መዝገበ ቅዱሳን
25.5K subscribers
1.97K photos
9 videos
6 files
27 links
የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው! መ/ሳ 1÷7
Bewust mesimer lemanegager
@Yesadkusitota
የሰማነውን እንናገራለን
ያየነውን እንመሰክራለን
Download Telegram
††† መስከረም 4 ቀን የሚከበሩ የቅዱሳን በዓላት †††

††† እንኳን ለታላቁ ነቢይ ቅዱስ ኢያሱ እና ለቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቅዱስ ኢያሱ ነቢይ ወመስፍን †††

††† ቅዱሱ የተወለደው በምድረ ግብፅ በባርነት ከነበሩ እሥራኤላውያን ሲሆን የቀደመ ስሙ #አውሴ ይባላል:: ዘመኑ #እግዚአብሔር ሕዝቡን ከ215 ዓመታት ባርነት ሊያወጣ የተቃረበበት ነውና #ሊቀ_ነቢያት_ሙሴ ከምድያም ሲመለስ ከመረጣቸው ተከታዮቹ ዋነኛው ኢያሱ ነበር:: እሥራኤል ከባርነት ሲወጡ ሙሴ 80 ዓመቱ: ኢያሱ ደግሞ 40 ዓመቱ ነበር::

ሕዝቡ አንገተ ደንዳና ነበርና ለ40 ቀን የታሠበላቸውን መንገድ 40 ዓመት እንዲሆን አደረጉት:: በዚህ ጊዜ ኢያሱ ከመምሕሩ ከሙሴና ከሕዝቡ አልተለየም:: አውሴን ኢያሱ ብሎ ስም የቀየረለት ሙሴ ሲሆን ይሔውም በፈቃደ እግዚአብሔር ነው::

ኢያሱ ማለት " #መድኃኒት" ማለት ነው:: ለዚሕም ምክንያቶች አሉት:-
1.ለጊዜው አማሌቃውያንን ድል ነስቶ ሕዝቡን አድኗል: ምድረ ርስትን አውርሷል::
2.ለፍጻሜው ግን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ (ጥላ) እንዲሆን ነው::

ቅዱስ ኢያሱ በበርሃው ለዘመናት እግዚአብሔርን አምልኮታል:: ሊቀ ነቢያትን ታዞታል (አገልግሎታል): እሥራኤልንም የጦር አለቃ ሆኖ ከአሕዛብ እጅ አድኗቸዋል:: በዚህም በእግዚአብሔርና በሕዝቡ ዘንድ ሞገስን አግኝቷል:: ቅዱስ ሙሴ #ደብረ_ናባው ላይ ባረፈ ጊዜ ሕዝቡን: ካሕናቱንና ታቦተ ጽዮንን ተረከበ:: ይህን ጊዜ ዕድሜው 80 እየሆነ ነበር::

††† እግዚአብሔርም ኢያሱን "ከአንተ ጋር ነኝ" ብሎ በሕዝቡ ላይ ነቢይና መስፍን (አስተዳዳሪ) እንዲሆን ሾመው:: ቅዱሱም ሰላዮችን ልኮ አስገምግሞ:
¤ባሕረ ዮርዳኖስን ከፍሎ:
¤ሕዝቡን አሻግሮ:
¤የኢያሪኮን ቅጥር 7 ጊዜ ዙሮ:
¤በኃይለ እግዚአብሔር አፍርሶ:
¤የኢያሪኮን ነገሥታት አጥፍቶ:
¤ለሕዝቡ ምድረ ርስትን አወረሰ::

የገባዖን ሰዎች "አድነን" ብለው በላኩበት ጊዜ ነገሥተ አሞሬዎንን ይወጋ ዘንድ ኢያሱ ወጣ:: እነዛን ግሩማን ነገሥታት በፈጣሪው ኃይል: በጦርና በተአምራት ድል ነስቶ የእግዚአብሔር ስሙ ከፍ ከፍ አለ:: በዚሕች ዕለትም ለ12ቱ ነገደ እሥራኤል ርስትን ሲያካፍል ፀሐይን በገባዖን: ጨረቃን ደግሞ በቆላተ ኤሎም (በኤሎም ሸለቆ) አቆመ::

ሰባት #አሕጉራተ_ምስካይ(የመማጸኛ ከተሞችን) ለየ:: ነቢይና መስፍን ሆኖ ሕዝቡን ለ40 ዓመታት አገለገለ:: በመጨረሻም ለሕዝቡ:- "እኔና ቤቴ እግዚአብሔርን እናመልካለን:: (ኢያ. 24) እናንተስ?" አላቸው:: እነርሱም "እኛም እንዳንተ ነን" አሉት:: ለዚህም ምልክት ይሆን ዘንድ 3 ገጽ ያላት ሐውልትን በመካከላቸው አቆመ::

