መዝገበ ቅዱሳን
20.7K subscribers
1.92K photos
9 videos
6 files
25 links
የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው! መ/ሳ 1÷7
Bewust mesimer lemanegager
@Yesadkusitota
የሰማነውን እንናገራለን
ያየነውን እንመሰክራለን
Download Telegram
🌸 " ክርስቶስ አይደለም ብሎ ኢየሱስን ከሚክድ በቀር ውሸተኛው ማን ነው? አብንና ወልድን የሚክድ ይህ የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው።" (1ኛ ዮሐ 2:22) 🌸

#መልስ ለደቂቀ ኤልያሳውያን 👉 / የሐሰተኛው ኤልያስ ተከታዮች።/ ክፍል 1

" እናንተስ እኔ ማን እንደ ሆንሁ ትላላችሁ? ብሎ ጠየቃቸው። ጴጥሮስም። አንተ ክርስቶስ ነህ ብሎ መለሰለት።"(ማር 8:29) እኛም ጌታ ሆይ ዛሬም ነገም ለዘላለምም አንተ ክርስቶስ ነህ እንልካለን።

አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በነቢዩ ኤልያስ ስም የሚነግደውን የሐሰተኛ የኤልያስን መንፈስን ከአለማችን አስወግዶ ለህዝበ ክርስቲያኖች አንድነቱን ይሰጠን ዘንድ ጸልዩ!

ደቂቀ ኤልያሳውያን ክርስቶስ የሚለውን ስም መስማትም ሆነ ማየትም አይፈልጉም። ምክንያታቸውም ቃሉ የግሪክ ነው አንቀበልም እኛ ኢትዮጵያውያን ነን... ብለው የማይመስል መልስ ይመልሳሉ። ኢትዮጲያዊነትማ ክርስቶስ የሚለውኖ ስም የሚያስክድ ሳይሆን እንደ ጃንደረባው ባኩስ ክርስቶስ በሚለው ስም አሳምኖ በስሙ የሚያስጠምቅ ማንነት ነው ሐዋ 8:37-38። ቃሉ የምንም ይሁን ክርስቶስ የሚለው ስም በሐዋርያት የተሰበከ ፣ በአበው የተመሰከረ ፣ በሰማዕታት ልብ ውስጥ ያለ በደማቸውም የተጻፈ የአምላካችን ስም ነው። ቃሉ የግሪክ ቃል ነው ብሎ አልቀበልም ማለት የቋንቋ ዘረኝነትን ያሳያል። እግዚአብሔር አምላክ ለሐዋርያት ሀብተ ልሳንን የሰጠው በዘር እንዲከፋፈሉበት ሳይሆን ወንጌልን ለአለም እንዲያስተምሩበት ነው። ሂዱና አህዛብን አስተምሩ ሲላቸው እንዲሁ ወደ አለም አላካቸውም። ልሳንን - ቋንቋን ገልጦላቸው ነው። ከተገለጠላቸው 71 ቋንቋዎች መካከል አንዱ ደግሞ ግሪከኛ ነው። ስለዚህ ከአጉል ፍልስፍና ወጥተን ክርስቶስ በሚለው ስም አምነን ከእግዚአብሔር ዳግም ብንወለድ ይበጀናል።

ኢየሱስ ክርስቶስ የስሙ ትርጉም።

#ኢየሱስ 👉 ኢየሱስ ማለት አዳኝ መድኃኒት ማለት ነው፡፡ ይህ ስሙ ቅድመ ዓለም በአብ ኅሊና ታስቦ ይኖር እንደነበር መልክአ ኢየሱስ ይመሰክራል፡፡ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል እመቤታችንን ሲያበሥራት “ስሙንም ኢየሱስ ትይዋለሽ” ብሏታል፡፡ ሉቃ. 1.21፡፡ እመቤታችንና ዮሴፍ ጌታ በስምንት ቀኑ ወደ ቤተ ግዝረት ሲገባ በመልአኩ እንደ ተነገራቸው ኢየሱስ ብለው ጠሩት፡፡ ሉቃ. 2÷21፡፡ ከአምልኮ ጸሎት ፈውስና አገልግሎት የሚከናወነው በዚህ በስሙ ነው፡፡ ይህ ስም የባሕታዊያን የተመስጦ ማዕከል የማኅሌታዊያን የዜማቸው ጣዕም የሰባክያን የአትሮንሳቸው ግርማ ሞገስ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን ከዚህ ስም ውጭ ውበት ደምግባት የላትም፡

