ተቀበሉ።

ቅዱስ አብሮኮሮንዩስን ግን ምን እንደሚያደርግበት እስቲአስብ ድረስ ሦስት ቀን አሠረው ከዚህም በኋላ አውጥቶ እንዲህ አለው ልብህ እንዲመለስ ነፍስህንም እንድታድን ለአማልክትም እንድትሠዋ እነሆ በአንተ ላይ ሦስት ቀናት ታገሥኩ። ቅዱሱም እንዲህ ብሎ መለሰለት መኰንን ሆይ የለም ልቤ ወደ ስሕተት አይመለስም ክብር ይግባውና ከጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ አውቄ ተረድቼአለሁ ጣዖታቱም ሁሉ ከዕንጨትና ከደንጊያ በሰው እጅ የተሠሩ ፍጡራን ናቸው እንጂ አማልክት አይደሉም አይጐዱም አይጠቅሙም።

መኰንኑም ሰምቶ እጅግ ተቆጣ ጐኖቹንም በሰይፍ እንዲሰነጣጥቁ አዘዘ አርኬላዎስ የሚባል ባለ ሰይፍም የቅዱሱን ጐኖቹን ሊሠነጥቅ እጁን ዘረጋ ያን ጊዜም እጁ ደረቀች ወድቆም ሞተ። መኰንኑም ተቆጥቶ በምድር ጥለው ይገርፉት ዘንድ አዘዘ እንደ አዘዘም ገረፉት በሰይፍም ጐኖቹን ሠንጥቀው በቍስሉ ውስጥ መጻጻ ጨመሩ እስከ ወህኒ ቤትም ድረስ በእግሩ ጐተቱት በዚያም ሁለት ቀኖች ኖረ ከዚህም በኋላ አውጥቶ እሳትን በተመላች ጕድጓድ ውስጥ ጣለው ክብር ይግባውና ጌታችንም አዳነው ምንም ምን አልነካውም።

ብዙ ከማሠቃየቱም የተነሣ መኰንኑ በሰለቸ ጊዜ ራሱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘና ቆረጡት በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ታላቁ_ቅዱስ_መቃርስ

ዳግመኛም በዚሀች ዕለት የታላቁ አባ መቃርስ መታሰቢው ሆነ፡፡ መቃርስ (መቃርዮስ) ማለት ‹‹ቅዱሱ ለእግዚአብሔር›› ማለት ነው፡፡ ከደቡባዊ ግብፅ ከተወደዱ ደጋግ ክርስቲኖች የተገኘ ታላቅ አባት ነው፡፡ አባታቸው አብርሃም እናታቸው ሣራ ይባላሉ፡፡ እነርሱም መጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንዳሉት እንደ አብርሃምና ሣራ እጅግ ደጎች ነበሩ፡፡ ልጅ ግን አልነበራቸውምና በስለት መቃርስን ወለዱ፡፡ ሲያድጉም በግድ ያለፈቃዳቸው ሚስት አጋቧቸው፡፡ አባ መቃርስ ግን ወደ ሙሽራይቱ በገቡ ጊዜ ዐውቀው እንደታመሙ ሆነው ተኙ፡፡ ‹‹ከበሽታዬ ለጥቂት ጊዜ ጤና ባገኝ ወደ ገዳም ልሂድ›› ብለው ወደ አስቄጥስ በረሃ ሄዱ፡፡ መልአክም ተገልጦ ‹‹ይህች አስቄጥስ የአንተና የልጆችህ ርስት ናት›› አላቸው፡፡ ወደ ቤተሰባቸውም በተመለሱ ጊዜ ሙሽራ እጮኛቸው በድንግልና እንዳለች ሞታ ደረሱ፡፡ ከጥቂት ቀንም በኋላ እናትና አባታቸውም ዐረፉ፡፡ እርሳቸውም ንብረታቸውን ሁሉ ለድሆች መጽውተው ገዳም ገቡ፡፡ ሕዝቡም ደግነታቸውንና እውነተኛነታቸውን አይተው ትንሽ ማረፊያ ሠርተው ሌሎች እንዲያገለግሏቸው አደረጉ፡፡