ይህችውም የቅድስት #ድንግል_ማርያም ምሳሌ ናት:: ሐውልቷ 3 ገጽ እንዳላት እመቤታችንም በ3 ወገን (በነፍስ: በሥጋ: በልቡና) ድንግል ናት:: አንድም በ3 ወገን (ከኃልዮ: ከነቢብ: ከገቢር ኃጢአት) ንጽሕት ናት:: ለዚህም ነው #አባ_ሕርያቆስ
"ሐውልተ ስምዕ ዘኢያሱ" (የኢያሱ የምስክር ሐውልት አንቺ ነሽ) ሲል ያመሰገናት::

ታላቁ ነቢይ ኢያሱ ግን ከግብጽ በወጡ በ80 ዓመት: በተወለደ በ120 ዓመቱ (ጥሬው መጽሐፍ ቅዱስ በ110 ዓመቱ ይላል) በወገኖቹ መካከል ዐርፎ በያዕቆብ መቃብር ተቀበረ:: እሥራኤልም ለ30 ቀናት አለቀሱለት::

††† ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ †††

††† አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ ወንጌሉ እንደነገረን በመንግስተ ሰማያት ታላቁ ሰው ወንጌላዊው ዮሐንስ ነው::

ቅዱሱ ሐዋርያ ከዘብዴዎስና ከማርያም ባውፍልያ ተወልዶ: በገሊላ አካባቢ አድጐ: ገና በወጣትነቱ መድኃኔ ዓለምን ተከትሎታል:: ቅዱስ ዮሐንስ ከሐዋርያት ቀድሞ ጌታን ከመከተሉ ባሻገር በምንም ምክንያት ከጐኑ አይጠፋም ነበር:: ስለ ንጽሕናውና በጐ የፍቅር ሕሊናው ሕጻን ሳለ በወንድሞቹ ሐዋርያት ዘንድ ሞገሱ ከፍ ያለ ነው::

ጌታችንን እስከ እግረ #መስቀሉ ድረስ በመከተሉ ድንግል እመቤታችንን ተቀብሏል:: ከእርሷ ጋር ለ15 ዓመታት ቢቀመጥ መዝገበ ምሥጢር ሆነ:: ስንኩዋን ከሰው ልጆች ይቅርና ከልዑላኑ መላዕክትም ማዕረጉ ከፍ አለ:: ሰው ቢበቃ መላእክትን ሊያይ ይቻለዋል:: ቅዱስ ዮሐንስን ግን መላእክት ሊያዩት ይከብዳቸዋል:: ከፍጥረት ወገን ከእመ ብርሃን ቀጥሎ ክቡር እርሱ ነው::

ቅዱሱ ከጌታችን ዕርገት በሁዋላ ለ70 ዓመታት በዚህ ምድር ሲኖር አብዛኛውን ጊዜውን ያሳለፈው በኤፌሶን አካባቢ ነው:: ሕዝቡን ወደ ክርስትና ለማምጣት በአፍም በመጽሐፍም ደክሟል::

ሶስት መልዕክታት: ራዕዩንና ወንጌልን ጽፎላቸዋል:: ሕይወትን ስለ ሰበከላቸው በፈንታው ብዙ አሰቃይተውታል:: ከእሳት እስከ ስለት: እስከ መጋዝም በስተእርጅና ደርሶበታል:: እርሱ ግን በትእግስቱ ገንዘብ አድርጉዋቸዋል::

††† እናት ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ዮሐንስን ስትጠራው እንዲሕ ነው:-
¤ወንጌላዊ
¤ሐዋርያ
¤ሰማዕት ዘእንበለ ደም
¤አቡቀለምሲስ (ምሥጢራትን ያየ)
¤ታኦሎጐስ (ነባቤ መለኮት)
¤ወልደ ነጐድጉዋድ
¤ደቀ መለኮት ወምሥጢር
¤ፍቁረ እግዚእ
¤ርዕሰ ደናግል (የደናግል አለቃ)
¤ቁጹረ ገጽ
¤ዘረፈቀ ውስተ ሕጽኑ ለኢየሱስ (ከጌታ ጎን የሚቀመጥ)
¤ንስር ሠራሪ
¤ልዑለ ስብከት
¤ምድራዊው መልዐክ
¤ዓምደ ብርሃን
¤ሐዋርያ ትንቢት
¤ቀርነ ቤተ ክርስቲያን
¤ኮከበ ከዋክብት

††† በዚህች ዕለት ቅዱሱ ሐዋርያ ከእናቱ #ማርያም_ባውፍልያ: ከአባቱ #ዘብዴዎስ መወለዱን ቤተ ክርስቲያን ታስተምራለች::

