መዝገበ ቅዱሳን
23.9K subscribers
1.97K photos
9 videos
6 files
27 links
የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው! መ/ሳ 1÷7
Bewust mesimer lemanegager
@Yesadkusitota
የሰማነውን እንናገራለን
ያየነውን እንመሰክራለን
Download Telegram
ሀዋርያ ቶማስ ግን ያን ጊዜ አልነበረም በደመና ላይ ተጭኖ እርሱ ሲመጣ መላእክት ሲአሳርጓት እመቤታችንን አገኛት መላእክትም ለአምላክ እናት ለእመቤታችን ድንግል ማርያም ና እጅ ንሳ አሉት እርሱም ሰገደላትና ተሳለማት ከእርሷም ተባረከ ከዚህም በኃላ ወደ ሀዋርያት ደረሰ ። እነርሱም እመቤታችንን ማርያምን እንደ አረፈችና እንደ ቀበርዋትም ነገሩት ቶማስም ስጋዋን እስከማይ አላምንም አላቸው።

ስጋዋንም ያሳዪት ዘንድ ወደ መቃብርዋ በአደረሱት ጊዜ በመቃብር ውስጥ ስጋዋን አላገኙም ደንግጠውም አደነቁ ያን ጊዜ ከመላእክት ጋር ወደ ሰማይ ስታርግ እመቤታችንን እንዳገኛት ቶማስ ነገራቸው። ሀዋርያትም ይህን በሰሙ ጊዜ የእመቤታችንን እርገቷን ስለ አላዩ እጅግ አዘኑ ስጋዋን በምድር ውስጥ ይተው ዘንድ እንዳልወደደ መንፈስ ቅዱስ አስገነዘባቸው። ከዚህም በኃላ አንድ ጊዜ ደግሞ እርሷን ያሳያቸው ዘንድ እንዳለው ጌታችን ቃል ኪዳን በማድረግ ተስፋ ስጣቸው እነርሱም እስከ ነሀሴ አስራ ስድስት በረስፋ ኖሩ።

የእመቤታችንም የእድሜዋ ዘመን ስልሳ አራት አመት ነው በአባትና እናቷ ቤት ሶስት አመት ከሰባት ወር በቤተ መቅደስም አስራ ሁለት አመት በዮሴፍም ቤት ሰላሳ አራት አመት ከሶስት ወር ከጌታ እርገት በኃላ በወንጌላዊ ዮሀንስ ቤት አስራ አራት አመት ነው።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅድስት_ኢላርያ

በዚህችም እለት የሮሜ አገር ንጉስ የዘይኑን ልጅ የከበረች ኢላርያ አረፈች። የዚችም ቅድስት አባቷ እግዚአብሔርን የሚውድ ሀይማኖቱ የቀና ነው ይቺን ቅድስት ኢላርያንና ሁለተኛዋን እኃቷን ወለደ ከእንርሱም በቀር ወንድ ልጅ የለውም። ይቺም ቅድስት ኢላርያ የምንኮስና ልብስን የመላእክትንም አስኬማ ትለብስ ዘንድ የምትመኝ ሆነች ከቤተመንግስትም ወጥታ ልብሷን ለውጣ የወንድ ልብስ ለብሳ ወደ ግብፅ ሀገር ሄድች።

ከዚያም ወደ አስቄጠስ ገዳም ደረሰች በዚያም ስሙ አበሰ ባውሚን የሚባለውን ፍፁም ሽማግሌ ፃድቅ ሰውን አግኝታ ሀሳቧን ሁሉ ነገረችው እርሷ ሴት እንደ ሆነችም አስረዳችው እርሱም ምስጢሯን ሰውሮ ለብቻዋ በዋሻ ውስጥ አስገባት ይጎበኛትና ልትሰራው የሚገባትን ያስተምራት ነበር። እንዲህም ሆና አስራ ሁለት አመት ኖረች ፅህም ስለሌላትም ለአረጋውያን መነኰሳት ጃንደረባ ትመስላቸው ነበር።በወንድ ስም አጠራርም አባ ኢላርዮን ብለው ይጠሩዋታል።

ከአባቷ ዘንድ በቀረችው በሁለተኛዋ ግን ርኩስ ሰይጣን አደረባትና ያሰቃያት ጀመር ያድኗትም ዘንድ ለባለ መድሀኒቶች አባቷ ብዙ ገንዘብ ሰጠ ግን አልተቻላቸውም። ከዚህም በኃላ የከበሩ አረጋውያን መነኮሳት ወዳሉበት አስቄጥስ ገዳም ይልካት ዘንድ መኳንንቶቹ መከሩት የቅድስናቸው ወሬ በሮም ሀገሮች ሁሉ ተሰምቷልና በዚያንም ጊዜ ወደ ቅዱሳኑ ከብዙ ሰራዊት ጋር ላካት ለቅዱሳኑም መልእክትን ፃፈላቸው እንዲህ ሲል የተከበራችሁ አባቶቼ ሆይ የደረሰብኝን ኃዘን አስረዳችኃለሁ እግዚአብሔር ሁለት ሴቶቸ ልጆችን ሰጥቶኝ ነበር።

አንዲቱ ከአለም ሸሸች ወደየት ቦታ እንደምትኖር አላውቅም በሁለተኛዪቱም በላይዋ ርኩስ መንፈስ ተጫነበት እኔ መፅናኛ ትሆነኛለች ብዬ እየሰብኩ ነበር አሁንም በፀሎታቸሁ እግዚአብሔር ያድናት ዘንድ በላይዋ እንድትፀልዩ አኔ ቅድስናችሁን እለምናሉ።

ቅዱሳን መነኮሳትም የንጉሱን ደብዳቤ በአነበቡ ጊዜ በላይዋ ሊፀልዩ ጀመሩ በላይዋ ያደረ ሰይጣንም ከኢላርዮን በቀር ከማደሪያዬ የሚያሰጠኝ የለም ብሎ ጮኸ። አርጋውያኑም ጃንደረባ የሚሏትን ኢላርያን ጠርተው እግዚአብሄር እስከ አዳናት ድረስ የንጉሱን ልጅ ወስደህ በላይዋ ፀልይ አሏት ቅድስት ኢለርያም እኔ በደለኛ ሰው ነኝ ይህን ጭንቅ የሆነ ስራን መስራት አልችልም አለቻቸው።

በአሰገደድዋትም ጊዜ ወደ በአትዋ ወሰዳ በላይዋ ፀለየች ሰይጣነም ትቷት ሸሸ እህቷ እንደሆነች ታውቃለች ስለዚህ አቅፋ ትስማት ነበር ስለ ናፍቆቷና ስለ ፍቅርዋ ወደ ውጭ ወጥታ ታለቅሳለች።

ከዚህም በኃላ ወደ ከበሩ አረጋውያን አደረሰቻችና እነሆ በፀሎታችሁ እግዚአብሔር አድኗታል ወደ አባቷ መልሷት አለቻቸው። እነርሱም እጅግ ደስ ብሏቸው ወደ አባቷ መለሱዋት ለእግዚአብሔርም ምስጋና አቀረቡ።

ወደ ሮሜ አገርም ወደ አባቷ በደረሰች ጊዜ አባትና እናቷ ስለ መዳንዋ በእርሷ እጅግ ደስ አላቸው የቤተ መንግስትም ሰዎችም ሁሉ እግዚአብሔርን አመሰገኑት።

አባቷም በገዳም ከቅዱሳን አባቶች ጋር አኗኗርሽ እንዴት ነበር ብሎ ጠየቃት እርሷም እንዲህ ብላ ነገረችው ያ ያዳነኝ አባ ኢላርዮን የሚባል አባት አብዝቶ ይወደኛል አቅፎም ይስመኛል ንጉሱም ይህን ሰምቶ በልቡ ታወከ ለመነኩሴ ሴቶችን መሳም ይገባዋልን አለ። በዚያንም ጊዜ በእኔ ላይ ይፀልይ ዘንድ አገሬንም ይባርክ ዘንድ ልጄን ያዳናትን አባ ኢላርዮንን ወደኔ ላኩት የሚል ደብዳቤ ፅፎ ወደ ቅዲሳን አረጋውያን ላከ።

አረጋውያንም ቅድስት ኢላርያን ጠርተው ወደ ንጉስ እንድትሄድ አዘዙዋት እርሷም ይተዋት ዘንድ አረጋውያን አባቶችን አልቅሳ ለመነቻቸው። እንርሱም እንዲህ አሉዋት ይህ ንጉስ ክርስቲያኖችን የሚወድ ፃድቅ ነው ቅዱሳት መፃህፍትም እንደሚያዙን ትእዛዙን መተላለፍ አይቻለንም ይህንንም ብለው አስገድደው ላኩዋት።

ወደ ንጉሱም በደረሰች ጊዜ ንጉሱና የቤተ መንግስት ሰዎች ሁሉም በክብር ተቀብለው ተሳለሟት ከዚህም በኃላ ንጉሱና ንግስቲቱ ለብቻቸው ሆነው ወደ ውስጠኛው አዳራሽ አስገለሉዋትና ንጉሱ እነዲህ ብሎ ጠየቃት አንተ ልጄን እንደምትስማት በሰማሁ ጊዜ በሀሳቤ ታውኬ አለሁ መነኩሴ ሴትን መሳም አይገባውምና ይህን ነገር ትገልጥልኝ ዘንድ እሻለሁ።

የከበረች ኢላርያም በነገርኳችሁ ጊዜ ወደ አስቄጥስ ገዳም መሄድን ላትከለክሉኝ የከበረ ወንጌልን አምጥታችሁ ማሉልኝ አለቻቸው እነርሱም እንዳለችው ማሉላት። በዚያንም ጊዜ ልጃቸው ኢላርያ እንደሆነች ነገረቻቸው። አወጣጧም እንዴት እንደሆነ ልብሶቿንም ለውጣ የወንድ ልብስ እንደለበሰች አስረዳቻቸው በአካሏም ውስጥ ያለ ምልክትን አሳየቻቸው።

በዚያንም ጊዜ ታላቅ ጩኸትን ጮኹ አቅፈው እየሳሟት አለቀሱ ከእኛ ዘንድ እንድትሄጂ ከቶ አንተውሽም አሏት እርሷም በከበረ ወንጌል የማላችሁትን መሀላ አስቡ አለቻቸው። እነርሱም ከእርሱ ጋር አርባ ቀን ያህል እንድትኖር ለመኑዋትና አርባ ቀን አብራቸው ኖረች ከዚህም በኃላ ወደ ቦታዋ ሄደች።

ከዚያችም እለት ወዲህ በአስቄጥስ ገዳም ለሚኖሩ ቅዱሳን የከበሩ አረጋውያን መነኮሳት ለፍላጊታቸው ይሆን ዘንድ የግብፅን ምድር ሁሉ ግብር እንዲሰጧቸው ንጉስ ዘይኑን አዘዘ በዚያንም ወራት በአባ መቃርስ ገዳም አራት መቶ የመነኮሳትን ቤቶች ሰሩ በአባ ዮሀንስም ገዳም ሰባት መቶ በአባ ሙሴ ገዳም ሶስት መቶ ቤቶችን ሰሩ። ከዚህም በኃላ ቅድስት ኢላርያ አምስት አመት ከኖረች በኃላ አረፈች ከእረፍቷም አስቀድሞ እርሷ ሴት እንደሆነች ያወቀ የለም።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ጎርጎርዮስ_ዘኑሲስ

