መዝገበ ቅዱሳን
24.2K subscribers
1.97K photos
9 videos
6 files
26 links
የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው! መ/ሳ 1÷7
Bewust mesimer lemanegager
@Yesadkusitota
የሰማነውን እንናገራለን
ያየነውን እንመሰክራለን
Download Telegram
=>+"+ እንኩዋን ለአጋእዝተ ዓለም #ሥላሴ እና ለቅዱሳን
አበው #አብርሃም: #አባ_ሲኖዳ እና #አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋሥጫ
ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ +"+

+"+ #ሥሉስ_ቅዱስ +"+

=>በአንድነቱ ምንታዌ (ሁለትነት): በሦስትነቱ ርባዔ (አራትነት)
የሌለበት የዘለዓለም አምላክ: የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪ
#እግዚአብሔር ነው:: #አብ : #ወልድ : #መንፈስ_ቅዱስ
በስም: በአካል: በግብር ሦስትነት: በባሕርይ: በሕልውናና
በፈቃድ አንድነት የጸኑ ናቸው:: በዚህ ጊዜ ተገኙ: በዚህ ጊዜ
ያልፋሉ አይባሉም:: መጀመሪያም መጨረሻም እነርሱ ናቸውና::

+ርሕሩሐን ናቸውና በእናት ሥርዓት " #ቅድስት_ሥላሴ "
እንላቸዋለን:: የሚጠላቸው (የማያምንባቸውን) አይጠሉም::
የሚወዳቸውን ግን እጽፍ ድርብ ይወዱታል:: በቤቱም መጥተው
ያድራሉ::

+ከፍጥረታት ወገን ከእመቤታችን ቀጥሎ የአብርሃምን ያህል
በሥላሴ ዘንድ የተወደደ ፍጡር የለም:: አባታችን
#ቅዱስ_አብርሃም የደግነት ሁሉ አባት ነውና በኬብሮን
በመምሬ ዛፍ ሥር ሥላሴን ተቀብሎ አስተናግዷል:: ሥላሴ
አኀዜ ዓለም (ዓለምን በእጁ የያዘ) ነው:: ነገር ግን በፍቅር
ለሚሻው በፍቅር ይመጣል::

+አባታችን አብርሃም በ99 ዓመቱ: እናታችን ሣራ በ89 ዓመቷ
ሥላሴን በድንኩዋናቸው አስተናገዱ:: አብርሃም እግራቸውን
አጠበ:: (ወይ መታደል!) በጀርባውም አዘላቸው:: (ድንቅ አባት!)
ምሳቸውንም አቀረበላቸው:: እንደሚበሉ ሆኑለት:: በዚያው
ዕለትም የይስሐቅን መወለድ አበሠሩት:: #ቅድስት_ሣራ ሳቀች::
እንደ ዘንድሮ ወገኖቻችን የማሾፍ አይደለም:: ደስታና ጉጉት
የፈጠረው እንጂ:: ሥላሴ "ምንት አስሐቃ ለሣራ በባሕቲታ"
ብለው ነበርና በዚህም ምክንያት ነው " #ይስሐቅ" የተባለው::

+ሥላሴን ያስተናገደች ድንኩዋን (ሐይመት) የድንግል
እመቤታችን ማርያም ምሳሌ ናት:: በድንግል ላይ #አብ
ለአጽንኦ: #መንፈስ_ቅዱስ ለአንጽሖ: #ወልድ በተለየ አካሉ
ለሥጋዌ በእርሷ ላይ አርፈዋል / አድረዋልና::

+"+ #ታላቁ_አባ_ሲኖዳ +"+

=>የባሕታውን ሁሉ አለቃቸው ታላቁ ቅዱስ ሲኖዳ:-
¤በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን የተወለደ
¤በእናቱ ማሕጸን ሳለ መላእክት በሰይፈ እሳት ይጠብቁት የነበረ
¤የታላቅነት ትንቢት የተነገረለት
¤ገና ሳይወለድ ሥውራን አበው የሰገዱለት
¤በሕጻን ሰውነቱ ጾምና ጸሎትን የጀመረ
¤የልጅነት ቁርስና ምሳውን ለነዳያን ያካፍል የነበረ
¤በ9 ዓመቱ ወደ በርሃ የመነነ
¤የአባ አብጐል ደቀ መዝሙር የሆነ አባት ነው::