††† አባ ሙሴ ዻዻስ †††

እሥራኤላዊ ሲሆኑ ከአቡነ #ሰላማ ቀጥለው የመጡ የሃገራችን ዻዻስ ናቸው:: ፍጹም ገዳማዊና ትጉህ: ባለ ረዥም ዕድሜ ጻድቅም ናቸው::

ገዳማቸው #ወሎ ውስጥ ቢገኝም አስታዋሽ ያጣ ይመስላል:: መናንያኑ ለዕለት እንኩዋ የሚቀምሱት አጥተው ሲቸገሩ መመልከቱ እጅግ ያማል::

††† በቅዱስ ዮሐንስ ላይ ያደረ የእመቤታችን ድንግል ማርያምና የአንድ ልጇ ፍቅር በእኛም ላይ ይደር:: ቸሩ ጌታ ስም አጠራራቸው ካማረና ከከበረ ወዳጆቹ በረከትን ያሳትፈን::

††† መስከረም 4 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ኢያሱ ወልደ ነዌ (ነቢይና መስፍን)
2.ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ (ልደቱ)
3.ቅዱሳን ዘብዴዎስና ማርያም ባውፍልያ
4.አባ መቃርስ ሊቀ ዻዻሳት
5.አባ ሙሴ ዻዻስ

††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ
2.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት
3.ቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ (ሰማዕት)

††† "አሁንም እግዚአብሔርን ፍሩ:: በእውነተኛም ልብ አምልኩት . . . እግዚአብሔርን ማምለክ ክፉ መስሎ ቢታያችሁ . . . የአሞራውያንን አማልክት ታመልኩ እንደ ሆነ: የምታመልኩትን ዛሬ ምረጡ:: እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን::" †††
(ኢያሱ. 24:14)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††@yedingelsitota

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
@petroswepawulos
ዘካርያስም ወታደሮችን እንዲህ አላቸው ሕፃኑን እኔ ወደሌላ ቦታ ወስጄዋለሁ ከእኔ ጋራ መጥታችሁ ራሳችሁ ከዚያ ቦታ ውሰዱት ወደ ቤተ መቅደስም እስከ አስገባቸው ድረስ ወታደሮቹ አብረውት መጡ። እርሱም ሕፃኑን ልጁን በመሠዊያው ጠርዝ ላይ አኑሮ ጸለየበት ይህም የልጁን መወለድ የእግዚአብሔር መልአክ ለእርሱ የነገረበት ነው።

ያን ጊዜም የእግዚአብሔር መልአክ ሕፃኑን ዚፈታ ወደሚባል በረሀ ነጥቆ ወሰደው ሕፃኑንም ባላገኙት ጊዜ አባቱን ዘካርያስን ገደሉት። ስለዚህም ጌታችን አይሁድን በቤተ መቅደሰ መካከል የገደላችሁት የዘካርያስ ደም በላያችሁ ይደርሳል አላቸው ለመገደሉ ምክንያት አይሁድ ናቸውና እንዲህ አለ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ዲማድዮስ

በዚህች ቀን የከበረ ዲማድዮስ ከግብጽ ደቡብ ደንጡ ከሚባል አውራጃ ደርሰባ ከሚሏት ከተማ በሰማእትነት አረፈ። እርሱ ሁል ጊዜ ወደ ቤተ ክርስቲያን ይገሠግሣል ድኆችንና በሽተኞችን መጐብኘትንም ይወዳል።

ብርሃናዊ ሰውም ተገልጦለት ሒዶ የሰማእትነት አክሊልን እንዲቀበል አዘዘው ሰማያዊ የሆነ ቃል ኪዳንንም ገባለት በዚህም እጅግ ደስ አለው።

አባቱንና እናቱንም ትቶ ከሀረጉ ወጣ ስለ ከበረ ስሙ በሚቀበለው መከራ ውስጥ ርዳታ እንዲሰጠው እንዲአጸናው ወደ እግዚአብሔር ጸለየ ወደ ሀገር አትሪብም ሔዶ በመኰንኑ ፊት ክብር ይግባውና በጌታችን ክርስቶስ ታመነ።

መኰንኑም ታላቅ ስቃይን አሰቃይቶ የእስክንድርያ አገረ ገዥ ወደ ሆነ ወደ ሉክያኖስ ሰደደው። በመርከብም ውስጥ ሳለ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገለጠለት በብዙ ደስታም አረጋግቶትና አጽናንቶ ቃል ኪዳንን ሰጠው ልቡናውም ፈጽሞ እጅግ ደስ አላት።