በዚህችም እለት የኑሲስ ኤጲስቆጶስ የባስልዮስ ወንድም የከበረ ጎርጎርዮስ የእፍቱ መታሰቢያ ነው እነሆ የአባቱንና የወንድሙን መታሰቢያቸውን በዚህ ወር ጥር ስድስት ቀን ፅፈናል።
የእግዚአብሄርም መልአክ መጥቶ በርቺ ኃይልንም ልበሺ ሀዋርያው ጢሞቴዎስም ወዳንቺ መጥቶ የወንጌልን ትእዛዝ ያሰተምርሻል አላት።ወዲያውኑ ጢሞቴዎስ መጥቶ የቤቷን ግድግዳ ሰንጥቆ ወደርሷ ገባ ሁሉንም አስተማራት ከበታቹም ውኃ ፈለቀ በውኃውም ላይ ፀለየና በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠመቃትና ከእርሷ ዘንድ ሄደ።

በዚያንም ጊዜ ቅድስት ኦርኒ ተነስታ የአባቷን ጣዖቶች ሰበረች አባቷና እናቷም በመጡ ጊዜ እንደቀድሞው ስለ ጋብቻ ተናገርዋት እርሱም እኔስ ለሰማያዊ ሙሽራ ኢየሱስ ክርስቶስ ተጠርቻለሁ በስሙም ተጠምቄአለሁ አለቻቸው።

ንጉስ አባቷም የልጁን ነገር በሰማ ጊዜ ታላቅ ቁጣን ተመላ ከአዳራሽዋም እየጎተተ አወረዳት እናቷም እያለቀሰች በራስዋም ላይ አመድ እየነሰነሰች ትከተላት ነበር በሰንሰለት ታስረው የሚቀለቡ አራት ፈረሶችን አምጥተው ከጅራታቸው ላይ ቅድስት አርኒን በራስዋ ጠጉር አስረው እንዲአስጎትቷት ንጉስ አባቷ አዘዘ። አንዱ ፈረስም ስንሰለቱን በጥሶ ሲያመልጥ የንጉሱን ቀኝ እጅ ቆረጠውና ወዲያውኑ ወድቆ ሞተ የከበረች ኦርኒም ተነስታ ፀሎት አደረገችና ንጉስ አባቷን ከሞት አስነሳችው የተቆረጠ እጁንም እንደቀድሞው መለሰችው ህዝቡም ይህን ድንቅ ስራ አይተው ከንጉስ አባቷ ጋር በክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ በእጆቿም ሰላሳ ሽህ ያህል ሰዎች ተጠመቁ።

ንጉስ ዳኬዎስም ሰምቶ ወደዚያች አገር ገባ የከበረች ኦርኒንም ይዞ በራስዋ ጠጉር ይሰቅሏት ዘንድ አዘዘ በጨመሩዋትም ጊዜ ሁሉም በእግዚአብሄር ኃይል ሞቱ ደግሞ በመጋዝ እንዲሰነጥቋት አዘዘ መጋዙም ተሰበረ ንጉሱም ሞተ።

የዳኬዎስም ልጁ ሰምቶ መጣ ያቺንም አገር ከበባት ቅድስት ኦርኒንም ይዞ የተሳሉ መርፌዎችንም በእጆቿና ሸእግሮቿ እንዲሰገስጉ በጀርባዋም ላይ አሻዋ የተመላ ዳውላ አድርገው ከአራት ፈረሶች ላይም አስረው ስጋዋ ተበጠጥሶ እስቲጠፋ ድረስ እንዲአስሮጧቸው አዘዘ በዚህም አልቻሏትም።ያንንም ከሀዲ የእግዚአብሄር መልአክ ኦርኒም ጦር ወግቶ ገደለው የከበረች ኦርኒም ሀይማኖትን እያስተማረች በሽተኞችን እየፈወሰች ሙታንን እያስነሳች ተቀመጠች።

አራተኛ ንጉስም መጣ የቅድስት ኦርኒንም ዜና ሰምቶ ወደርሱ አስቀረባትና ለአማልክት ትሰዋ ዘንድ አስገደዳት እምቢ ባለችውም ጊዜ ከእሳት ውስጥ እንዲጨምሩዋት አዘዘ ከእሳትም ውስጥ በደኃና ወጥታ የረከሱ አማልክቶቹን ዘለፈች ንጉሱም ይህን ድንቅ ስራ አይቶ በክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመነ።

አምስተኛው የፋርስ ንጉስ መጣ የከበረች ኦርኒንም ይዞ በእጁ በያዘው ጦር ወጋትና ሞተች ከእግዚአብሄር የታዘዘ መልአክም መጥቶ ከሞት አስነሳት በክብር ባለቤትም በክርስቶስ ስም እያስተማረች ወደ ከተማው ውስጥ ገባች ከጥቂት ቀኖችም በኃላ ተድላ ደስታ ወዳለበት ገነት ተነጥቃ ወጣች።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ጎርጎርዮስ_ነባቤ_መለኮት

በዚችም ቀን የመለኮትን ነገር የሚናገር የጎርጎርዮስ መታሰቢያ ነው። ቅዱስ ጎርጎርዮስ ነባ መለኮት በሌላም በኩል "ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ" እየተባለም ይጠራል፡፡ ሀገሩ ቂሳርያ ነው፡፡ በመጀመሪያ የሕግ ባለሙያ የነበረ ሲሆን በኋላ ግን የቍስጥንጥንያ ሊቀጳጳስ ሆኖ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በሐዋርያነት አገልግሏል፡፡

በደራሲነቱ ምድራውያን መላእክት ከተሰኙት ቅዱሳን ውስጥ አንዱ ነው፡፡ የአምላክን ሰው መሆንና ምሥጢረ ሥላሴን እጅግ አስፍቶና አራቆ ያስተማረ ከመሆኑም በላይ ‹‹ዳግማዊ ዮሐንስ ነባቤ መነኮት›› ተብሎ እስኪጠራ ድረስ በነገረ መለኮት የተራቀቀ ታላቅ ሊቅ መምህር ነው፡፡ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙን የማይጠቅስ መጽሐፍና መምህር የለም፡፡ ሃይማኖተ አበው አጥብቆ የሚጠራው የቤተ ክርስቲያናችን መመኪያ ነው፡፡ የአርመንን ኦርቶዶክስ ያቀና ሲሆን መንበሩን የኖኅ መርከብ ባረፈችበት አራራት ተራራ ላይ ነው የሠራው፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_አክርስጥሮስ

በዚች እለት ተጋዳይ የሆነ መነኰስ የከበረ አክርስጥሮስ አረፈ። ይህም አባት በዮርዳኖስ ገዳም የሚኖር ነበር ከመነኰሳቱም አንዱ እየሰገደ እንዲህ ብሎ ጠየቀው "አባቴ አክርስጥሮስ ሆይ ከኔ ጋር ፍቅርን አደርግ እጠቀምበትም ዘንድ ስራህን ሁሉ ንገረኝ" አለው።

ሽማግሌውም አክርስጥሮስም እንዲህ ብሎ መለሰለት "ልጄ ሆይ ግልማሳ ሆኜ ሳለ በመነኰስኩ ጊዜ በዚያ እፀልይ ዘንድ በለሊት ወደ ቅዱስ ቴዎድሮስ መቅደስ እሄድ ነበር። አስራ ሁሉት ደረጃዎችም አሏት በየአንዳንዱ ደረጃ መቶ መቶ ስግደቶችን እሰግዳለሁ ደውልንም በሚደውሉ ጊዜ ወደ ቤተክርስቲያን በመግባት ከወንድሞች ጋር የማህበሩን የፀሎት ስርአት እፈስማለሁ እንዲሁም በማድረግ አስር አመት ኖርኩ።"

"ከሌሊቶቹም በአንዲቱ የተለመደ ፀሎቴን ከፈሰምኩ በኃላ ልቡናዬ በተመስጦ ተማረከ ነጫጭ ልብሶችን የለበሱ ሁለት ሰዎች መቅረዚችን ሲያበሩ እኩሌታዎቹ ሲበሩ እኩሌታዎቹም ሲጠፉ አየሁ። "

"እኔም ይህ ስራ ምንድንው አልኳቸው እንዚያም አባቶች ባልንጀራውን የሚወድ መቅረዙ የበራበታል አሉኝ እኔም ደግሜ መቅረዜ የቱ ነው አልኃቸው እነርሱም ሂድ ከወንድሞችህ ጋር ተፈቀር እኛ እናበራልሀለን አሉኝ በነቃሁም ጊዜ ማንንም አላገኘሁም።"

ከዚህም በኃላ አባ አክርስጥሮስ ብቻውን ወደ ደብረ ሲና ሄዶ በዚያ እየተጋደለ ሀምሳ አመት ኖረ ወደርሱም እንዲህ የሚለው ቃል መጣ "ከአባቶችህ ጋር ትኖር ዘንድ ወደ ገዳምህ ተመለስ ከዚህም በኃላ በተመለሰ ጊዜ በሰላም አረፈ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በከበሩ ቅዱሳን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ጥር እና #ከገድላት_አንደበት)
#መጋቢት_2

መጋቢት ሁለት በዚች ቀን የኒቅዮስ ኤጲስቆጶስ #ቅዱስ_አባ_መከራዊ በሰማዕትነት ሞተ። የሮሀ አገር የሆነ የተሠወረውን የሚያይ #ቅዱስ_ጎርጎርዮስ አረፈ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አባ_መከራዊ_ዘሃገረ_ኒቅዮስ

መጋቢት ሁለት በዚች ቀን የኒቅዮስ ኤጲስቆጶስ አባ መከራዊ በሰማዕትነት ሞተ። ይህም አባት በግብጽ ደቡብ ከምትገኝ ከእስሙናይን ከታላላቆቿ ወገን ነው። ለኒቅዮስ ከተማም ኤጲስቆጶስነት ተሾመ።

የስደትና የመከራ ወራት በሆነ ጊዜም ስሙ ዮፋንስ የሚባል መኰንን ወደዚያች አገር ከንጉሥ ተልኮ መጣ። የክርስቲያን ወገኖችንም ያሠቃይ ዘንድ ጀመረ። የዚህንም የቅዱስ ኤጲስቆጶስ አባ መከራዊን ዜና ሰምቶ ወደርሱ ያመጡት ዘንድ ወታደሮቹን ላከ እርሱም ወደ መኰንኑ ከመሔዱ በፊት ወደ ቅዱስ መሠዊያው ገባ እጆቹንም ዘርግቶ ጸለየ። ንዋየ ቅዱሳቱንና የመቀደሻውን ልብሶች በመቅደሱ ውስጥ አኖረ።

ከዚያም በኋላ ቤተ ክርስቲያኑን ይጠብቅ ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ፈጽሞ ማለደ። በላያችሁ የፀሐይ ብርሃን ይወጣ ዘንድ ያልተዋችሁ የጽዮን ልጅ ደጆች ሆይ ለእግዚአብሔር ቤት ማገልገያ የሆነ ነዋየ ቅዱሳቱን ጠብቁ እያለ ታላቅ ልቅሶ በማልቀስ ጮኸ።

ከዚህም በኋላ ከንጉሥ መልክተኞች ጋራ ወጥቶ ሔደ ወደ መኰንኑም ቀረበ። ስለ ስሙና ስለ አገሩ ስም ስለ ሥራውም ጠየቀው። የኒቅዮስ ከተማ ኤጲስቆጶስ እንደሆነም ባወቀ ጊዜ እንዲገርፉትና እንዲያጐሳቁሉት ብርና እርሳስም አቅልጠው በአፉ እንዲጨምሩ አዘዘ።

እግዚአብሔርም የሚያጸናውና የሚያስታግሠው ሆነ። ያለ ጉዳትም በጤንነት መልሶ ያነሣው ነበር። ከዚህም በኋላ ወደ እስክንድርያ ገዥ ወደ ኄርሜኔዎስ ሰደደው። እርሱም ቅዱስ አባ መከራዊን እንዲአሥሩት አዘዘ። እግዚአብሔርም በእጆቹ ብዙዎች ድንቆች ተአምራትን አደረገ ከተአምራቱም አንዱ ለአቅፋስ ከተማ ሹም ለሆነ ለዮልዮስ ስሙ አውካሪስጦስ የሚባል እጆቹና እግሮቹ ሽባ የሆነ ልጅ ነበረው አባ መከራዊም በላዩ ጸለየ። ከደዌውም አዳነው።