ከዕለታትም በአንድ ቀን አንዲት ሴት ልጅ ከጎረምሳ አርግዛ ሳለ ጎረምሳው ‹‹አባትሽ ሲጠይቅሽ ከአባ መቃርስ አረገዝኩ በይ›› ብሎ መከራትና ለአባቷ እንደተባለችው ተናገረች፡፡ ‹‹አባ መቃርስ በግድ ደፍረውኝ አረገዝኩ›› አለች፡፡ የከተማው ሰውም አባ መቃርስን ከበዓታቸው አውጥተው ለሞት እስኪደርሱ ድረስ ደበደቧቸው፡፡ መላእክትም በሰው አምሳል ተገልጠው ዋስ ሆነው ለልጅቷም ምግቧን ሊሰጡ ተስማምተው ወደ በዓታቸው መለሷቸው፡፡ አባ መቃርስም ለራሳቸው ‹‹መቃርስ ሆይ እንግዲህ ባለ ሚስትና ባለ ልጅ ሆነሃልና ሌሊትና ቀን መሥራት ይገባሃል›› እያሉ ቅርጫቶችን እየሠፉ ለሚያገለግላቸው ልጅ እየሰጡት እርሱ ሸጦ እያመጣ ብዙውን ለዚያች በዝሙት ጸንሳ በሳቸው ላሳበበች ሴት ይሰጡ ጀመር፡፡ መውለጃዋም በደረሰ ጊዜ እስከ 4 ቀን ድረስ በጽኑ ሥቃይ ቆየች፡፡ እውነቱንም ተናግራ ንስሓ በገባች ጊዜ ወደ አባ መቃርስ ዘንድ አደረሷት፡፡ ሕዝቡም ሁሉ ‹‹አባታችን ይቅር በሉን›› ብለው ከእግራቸው ላይ ሲወድቁ ይቅር ብለዋቸው ቀድሰው አቆረቧቸው፡፡

ከዚህ በኋላ መልአኩ ወስዶ አስቄጥስ ገዳም አደረሳቸው፡፡ የቅዱሳኑ የመክሲሞስና የዱማቴዎስ በዓት ወደ ሆነች ቦታም አስገብቶ በዚያ በልጆቻቸው ቦታ ላይ በዓታቸውን እንዲያጸኑ ነገራቸው፡፡ አባ መቃርስ ወደ አባ እንጦንስ ዘንድም በመሄድ በረከታቸውንና ምክራቸውን ይቀበሉ ነበር፡፡ ሰይጣናትም በእርሳቸው ላይ የሚያደርሱትን ክፉ ነገር ሲመካከሩ ይሰሟቸው ነበር፡፡ በእሳት እያቃጠሉ ፈተኗቸው፣ የዝሙት መንፈስ እያመጡም ፈተኗቸው፣ በዚህም ትዕግስትን ቢያደርጉ በሌላም ዓለማዊ ክብርን መውድን፣ ትዕቢትን፣ መመካትን፣ ታካችነትን፣ ስድብን፣ ሃይማኖት
#ሐምሌ_14

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሐምሌ ዐሥራ አራት በዚች ቀን የጌታ ክርስቶስ ጭፍራ #ቅዱስ_አብሮኮሮንዮስ በሰማዕትነት አረፈ፣ የታላቁ #አባ_መቃርስ እና #የሰማዕቱ_አሞንዮስ መታሰቢያቸው ሆነ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_አብሮኮሮንዮስ