መኰንኑ ሉክያኖስም በጽኑዕ ስቃይ አሰቃይቶ ራሱን በሰይፍ ቆረጠ የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግስተ ሰማያት ተቀበለ። የሀገሩ ሰዎችም መጥተው ስጋውን ወሰዱ ታላቅ ክብርንም አከበሩት ከስጋውም ታላላቅ የሆኑ ድንቆችና ተአምራት ተገለጡ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_አሮን_ካህን

በዚህች ቀን የካህኑ አሮን በትሩ ለምልማ የተገኘችበት ነው። በቤተ ክርስቲያን ትውፊት መሠረት የቅዱሱ ካህን የአሮን በትር ሳይተክሏትና ውሃ ሳያጠጧት ለምልማ፣ አብባ፣ አፍርታ የተገኘችው በዚህ ቀን ነው። ዳታን፣ አቤሮንና ቆሬ ከተከታዮቻቸው ጋር በፈጠሩት ሁከት ምድር ተከፍታ ከዋጠቻቸው በሁዋላ እግዚአብሔር የ12ቱን ነገደ እሥራኤል በትር ሰብስቦ ሲጸልይበት እንዲያድር ሙሴን አዞት እንዲሁ ሆነ።

በነጋም ጊዜ ይህቺ ደረቅ የነበረች በትረ አሮን 12 ፍሬ (ለውዝ፣ ገውዝ፣ በኩረ ሎሚ) አፍርታ ተገኘች። (ዘኁ. 17፥1-11) ለጊዜው ክህነት ከቤተ አሮን እንዳይወጣ ምልክት ሆናለች። ለፍጻሜው ግን ምሳሌነቷ ለድንግል
ማርያም ነው። እመ ብርሃን የወንድ ዘር ምክንያት ሳይሆናት አምላክን ወልዳ ተገኝታለችና።

"ጸናጽል ዘውስተ ልብሱ ለአሮን ካህን ወዓዲ በትር እንተ ሠረጸት ወጸገየት ወፈረየት" እንዳለ #አባ_ሕርያቆስ። (#ቅዳሴ_ማርያም)

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም ቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_መስከረም)
#ግንቦት_1

በግንቦት አንድ በዚህችም ቀን አምላክን የወለደች #እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም ተወለደች፣ የከበረ #አባ_ሕርያቆስ ዘሃገረ ብሕንሳ የእመቤታችንን ቅዳሴ የደረሰበት ነው፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ልደታ_ለማርያም

በግንቦት አንድ በዚህችም ቀን አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደች እርሷም ለሰው ሁሉ ወገን ድኀነት የሆነባት ናት። ከወንዶች ወገን የከበረ አባቷም ስሙ ኢያቄም ከሴቶች ወገን የከበረች ሚስቱ ሐና ይባላሉ። ሁለቱም ልጅ በማጣት ሲያዝኑ ኖሩ በዚያ ወራት የመካኖችን መብዓ ካህናቱ አይቅበሉም ነበርና።

እነርሱም ከሰው የሚደርስባቸውን ሽሙጥና ኅዘናቸውን ያርቅላቸው ዘንድ በቀንና በሌሊት ወደ እግዚአብሔር ፈጽሞ ይማልዱ ነበር። ሰውን የሚወድ እግዚአብሔርም ከዘራቸው ለዓለሙ ሁሉ መድኃኒት ይሆን ዘንድ መልካም የሆነ ኀሳባቸውን ተመለከተ።

ክቡር እያቄምም አርባ ቀን እስኪፈጸም በተራራ ውስጥ ቁሞ ሲጸልይ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ተገለጸለትና ለዓለሙ ሁሉ ድኀነት የሚደረግባት ዘር እንደሚሰጠው አበሠረው።

በፍጹም ልብ አምኖ ከተራራው ወረደ ለተመሰገነች ሚስቱ ለሐናም ከእግዚአብሔር መልአክ የሰማውን ያንን ራእይ ነገራት ቃሉ እውነት እንደሆነ እርሷም አመነች ልዑል እግዚአብሔርንም አመሰገኑት።

የተመሰገነች ቅድስት ሐናም ከእርሷ የሚወለደውን በዘመኑ ሁሉ ለቤተ እግዚአብሔር አገልጋይ ታደርገው ዘንድ ለእግዚአብሔር ስለትን ተሳለች። ከዚህም በኋላ ይቺን የከበረች ሕፃን ፀንሳ ወለደች ስሟንም ማርያም ብላ ሰየመቻት ትርጓሜውም እመቤት ነው ደግሞም ሀብትና ስጦታ ማለት ነው።