ከዚህ በኋላ በዮልዮስ ቤት ቀድሶ ለአማንያን ሥጋውንና ደሙን አቀበላቸው። ስለ ሥጋውም እንዲአስብና ገድሉንም እንዲጽፍለት ከዮልዮስ ጋራ ስምምነት አደረገ። መኰንኑ ኄርሜኔዎስም አባ መከራዊ ስለ አደረጋቸው አስደናቂ ተአምራት በሰማ ጊዜ በተለያየ ሥቃይ ያሠቃዩት ዘንድ አዘዘ።

ሕዋሳቶቹ እስቲቆራረጡ በመንኰራኵሮች ውስጥ አስገብተው አሠቃዩት። ለነጣቂዎች አንበሶችም ጣሉት በባሕርም አሠጠሙት በእሳት ምድጃ ውሰጥም ጨመሩት። ቅዱስ አባ መከራዊ በሥቃዩ ሁሉ በክብር ባለቤት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል የሚታገሥና የሚጸና ሆነ። ጌታም ያለ ጉዳት መልሶ በጤንነት ያስነሣው ነበር።

የእመቤታችን የድንግል ማርያምን ቤተ ክርስቲያን የምታገለግል አንዲት ድንግል እኅትም ነበረችው። ሁለት ወንድሞችም ነበሩት የአንደኛው ስም ዮሐንስ የሁለተኛውም ይስሐቅ ይባላል በእሥር ቤትም ሳለ ወደርሱ መጡ አንተ ስለ አባታችን ፈንታ አባት ሆነኽን ነበር እነሆ የሙት ልጆች እንሆን ዘንድ ትተኸን ትሔዳለህ እያሉ በፊቱ አለቀሱ። እርሱም አጽናንቶ ወደ ቤቶቻቸው አሰናበታቸው። ዮልዮስም የዚህን ሽማግሌ ሞት በጽሑፍ እዘዝ ከእርሱም ታርፋለህ ብሎ መኰንኑን መከረው። ቃሉንም ተቀብሎ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ ።በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነትን አክሊል ተቀዳጀ።

ዮልዮስም የቅዱስ አባ መከራዊን ሥጋ ወስዶ በከበሩ በወርቅ ልብሶች ገነዘው በደረቱም ላይ የወርቅ መስቀል አደረገ ወደ ሀገሩ ወደ ኒቅዮስም ከአገልጋዮቹ ጋራ ሰደደው። መልካም ነፋስም ሆኖላቸው መርከቢቱ ፈጥና ሔደች በከተማውም በር አንጻር ደርሳ ቆመች። ቀዛፊዎችም ሊያንቀሳቅሱዋት ፈልገው ነበር ግን አልተቻላቸውም አብዝተው በደከሙም ጊዜ ሥጋዬ በውስጡ እንዲኖር እግዚአብሔር የፈቀደው ቦታ ይህ ነው የሚል ቃል ከበድኑ ወጣ።

ይህንንም ለሀገር ሰዎች ነገሩአቸው የሰሌን ዝንጣፊም እየያዙ ወደርሱ መጡ በሀገራቸውም ውስጥ እርሱ በመረጣት ቦታ እስከ አኖሩት ድረስ በታላቅ ክብር ተሸክመው ወሰዱት።

መላው የሕይወቱ ዘመን አንድ መቶ ሠላሳ አንድ ሆነ። መጻሕፍትን እስከተማረ ድረስ ስምንት ዓመት በዲቁና ሹመት ሃያ አራት ዓመት ከዚያም ቅስና ተሹሞ በቅስና አገልገሎት ሠላሳ ዓመት ኖረ ከዚያም በኋላ ኤጲስቆጶስ ሁኖ ተሾመ። በዚህም ስልሳ ዘጠኝ ዓመት ኑሮ መልካም ተጋድሎውን ፈጸመ። የሕይወት አክሊልንም ከክብር ባለቤት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ተቀበለ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ጐርጐርዮስ_ረዓዬ_ኅቡዓት

ዳግመኛም በዚች ቀን የሮሀ አገር የሆነ የተሠወረውን የሚያይ ቅዱስ ጎርጎርዮስ አረፈ። ይህም ቅዱስ ሰው አስቀድሞ አመፀኛና ኃጥእ ነበረ ከዚህም በኋላ ከዐመፁ ወደ እግዚአብሔር በንስሓ ተመልሶ መነኰሰ። የጻድቃንን ማደሪያና ብዙ ዋጋቸውን የኃጥአንንም ኵነኔና እየራሱ የሆነ ሥቃያቸውን እግዚአብሔር እስከ አሳየው ድረስ ብዙ ተጋደለ።

ቅዱስ ጐርጐርዮስ ሃገሩ ሮሃ (ሶርያ አካባቢ) ሲሆን ረዓዬ ኅቡዓት (ምሥጢራትን የተመለከተ) ይባላል:: ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:- ቅዱሱ ተወልዶ ባደገባት ሃገር ይህ ቀረው የማይባል ኃጢአተኛ ሰው ነበር:: ታዲያ ምንም ኃጢአተኛ ሰው ቢሆን እመቤታችን ድንግል ማርያምን በፍፁም ልቡ ይወዳት ነበርና በመዳን ቀን ጥሪ ለንስሐ አበቃችው::

ከዚያች ዕለት ጀምሮም ቅዱስ የእግዚአብሔር ሰው ንጹሕ የቤተ ክርስቲያን መስዋዕት ጽኑዕ የበርሃ ምሰሶ ሆነ:: ድንግል እመቤታችንም ከነሥጋው ወደ ሰማያት ወስዳ ገነትና ሲዖልን አሳይታ ከአዳም፣ ኖኅ፣ አብርሃም፣ ሙሴ፣ ዳዊትን ከመሰሉ ቅዱሳን ጋር አስተዋውቃ ከዚህም በላይ የሆነና በሰብአዊ አንደበት የማይነገር ብዙ ምሥጢር አሳይታ ወደ ምድር መልሳዋለች::

ቅዱስ ጐርጐርዮስ በሰማይ (በገነት) በነበረው ቆይታ ክብረ ቅዱሳንን ተመልክቶ አድንቋል:: በተለይ በፍጹምነት ድንግልናቸውን የጠበቁ ቅዱሳንና ቅዱሳት ደናግል አኗኗራቸው ከአምላክ እናት ከሰማይ ንግሥት ከእመቤታችን ከድንግል ማርያም ጋር መሆኑን አይቷል:: "የለበሱት ልብስም በፍጡር አንደበት ተከናውኖ ሊነገር የሚቻል አይደለም" ይላል:: የደናግል ፊታቸው ከፀሐይ 7 እጅ ያበራልና ግርማቸው ያስፈራል::

ቅዱሱ ሰው በዚያው በሰማይ ሳለ ደግሞ ይህንን ተመለከተ:: አንድ አረጋዊ ጽሕሙ ተንዠርግጐ የብርሃን ካባ ላንቃ ለብሶ ይመጣል:: ቅዱሳን መላእክት በፊት በኋላ በቀኝ በግራ ከበውት ሳለ እግዚአብሔርን ሊያመሰግን ጀመረ::

"እግዚኦ እግዚእነ ጥቀ ተሰብሐ ስምከ በዲበ ምድር (አቤቱ ጌታችን በምድር ሁሉ ስምህ የተመሰገነ ሆነ)" ሲል . . . መላእክቱ በዝማሬ አጀቡት:: በዚህ ጊዜም ታላቅ መናወጥ ሆነ:: ደናግሉም የቅዱሱን ሽማግሌ በረከቱን ተሳተፉ:: ይህ አመስጋኝ ሽማግሌ ልበ-አምላክ ጻድቅ የዋህና የእሥራኤል ንጉሥ የሆነው ዳዊት ነበር:: በምን ታወቀ ቢሉ:- በበገናው:: አንድም እመቤታችን "አባቴ ዳዊት!" ብላ ስትጠራው ጐርጐርዮስ ሰምቷልና::

በመጨረሻም እመቤታችንን በፍጹም ክብርና ግርማ ተመልክቷት ሐሴትን አድርጓል:: እመብርሃንም "ተወዳጅና ንጹሕ ሰው ነህ" ስትል ቅዱስ ጐርጐርዮስን አመስግናዋለች:: ስለዚህ ዓለምም እንዲህ የሚል መልእክትን ልካለች::
#ኅዳር_21

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ኅዳር ሃያ አንድ በዚህች ቀን የእመቤታችን #የቅድስት_ጽዮን_ድንግል_ማርያም የበዓልዋ ነው፣ ከሮሜ አገር የሆነ #ቅዱስ_ጎርጎርዮስ አረፈ፣ ሊቀ ጳጳሳት #ቅዱስ_አባት_ቆዝሞስ አረፈ፣ #ቅዱስ_አባት_አባ_ዮሐንስ ዘአስዩጥ አረፈ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅድስት_ጽዮን_ድንግል_ማርያም

ኅዳር ሃያ አንድ በዚች ቀን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የበዓልዋ መታሰቢያ ነው።

"ጽዮን" ማለት "ጸወን - አምባ - መጠጊያ" ማለት ነው። አንድም በምሥጢሩ "ማሕደረ አምላክ" ማለት ነው። ጽዮን የሚለው ስም በቁሙ ለቅዱስ ዳዊት ተራራና ለኪዳኑ ጽላት ሲያገለግል በትንቢታዊ ምሥጢሩ ግን ለድንግል ማርያም ለቤተ ክርስቲያንና ለዘለዓለማዊት ርስት ያገለግላል።

እግዚአብሔር ከዘመነ አበው በሁዋላ በጊዜው ለእሥራኤላውያን ክብር፣ ሞገስ፣ አምባ የምትሆናቸውን ታቦተ ጽዮንን በቅዱስ ሙሴ አማካኝነት ሰጥቷቸዋል። (ዘጸ. 31፥18) ከዚያም ለ500 ዓመታት ከእነሱ ጋር በመሆኗ በፈጣሪና በእነሱ መካከል ድልድይ ሆና ኖራለች።

ከዚያም ባለቤቱ ሲፈቅድ በዘመነ ሳባ በቀዳማዊ ምኒልክ (እብነ መለክ-እብነ ሐኪም) አማካኝነት ወደ ኢትዮዽያ መጥታለች። እነሆ በሃገራችን የ3ሺ ዓመት ቆይታዋን ልትደፍን የቀራት ጥቂት ዓመታት ብቻ ናቸው። ጌታ እንደ ፈቀደ ቅዱስ መስቀሉንና ታቦተ ጽዮንን ይዘን ይሔው በቸርነቱ እንኖራለን።

ያም ሆኖ ታቦተ ጽዮንን መስረቅ የሚፈልጉ ብዙ ቀሳጢዎች እንዳሉ እናውቃለን። ግን አንጨነቅም። ምክንያቱም የመጣችውም የምትጠበቀውም በፈቃደ እግዚአብሔር ነውና እንጸልያለን እንጂ አንጨነቅም። በተለያየ ወሬም ራሳችንን አናማጥንም። ባለቤቱ እንድትሔድ ከፈቀደ ደግሞ ማንም ጉልበተኛ አያስቀራትም።

ታቦተ ጽዮን ብዙ ጊዜ "ጽላተ ኪዳን፣ ታቦተ ሕጉ" እየተባለች ትጠራለች። "ጽሌ" ማለት "ሰሌዳ" እንደ ማለት ሲሆን "ጽላት" ደግሞ በብዙ ቁጥር ነው። "ኪዳን" ደግሞ በፈጣሪና በሰው ልጆች መካከል ያለ "ውል - ስምምነት" ነው።