+ሲመነኩስም በእግዚአብሔር ትእዛዝ #የሠለስቱ_ደቂቅ
አስኬማ: #የኤልያስ ቆብዕ እና የመጥምቁ #ዮሐንስ ቅናትን
(መታጠቂያ) ከያሉበት መላእክት አምጥተውለት የመነኮሰ
¤ዓለምን በሙሉ በጸሎቱ ይጠብቅ የነበረ
¤የግብፅን በርሃ በብርሃን የሞላ
¤በርካታ ድርሰቶችን የደረሰ
¤ያለ ማቇረጥ በየቀኑ ከ100 ዓመታት በላይ ከጌታችን ክርስቶስ
ጋር የተነጋገረ
¤ደመናትን ተጭኖ ይሔድ የነበረና
¤ያለ ዕረፍት ለ111 ዓመታት ከ2 ወራት ፈጣሪውን ያገለገለ
አባት ነው::

+በዚህም ምክንያት አንድ ቀን ገዳማውያን ሁሉ እየሰሙ
እንዲህ የሚል ቃል ከሰማይ መጣ:: "ሲኖዳ ተሠይመ
#አርሲመትሪዳ " (ሲኖዳ አርሲመትሪዳ ሆኗል:: ማለትም
ለባሕታውያን ሁሉ አለቃ ሁኖ ተመርጧል ማለት ነው:: )

+ቅዱሱ የጌታችንን እግር እያጠበም ይጠጣ ነበር::
+በዚህች ዕለት በ120 ዓመቱ ጌታችን ወርዶ ሲያሳርገው
#አቡነ_ኪሮስ "ታላቅ ምሰሶ (ታላቅ ዛፍ) ወደቀ" ብለው
አልቅሰዋል:: #ሲኖዳ ማለት "ደግ ሰው" ማለት ነው::

+"+ #አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ ( #GIYORGIS_OF_SEGLA )
+"+

=>ታላቁ ኢትዮዽያዊ ሊቅና ጻድቅ የተወለደው ወሎ #ጋስጫ
ውስጥ በ1358 ዓ/ም ነው:: ከልጅነቱ ትምሕርት አልገባሕ
ቢለውም በልቡናው ግን ቅን እና ታዛዥ ነበር:: መምሕሩ
"ትምሕርት አይገባውምና ውሰዱት" ቢላቸው "የእግዚአብሔር
ነውና ያገልግላችሁ" ብለው መለሱት:: መገፋቱን የተመለከተ
#አባ_ጊዮርጊስ #እመቤታታችንን ከልቡ ይወዳት ነበረና
ይማጸናት ገባ::

+ቀን ቀን ገዳሙን ሲረዳ: እሕል ሲፈጭና ሲከካ: ላቡንም
ሲያፈስ ውሎ ሌሊት ደግሞ ሲጸልይ ያነጋ ነበር:: ድንግል
እመቤታችን ጸሎቱን ሰምታለችና #ቅዱስ_ዑራኤልን አስከትላ
መጣችለት:: በንጹሐት እጆቿ ባርካው ምሥጢርንም ነገረችው::
"ወነገረቶ ሐምስተ ቃላተ" እንዲል:: ጽዋዐ ልቡናን አጠጥታው
ተሠወረችው::

+ከዚህች ሰዓት ጀምሮ አባ ጊዮርጊስ ፍጹም ተለወጠ:: በጽድቁ
ላይ የሊቅነትን ካባ ደረበ:: ቅዱሳት መጻሕፍትን ይተነትናቸው:
መናፍቃንንም ምላሽ ያሳጣቸው ገባ:: የተረጐማቸውና
ያተታቸውን ሳይጨምር 41 ድርሰቶችን ደረሰ:: (መጽሐፈ
ሰዓታት: መጽሐፈ ምሥጢር: አርጋኖን: ኆኅተ ብርሃን: ውዳሴ
መስቀል: ወዘተ . . . የእርሱ ድርሰቶች ነበሩ)

+ስለ ሃይማኖትም ጠበቃ ነበር:: ስለ ቅድስናውና ውለታው የኢ/
ኦ/ተ/ቤ እንዲህ ትጠራዋለች:-
1. #ሊቀ_ሊቃውንት
2. #በላዔ_መጻሕፍት
3. #ዓምደ_ሃይማኖት
4. #ዳግማዊ_ቄርሎስ
5. #ጠቢብ_ወማዕምር

+ጻድቁ ሊቅ በተወለደ በ60 ዓመቱ በ1418 ዓ/ም በዚህች ቀን
ዐርፏል:: አባ ጊዮርጊስ የተወለደውም ያረፈውም ሐምሌ 7 ቀን
ነው::

=>የሥላሴ ቸርነት: የአብርሃም ደግነት: የአበው አባ ጊዮርጊስና
አባ ሲኖዳ በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን::