በእውነት የዓለሙ ሁሉ እመቤት ናት ሁላችን በእርሷ ሰማያዊ ሀብት ልጅነትን ያገኘንባት። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን የሥጋና የነፍስ መድኃኒት የሆነች እርሷን እናቱን ለሰጠን በረከቷም ከሁላችን የክርስቲያን ወገኖች ጋራ ለዘላለሙ ይኑር አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አቡነ_ሕርያቆስ_ዘብሕንሳ

በዚህች ቀን የከበረ አቡነ ሕርያቆስ ዘሃገረ ብሕንሳ የእመቤታችንን ቅዳሴ የደረሰበት ነው፡፡ ሕርያቆስ ማለት ‹‹ኅሩይ-የተመረጠ›› ማለት ነው፡፡ እንዲሁም ደግሞ ምሥጢረ ሥላሴን ከሁሉ ይልቅ አራቆ ይናገራልና አባቶቻን ሕርያቆስ ማለት ‹‹ረቂቅ›› ማለት ነው ይሉታል፡፡ ‹‹አብ ፀሐይ ወልድ ፀሐይ መንፈስ ቅዱስ ፀሐይ›› ብሎ አመስግኗልና አሁንም ሕርያቆስ ማለት ‹‹ፀሐይ›› ማለት ነው ይሉታል፡፡ ደግሞም የምእመናንን ልቡና በትምህርቱ ብሩህ አድርጓልና ሕርያቆስ ማለት ‹‹ብርሃን›› ማለት ነው፡፡ አንድም ደግሞ ሕርያቆስ ማለት ‹ንብ› ማለት ነው፡፡ ንብ የማትቀምሰው አበባ እንደሌለ ሁሉ ሕርያቆስም ያልቀሰመው ሰማያዊ ዕውቀት የለምና እርሱን የማይጠቅሰው ሊቅ የለም፡፡

አባ ሕርያቆስ ስለ ምሥጢረ ሥላሴ እና ስለ ምሥጢረ ሥጋዌ የሚያመሰጥረውን እመቤታችንን በተለያዩ ምሳሌያት እየመሰለ የሚያመሰግንበትን ድንቅ የሆነውን ድርሰቱን ‹‹ቅዳሴ ማርያምን›› ሰማያዊ ምሥጢር ወለል ብሎ ተከፍቶለት ደርሶታል፡፡ የብሕንሳው ኤዺስቆዾስ ስላረፉ በእሳቸው ምትክ የሚሾሙትን ሲያፈላልጉ መንፈስ ቅዱስ አባ ሕርያቆስን መረጣቸው፡፡ የከበሩ ሐዋርያት ‹‹የተማረና ግብረ ገብ የሆነ ይሾም›› ብለው ሥርዓት ሠርተዋል፡፡ ደግሞም ‹‹ሁለቱን አስተባብሮ የያዘ ባይገኝ የተማረ ከሆነ ይሾም›› ብለዋል፡፡ ምክንያቱም በትምህርቱ መናፍቃንን ተከራክሮ ይመልሳልና ነው፡፡ ደግሞም ‹‹ግብረ ገብም ከሆነ ይሾም›› ብለዋል፡፡ ምክንያቱም በጸሎቱ ይጠብቃል በትሩፋቱ ያጸድቃልና ነው፡፡ በዚህም መሠረት አባ ሕርያቆስ ያልተማረ ነገር ግን ግብረ ገብ ነውና ‹‹ትምህርቱን ውሎ አድሮ ያደርገዋል›› ብለው ሾሙት፡፡ አባ ሕርያቆስም የተማረው ለጸሎት ለቅዳሴ ያህል ትንሽ ነበር፡፡ ከዚህም በኋላ ይህ ቅዱስ አባት በብሕንሳ ገዳም በ10000 መነኮሳት እና በ10000 መነኮሳይያት ላይ ተሹሞ የገዳሙ አስተዳዳሪ ሆነ፡፡