"ታቦት" ማለት "ማሕደር-ማደሪያ" እንደ ማለት ነው። ሕጉ የተጻፈባቸውን ሰላድው "ጽላት" ስንላቸው የጽላቱ ማደሪያ ደግሞ "ታቦት" ይባላል። ጽላት (ታቦትን) ያመጣ ፈጣሪ ነው። በሐዲስ ኪዳንም ምሥጢርና ሐተታ ቢኖረውም 2 ቦታ ላይ ስለ ታቦት ተጠቅሶ እናገኛለን። (2ቆሮ.6፥16 ፣ ራዕይ.11፥19)

በመጨረሻም ኅዳር ሃያ አንድ ቀን ጽዮን ማርያምን የምናከብርባቸውን ምክንያቶች እንመለከታለን።

#በዚህች_ቀን:-
✞ ታቦተ ጽዮን (ጽላተ ኪዳን) ለሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ መሰጠቷን እናስባለን።

✞ ታቦተ ጽዮን በምርኮ በሄደችበት በሀገረ ፍልስጤም ዳጎን የተባለ የአህዛብን ጣኦት አድቅቃ በድል የተመለሰችበትን ዕለት በማሰብ።

✞ በዘመነ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በአሚናዳብ ሠረገላ ሁና ከአቢዳራ ቤት ስትመጣ ቅዱሱ ንጉሥ በታላቅ ሐሴት በፊቷ ዘመረ። አገለገለ። ምድራዊ ክብሩን እስኪረሳ ድረስ ለታቦተ አምላክ የተቀኘላት በማሰብ።

✞ ታቦተ ጽዮን ንጉሥ ሰሎሞን ወደ ሠራላት ቤተመቅደስ በክብር የገባችበትን ዕለት በማሰብ፤

✞ የቀደሙ ነብያት ስለእመቤታችን በተለያየ አምሳል ያዩበት ለምሳሌ፦ ነብዩ ዕዝራ በሃገር መንፈሳዊት፣ ሕዝቅኤል በተዘጋች ቤተመቅደስ፣ ዘካርያስ በተቅዋመ ወርቅ ወዘተ ያዩበትን ዕለት በማሰብ፤

✞ ቀዳማዊ ምኒሊክ ከዐሥራ ሁለቱ ነገድ እስራኤል የበኩር ልጅ ጋር ሊቀ ካህናቱን አዛሪያስንና ታቦተ ጽዮንን ይዞ አክሱም የደረሰበትን ዕለት በማሰብ፤

✞ በዘመነ አፄ ባዜን (በ4 ዓ/ም አካባቢ) አማናዊት ጽዮን ድንግል ማርያም ወደ አክሱም ጽዮን በስደት መጥታ ገብታለች። በዚህ ጊዜም 2ቱ ጽዮኖች ሲገናኙ ታላቅ ብርሃን አክሱምን ውጧታልና ይህንንም በማሰብ፤

✞ በአብርሃ ወአፅብሃ ዘመነ መንግስት ክርስትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሃይማኖት ሆኖ አዋጅ የታወጀበትን በማሠብ፤

✞ አብርሃ ወአጽብሃ በወርቅና በዕንቁ ያሠሩት ባለ አሥራ ሁለት ክፍል ቤተ መቅደስ ለመጀመሪያ ጊዜ ቅዳሴ ቤቱ የተከበረበት ዕለት በመሆኑ፤

✞ በዘጠነኛው መቶ ክፍለ ዘመን ዮዲት ጉዲት አብያተ ክርስቲያንን ስታቃጥል ታቦተ ጽዮንን ይዘው ወደ ዝዋይ ሀይቅ ከተሰደዱ በኋላ ዘመነ ሰላም ሲጀመር አክሱም በነበሩ ካህናት አስታዋሽነት ከዝዋይ ወደ አክሱም የገባችበት ዕለት በመሆኑ፤

በእነዚህ ምክንያቶች በመላው ኢትዮጵያ በተለይም በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ከፍ ባለ መንፈሳዊ በዓል እናከብራለን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ጎርጎርዮስ_ዘሮሜ

በዚህችም ዕለት ከሮሜ አገር የሆነ ተአምራትን የሚያደርግ ቅዱስ ጎርጎርዮስ አረፈ። ይህም ቅዱስ ከታናሽነቱ ጀምሮ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት የቀናች ሃይማኖትንም ተምሮ እውነተኛ ክርስቲያን ሆነ። ከዚህም በኋላ የዚህን ዓለም ኃላፊነት የማታልፍ የመንግሥተ ሰማያትንም ኑሮ አሰበ ኀሳቡንም ሁሉ ስለ ነፍሱ ድኅነት አደረገ።

የዚያቺም አገር ኤጲስቆጶስ በኤጲስቆጶስነቱ ሥራ ይራዳው ዘንድ ለመነው እርሱ ግን አልፈቀደም ከውዳሴ ከንቱ የሚሸሽ ሁኗልና ወደ ገዳምም ገብቶ ጽኑዕ የሆነ ተጋድሎንም መጋደል ጀመረ።

የዚያቺም አገር ኤጲስቆጶስ በአረፈ ጊዜ ኤጲስቆጶስ የሚያደርጉት ፈልገው አጡ ስለዚህም ተሰብስበው ሳሉ የመለኮትንም ነገር የሚናገር ጎርጎርዮስ ከእሳቸው ጋር ሳለ ገዳማዊ ጎርጎርዮስን ፈልጋችሁ በእናንተ ላይ ሹሙት የሚል ቃል ከሰማይ ወደ እነርሱ መጣ ።

በበረሀውም ውስጥ በፈለጉት ጊዜ አላገኙትም እየፈለጉትም ብዙ ቀን ኖሩ እርሱ ግን በአቅራቢያቸው ይኖር ነበር። ባለገኙትም ጊዜ በአንድ ምክር ተስማምተው በሌለበት ወንጌል ይዘው በላያቸው ኤጲስቆጶስነት ሾሙት ስሙንም የመለኮትን ነገር በሚናገር በጎርጎርዮስ ስም ጎርጎርዮስ ብለው ሰየሙት።

ከዚህም በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ ለቅዱስ ጎርጎርዮስ ተገልጦ ተነሥተህ ወደ እነርሱ ሒድ እነሆ በላያቸው ኤጲስቆጶስነት ሹመውልሃልና ይህም ከእግዚአብሔር የሆነ ነው አለው። ያን ጊዜም ወደ እነርሱ ወረደ የአምላክን ትእዛዝ መተላለፍ ፈርቷልና በአዩትም ጊዜ ወጥተው በታላቅ ክብር ተቀበሉት የሹመቱንም ሥርዓት ፈጸሙ።

እግዚአብሔርም ቊጥር የሌላቸው ብዙዎች ተአምራትን በእጆቹ ገለጠ ስለዚህም ገባሬ መንክራት ጎርጎርዮስ ተብሎ ተጠራ ። ከብዙዎች ተአምራቱም አንዲቱ ሁለት ወንድማማቾች ነበሩ ከእርሷም ብዙ ዓሣዎችን የሚያጠምዱበት ታናሽ ባሕር ነበረቻቸው አንዱም አንዱ የኔ ናት በማለት እርስበርሳቸው ተጣሉ ስለዚችም ባሕር በመካከላቸው ይፈርድ ዘንድ ወደ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ለመሔድ ተስማሙ እርሱም ከሁለት ተካፍሉ ብሎ አዘዛቸው እንዳዘዛቸውም ባልተስማሙ ጊዜ ስለዚያች ባሕር እግዚአብሔርን ለመነው በዚያንም ጊዜ ባሕሪቱ ደርቃ የምትታረስ ምድር ሆነች በመካከላቸውም ሰላም ሆነ በእጆቹ ስለሚደረጉ ድንቆች ተአምራት ዜናው በሁሉ አገር ተሰማ በጎ አገልግሎቱንም ከፈጸመ በኋላ በሰላም አረፈ ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_አባት_ቆዝሞስ_ሊቀ_ጳጳሳት
#ታኅሣሥ_15

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም

ታኅሣሥ ዐስራ አምስት በዚህች እለት #ቅዱስ_ጎርጎርዮስ_ዘአርማንያ ዕረፍታቸው ነው፣ ታላቁ ኢትዮጵያዊ ጻድቅ #አቡነ_ኤዎስጣቴዎስ_ከፋሌ_ባህር ልደታቸው ነው፣ #የቅዱስ_አቡነ_ሉቃስ_ዘዓምድ ዕረፍታቸው ነው፣ የእኔ ቢጤ የነበሩትና ጽድቃቸውን ማንም ሳያውቅባቸው የኖሩት #የአባ_ቆራይ ዕረፍታቸው ነው፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ጎርጎርዮስ_ዘአርማንያ

ታኅሣሥ ዐስራ አምስት በዚህች እለት የአርማንያ አገር ኤጲስቆጶስ አባ ጎርጎርዮስ ዕረፍታቸው ነው፡፡ ይህንንም ቅዱስ የንጉሡን ትእዛዝ ስመተላለፋና ለአማልክት አልሠዋም ስላለ የአርማንያ ንጉሥ ድርጣድስ አሠቃይቶ ጥልቅ ወደ ሆነ ደረቅ ጒድጓድ ውስጥ ጨመረው በዚያ ዐሥራ አምስት ዓመት ኖረ። እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነበር አንዲቷን አሮጊትም ሁል ጊዜ ምግቡን እነሰድታመጣለት አደረጋት ሕያው እንደሆነም የሚያውቅ የለም።

ንጉሥ ድርጣድስም ቅድስት አርሴማን ለማግባት ሽቶ ነበርና በእርሷ ምክንያት ደናግሎችን ገደላቸው። የእሊህ ደናግልም ሥጋቸው በተራራ ላይ እንደ ወደቀ ነበር ንጉሡም ስለ ገደላቸው ደናግል ይልቁንም ውበቷንና ደም ግባቷን እያሰበ ስለ ቅድስት አርሴማ አብዝቶ የሚያዝንና የሚጸጸት ሆነ።

ከዚህም በኋላ ወገኖቹ ለመኑት እንዲህም አሉት አውሬ ታድን ዘንድ በፈረስ ተቀመጥና ወደ ዱር እንውጣ የልብህም ኀዘን ይወገድልሃል። በዚያንም ጊዜ አውሬ ለማደን በፈረሱ ተቀምጦ ወደ ዱር ወጣ። የሚነክስ ሆነ ወገኖቹንም ነከሳቸው እግዚአብሔርም መልኩን ለውጦ እንደ እሪያ አደረገው ያገኘውን ሁሉ የሚነክሰ ሆነ። እንዲሁም ከቤተ መንግሥት ሰዎች በብዙዎቹ ላይ ሰይጣን አደረባቸው ታላቅ ድንጋጤም ሆነ ይህም ሁሉ የሆነ ስለ ቅዱሳት ደናግልና ስለ ቅድስት አርሴማ ነው።

የንጉሡ እኅት ግን "ጎርጎርዮስን ከጒድጓድ ካላስወጣችሁት ድኅነት የላችሁም" የሚላት ሰው በራእይ አየች ይህንንም ለወገኖቿ ነገረች እርሱ አስቀድሞ በጒድጓድ ውስጥ የሞተ ስለ መሳላቸው ደነገጡ። በዚያንም ጊዜ ወደ ጒድጓድ ሔዱ በሕይወት እንዳለም ያወቁ ዘንድ ወደ ጒድጓዱ ውስጥ ገመዶችን አወረዱና ገመዶቹን እንዲይዝ ወደርሱ ጮኹ እርሱም ገመዶችን ያዘ ስበው አወጡት አጥበውም ንጹሕ ልብስን አለበሱት በበቅሎም አስቀምጠው ወደ ቤተ መንግሥት አደረሱት። በዚያንም ጊዜ በሰማዕትነት ስለሞቱ ደናግል ሥጋ ጠየቀ እነርሱም የደናግሉ ሥጋቸው ወዳለበት መርተው አደረሱት የዱር አራዊትና አዕዋፍ ሳይበሏቸው በደኅና አገኛቸው ያማሩ ቦታዎችን አዘጋጅተው በውስጣቸው ያኖሩዋቸው ዘንድ አዘዘ እንዳዘዛቸውም አደረጉ።