=>ሐምሌ 7 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱሳን አብርሃምና ሣራ (ሥላሴን ያስተናገዱ)
2.ብሥራተ ልደተ ይስሐቅ
3.ታላቁ አባ ሲኖዳ (የባሕታውያን ሁሉ አለቃ)
4.አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ (ሊቀ ሊቃውንት: ኢትዮዽያዊ
የሃይማኖት ምሰሶ)
5.ቅዱስ አግናጥዮስ ዘአንጾኪያ (ምጥው ለአንበሳ)
6.አባ መቃቢስ
7.አባ አግራጥስ

=>ወርሐዊ በዓላት
1.አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት
2.አባ ባውላ ገዳማዊ
3.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ

=>+"+ እግዚአብሔርም ለአብርሃም ተስፋ በሰጠው ጊዜ:-
'በእውነት እየባረክሁ እባርክሃለሁ:: እያበዛሁም አበዛሃለሁ'
ብሎ ከእርሱ በሚበልጥ በማንም ሊምል ስላልቻለ በራሱ ማለ::
እንዲሁም እርሱ ከታገሠ በሁዋላ ተስፋውን አገኘ:: +"+ (ዕብ.
6:13)
=>+"+ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ: የእግዚአብሔርም ፍቅር:
የመንፈስ ቅዱስም ሕብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን:: አሜን:: +"+
(ቆሮ. 13:14)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
#ነሐሴ_26

ነሐሴ ሃያ ስድስት በዚህች ቀን ለአብርሃም ሚስት ለተመሰገነች #ቅድስት_ሣራ መታሰቢያዋ ነው፣ የከበረ #አባ_ሞይስስና_እኅቱ_ሣራ በሰማዕትነት ሞቱ፣ የከበሩ መነኰሳት #ቅዱሳን_አጋቦስና_ቴክላ በሰማዕትነት ሞቱ፣ የከበሩ አባቶቻችን #አቡነ_ኢየሱስ_ሞዐ እና #አቡነ_ሀብተ_ማርያም የተፀነሱበት ዕለት ነው፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅድስት_ሣራ

ነሐሴ ሃያ ስድስት በዚህች ቀን ለአብርሃም ሚስት ለተመሰገነች ሣራ መታሰቢያዋን እናደርግ ዘንድ የቤተ ክርስቲያን መምህራን አባቶች አዘዙ።

ይቺንም ክብርተ ማሕፀን የሆነች ጡቶቿም የተባረኩ ክብርት ሣራን የጌራራ ንጉሥ አቤሜሌክ ባል እንዳላት ሳያውቅ በወሰዳት ጊዜ እንዳይቀርባት እግዚአብሔር ገሠጸው በደዌም ቀሠፈው ባሏ አብርሃምም በጸለየለት ጊዜ ከደዌው ተፈወሰ ከዚህም በኋላ ከብዙ ገንዘብ ጋራ ወደ ባሏ መለሳት።

ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር በሦስትነቱ ተገልጦ ወደ ቤቷ እንግድነት በመጣ ጊዜ ለአብርሃምም የይስሐቅን መወለድ በነገረው ጊዜ ሣራም በድንኳኑ ውስጥ ሳቀች እንዲህ ስትል እስከ ዛሬ ገና ነኝን ጌታዬም አርጅቷል።

እግዚአብሔርም አብርሃምን እንዲህ አለው ሣራን ለብቻዋ ምን አሳቃት እስከ ዛሬ ገና ነኝን ጌታዬም አርጅቷል እኔም አሁን አርጅቻለሁ ብላ በውኑ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለን። ከዚህም በኋላ ሣራ ፀንሳ እግዚአብሔር ባለው ወራት በርጅናዋ ለአብርሃም ወንድ ልጅን ወለደች።

ይስሐቅም በአደገ ጊዜ ልጅዋ ይስሐቅን ከእስማኤል ጋራ ሲጫወት አየችው። አብርሃምንም ሣራ እንዲህ አለችው ይቺን ባሪያ ከነልጅዋ አባራት የባሪያ ልጅ ከልጄ ከይስሐቅ ጋራ አይወርስምና። ይህም ነገር ለአብርሃም ስለ ልጁ እስማኤል እጅግ ጭንቅ ሆነበት።

እግዚአብሔርም አብርሃምን እንዲህ አለው የዚህ ልጅ የዚችም ባሪያ ነገር በፊትህ ጭንቅ አይሁንብህ የምትልህን ሁሉ ሣራን ስማት ከይስሐቅ ዘር ይተካልሃልና።