#ክርስቶስ 👉 ክርስቶስ ማለት የተቀባ መሲህ ማለት ነው፡፡ አይሁድ የጠበቁት መሲህ ነቢያትና ጻድቃን ሊያዩት የናፈቁትጌታ የነፍስ ነጻ አውጪ ስለሆነ ክርስቶስ አሉት፡፡ " ክርስቶስ ነው ብሎ በኢየሱስ የሚያምን ሁሉ ከእግዚአብሔር ተወልዶአል፥ ወላጁንም የሚወድ ሁሉ ከእርሱ የተወለደውን ደግሞ ይወዳል።"(1ኛ ዮሐ 5:1) ዕብራይስጡ "ማሽያሕ" ይላል። ትርጉሙ የተቀባ መሲሕ ማለት ነው። ክርስቶስ ማለት ቅቡዕ ማለት ነውና። እናም ጌታ ራሱ ቅብዕ/ቅባት/፤ ራሱ ቀቢዕ /የሚቀባ/፤ ራሱ ተቀቢ /የተቀባ/ ነው ይህን ልብ በሉ። ክርስቶስ ማለት ከግሪክኛ ቋንቋ #Χριστός ነው ፤ በአረብኛ ﻣﺴﻴﺢ ፤ מָשִׁ֫יחַ የሚለው የእብራይስጥ ቃል “መሢሕ” משיחא የሚለው የአረማይ ቃል ሴማዊ መነሻ ሲኖረው ትርጉሙ “የተቀባ” ማለት ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ ለደቂቀ ኤልያሳውያንና ለመሰሎቻቸው መልዕክት አለው ይህም በግሪካዊ አይሁዳዊ እያላቹህ ህዝቡን በቋንቋና በዘር አትከፋፍሉ ይላል " በአይሁዳዊና በግሪክ ሰው መካከል ልዩነት የለምና፤ አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ ነውና፥ ለሚጠሩትም ሁሉ ባለ ጠጋ ነው፤"(ሮሜ 10:12) ይህ ክርስቶስ የሚለውን ስም 👉 ልጅነትን ሲያሰጥ፣ ሽባውን ሲተረትር ፣ አይንን ሲያበራ፣ አጋንትን ሲቀጣና የሞተን ሲያስነሳ አይተናል፤ ያየነውንም እንመሰክራለን ''ጴጥሮስ ግን። ብርና ወርቅ የለኝም፤ ይህን ያለኝን ግን እሰጥሃለሁ፤ በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሣና ተመላለስ አለው፤ በቀኝ እጁም ይዞ አስነሣው፤ በዚያን ጊዜም እግሩና ቍርጭምጭምቱ ጸና፥'' / ሐዋ 3:6-7 / ሐዋ 8:12/

ይህ ብቻ አይደለም ደቂቀ ኤልያሳውያን (የሐሰተኛው ኤልያስ ተከታዮች) ኦርቶዶክስ የሚለውን ስምንም አይቀበሉም። ምክንያታቸውም ያው እንደተለመደው የግሪክ ቃል ነው የሚል ነው። እነዚህ ሰዎች ልክ አህተ ማርያም ተከታዮች ጋርም ያመሳስላቸዋል። እነርሱም ኦርቶዶክስ የሚው ቃል የግሪክ ነው ብለው አይቀበሉትም። ከዚህ የምንረዳው ነገር ቢኖር የሚመራቸው እርኩስ መንፈስ አንድ እንደሆነ ነው።

ኦርቶዶክስ ማለት ምን ማሐት ነው?

“ኦርቶዶክስ” የሚለው ቃል የግሪክ ቃል ሲሆን የተቀናበረው “ኦርቶ” እና “ዶክስ” ከሚሉት ሁለት ቃላት ነው፡፡ትርጉማቸውም ኦርቶ ማለት ቀጥተኛ: ትክክለኛ : ርትዕት ማለት ሲሆን ዶክስ ማለት ደግሞ እምነት/ሃይማኖት ማለት ነው፡፡ በአንድነት ሲሆኑ ኦርቶዶክስ ማለት ቀጥተኛ፡ ትክክለኛ ፥ ርትዕት እምነት/ሃይማኖት ማለት ነው ኤር 6:16 - ኤፌ 4:5/

👉 ኦርቶዶክስ የሚለው ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ አገልግሎት ላይ የዋለው በ325 ዓ.ም በኒቅያ ጉባዔ ነው፡፡ በኒቅያ “ወልድ ፍጡር ነው” የሚለውን የአርዮስን የክህደት ትምህርት ለማውገዝና ሃይማኖታቸውን ለማፅናት የተሰበሰቡ ሃይማኖታቸው የቀና 318ቱ ሊቃውንት ይህን ቃል የተጠቀሙት ሐዋርያት ያስተማሯት ሃይማኖት ቀጥተኛና ትክክለኛ ናት ለማለት ነው፡፡ ሌሎች እንደ አርዮስ ክህደት ያሉት በየዘመኑ የሚነሱት ልዩ ልዩ አዳዲስ ትምህርቶች የምንፍቅና መሆናቸውን ለማረጋገጥ ይህችን ሃይማኖት ኦርቶዶክስ ብለዋታል፡፡ ይህንን ስም አልቀበልም ማለት የአበው የቀናች ሀይማኖትን እንደ መካድ ነው። ። #ተዋህዶ ማለትስ ከየት የመጣ ነው? ተዋህዶ ማለት ተዋሃደ ከሚለው የግእዝ ግስ የተወሰደ ሲሆን ትርጉሙ አንድ ሆነ መለኮትና ስጋ አንድ ሆነ ማለት ነው፡፡ ከሁለት አካል አንድ አካል ፤ከሁለት ባህሪ አንድ በህሪ ሆነ ማለት ነው በሌላ አካሄድ ደግሞ ተዋሃደ ማለት መለኮት ስጋ ለበሰ ከድንግል ማርያም ከስጋዋ ስጋ ከነብሷ ነብስ ነሳ ማለታችን ነው፡፡ ይህም ደግሞ ግልፅ የሆነ እውነት ነው ዮሐ1:1/ዮሐ 1:14/ ገላ 4:4/፡፡ በመጨረሻም ቅዱስ አትናቴዎስ በተናገረውን ንግግር እንጨርስ " ኦርቶዶክስ ማለት ክርስቶስ ያስተማራት ሐዋርያት የሰበኳት አበውን የጠበቋት ናት'' ( ቅዱስ አትናቴዎስ 296-373 ዓ.ም)

ክርስቶስን በማመን በቀናችው በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት እንጽና።

ክፍል 2 ይቀጥላል።
@petroswepawulos