ከዚህም በኋላ ንጉሡን ያድነው ዘንድ ሕዝቡ ለመኑት ንጉሡም ወዳለበት ዱር አደረሱት እርሱም "ከክፉ ሥራህ ትመለሳለህን? ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታምናለህን?" አለው። እሪያ የሆነውም ንጉሥ አዎን እንደሚል ራሱን ዘንበል አድርጎ አመለከተ በዚያንም ጊዜ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ጸለየ ከንጉሡም ላይ በእሪያ አምሳል ሰይጣንን አስወጣው። የንጉሡም አእምሮውና መልኩ እንደ ቀድሞው ተመለሰለት ነገር ግን ዳግመኛ እንዳይታበይ ከእግሩ ላይ የእሪያ ጥፍር አስቀረ ፈጣሪውም ተገዢ ይሆን ዘንድ ዳግመኛም የቤተ መንግሥት ሰዎችን ሁሉንም አዳናቸው ከላያቸውም አጋንትን አስወጥቶ ሰደዳቸው።

ከዚህም በኋላ የአርማንያን ሰዎች ሁሉንም ሰበሰባቸውና ሥርዓትን ሠራላቸው ስምንት ቀንም እንዲጾሙ አዘዛቸው እንዳዘዛቸውም አደረጉ የእግዚአብሔርንም ሕግ እያስተማራቸው ኖረ። ዳግመኛም ክብር ይግባውና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው መሆኑን አስተማራቸው ታላቆችም ታናናሾችም ትምህርቱን ተቀበሉት ለአርማንያ ሰዎች ሃይማኖትን የመቀበላቸው ምክንያት ይህ ነው።

ከዚህም በኋላ የክርስትና ጥምቀትን ያጠምቃቸው ዘንድ ቅዱስ ጎርጎርዮስን ለመኑት እርሱም "እኔ ካህን ስለአልሆንኩ አይገባኝም ነገር ግን የሚያጠምቃችሁን ካህን ይልክላችሁ ዘንድ ወደሮሜ ሊቀ ጳጳሳት መልክተኞችን ላኩ" አላቸው። በዚያንም ጊዜ ከርሱ ጋር ወደ ንጉሥ አኖሬዎስና ወደ ሊቀ ጳጳሳቱ መልክተኞችን ልከው የአርማንያ ሰዎች ወደ እግዚአብሔር እንደተመለሱ አስረዱአቸው ንጉሡም ሊቀ ጳጳሳቱም ሰምተው ደስ አላቸው ከዚህም በኋላ ሊቀ ጳጳሳቱ ለአርማንያ አገር ሊቀ ጳጳሳት ይሆን ዘንድ ቅዱስ ጎርጎርዮስን ሾመው ወደ አርማንያን ንጉሥ ወደ ድርጣድስም በክብር ላከው።

ቅዱስ ጎርጎርዮስም ተሹሞ ወደ አርማንያ አገር በደረሰ ጊዜ በመምጣቱ ደስ ተሰኙበት እርሱም የአርማንያን ሰዎች ሁሉንም አጠመቃቸው በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያምም ስም ያማረች ቤተ ክርስቲያን ሠራላቸው ሃይማኖንትም ከአጸናቸውና መልካም ጉዞንም ከፈጸመ በኋላ ታኅሣሥ15 ቀን በሰላም በፍቅር ዐረፈ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አቡነ_ኤዎስጣቴዎስ_ከፋሌ_ባህር

ዳግመኛም በዚህች ዕለት አጽፋቸውን እንደጀልባ ተጠቅመው የኢያሪኮን ባሕር የተሻገሩት ታላቁ ኢትዮጵያዊ ጻድቅ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ከፋሌ ባሕር ልደታቸው ነው፡፡ ኢትዮጵያዊው ጻድቅ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ አባታቸው ክርስቶስ ሞዐ ሲሆን እናታቸው ስነ ሕይወት ይባላሉ፡፡ ደጋግ የሆኑ ወላጆቻቸው በሃይማኖትና በምግባር ኮትኩተው አሳደጓቸው፡፡ በአደጉም ጊዜ ከአባ ዘካርያስ እጅ መነኮሱ፡፡ ታላላቅ ቅዱሳን እስኪያደንቋቸው ድረስ በጽኑ ተጋደሎ ሲኖሩ ጌታችን ከቅዱሳን መላእክቱ ጋር ተገልጦላቸው በንፍሐት መንፈስ ቅዱስን አሳደረባቸው፡፡ ‹‹ከእናትህ ማኅፀን የመረጥኩህ ወዳጄ ኤዎስጣቴዎስ ሆይ ለብዙዎች ወንጌልን ትሰብክ ዘንድ ከኢትዮጵያ እስከ አርማንያ ድረስ መምህር አደረግሁህ፡፡ አንተን የሰማ እኔን ሰማ፣ አንተንም ያልሰማ እኔን ያልሰማ ነው›› ካለቸው በኋላ ወደ ሰማይ በክብር ዐረገ፡፡

አባታችን ቅስናን ከተሸሾሙ በኋላ ወንጌልን መስበክ ጀመሩ፡፡ እነ አቡነ አብሳዲን ጨምሮ ብዙዎችንም አመንኩሰው ደቀ መዛሙርቶቻቸው አደረጓቸው፡፡ እጅግ አስገራሚ ተአምራትን በማድረግ ለብዙ ሕሙማን መድኃኒት ሆኗቸው፡፡ ልጆቻቸውን ሰብስበው ከመናፍቃን ጋር በፍጹም እንዳይቀላቀሉ በመምከር አቡነ አብሳዲን ሾመውላቸው ወደ ኢየሩሳሌም በመሄድ ቅዱሳት ቦታዎችን ተሳለሙ፡፡ በመንገዳቸውም የክርስቶስን ወንጌል እየሰበኩ ብዙዎችን ወደ ቀናች ሃይማኖት መለሷቸው፡፡ ወደ አርማንያም ሄደው ወደ ኢያሪኮ ባሕር በደረሱ ጊዜ መርከበኞችን እንዲያሳፍሯቸው ቢለምኗቸው እምቢ አሏቸው፡፡ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ግን አጽፋቸውን በባሕሩ ላይ ዘርግተው በስመ ሥላሴ አማትበው አጽፋቸውን እንደመርከብ አድርገው ልጆቻቸውን ይዘው ባሕሩን ተሻገሩ፡፡ ልጆቻቸውን ‹‹ልጆቼ በልባችሁ ቂምንና ሽንገላን እንዳታኖሩ ተጠበቁ፣ ለእኔ ግን ከእናንተ አንዱ እንደሚጠፋ ይመስላኛል›› አሏቸው፡፡ ይህንንም እንዳሉ ከመካከላቸው አንዱ የቂም በቀል መከማቻ ነበርና ወዲያው ሰጠመ፡፡

አባታችን አርማንያ ደርሰው ከሊቀ ጳጳሳቱ ጋር ቡራኬን ከተሰጣጡ በኋላ ማስተማር ጀመሩ፡፡ የአርማንያ ሰዎች ሁሉም በሃይማኖት አንድ እስኪሆኑ ድረስ ታላላቅ ተአምራትን እያደረጉ አስተምረው አጠመቋቸው፡፡ አባታችን ጊዜ ዕረፍታቸው ሲደርስ ጌታችን ተገልጦላቸው ታላቅ ቃልኪዳን ከሰጣቸው በኋላ መስከረም 18 ቀን ዐርፈው ሊቀ ጳጳሳቱና ካህናቱ በታላቅ ክብር ገንዘው በሰማዕቱ በቅዱስ መርምህናም ቤተ ክርስቲያን ቀብረዋቸዋል፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አቡነ_ሉቃስ_ዘዓምድ
ከዚህም በኋላ መኰንኑ እለእስክንድሮስ ቂርቆስንና እናቱን ወደ አደባባይ ያመጡአቸው ዘንድ አዘዘ ያን ጊዜ አንደበቱ ተፈትቶ ነበርና እንዲህም አለ ሕፃኑንና እናቱን ከቆዳቸው ጋር ራሳቸውን ላጩአቸውና በላያቸው የእሳት ፍሞችን ጨምሩ እርር ብለው እንዲቃጠሉ ዳግመኛም አራት ችንካሮችን ከትከሻዎቹ እስከ ተረከዙ ድረስ እንዲተክሉበት አዘዘ የእግዚአብሔርም መልአክ መጥቶ ሥቃዮችን ከርሱ አራቀ።

ዳግመኛም ከጥዋት እስከ ማታ ከሥቃይ መሣሪያዎች ውስጥ ጨምረው አዋሏቸው ግን ማሠቃየት ተሳናቸው። ከዚህም በኋላ ከማምጠቂያው ውስጥ ጨምረው መገዙአቸውና አመድ እስከሆኑ ከቅባትና ከጨው ጋር በብረት ምጣድ ውስጥ ቆሉአቸው ጌታችንም ከሞት አስነሥቶ አዳናቸው።

ወደ መኰንኑም በገቡ ጊዜ እንዲህ አላቸው በእውነት ከሙታን ተለይታችሁ የተነሣችሁ ከሆነ ይህ ጫማዬ ከእግሬ ወጥቶ እንደ ቀድሞው ሕያው እንዲሆን አድርጉ ሕፃን ቂርቆስም በጸለየ ጊዜ ያ ጫማ ታለቅ በሬ ሆነ ከአንገቱም ፍየል ወጣ።

በዚያንም ሰዓት ለዐሥራ አንድ ሽህ አራት ሰዎች በሬውንና ፍየሉን አርደው ምሳ እንዲያደርጉላቸው መኰንኑ አዘዘ እንዲህም አለ ይህ በቅቷቸው ከጠገቡ ከዚህም ሌላ ምግብ ካልፈለጉ የተሠራው ሁሉ ዕውነተኛ ነዋሪ ነው። ከዚህም በኋላ አርደው ምሳ አደረጉላቸውና ከፍየሉ ሥጋ ስድስት እንቅብ ከበሬው ሥጋ አራት እንቅብ አተረፉ መኰንኑም የተረፈውን ሥጋ አይቶ ወደ ባሕር እንዲጥሉት አዘዘ።

መኰንኑም ቢያፍር የሕፃኑን ምላስ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ ጌታችንም ምላሱን መለሰለት ዳግመኛም በታላቅ ጋን ውኃ እፍልተው ሕፃን ቂርቆስንና እናቱን ኢየሉጣን ይጨምሩአቸው ዘንድ አዘዘ እናቱም አይታ ፈረች። ልጅዋም ወደ እግዚአብሔር በጸለየላት ጊዜ አምላካዊ ኃይልን አሳደረባትና ከልጅዋ ጋር ወደ ጋኑ ገባች። እንደ ውርጭም ቀዝቀዛ ሆነ ደግሞም በውስጡ መንኰራኲር ወዳለበት የብረት ምጣድ እንዲጨምሩአቸውና ሥጋቸው እሰከሚቦጫጨቅ እንዲስቡአቸው አዘዘ የእግዚአብሔርም መልአክ በሕይወት አወጣቸው።

መኰንኑም እነርሱን ማሸነፍ በተሳነው ጌዜ ቸብቸቧቸውን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ በዚያን ጊዜ ለስም አጠራሩ ስግደት የሚገባው የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወረደ ሕፃን ቂርቆስንም የምትሻውን ለምነኝ አለው።