ይህም ነገር ታላቅ ምሥጢር አለው የተመሰገነ ጳውሎስ ቅድስት ሣራን የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ አድርጓታልና። ከዚህም በኋላ በበጎ እርጅና በአረፈች ጊዜ ከኬጢያዊ ኤሞር ልጆች በገዛው ቦታ ቀበራት።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱሳን_ሞይስስና_እህቱ_ሣራ

በዚህች ቀን የከበረ አባ ሞይስስና እኅቱ ሣራ በሰማዕትነት ሞቱ።

የእሊህም ቅዱሳን ወላጆቻቸው ደጎች እጅግም ባለጸጎች ናቸው። የከበረ ሞይስስ ወላጆቹ ከአረፉ በኋላ እኅቱ ሣራን ሊአጋባትና ወላጆቹ የተዉትን ገንዘብም ሊሰጣት እርሱም ወደ ገዳም ሒዶ ሊመነኵስ አሰበ።

ይህን አሳቡንም በነገራት ጊዜ እንዲህ ብላ መለሰችለት እኔን ልታጋባኝ ከወደድክ አስቀድሞ አንተ አግባ አርሱም እንዲህ አላት እኔ ብዙ ኃጢአት ሠርቻለሁ ስለዚህ ኃጢአቴን ለመደምሰስ እመነኵስ ዘንድ እሻለሁ ማግባት አይቻለኝም የነፍሴን መዳኛ አስባለሁ እንጂ ።

ሁለተኛም እንዲህ ብላ መለሰችለት አንተ ነፍስህን ስታድን እኔን በዓለም ወጥመድ ውስጥ እንዴት ትጥለኛለህ። እርሱም እንዲህ አላት ምንኵስና ከፈለግሽ ስለ ራስሽ የምታውቂ አንቺ ነሽ እኔም የወደድሺውን አደርግልሻለሁ።

እንዲህም አለችው ለነፍስህ የምታደርገውን ለኔም እንዲሁ አድርግ እኛ ሁለታችን ከአንድ ባሕርይ ከአንድ አባት ከአንዲት እናት የተገኘን ነንና የልቧንም ቆራጥነት አይቶ ወዲያውኑ ከእርሷ ጋራ ተነሣ ገንዘባቸውንም ሁሉ ለድኆችና ለምስኪኖች በተኑ።

ከዚህም በኋላ እኅቱ ሣራን ወሰዳት ከእስክንድርያ ከተማ ውጭ ወዳለ የደናግል ገዳም ውስጥ አስገባት እርሱም ከወንዶች ገዳም ገብቶ በዚያ ተጋድሎን ተጋደለ። እንዲሁ እኅቱም ጽኑዕ በሆነ ገድል ተጠምዳ እየተጋደለች ሁለቱም ሳይገናኙ ዐሥር ዓመት ኖሩ።

በሊቀ ጳጳሳት አባ ድሜጥሮስ የሹመት ዘመን ሳዊርያኖስ የሚባል ከሀዲ ተነሥቶ የክርስቲያንን ወገኖች ማሠቃየት ጀመረ። ከመነኰሳት ገዳማትም ብዙዎች በሰማዕትነት ሞቱ። አባ ሞይስስም ተነሣ ሊሰናበታትም ወደ እኅቱ ሣራ ላከ በሰማዕትነት መሞት እንደሚሻም ነገራት።

ሣራ እኅቱም በሰማች ጊዜ ወዲያውኑ ተነሣች ሒዳ በሰማዕትነት ትሞት ዘንድ እንድታሰናብታት እመ ምኔቷን ለመነቻት እመ ምኔቷም ጸለየለችላት ሰላምታም ሰጥታ አሰናበተቻት እርሷም ደናግሉን ሁሉ ተሰናበተቻቸው።

ከዚህም በኋላ ወደ ወንድሟ ሔደች በጐዳናም አገኘችውና እርስ በርሳቸው ሰላም ተባባሉ ወደ እስክንድርያ ከተማም ገብተው በመኰንኑ ፊት ቁመው በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመኑ መኰንኑም ጽኑዕ ሥቃይን አሠቃያቸው ከዚህም በኋላ ራሳቸውን በሰይፍ አስቆረጠ። በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበሉ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#መነኰሳት_አጋቦስና_እህቱ_ቅድስት_ቴክላ

በዚህችም ቀን የከበሩ መነኰሳት አጋቦስና ቴክላ በሰማዕትነት ሞቱ። እሊህም ቅዱሳን በከሀዲው ሉልያኖስ ዘመን መከራ በመቀበል ተጋደሉ ። ከመኳንንቶቹም አንዱ ጽኑዕ ሥቃይን አሠቃያቸው ። ሥቃያቸውም በአሰለቸው ጊዜ ለአንበሶች ጣላቸውና ገድላቸውን ፈጽመው የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበሉ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አቡነ_ኢየሱስ_ሞዐ