አባ ሕርያቆስ እመቤታችንን እጅግ ከመውደዱ የተነሣ ስሟን እንኳን ሲጠራ በመስጦ ልቡናው ይሰወርበት ነበር፡፡ ዘወትር ፍቅሯ ከማሰብ በቀር ሌላም አያስብም ነበር፡፡ እርሱ የነበረበት ዘመን የሊቃውንት ዘመን ስለነበር ሁሉም ለትምህርት ሲተጉ አባ ሕርያቆስ ግን ለጸሎትና ለደግነት ብቻ ይተጋ ነበር፡፡ የአባ ሕርያቆስ የሌት ተቀን ሞኞቱ ‹‹እንደ ቅዱስ ኤፍሬም የእመቤታችን ምስጋና እንደ ባሕር አሸዋ እንደ ሰማይ ኮከብ በዝቶልኝ እንደልብስ ለብሼም እንደ ምግብ ተመግቤው›› የሚል ነበር፡፡ ከልጅነቱ ጀምሮም እጅግ ስለሚወዳት እመቤታችንም ትጠብቀው ነበር፡፡ ከዕለታት በአንደኛው ቀን አባ ሕርያቆስ በበረኃ ብቻውን እየተጓዘ ሳለ የእመቤታችንን ፍቅር በልቡ ሲያመላልስ ስሟን እያነሣ ሲዘምር በተመሥጦ ውስጥ ሆኖ መንገድ ሳተና ከታላቅ ገደል ጫፍ ደርሶ ሳያስበው ወደቀ፡፡ ከገደሉም ጫፍ ደርሶ ከወደቀ በኋላ እጅግ ደንግጦ ራሱን ቢመለከት አካሉ ሳይጎድል ልብሱ ሳይቆሽሽ አገኘው፡፡ በዚህም ተገርሞ ያለበትን አካባቢውን ቢያማትር ራሱን ብርሃንን በተሞላ የልብስ ዘርፍ ላይ አገኘው፡፡ ያም ብርሃንን የተሞላ የልብስ ዘርፍ የእመቤታችን የቀሚሷ ዘርፍ ነው፡፡ በዚህም እጅግ ደንግጦ ‹‹እመ ብርሃን›› ብሎ ጮኸ፡፡ እመቤታችንም ከፊቱ ቁማ ተገለጠችለት፡፡ እርሱም የብርሃን እናቱ ድንግል ወላዲተ አምላክን በገሃድ በዐይኑ አጠገቡ ቆማ ቢያያት በደስታ ዘለለ፡፡ እመቤታችንም በቃሏ አነጋግራው ባርካው ተሰወረችው፡፡ እርሱም ፍቅሯ ጣዕሟ ቢመስጠው ከሰው ሳይገናኝ ምግብም ሳይበላ እዚያው እገደሉ ውስጥ አንድ ዓመት በምስጋና ብቻ በተመስጦ ኖሯል፡፡ በኋላም እመቤታችን ድጋሚ ተገልጣለት ከገደሉ አውጥታ ወደ ሀገሩ አድርሳዋለች፡፡

ከዚህም በኋላ አባ ሕርያቆስ እርሱ በተሾመባ በብሕንሳ ገዳም ሴትና ወንድ ያልተለየባት ገዳም ነበረችና በዚህች ገዳም የተሾመው አባ ሕርያቆስ ብዙም ትምህርት ስላልነበረው ይንቁት ነበር፡፡ ‹‹ከመጠምጠም መማር ይቅደም›› እንዲሉ ‹‹ከመሾም በፊት መማር አይቀድምም›› እያሉም ይዘብቱበት ነበር፡፡ እርሱ ግን እንደጠሉኝ ልጥላቸው ሳይል በፍቅር በትሕትና ይመክራቸው ነበር፡፡ እነርሱ ግን ‹‹በምን ምክንያት እንሻረው›› እያሉ ይመክሩ ነበር፡፡ ከዕለታት በአንድ ቀን ‹‹ቀድሰህ አቁርበን እንበለውና አይሆንም ካለን በዚህ ምክንያት እንሻረው?›› ብለው መከሩ፡፡ እርሱም ሥርዓተ ቅዳሴውን ፈጽሞ ወደፍሬ ቅዳሴው ሲደርስ የትኛውን ከባድ ቅዳሴ ቀድስ እንበለው?›› እያሉ ይመካከሩ ጀመር፡፡ እርሱ ግን ከቅዳሴ ሐዋርያት በቀር የሚያውቀው አልነበረም፡፡ አባ ሕርያቆስ እያዘነ ወደ መንበሩ ዞሮ ‹‹እመቤቴ ሆይ! መናቄን መገፋቴን ተመልከች›› ሲል ወዲያው እመቤታችን ወርዳ ጠራችውና በዘርፋፋው ቀሚሷ ላይ ረቂቅ የሆነ ቅዳሴን አሳየችው፡፡ የለመኗትን የማትነሣ፣ የነገሯትን የማትረሣ የብርሃን እናቱ እመቤታችንም የልቡን መሻት ተመልክታ ‹‹ጎስዐ ልብየ ቃለ ሠናየ ልቡናዬ በጎ ነገርን አወጣ›› በማለት ጀምሮ ‹‹ዛሬም አብን ወልድንና መንፈስ ቅዱስን እናመስግን›› እስከሚለው ድረስ ሰተት አድርጋ አስደርሳዋለች፡፡ እነርሱም ይህንን ግሩም የሆነውን ቅዳሴውን አደነቁ፡፡
††† 🌻✝️መስከረም 4 ቀን የሚከበሩ የቅዱሳን በዓላት †††🌻✝️