ሕፃኑም ሥጋዬ በምድር አይቀበር ስሜን ለሚጠራ መታሰቢያዬን ለሚያደርግ ቤተ ክርስቲያኔን ለሚሠራ የተጋድሎዬን መጽሐፍ ለሚጽፍና ለሚያጽፍ ወይም ለሚያነበው ለቤተ ክርስቲያኔ መባ ለሚያገባ በውስጧም ለሚጸልይ ለሁሉም ፍላጎታቸውን ስጣቸው ኃጢአታቸውንም ይቅር በል ስሜም በሚጠራበት በዚያች ቦታ የከብት ዕልቂት አይምጣ በሰውም ላይ እባር ቸነፈር በእህልም ላይ ድርቅ የውኃም ማነስ አይሁን።

መድኃኒታችንም የለመንከኝን ሁሉ እሰጥሃለሁ አንተም በቀኜ ትኖራለህ ሥጋህንም ኤልያስ በዐረገበት ሠረገላ ውስጥ አኖራለሁ አለው ሕፃን ቂርቆስም በሰማ ጊዜ እጅግ ደስ ብሎት ጌታችንን አመሰገነው። ከዚህም በኋላ በሌሊቱ እኩሌታም ከእናቱ ጋር አንገቱን ተቆረጠ መድኃኒታችንም በማይጠፋ አክሊል ጋረደው ነፍሶቻቸውንም በታላቅ ክብር ከእርሱ ጋር አሳደገ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_አብድዩ_ነቢይ

በዚህች ቀን ዕውነተኛ ነብይ አብድዩ አረፈ። ይህም ነብይ የሐናንያ ልጅ ነው። በንጉሥ ኢዮሳፍጥም ዘመን ትንቢት ተናገረ እግዚአብሔርም ስለ ትንሣኤና ስለ ፍርድ ቀን በቃሉ ነገረው።

ሁለተኛም ከእስራኤል ልጆች የሚሆነውን ከአሕዛብም ለቀሩት አጸናቸው አብዝቶ መከራቸውም ገሠጻቸውም። ይህም ንጉሥ አካዝያስ ይጠሩት ዘንድ ወደ ኤልያስ ከላካቸው ሦስተኛ መስፍን ነው። ከእርሱ አስቀድመው የመጡ እነዚያን ሁለት መስፍኖች በኤልያስ ቃል እሳት ከሰማይ ወርዳ ከእነርሳቸው ጋር ካሉ ወታደሮች ጋር በላቻቸው።

ይህ ግን ወደ ኤልያስ በመጣ ጊዜ በፊቱ ተንበርክኮ ሰግዶ ተገዛለት እንዲህም አለው የእግዚአብሔር ሰው ተገዛሁልህ የእሊህ የባሮችህ ሰውነትና የኔ ሰውነት በፊትህ ትክበር በእግዚአብሔር ነቢይ ላይ ፈጽሞ አልታበየምና ነቢዩ ኤልያስም ራራለት ወርዶም ከርሱ ጋር ወደ ንጉሡ ሔደ።

ይህም አብድዩ ከምድራዊ ንጉሥ አገልግሎት የኤልያስ አገልገሎት እንደምትበልጥ የኤልያስም አገልገሎት ለሰማያዊ ንጉሥ አገልገሎት ታደርሳለችና ይህን በልቡ ዐወቀ ስለዚህ ምድራውያን ነገሥታትን ማገልገል ትቶ ነቢይ ኤልያስን ተከተሎ አገለገለው በላዩም ከእግዚአብሔር ሀብተ ትንቢት አደረበትና ትንቢትን የሚናገር ሆነ የትንቢቱም ወራት ሃያ ዓመት ነው ከጌታችን ሥጋዌ በፊት በዘጠኝ መቶ ዓመት በሰላም በፍቅር አንድነትም አረፈ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ጎርጎርዮስ_ዘኑሲስ

በዚህችም ቀን ዳግመኛ በሶርያ አገር ያሉ የክርስቲያን ወገኖች የቅዱስ ጎርጎርዮስን የዕረፍቱን መታሰቢያ በዓል ያከብራሉ። ይህም አባት በነፍስ በሥጋ በበጎ ሥራ ሁሉ ከወላጆቹ ጋር ፍጹም ነው። እርሱ እግዚአብሔርን መፍራትንና ትምህርቶችን ተምሮ ዐውቋልና የቋንቋም ትምህርት እጅግ የሚያውቅ የዮናናውያንንም ቋንቋ የሚያነብና የሚተረጒም ለቀና ሃይማኖትም የሚቀና ሆነ በውስጡም በጎ ሥራ በጎ ጠባይ ተፈጸመለት ኑሲስ በምትባል አገርም ላይ ሳይወድ በግድ መርጠው ኤጲስቆጶስነት ሾሙት እርሷም ደሴት ናት የእግዚአብሔርንም መንጋዎች ጠበቀ በትምህርቱና በድርሰቶቹም ልቡናቸውን ብሩህ አደረገ የብሉያትንና የሐዲሳትንም መጻሕፍት ተረጐመ።

ጳጳስ ሁኖ ስለነበረው ስለ ከሀዲው መቅዶንዮስ በንጉሥ ቴዎዶስዮስ ዘመን በቊስጥንጥንያ ከተማ የመቶ ሃምሳ ኤጲስቆጶሳት የአንድነት ስብሰባ በሆነ ጊዜ ይህ ጎርጎርዮስ ከአባቶች ኤጲስቆጶሳት ጋር ሁኖ የሰባልዮስን ወገኖች መቅዶንዮስንና አቡሊናርዮስን ተከራከራቸው መልስ አሳጥቶም አሳፈራቸው። ስሕተታቸውንም ገለጠ። ይህም የካቲት አንድ ቀን ተጽፎአል የእነዚህንም ክህደት አስወገደ በቃሉ ሰይፍነትም የንባባቸውን የስሕተት ሐረግ ቆራርጦ አጠፋ ከተሰበሰቡትም ጋር በሰላም ተመለሰ እነርሱ በድል አድራጊነት እነዚያም ከሀ**ድያን በኀፍረት ሆነው ተመለሱ ።

ወደ መልካም እርጅና ደርሶ እግዚአብሔርንም ደስ አሰኝቶ አገልገሎ በሰላም አረፈ እነሆ በዚህ ወር ጥር ሃያ አንድ ቀን ከገድሉ ጥቂት ጽፈናል ይኸውም በግብጻውያን ዕረፍቱ ነው።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ጥር)
#ጥር_21

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ጥር ሀያ አንድ በዚች ቀን ለእመቤታችን ለከበረች #ድንግል_ማርያም የእረፍቷ መታሰቢያ ነው፣ የከበረች #ቅድስት_ኢላርያ አረፈች፣ የባስልዮስ ወንድም የከበረ #ቅዱስ_ጎርጎርዮስ የእረፍቱ መታሰቢያ ነው፣ የካህኑ ኬልቅዩ ልጅ ታላቁ #ነቢይ_ኤርምያስ መታሰቢያው ነው።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#በዓለ_አስተርዕዮ_ማርያም

ጥር ሀያ አንድ በዚች ቀን አምላክን ለወለድች ለእመቤታችን ለከበረች ድንግል ማርያም የእረፍቷ በአል መታሰቢያ ነው።ያን ጊዜ እመቤታችን በልጅዋ በጌታችን በፈጣሪያችንና በመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በከበረ መቃበሩ ቦታ ትፀልይ ነበረ ከዚህም አለም እንደምትለይ መንፈስ ቅዱስ ነገራት ከዚህም በኃላ ከደብረ ዘይት ደናግል መጡ ጌታችን ነግሮዋቸዋልና እርሷም ነገረቻቸው።

በዚያንም ጊዜ እመቤታችን እንዲህ ብላ ፀለየች፦ "ልጄ ወዳጄ ጌታዬና ፈጣሩዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ልመናዬን ተቀብለህ ደቀ መዝሙርህን ዮሀንስን በዚች ሰአት አምጣው።እንዲሁም ህያዋን እንደሆኑ ሀዋርያትን ሁሉንም ነፍሳቸውንም የለየሀቸውን አምጣቸው አንተ የህያዋንና የሙታን አምላክ ነህና ላንተም ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን።

በዚያንም ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ ትእዛዝ ከኤፌሶን አገር ዮሀንስን ደመና ተሸክማ ወደ እመቤታችን ማርያም አደረሰችው ሰገደላትና በፊቷ ቁሞ እንዲህ አላት ሰላምታ ይገባሻል ጌታችንን ፈጣሪያችንንና መድኃኒታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን የወለድሺው ፀጋን የተመላሽ ደስ ይበልሽ አንቺ ከዚህ አለም ተለይተሽ በክብር በምስጋና ወደ ዘላለም ህይወት ትሄጂአለሽና። ይህም ስሙ ክብር ምስጉን የሆነ ጌታችንና ፈጣሪያችን ድንቆች ተአምራቶችን በአንቺ ላይ ከገለጠ በኃላ ነው።

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ይህን በሰማች ጊዜ እጅግ ደስ አላትእግዚአብሄርንም እንዲህ ብላ አመሰገነችው ፈጣሪዬ ጌታዬ ላንተ ምስጋና ይሁን አንተ የለመንኩህን ሰጥተኸኛልና አሁንም ነፍሴን ተቀብለው ወደ ሰማይ ወደ አንተ ሊአሳርጓት ከሚመጡ መላእከቶችህ ጋር በመምጣትህ የምለምንህን ሁሉ ስጠኝ።

በዚያንም ጊዜ ከሰማይ እንዲህ የሚል ቃል መጣ እነሆ አሁን መላእክት ይደርሳሉ ሀዋርያትም ሁሉ ከምድር ዳርቻ በደመና ተጭነው ለሰማይና ለምድር ጌታ ለኢየሱስ ክርስቶስ እናቱ ወደ ሆነች ወደ ቅድስት ድንግል ይደርሳሉ።

ወዲያውኑ ሁሉም ሀዋርያት የሞቱትም ከመቃብራቸው ተነስተው ወደ እመቤታችን ደርሰው ሰገዱላት አምላከችን ከአንቺ የተወለደ ፀጋን የተመላሽ ሆን ደስ ይበልሽ እርሱ ከዚህ አለም ለይቶ ቃል ኪዳን እንደሰጠሽ በክብር በምስጋና ከርሱ ጋር ያሳርግሻልና አሏት።

በዚያንም ጊዜ እመቤታችን በአልጋዋ ላይ ተቀመጠች ሀዋርያትንም እንዲህ አለቻቸው ፈጣሪዬ ፈጣሪያቸው ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሚመጣ እናንተንም እንዳየኃችሁ እንደማየው አሁን አውቅሁ ከዚህ ከስጋዬም ወጥቼ ወደዘላለም ህይወት እሄዳለሁ ነገር ግን ትነግሩኝ ዘንድ እሻለሁ ከዚህም አለም እንደምለይ ከወዴት አወቃችሁ ።

ጴጥሮስና ሐዋርያት ሁሉም ወዳንቺ እንመጣ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ አዘዘን በደመና ላይም በተጫን ጊዜ ወዳንቺ እንደ አይን ጥቅሻ ፈጥነን ደረስን አሏት።

እመቤታችንም ማርያምም ይህን ነገር ከሀዋርያት በሰማች ጊዜ ድምጿን ከፍ አድርጋ እንዲህ አለች ጌታዬና ፈጣሪዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ክቡር ምስጉን የሆነ ስምህን ፈፅሜ አመሰግናለሁ።የእኔን የአገልጋይህን መከራ ተመልክተህ ድንቅ ኃይልህን አድርገህልኛልና ከእንግዲህ ወዲያ ትውልድ ሁሉ ያከብሩኛል ያመሰግኑኛል።