ሐምሌ ዐሥራ አራት በዚች ቀን የጌታ ክርስቶስ ጭፍራ ቅዱስ አብሮኮሮንዮስ በሰማዕትነት አረፈ። የዚህም ቅዱስ ትውልዱ ከኢየሩሳሌም ነው የአባቱ ስም ክርስቶፎሮስ ነው ትርጓሜውም ክርስቶሰን የለበሰ ማለት ነው። ክርስቲያንም ነበረ የእናቱም ስም ቴዎዶስያ ነው እርሷ ግን ጣዖታትን ታመልክ ነበረች።

አባቱም በአረፈ ጊዜ እናቱ ወሰደችው ከእርሱም ጋራ ብዙ ገንዘብ ይዛ ወደ አንጾኪያ ከተማ ሔደች ልጅዋንም በእስክንድርያ ከተማ ገዥ አድርጎ ይሾመው ዘንድ ለዲዮቅልጥያኖስ እጅ መንሻ ሰጠችው እርሱም ሾመው የሹመት ደብዳቤውንም ጽፎ ክርስቲያኖችን እንዲአሠቃይ አዘዘው።

ከአንጾኪያም ከተማ ወጥቶ ጥቂት እንደተጓዘ ወደእርሱ የሚያስፈራ ቃል ከሰማይ መጣ በስሙም ጠርቶ እንዲህ አለው ከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ እንዳዘዘህ ብታደርግ አንተ በክፉ አሟሟት ትሞታለህ።

እርሱም ራስህን ትገልጥልኝ ዘንድ ጌታዬ ሆይ እለምንሃለሁ አለው ወዲያውኑም የብርሃን መስቀል ታየው ዳግመኛም በኢየሩሳሌም የተሰቀልኩ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ እኔ ነኝ የሚለውን ቃል ሰማ።

ይህንንም ቃል በሰማ ጊዜ እጅግ ፈራ ተመልሶም ከአንጥረኛ ዘንድ የወርቅ መስቀል አሠራ ከዚህም በኋላ ወደ እስክንድርያ ከተማ ተጓዘ በጉዞውም ውስጥ ሊገድሉት ዐመፀኞች አረማውያን ተነሡበት እርሱም በእነርሱ ላይ በርትቶ ክብር ይግባውና በጌታ ክርስቶስ መስቀል ድል አደረጋቸው።

እናቱም በጦርነት ላይ ለረዱህና ላዳኑህ አማልክት መሥዋዕትን ሠዋ አለችው እርሱም እንዲህ አላት እኔስ አዳኝ በሆነ በመስቀሉ ኃይል ላዳነኝ ክብር ይግባውና ለእግዚአብሔር እሠዋለሁ።

ይህንንም በሰማች ጊዜ ልጅዋ አብሮኮሮንዮስ ክርስቲያን እንደሆነ ወደ ዐመፀኛው ዲዮቅልጥያኖስ ልካ ነገረችው። ዲዮቅልጥያኖስም ጭፍራ ልኮ ወደ ቂሣርያ ከተማ አስወሰደው የቂሣርያውንም ገዥ ስለ ርሱ እንዲመረምርና እንዲአሠቃየው አዘዘው።

ከዚህም በኋላ ወደ መኰንኑ በአቀረቡት ጊዜ በፊቱ ቁሞ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ ለመሞት እስቲደርስም ጽኑዕ ግርፋትን ገረፈው ከዚህም በኋላ አሠረው። በዚያችም ሌሊት ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በታላቅ ብርሃን ውስጥ ታየው ከእርሱም ጋራ ብርሃናውያን መላእክት ነበሩ ከማሠሪያውም ፈታውና በመለኮታዊ እጁ ዳሰሰው ከቍስሎቹም ሁሉ አዳነው።