†††🌻✝️ እንኳን ለታላቁ ነቢይ ቅዱስ ኢያሱ እና ለቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††🌻✝️

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

†††🌻✝️ ቅዱስ ኢያሱ ነቢይ ወመስፍን🌻✝️ †††

††† ቅዱሱ የተወለደው በምድረ ግብፅ በባርነት ከነበሩ እሥራኤላውያን ሲሆን የቀደመ ስሙ #አውሴ ይባላል:: ዘመኑ #እግዚአብሔር ሕዝቡን ከ215 ዓመታት ባርነት ሊያወጣ የተቃረበበት ነውና #ሊቀ_ነቢያት_ሙሴ ከምድያም ሲመለስ ከመረጣቸው ተከታዮቹ ዋነኛው ኢያሱ ነበር:: እሥራኤል ከባርነት ሲወጡ ሙሴ 80 ዓመቱ: ኢያሱ ደግሞ 40 ዓመቱ ነበር::

ሕዝቡ አንገተ ደንዳና ነበርና ለ40 ቀን የታሠበላቸውን መንገድ 40 ዓመት እንዲሆን አደረጉት:: በዚህ ጊዜ ኢያሱ ከመምሕሩ ከሙሴና ከሕዝቡ አልተለየም:: አውሴን ኢያሱ ብሎ ስም የቀየረለት ሙሴ ሲሆን ይሔውም በፈቃደ እግዚአብሔር ነው::

ኢያሱ ማለት " #መድኃኒት" ማለት ነው:: ለዚሕም ምክንያቶች አሉት:-
1.ለጊዜው አማሌቃውያንን ድል ነስቶ ሕዝቡን አድኗል: ምድረ ርስትን አውርሷል::
2.ለፍጻሜው ግን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ (ጥላ) እንዲሆን ነው::

ቅዱስ ኢያሱ በበርሃው ለዘመናት እግዚአብሔርን አምልኮታል:: ሊቀ ነቢያትን ታዞታል (አገልግሎታል): እሥራኤልንም የጦር አለቃ ሆኖ ከአሕዛብ እጅ አድኗቸዋል:: በዚህም በእግዚአብሔርና በሕዝቡ ዘንድ ሞገስን አግኝቷል:: ቅዱስ ሙሴ #ደብረ_ናባው ላይ ባረፈ ጊዜ ሕዝቡን: ካሕናቱንና ታቦተ ጽዮንን ተረከበ:: ይህን ጊዜ ዕድሜው 80 እየሆነ ነበር::

††† እግዚአብሔርም ኢያሱን "ከአንተ ጋር ነኝ" ብሎ በሕዝቡ ላይ ነቢይና መስፍን (አስተዳዳሪ) እንዲሆን ሾመው:: ቅዱሱም ሰላዮችን ልኮ አስገምግሞ:
¤ባሕረ ዮርዳኖስን ከፍሎ:
¤ሕዝቡን አሻግሮ:
¤የኢያሪኮን ቅጥር 7 ጊዜ ዙሮ:
¤በኃይለ እግዚአብሔር አፍርሶ:
¤የኢያሪኮን ነገሥታት አጥፍቶ:
¤ለሕዝቡ ምድረ ርስትን አወረሰ::

የገባዖን ሰዎች "አድነን" ብለው በላኩበት ጊዜ ነገሥተ አሞሬዎንን ይወጋ ዘንድ ኢያሱ ወጣ:: እነዛን ግሩማን ነገሥታት በፈጣሪው ኃይል: በጦርና በተአምራት ድል ነስቶ የእግዚአብሔር ስሙ ከፍ ከፍ አለ:: በዚሕች ዕለትም ለ12ቱ ነገደ እሥራኤል ርስትን ሲያካፍል ፀሐይን በገባዖን: ጨረቃን ደግሞ በቆላተ ኤሎም (በኤሎም ሸለቆ) አቆመ::

ሰባት #አሕጉራተ_ምስካይ(የመማጸኛ ከተሞችን) ለየ:: ነቢይና መስፍን ሆኖ ሕዝቡን ለ40 ዓመታት አገለገለ:: በመጨረሻም ለሕዝቡ:- "እኔና ቤቴ እግዚአብሔርን እናመልካለን:: (ኢያ. 24) እናንተስ?" አላቸው:: እነርሱም "እኛም እንዳንተ ነን" አሉት:: ለዚህም ምልክት ይሆን ዘንድ 3 ገጽ ያላት ሐውልትን በመካከላቸው አቆመ::