ፀሎቷንና ምስጋናዋን ስትጨርስ ሀዋርያትን እንዲህ አለቻቸው እጣን አምጥታችሁ በማጠን የጌታዬን ኢየሱስ ክርስቶስን ስሙን ጥሩት እነርሱም እንዳዘዘቻቸው አደረጉ ።በዚያንም ጊዜ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እልፍ አእላፍት መላእክት አጅበው እያመሰገኑት መጣና አረጋጋት ያዘጋጀላትንም ተድላ ደስታ ነገራት በዚያንም ብዙዎች ድንቆች ተአምራቶች ተደረገ እውሮች አይተዋልና፣አንካሶች ቀንተው ሄደዋልና ደንቆሮዎች ሰምተዋልና ለምፃሞች ነፁ አጋንንትም ከሰዎች ወጥተው ሄዱ ዲዳዎች ተናገሩ በሽታና ደዌ ያለበት ሁሉ ዳነ እመቤታችን ድንግል ማርያም ወዳለቸወበት ቤት በቀረብ ጊዜ ከደዌያቸው ይፈወሳሉና።

ከዚህም በኃላ እመቤታችን ተወዳጅ ልጅዋን እንዲህ አለችው በአየር ውስጥ ተበትነው ከሚኖሩ ከሚያስደነግጡ ግሩማን መላእክት የተነሳ ከእሳት ባህርም እፈራለሁ ጌታችንም ከእናንተ ለማንም በአለሁ ላይ ስልጣን የለውም አላት።

ከስጋዋም የምትለይበት ጊዜ ሲደርስ ሀወሰርያትና ደናግል ትባርካቸው ዘንድ እያለቀሱ ለመኑዋት እጃዋን በላያቸው ዘርግታ ባረከቻቸው በዚያንም ጊዜ ጌታችን ንፅህት ነፍሷን ከስጋዋ ለይቶ በመለኮታዊ እጆቹ ይዞ በብርሀን ልብስ አጎናፅፎ ወደ ከፍተኛ መኖሪያ ከእርሱ ጋር አሳረጋት ስጋዋን ግን እንደሚገባ ገንዘው ወደ ጌቴሴማኒ ተሸክመው እንዲወስዷት ሀዋርያትን አዘዛቸው።

ነፍሷ ከስጋዋ ከመውጣቷ በፊት በሰው አንደበት ይህ ነው ተብሎ የማይነገር ብርሀንን እያየች ነበር የክብር ባለቤት ጌታችን ክርስቶስም እንግዲህ ስጋሽን ተድላ ወዳለበት ገነት አፈልሳለሁ ዳግመኛም ስጋሽን ከነፍስሽ ጋር አዋህጄ አስነስቼ መላእክት በውስጡ በፊትሽ ሆነው በሚያመሰግኑበት ተመሳሳይ በሌለው ተድላ ደስታ በአለበት ማደሪያ አኖርሻለሁ አላት።

እመቤታችንም እንዲህ አለች አቤቱ በረቀቀ ጥበብህ ይህን ሁሉ የሰራህ አመሰግንሀለሁ ሁለተኛም ልመናዬን ትሰማ ዘንድ እለምንሀለሁ በስሜ ወደ አንተ የሚለምነውን ሁሉ ልመናውን ተቀበለው በመከራም ውስጥ ሆኖ ስሜን ጠርቶ ወዳንተ የሚለምነውን ከመከራው ሁሉ አድነው በሰማይም በምድርም በስራው ላይ ሁሉ አንተ ከሀሊ ነህና መታሰቢያዬን በውስጧ የሚያደርጉትን ቦታ ሁሉ ባርክ በእኔ ስም የሚያቀርቡትን የሁሉንም መስዋእታቸውን ተቀበል።

ጌታችንም እንዲህ ብሎ መለሰላት የለመንሽኝን ሁሉ አደርግልሻለሁ ደስ ይበልሽ ከእኔ ከአባቴ ከመንፈስ ቅዱስ ዘንድ ፀጋ ክብር ባለሟልነት ተሰጥቶሻልና ስምሽንም ጠርቶ የሚለምን ሁሉ በዚህም አለም በሚመጣውም አለም አይጠፋም።

እመቤታችንም ከአረፈች በኃላ ጌታችን እንዳዘዘ ወደ ጌቴሴማኒ ሊወስዷት ሀዋርያት ገንዘው ተሸከሟት። አይሁድም በሰሙ ጊዜ ስጋዋን ሊአቃጥሉ ወጡ ከእነርሱም አንዱ ከምድር ላይ ይጥላት ዘንድ የእመቤታችንን አልጋዋን ያዘ ያን ጊዜ ከእግዚአብሄር የታዘዘ መልአክ እጆቹን በእሳት ሰይፍ ቀጣውና እጆቹ በአልጋዋ ላይ ተንጠለጠሉ።

ያን ጊዜ በጌታችን አምኖ ወደ እመቤታችን እያለቀሰ እንዲህ ብሎ ለመነ የእውነተኛ አምላክ የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እናት አንቺ በእውነት ድንግል የሆንሽ በእኔ ላይ ይቅርታ ታደርጊ ዘንድ እለምንሻለሁ በሀዋርያትም ልመና እጆቹ ተመልሰው እንደቀድሞው ደኅነኞች ሆኑ።

በቀበሩዋትም ጊዜ ከዚያ ሶስት ቀን ኖሩ እረፍቷም የሆነው እሁድ ቀን በጥር ወር በሀያ አንድ በዚች ቀን ነበረ ጌታችንም ብርሀናውያን መላእክትን ላከ እነርሱም ስጋዋን ከመቃብር ወስደው በገነት ውስጥ በእፀ ህይወት ስር አኖሩዋት።

ሀዋርያ ቶማስ ግን ያን ጊዜ አልነበረም በደመና ላይ ተጭኖ እርሱ ሲመጣ መላእክት ሲአሳርጓት እመቤታችንን አገኛት መላእክትም ለአምላክ እናት ለእመቤታችን ድንግል ማርያም ና እጅ ንሳ አሉት እርሱም ሰገደላትና ተሳለማት ከእርሷም ተባረከ ከዚህም በኃላ ወደ ሀዋርያት ደረሰ ። እነርሱም እመቤታችንን ማርያምን እንደ አረፈችና እንደ ቀበርዋትም ነገሩት ቶማስም ስጋዋን እስከማይ አላምንም አላቸው።
ስጋዋንም ያሳዪት ዘንድ ወደ መቃብርዋ በአደረሱት ጊዜ በመቃብር ውስጥ ስጋዋን አላገኙም ደንግጠውም አደነቁ ያን ጊዜ ከመላእክት ጋር ወደ ሰማይ ስታርግ እመቤታችንን እንዳገኛት ቶማስ ነገራቸው። ሀዋርያትም ይህን በሰሙ ጊዜ የእመቤታችንን እርገቷን ስለ አላዩ እጅግ አዘኑ ስጋዋን በምድር ውስጥ ይተው ዘንድ እንዳልወደደ መንፈስ ቅዱስ አስገነዘባቸው። ከዚህም በኃላ አንድ ጊዜ ደግሞ እርሷን ያሳያቸው ዘንድ እንዳለው ጌታችን ቃል ኪዳን በማድረግ ተስፋ ስጣቸው እነርሱም እስከ ነሀሴ አስራ ስድስት በረስፋ ኖሩ።

የእመቤታችንም የእድሜዋ ዘመን ስልሳ አራት አመት ነው በአባትና እናቷ ቤት ሶስት አመት ከሰባት ወር በቤተ መቅደስም አስራ ሁለት አመት በዮሴፍም ቤት ሰላሳ አራት አመት ከሶስት ወር ከጌታ እርገት በኃላ በወንጌላዊ ዮሀንስ ቤት አስራ አራት አመት ነው።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅድስት_ኢላርያ

በዚህችም እለት የሮሜ አገር ንጉስ የዘይኑን ልጅ የከበረች ኢላርያ አረፈች። የዚችም ቅድስት አባቷ እግዚአብሔርን የሚውድ ሀይማኖቱ የቀና ነው ይቺን ቅድስት ኢላርያንና ሁለተኛዋን እኃቷን ወለደ ከእንርሱም በቀር ወንድ ልጅ የለውም። ይቺም ቅድስት ኢላርያ የምንኮስና ልብስን የመላእክትንም አስኬማ ትለብስ ዘንድ የምትመኝ ሆነች ከቤተመንግስትም ወጥታ ልብሷን ለውጣ የወንድ ልብስ ለብሳ ወደ ግብፅ ሀገር ሄድች።

ከዚያም ወደ አስቄጠስ ገዳም ደረሰች በዚያም ስሙ አበሰ ባውሚን የሚባለውን ፍፁም ሽማግሌ ፃድቅ ሰውን አግኝታ ሀሳቧን ሁሉ ነገረችው እርሷ ሴት እንደ ሆነችም አስረዳችው እርሱም ምስጢሯን ሰውሮ ለብቻዋ በዋሻ ውስጥ አስገባት ይጎበኛትና ልትሰራው የሚገባትን ያስተምራት ነበር። እንዲህም ሆና አስራ ሁለት አመት ኖረች ፅህም ስለሌላትም ለአረጋውያን መነኰሳት ጃንደረባ ትመስላቸው ነበር።በወንድ ስም አጠራርም አባ ኢላርዮን ብለው ይጠሩዋታል።

ከአባቷ ዘንድ በቀረችው በሁለተኛዋ ግን ርኩስ ሰይጣን አደረባትና ያሰቃያት ጀመር ያድኗትም ዘንድ ለባለ መድሀኒቶች አባቷ ብዙ ገንዘብ ሰጠ ግን አልተቻላቸውም። ከዚህም በኃላ የከበሩ አረጋውያን መነኮሳት ወዳሉበት አስቄጥስ ገዳም ይልካት ዘንድ መኳንንቶቹ መከሩት የቅድስናቸው ወሬ በሮም ሀገሮች ሁሉ ተሰምቷልና በዚያንም ጊዜ ወደ ቅዱሳኑ ከብዙ ሰራዊት ጋር ላካት ለቅዱሳኑም መልእክትን ፃፈላቸው እንዲህ ሲል የተከበራችሁ አባቶቼ ሆይ የደረሰብኝን ኃዘን አስረዳችኃለሁ እግዚአብሔር ሁለት ሴቶቸ ልጆችን ሰጥቶኝ ነበር።

አንዲቱ ከአለም ሸሸች ወደየት ቦታ እንደምትኖር አላውቅም በሁለተኛዪቱም በላይዋ ርኩስ መንፈስ ተጫነበት እኔ መፅናኛ ትሆነኛለች ብዬ እየሰብኩ ነበር አሁንም በፀሎታቸሁ እግዚአብሔር ያድናት ዘንድ በላይዋ እንድትፀልዩ አኔ ቅድስናችሁን እለምናሉ።

ቅዱሳን መነኮሳትም የንጉሱን ደብዳቤ በአነበቡ ጊዜ በላይዋ ሊፀልዩ ጀመሩ በላይዋ ያደረ ሰይጣንም ከኢላርዮን በቀር ከማደሪያዬ የሚያሰጠኝ የለም ብሎ ጮኸ። አርጋውያኑም ጃንደረባ የሚሏትን ኢላርያን ጠርተው እግዚአብሄር እስከ አዳናት ድረስ የንጉሱን ልጅ ወስደህ በላይዋ ፀልይ አሏት ቅድስት ኢለርያም እኔ በደለኛ ሰው ነኝ ይህን ጭንቅ የሆነ ስራን መስራት አልችልም አለቻቸው።