በማግሥቱም መኰንኑ ስለ ቅዱሱ ዜና ሙቶ እንደሆነ ወይም አልሞተ እንደሆነ ጠየቀ ለእርሱ የሞተ መስሎት ነበረና። ቅዱሱም በመጣ ጊዜ ጤነኛ ሁኖ አየውና መኰንኑ አደነቀ በዚያ የነበሩ ሕዝቡም አይተው እጅግ አደነቁ እንዲህም እያሉ ጮኹ እኛ በግልጥ ክርስቲያን ነን በቅዱስ አብሮኮሮንዮስ አምላክ እናምናለን። ከእነርሱም ጋራ ሁለት መኳንንትና ዐሥራ ሁለት ሴቶች እናቱ ቴዎዶስያም ነበሩ መኰንኑም ራሶቻቸውን በሰይፍ እንዲቆርጧቸው አዘዘ። እነርሱም ቆረጡአቸው። በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ሐምሌ ስድስት ቀን ተቀበሉ።

ቅዱስ አብሮኮሮንዩስን ግን ምን እንደሚያደርግበት እስቲአስብ ድረስ ሦስት ቀን አሠረው ከዚህም በኋላ አውጥቶ እንዲህ አለው ልብህ እንዲመለስ ነፍስህንም እንድታድን ለአማልክትም እንድትሠዋ እነሆ በአንተ ላይ ሦስት ቀናት ታገሥኩ። ቅዱሱም እንዲህ ብሎ መለሰለት መኰንን ሆይ የለም ልቤ ወደ ስሕተት አይመለስም ክብር ይግባውና ከጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ አውቄ ተረድቼአለሁ ጣዖታቱም ሁሉ ከዕንጨትና ከደንጊያ በሰው እጅ የተሠሩ ፍጡራን ናቸው እንጂ አማልክት አይደሉም አይጐዱም አይጠቅሙም።

መኰንኑም ሰምቶ እጅግ ተቆጣ ጐኖቹንም በሰይፍ እንዲሰነጣጥቁ አዘዘ አርኬላዎስ የሚባል ባለ ሰይፍም የቅዱሱን ጐኖቹን ሊሠነጥቅ እጁን ዘረጋ ያን ጊዜም እጁ ደረቀች ወድቆም ሞተ። መኰንኑም ተቆጥቶ በምድር ጥለው ይገርፉት ዘንድ አዘዘ እንደ አዘዘም ገረፉት በሰይፍም ጐኖቹን ሠንጥቀው በቍስሉ ውስጥ መጻጻ ጨመሩ እስከ ወህኒ ቤትም ድረስ በእግሩ ጐተቱት በዚያም ሁለት ቀኖች ኖረ ከዚህም በኋላ አውጥቶ እሳትን በተመላች ጕድጓድ ውስጥ ጣለው ክብር ይግባውና ጌታችንም አዳነው ምንም ምን አልነካውም።

ብዙ ከማሠቃየቱም የተነሣ መኰንኑ በሰለቸ ጊዜ ራሱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘና ቆረጡት በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ታላቁ_ቅዱስ_መቃርስ

ዳግመኛም በዚሀች ዕለት የታላቁ አባ መቃርስ መታሰቢው ሆነ፡፡ መቃርስ (መቃርዮስ) ማለት "ቅዱሱ ለእግዚአብሔር" ማለት ነው፡፡ ከደቡባዊ ግብፅ ከተወደዱ ደጋግ ክርስቲኖች የተገኘ ታላቅ አባት ነው፡፡ አባታቸው አብርሃም እናታቸው ሣራ ይባላሉ፡፡ እነርሱም መጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንዳሉት እንደ አብርሃምና ሣራ እጅግ ደጎች ነበሩ፡፡ ልጅ ግን አልነበራቸውምና በስለት መቃርስን ወለዱ፡፡ ሲያድጉም በግድ ያለፈቃዳቸው ሚስት አጋቧቸው፡፡ አባ መቃርስ ግን ወደ ሙሽራይቱ በገቡ ጊዜ ዐውቀው እንደታመሙ ሆነው ተኙ፡፡ ‹‹ከበሽታዬ ለጥቂት ጊዜ ጤና ባገኝ ወደ ገዳም ልሂድ›› ብለው ወደ አስቄጥስ በረሃ ሄዱ፡፡ መልአክም ተገልጦ ‹‹ይህች አስቄጥስ የአንተና የልጆችህ ርስት ናት›› አላቸው፡፡ ወደ ቤተሰባቸውም በተመለሱ ጊዜ ሙሽራ እጮኛቸው በድንግልና እንዳለች ሞታ ደረሱ፡፡ ከጥቂት ቀንም በኋላ እናትና አባታቸውም ዐረፉ፡፡ እርሳቸውም ንብረታቸውን ሁሉ ለድሆች መጽውተው ገዳም ገቡ፡፡ ሕዝቡም ደግነታቸውንና እውነተኛነታቸውን አይተው ትንሽ ማረፊያ ሠርተው ሌሎች እንዲያገለግሏቸው አደረጉ፡፡

