መዝገበ ቅዱሳን
25.5K subscribers
1.97K photos
9 videos
6 files
27 links
የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው! መ/ሳ 1÷7
Bewust mesimer lemanegager
@Yesadkusitota
የሰማነውን እንናገራለን
ያየነውን እንመሰክራለን
Download Telegram
ደግና መናኙ የሃገራችን ንጉሥ መናኔ መንግስት #ተክለ_ሃይማኖት (ኃያል ሰገድ) ካረፉ ዛሬ 242 ዓመት ሆናቸው፡፡

✿በዚሁ ቤተ መንግስት የነገሡት በወጣትነታቸው ሲሆን ዘመኑም በ1763 ነበር፡፡
✿ለ7 ዓመታት በዘለቀው የንግሥና ዘመናቸው በዓታ ለማርያም ፡ ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ፡ ቅዱስ ቂርቆስን ጨምሮ 7 አድባራትን አንጸዋል፡፡ አባ ጃሌ ተክለ ሃይማኖትም የታነጸው በዘመናቸው ነበር፡፡
✿በጊዜው ወዲህ የስሑል (ስዑል) ሚካኤል ተጽዕኖ ነበረባቸው፡፡ ወዲያ ደግሞ ምናኔን ወዳጅ ነበሩና ወገባቸውን በሠንሠለት ታጥቀው ሲሰግዱ ያድሩ እንደነበር ይነገራል፡፡
✿ዘወትር ከዋልድባ ገዳም አበው ጋር ይላላኩ ነበርና ፡ በነገሡ በ7 ዓመታቸው መንግስታቸውን ትተው መንነዋል፡፡
✿በዋልድባ ሰቋር እንደ ተርታ ሰው ራሳቸውን ሰውረው ለ1 ዓመት ከ6 ወራት ትሕርምት በሁዋላ በዚህች ቀን ዐርፈው ተቀብረዋል፡፡
✿ስለዚህም #መናኔ_መንግስት እየተባሉ ሲጠሩ ይኖራሉ፡፡
✿መታሰቢያቸውም ባሠሯት በደብረ ኃይል ወደብረ ጥበብ በዓታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን ይደረጋል፡፡

እግዚአብሔር ከበረከታቸው አይለየን፡፡
@yedingelsitota