በአሰገደድዋትም ጊዜ ወደ በአትዋ ወሰዳ በላይዋ ፀለየች ሰይጣነም ትቷት ሸሸ እህቷ እንደሆነች ታውቃለች ስለዚህ አቅፋ ትስማት ነበር ስለ ናፍቆቷና ስለ ፍቅርዋ ወደ ውጭ ወጥታ ታለቅሳለች።

ከዚህም በኃላ ወደ ከበሩ አረጋውያን አደረሰቻችና እነሆ በፀሎታችሁ እግዚአብሔር አድኗታል ወደ አባቷ መልሷት አለቻቸው። እነርሱም እጅግ ደስ ብሏቸው ወደ አባቷ መለሱዋት ለእግዚአብሔርም ምስጋና አቀረቡ።

ወደ ሮሜ አገርም ወደ አባቷ በደረሰች ጊዜ አባትና እናቷ ስለ መዳንዋ በእርሷ እጅግ ደስ አላቸው የቤተ መንግስትም ሰዎችም ሁሉ እግዚአብሔርን አመሰገኑት።

አባቷም በገዳም ከቅዱሳን አባቶች ጋር አኗኗርሽ እንዴት ነበር ብሎ ጠየቃት እርሷም እንዲህ ብላ ነገረችው ያ ያዳነኝ አባ ኢላርዮን የሚባል አባት አብዝቶ ይወደኛል አቅፎም ይስመኛል ንጉሱም ይህን ሰምቶ በልቡ ታወከ ለመነኩሴ ሴቶችን መሳም ይገባዋልን አለ። በዚያንም ጊዜ በእኔ ላይ ይፀልይ ዘንድ አገሬንም ይባርክ ዘንድ ልጄን ያዳናትን አባ ኢላርዮንን ወደኔ ላኩት የሚል ደብዳቤ ፅፎ ወደ ቅዲሳን አረጋውያን ላከ።

አረጋውያንም ቅድስት ኢላርያን ጠርተው ወደ ንጉስ እንድትሄድ አዘዙዋት እርሷም ይተዋት ዘንድ አረጋውያን አባቶችን አልቅሳ ለመነቻቸው። እንርሱም እንዲህ አሉዋት ይህ ንጉስ ክርስቲያኖችን የሚወድ ፃድቅ ነው ቅዱሳት መፃህፍትም እንደሚያዙን ትእዛዙን መተላለፍ አይቻለንም ይህንንም ብለው አስገድደው ላኩዋት።

ወደ ንጉሱም በደረሰች ጊዜ ንጉሱና የቤተ መንግስት ሰዎች ሁሉም በክብር ተቀብለው ተሳለሟት ከዚህም በኃላ ንጉሱና ንግስቲቱ ለብቻቸው ሆነው ወደ ውስጠኛው አዳራሽ አስገለሉዋትና ንጉሱ እነዲህ ብሎ ጠየቃት አንተ ልጄን እንደምትስማት በሰማሁ ጊዜ በሀሳቤ ታውኬ አለሁ መነኩሴ ሴትን መሳም አይገባውምና ይህን ነገር ትገልጥልኝ ዘንድ እሻለሁ።

የከበረች ኢላርያም በነገርኳችሁ ጊዜ ወደ አስቄጥስ ገዳም መሄድን ላትከለክሉኝ የከበረ ወንጌልን አምጥታችሁ ማሉልኝ አለቻቸው እነርሱም እንዳለችው ማሉላት። በዚያንም ጊዜ ልጃቸው ኢላርያ እንደሆነች ነገረቻቸው። አወጣጧም እንዴት እንደሆነ ልብሶቿንም ለውጣ የወንድ ልብስ እንደለበሰች አስረዳቻቸው በአካሏም ውስጥ ያለ ምልክትን አሳየቻቸው።

በዚያንም ጊዜ ታላቅ ጩኸትን ጮኹ አቅፈው እየሳሟት አለቀሱ ከእኛ ዘንድ እንድትሄጂ ከቶ አንተውሽም አሏት እርሷም በከበረ ወንጌል የማላችሁትን መሀላ አስቡ አለቻቸው። እነርሱም ከእርሱ ጋር አርባ ቀን ያህል እንድትኖር ለመኑዋትና አርባ ቀን አብራቸው ኖረች ከዚህም በኃላ ወደ ቦታዋ ሄደች።

ከዚያችም እለት ወዲህ በአስቄጥስ ገዳም ለሚኖሩ ቅዱሳን የከበሩ አረጋውያን መነኮሳት ለፍላጊታቸው ይሆን ዘንድ የግብፅን ምድር ሁሉ ግብር እንዲሰጧቸው ንጉስ ዘይኑን አዘዘ በዚያንም ወራት በአባ መቃርስ ገዳም አራት መቶ የመነኮሳትን ቤቶች ሰሩ በአባ ዮሀንስም ገዳም ሰባት መቶ በአባ ሙሴ ገዳም ሶስት መቶ ቤቶችን ሰሩ። ከዚህም በኃላ ቅድስት ኢላርያ አምስት አመት ከኖረች በኃላ አረፈች ከእረፍቷም አስቀድሞ እርሷ ሴት እንደሆነች ያወቀ የለም።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ጎርጎርዮስ_ዘኑሲስ

በዚህችም እለት የኑሲስ ኤጲስቆጶስ የባስልዮስ ወንድም የከበረ ጎርጎርዮስ የእፍቱ መታሰቢያ ነው እነሆ የአባቱንና የወንድሙን መታሰቢያቸውን በዚህ ወር ጥር ስድስት ቀን ፅፈናል።

ይህም ቅዱስ ጎርጎርዮስ እጅግ የተማረ አዋቂ ነበረ በደሴቶችም ላይ ኤጲስቆጶስነት ተሾመ እነሆ በዚህ ወር በአስራ አምስት ቀን የሆነውን ከገድሉ ጥቂት እንፅፋለን።ስለርሱም እንዲህ ተባለ እርሱ መስዋእቱን ለማክበር በሚቀድስ ጊዜ በመሰዊያው ላይ ሲወርድ መንፈስ ቅዱስን የሚያየው ሆነ ከዚህም በኃላ ኪሩብን አየው በደረቱም ውስጥ አቀፈው በመሰዊያውም ላይ ሳለ ወደ ዝምታና ተደሞ አደረሰው ሰዎችም ሁሉ ስጋዊ እንቅልፍ የሚያንቀላፋ ይመስላቸው ነበር።

በኤጲስቆጶስነት ሹመት ሰላሳ ሶስት ዘመናት በተፈፀመለት ጊዜ ወንድሙ ቅዱስ ባስልዮስ ሊጠይቀው መጣ እርሱ ከተጋድሎ ብዛት የተነሳ በፅኑ ደዌ የሚታመም ሆኖ ነበርና በቅዱስ ባስልዮስ መምጣት ደስ አለው።
የእግዚአብሄርም መልአክ መጥቶ በርቺ ኃይልንም ልበሺ ሀዋርያው ጢሞቴዎስም ወዳንቺ መጥቶ የወንጌልን ትእዛዝ ያሰተምርሻል አላት።ወዲያውኑ ጢሞቴዎስ መጥቶ የቤቷን ግድግዳ ሰንጥቆ ወደርሷ ገባ ሁሉንም አስተማራት ከበታቹም ውኃ ፈለቀ በውኃውም ላይ ፀለየና በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠመቃትና ከእርሷ ዘንድ ሄደ።

በዚያንም ጊዜ ቅድስት ኦርኒ ተነስታ የአባቷን ጣዖቶች ሰበረች አባቷና እናቷም በመጡ ጊዜ እንደቀድሞው ስለ ጋብቻ ተናገርዋት እርሱም እኔስ ለሰማያዊ ሙሽራ ኢየሱስ ክርስቶስ ተጠርቻለሁ በስሙም ተጠምቄአለሁ አለቻቸው።

ንጉስ አባቷም የልጁን ነገር በሰማ ጊዜ ታላቅ ቁጣን ተመላ ከአዳራሽዋም እየጎተተ አወረዳት እናቷም እያለቀሰች በራስዋም ላይ አመድ እየነሰነሰች ትከተላት ነበር በሰንሰለት ታስረው የሚቀለቡ አራት ፈረሶችን አምጥተው ከጅራታቸው ላይ ቅድስት አርኒን በራስዋ ጠጉር አስረው እንዲአስጎትቷት ንጉስ አባቷ አዘዘ። አንዱ ፈረስም ስንሰለቱን በጥሶ ሲያመልጥ የንጉሱን ቀኝ እጅ ቆረጠውና ወዲያውኑ ወድቆ ሞተ የከበረች ኦርኒም ተነስታ ፀሎት አደረገችና ንጉስ አባቷን ከሞት አስነሳችው የተቆረጠ እጁንም እንደቀድሞው መለሰችው ህዝቡም ይህን ድንቅ ስራ አይተው ከንጉስ አባቷ ጋር በክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ በእጆቿም ሰላሳ ሽህ ያህል ሰዎች ተጠመቁ።

ንጉስ ዳኬዎስም ሰምቶ ወደዚያች አገር ገባ የከበረች ኦርኒንም ይዞ በራስዋ ጠጉር ይሰቅሏት ዘንድ አዘዘ በጨመሩዋትም ጊዜ ሁሉም በእግዚአብሄር ኃይል ሞቱ ደግሞ በመጋዝ እንዲሰነጥቋት አዘዘ መጋዙም ተሰበረ ንጉሱም ሞተ።

የዳኬዎስም ልጁ ሰምቶ መጣ ያቺንም አገር ከበባት ቅድስት ኦርኒንም ይዞ የተሳሉ መርፌዎችንም በእጆቿና ሸእግሮቿ እንዲሰገስጉ በጀርባዋም ላይ አሻዋ የተመላ ዳውላ አድርገው ከአራት ፈረሶች ላይም አስረው ስጋዋ ተበጠጥሶ እስቲጠፋ ድረስ እንዲአስሮጧቸው አዘዘ በዚህም አልቻሏትም።ያንንም ከሀዲ የእግዚአብሄር መልአክ ኦርኒም ጦር ወግቶ ገደለው የከበረች ኦርኒም ሀይማኖትን እያስተማረች በሽተኞችን እየፈወሰች ሙታንን እያስነሳች ተቀመጠች።

አራተኛ ንጉስም መጣ የቅድስት ኦርኒንም ዜና ሰምቶ ወደርሱ አስቀረባትና ለአማልክት ትሰዋ ዘንድ አስገደዳት እምቢ ባለችውም ጊዜ ከእሳት ውስጥ እንዲጨምሩዋት አዘዘ ከእሳትም ውስጥ በደኃና ወጥታ የረከሱ አማልክቶቹን ዘለፈች ንጉሱም ይህን ድንቅ ስራ አይቶ በክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመነ።

አምስተኛው የፋርስ ንጉስ መጣ የከበረች ኦርኒንም ይዞ በእጁ በያዘው ጦር ወጋትና ሞተች ከእግዚአብሄር የታዘዘ መልአክም መጥቶ ከሞት አስነሳት በክብር ባለቤትም በክርስቶስ ስም እያስተማረች ወደ ከተማው ውስጥ ገባች ከጥቂት ቀኖችም በኃላ ተድላ ደስታ ወዳለበት ገነት ተነጥቃ ወጣች።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ጎርጎርዮስ_ነባቤ_መለኮት

በዚችም ቀን የመለኮትን ነገር የሚናገር የጎርጎርዮስ መታሰቢያ ነው። ቅዱስ ጎርጎርዮስ ነባቤ መለኮት በሌላም በኩል "ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ" እየተባለም ይጠራል፡፡ ሀገሩ ቂሳርያ ነው፡፡ በመጀመሪያ የሕግ ባለሙያ የነበረ ሲሆን በኋላ ግን የቍስጥንጥንያ ሊቀጳጳስ ሆኖ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በሐዋርያነት አገልግሏል፡፡