ከዕለታትም በአንድ ቀን አንዲት ሴት ልጅ ከጎረምሳ አርግዛ ሳለ ጎረምሳው ‹‹አባትሽ ሲጠይቅሽ ከአባ መቃርስ አረገዝኩ በይ›› ብሎ መከራትና ለአባቷ እንደተባለችው ተናገረች፡፡ ‹‹አባ መቃርስ በግድ ደፍረውኝ አረገዝኩ›› አለች፡፡ የከተማው ሰውም አባ መቃርስን ከበዓታቸው አውጥተው ለሞት እስኪደርሱ ድረስ ደበደቧቸው፡፡ መላእክትም በሰው አምሳል ተገልጠው ዋስ ሆነው ለልጅቷም ምግቧን ሊሰጡ ተስማምተው ወደ በዓታቸው መለሷቸው፡፡ አባ መቃርስም ለራሳቸው ‹‹መቃርስ ሆይ እንግዲህ ባለ ሚስትና ባለ ልጅ ሆነሃልና ሌሊትና ቀን መሥራት ይገባሃል›› እያሉ ቅርጫቶችን እየሠፉ ለሚያገለግላቸው ልጅ እየሰጡት እርሱ ሸጦ እያመጣ ብዙውን ለዚያች በዝሙት ጸንሳ በሳቸው ላሳበበች ሴት ይሰጡ ጀመር፡፡ መውለጃዋም በደረሰ ጊዜ እስከ 4 ቀን ድረስ በጽኑ ሥቃይ ቆየች፡፡ እውነቱንም ተናግራ ንስሓ በገባች ጊዜ ወደ አባ መቃርስ ዘንድ አደረሷት፡፡ ሕዝቡም ሁሉ ‹‹አባታችን ይቅር በሉን›› ብለው ከእግራቸው ላይ ሲወድቁ ይቅር ብለዋቸው ቀድሰው አቆረቧቸው፡፡

ከዚህ በኋላ መልአኩ ወስዶ አስቄጥስ ገዳም አደረሳቸው፡፡ የቅዱሳኑ የመክሲሞስና የዱማቴዎስ በዓት ወደ ሆነች ቦታም አስገብቶ በዚያ በልጆቻቸው ቦታ ላይ በዓታቸውን እንዲያጸኑ ነገራቸው፡፡ አባ መቃርስ ወደ አባ እንጦንስ ዘንድም በመሄድ በረከታቸውንና ምክራቸውን ይቀበሉ ነበር፡፡ ሰይጣናትም በእርሳቸው ላይ የሚያደርሱትን ክፉ ነገር ሲመካከሩ ይሰሟቸው ነበር፡፡ በእሳት እያቃጠሉ ፈተኗቸው፣ የዝሙት መንፈስ እያመጡም ፈተኗቸው፣ በዚህም ትዕግስትን ቢያደርጉ በሌላም ዓለማዊ ክብርን መውድን፣ ትዕቢትን፣ መመካትን፣ ታካችነትን፣ ስድብን፣ ሃይማኖት ማጣትን፣