መዝገበ ቅዱሳን
23.5K subscribers
1.96K photos
9 videos
6 files
27 links
የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው! መ/ሳ 1÷7
Bewust mesimer lemanegager
@Yesadkusitota
የሰማነውን እንናገራለን
ያየነውን እንመሰክራለን
Download Telegram
ሐዋርያት ሆይ በእግዚአብሔር ፊት እስከምትቆሙ እጠብቃችሁ ዘንድ ከእኔ ርዳታን ሹ። የዚህ የመላእክት አለቃ የከበረ መልአክ ሩፋኤል ተአምራቶቹ ብዙ ናቸው ስለእኛ ይማልድ ዘንድ የበዓሉን መታሰቢያ ልናደርግ ይገባናል።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_መልከጼዴቅ

በዚህችም ቀን ለእግዚአብሔር ልጅ ምሳሌው የሆነ የመልከጼዴቅ መታሰቢያው ነው። መልከጼዴቅም ዐሥራ አምስት ዓመት በሆነው ጊዜ ከአዳም ሥጋ ጋር እንዲልከውና በምድር መካከል እንዲያኖረው እግዚአብሔር ኖኅን አዘዘው እርሷም ቀራንዮ ናት። የዓለም መድኃኒት ክርስቶስም መጥቶ በዚያ እንደሚሠዋ አዳምንም ከልጆቹ ሁሉ ጋር እንደሚያድነው አመለከተው።

ከዚህም በኋላ በአባቱ በኖኅ ትእዛዝ ሤም መልከጼዴቅን በሥውር ወሰደው የእግዚብሔርም መልአክ እየመራቸው ሔደው ወደ ቀራንዮ ተራራም አደረሳቸው መልከጼዴቅም ክህነትን ተሾመ። ዐሥራ ሁለት ደንጊያዎችንም ወስዶ መሠዊያ ሠራ ከሰማይ የወረደለትንም ኅብስትና ወይን መሠዊያ በሠራቸው ደንጊያዎች ላይ መሥዋዕትን አሳረገ።

ምግቡንም መላእክት ያመጡለታል ልብሱም ዳባ ነው በአባታችን አዳም ሥጋ ዘንድ ሲያገለግል ኖረ። አብርሃምም ከጦርነት ነገሥታትን ድል አድርጎ በተመለሰ ጊዜ ኅብስትንና ወይንን አቀረበለት አብርሃምም ከገንዘቡ ሁሉ ከዐሥር አንድ ሰጠው እርሱ ካህንም ንጉሥም ሁኖ ተሹሟልና።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አፄ_ዘርዓ_ያዕቆብ_ጻድቁ

በዚህችም ቀን የኢትዮጵያ ንጉሥ መልካም ስም አጠራር ያለው ዘርዐ ያዕቆብ አረፈ። ዘርዐ ያዕቆብ ብሎ ስሙን መልአክ ነው ያወጣለት፡፡ ሲወለድም ብርሃን ቤቱን ሞለቶት ታይቷል፡፡ ግማደ መስቀሉን ከአባቱ ከዐፄ ዳዊት ተረክቦ በማስመጣት በግሸን አስቀምጦታል፡፡ ንግሥቲቱ የዐፄ ዳዊት ሚስት የጻድቁን የደብረ ቢዘኑን የአቡነ ፊሊጶስን እግራቸውን አጥባቸው ስትጨርስ የእግራቸውን እጣቢ ከጠጣችው በኃላ የእምነቷን ጽናትና ጥልቀት አይተው ጻድቁ ባደረባቸው መንፈስ ቅዱስ ትንቢትን በመናገር "ከማኅፀንሽ ፍሬ ታላቅ ጻድቅ ልጅ ይወጣል" ብለው ትንቢት ነገሯት፡፡ በትንቢታቸውም መሠረት ታላቁ ጻድቅ ንጉሥ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ተወልዱ፡፡

ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ለሀገራችንም ሆነ ለቤተ ክርስቲያናችን ታላቅ ውለታ ውለዋል፡፡ ጣዖት አምልኮን ከሃገራችን ለማጥፋት ብዙ ሺህ ካህናትን አሰልጥነው በመላ አገራችን አሰማርተዋል፡፡ የኑፋቄ ችግሮችን ለመቅረፍ ጉባኤያትን አዘጋጅተዋል፡፡ ተአምረ ማርያምን ጨምሮ ከ11 ያላነሱ መጻሕፍትን በመንፈስ ቅዱስ አጋዥነት ደርሰው ለአገልግሎት አብቅተዋል፡፡ ብዙ መጻሕፍትን ከውጪ አስመጥተው አስተርጉመዋል፡፡ ሰው ሁሉ ለእመ ብርሃንና ለቅዱስ መስቀሉ ፍቅር እንዲገዛ ጥረት አድርገዋል፡፡ እመቤታችንን በፍጹም ልባቸው ከመውደዳቸው የተነሳ ዛሬም ድረስ በሃገራችን ድንግል ማርያም "የዘርዓ ያዕቆብ እመቤት" እየተባለች ትጠራለች፡፡ ብዙ አብያተ ክርስቲያናትን አንጸው ብዙ ሥርዓቶችም በሊቃውንት እንዲሠሩ አድርገው ሌሎች ብዙ በጐ ተግባራትንም ፈጽሞ በዚህች ዕለት በሰላም ዐርፈዋል፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ሰራጵዮን_ዘሰንዱን

በዚህችም ቀን ሰንዱን ከሚባል አገር ቅዱስ ሰራጵዮን አረፈ። ይህም ቅዱስ ከታናሽነቱ ጀምሮ የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍትን ትርጓሜያቸውንም ተማረ የዚህንም ዓለም ገንዘብ ሁሉ ትቶ ወደ አረሚ አገር ሔደ ራሱንም በሃያ ብር ሸጦ ማገልገል ጀመረ የሽያጩንም ዋጋ ጠበቀው። እንጀራ ሳይበላ ውኃ ሳይጠጣ ከስሕተታቸው ይመልሳቸው ዘንድ ሁል ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ይጸልይ ነበር።

ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት በሆነ በክርስቶስ አሳመናቸው ሕግንና ሥርዓትንም ሁሉ አስተማራቸው ከዚህም በኋላ ስለርሳቸው ራሱን ባሪያ አድርጎ እንደሸጠ እንጂ እርሱ ባሪያ እንዳልሆነ ነገራቸው ሽያጩንም ለድኆች እንዲሰጡት ሰጣቸው።

ከዚህም በኋላ መንካያውያን ወደሚባሉ ሕዝቦች ሒዶ ለነርሱም ራሱን ሸጠ የክብር ባለቤት ወደሆነ ክርስቶስ እምነት እስከመለሳቸው ድረስ ተገዛላቸው። ከዚህም በኋላ ደግሞ ወደ ሮሜ አገር ሒዶ በሰላም እስከ አረፈ ድረስ በጾምና በጸሎት እየተጋደለ ኖረ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በመልአኩና በቅዱሳኑ አማላጅነት ይማረን በረከታየውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ጳጉሜንና #ዲያቆን_ዮርዳኖስ_አበበ እና #ከገድላት_አንደበት)