ይህችውም የቅድስት #ድንግል_ማርያም ምሳሌ ናት:: ሐውልቷ 3 ገጽ እንዳላት እመቤታችንም በ3 ወገን (በነፍስ: በሥጋ: በልቡና) ድንግል ናት:: አንድም በ3 ወገን (ከኃልዮ: ከነቢብ: ከገቢር ኃጢአት) ንጽሕት ናት:: ለዚህም ነው #አባ_ሕርያቆስ
"ሐውልተ ስምዕ ዘኢያሱ" (የኢያሱ የምስክር ሐውልት አንቺ ነሽ) ሲል ያመሰገናት::

ታላቁ ነቢይ ኢያሱ ግን ከግብጽ በወጡ በ80 ዓመት: በተወለደ በ120 ዓመቱ (ጥሬው መጽሐፍ ቅዱስ በ110 ዓመቱ ይላል) በወገኖቹ መካከል ዐርፎ በያዕቆብ መቃብር ተቀበረ:: እሥራኤልም ለ30 ቀናት አለቀሱለት::

†††🌻✝️ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ🌻✝️ †††

††† አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ ወንጌሉ እንደነገረን በመንግስተ ሰማያት ታላቁ ሰው ወንጌላዊው ዮሐንስ ነው::

ቅዱሱ ሐዋርያ ከዘብዴዎስና ከማርያም ባውፍልያ ተወልዶ: በገሊላ አካባቢ አድጐ: ገና በወጣትነቱ መድኃኔ ዓለምን ተከትሎታል:: ቅዱስ ዮሐንስ ከሐዋርያት ቀድሞ ጌታን ከመከተሉ ባሻገር በምንም ምክንያት ከጐኑ አይጠፋም ነበር:: ስለ ንጽሕናውና በጐ የፍቅር ሕሊናው ሕጻን ሳለ በወንድሞቹ ሐዋርያት ዘንድ ሞገሱ ከፍ ያለ ነው::

ጌታችንን እስከ እግረ #መስቀሉ ድረስ በመከተሉ ድንግል እመቤታችንን ተቀብሏል:: ከእርሷ ጋር ለ15 ዓመታት ቢቀመጥ መዝገበ ምሥጢር ሆነ:: ስንኩዋን ከሰው ልጆች ይቅርና ከልዑላኑ መላዕክትም ማዕረጉ ከፍ አለ:: ሰው ቢበቃ መላእክትን ሊያይ ይቻለዋል:: ቅዱስ ዮሐንስን ግን መላእክት ሊያዩት ይከብዳቸዋል:: ከፍጥረት ወገን ከእመ ብርሃን ቀጥሎ ክቡር እርሱ ነው::

ቅዱሱ ከጌታችን ዕርገት በሁዋላ ለ70 ዓመታት በዚህ ምድር ሲኖር አብዛኛውን ጊዜውን ያሳለፈው በኤፌሶን አካባቢ ነው:: ሕዝቡን ወደ ክርስትና ለማምጣት በአፍም በመጽሐፍም ደክሟል::

ሶስት መልዕክታት: ራዕዩንና ወንጌልን ጽፎላቸዋል:: ሕይወትን ስለ ሰበከላቸው በፈንታው ብዙ አሰቃይተውታል:: ከእሳት እስከ ስለት: እስከ መጋዝም በስተእርጅና ደርሶበታል:: እርሱ ግን በትእግስቱ ገንዘብ አድርጉዋቸዋል::

††† እናት ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ዮሐንስን ስትጠራው እንዲሕ ነው:-
¤ወንጌላዊ
¤ሐዋርያ
¤ሰማዕት ዘእንበለ ደም
¤አቡቀለምሲስ (ምሥጢራትን ያየ)
¤ታኦሎጐስ (ነባቤ መለኮት)
¤ወልደ ነጐድጉዋድ
¤ደቀ መለኮት ወምሥጢር
¤ፍቁረ እግዚእ
¤ርዕሰ ደናግል (የደናግል አለቃ)
¤ቁጹረ ገጽ
¤ዘረፈቀ ውስተ ሕጽኑ ለኢየሱስ (ከጌታ ጎን የሚቀመጥ)
¤ንስር ሠራሪ
¤ልዑለ ስብከት
¤ምድራዊው መልዐክ
¤ዓምደ ብርሃን
¤ሐዋርያ ትንቢት
¤ቀርነ ቤተ ክርስቲያን
¤ኮከበ ከዋክብት

††† በዚህች ዕለት ቅዱሱ ሐዋርያ ከእናቱ #ማርያም_ባውፍልያ: ከአባቱ #ዘብዴዎስ መወለዱን ቤተ ክርስቲያን ታስተምራለች::

†††🌻✝️ አባ ሙሴ ዻዻስ🌻✝️ †††