በዚህች ቀን አባታቻን አቡነ ኢየሱስ ሞዐ የተፀነሱበት ዕለት ነው፡፡ ቅዱሱ አባት ሀገራቸው ጎንደር ክፍለ ሀገር ስማዳ ወረዳ ሲና ዳኅና በሚባል ቦታ ነሐሴ 26 ቀን ተፀንሰው ግንቦት 26 ቀን 1210 ዓ.ም ከአባታቸው ዘክርስቶስና ከእናታቸው እግዚእ ክብራ ተወለዱ። የተወለዱትም በቅዱስ ነአኲቶ ለአብ ዘመነ መንግስት ነው፡፡ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ የአቡነ ተክለ ሃይማኖት የቆብ አባት ሲሆኑ ታላቁን ሐይቅ ቅዱስ እስጢፋኖስን ገዳም የቆረቆሩ ደገኛ አባት ናቸው፡፡

ዕድሜያቸው 30 ዓመት እስከሚደርስ ድረስ ከቤተሰቦቻቸው ትምህርተ ሃይማኖትንና ግብረ ገብን ሲማሩ ከቆዩ በኋላ በ1240 ዓ.ም ይህንን ዓለም በመተው ወደ ደብረ ዳሞ ገዳም ገቡ፡፡ በደብረ ዳሞ ገዳም መነኰሳቱን እየረዱ፣ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት እያጠኑ፣ ቅዱሳት መጻሕፍትን እየገለበጡ ለሰባት ዓመታት ከቆዩ በኋላ የደብረ ዳሞ 3ኛ አበ ምኔት ከሆኑት ከአባ ዮሐኒ እጅ ምንኩስናን በ1247 ዓ.ም ተቀበሉ፡፡

አንድ ቀን ሌሊት መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ወደርሳቸው መጥቶ ‹‹የስምህ መክበርያ ወደሆነው ሐይቅ ወደ ተባለው ሥፍራ ሂድ›› አላቸው፡፡ አባታችንም ‹‹ቦታውን እንዴት ዐውቀዋለሁ?›› በማለት መልአኩን ቢጠይቁት ‹‹ተነሥ! ጉዞህን ጀምር ቦታውን እኔ አሳይሃለሁ›› አላቸው፡፡ አባ ኢየሱስ ሞዓ በመልአኩ እንደታዘዙት ከበዓታቸው ተነሥተው ተከተሉት፡፡ የብዙ ወራት መንገድ የሆነውን ጐዳናም በስድስት ሰዓት አደረሳቸው፡፡ በዚያን ወቅት ከሐይቅ ገዳም በስተ ሰሜን ወደነበረው ጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተ ክርስቲያን ደረሱ፡፡ ወደ ሐይቅ እስጢፋኖስ ከመግባታቸው በፊት ለ6 ወራት ያህል በጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተ ክርስቲያን አገልግለዋል፡፡ ያገለግሉበት በነበረው ቤተ ክርስቲያን ቀን ቀን ሕዝቡን ሲያስተምሩ በመዋል ሲመሽ ወደ ሐይቁ በመግባት ሲጸልዩ ያድሩ ነበር፡፡ በሐይቅ እስጢፋኖስና በዙርያው ለነበሩ አበውም ማታ ማታ አንድ ብርሃን ወደ ሐይቁ ሲገባ ጠዋት ጠዋትም ሲወጣ ይታያቸው ነበር፡፡ ከዚህም በኋላ አባታችን በገዳሙ አባቶች ልመናና በልዑል እግዚአብሔር ትዕዛዝ ወደ ሐይቅ ገዳም ገብተው አበምኔት ሆኑ፡፡
#ታኅሣሥ_14

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ታኅሣሥ ዐስራ አራት በዚህች እለት #ቅዱስ_መርምህናም እና እኅቱ #ቅድስት_ሣራ በሰማዕትነት ዐረፉ፣ መኑፍ ከሚባል አገር #ቅዱስ_ስምዖን በሰማዕትነት ዐረፈ፣ #የቅድስት_ነሳሒት ለዕረፍቷ ነው፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱሳን_መርምህናምና_እኅቱ_ሣራ

ታኅሣሥ ዐስራ አራት በዚህች እለት ቅዱሳን መርምህናምና እኅቱ ሣራ አርባ አገልጋዩቹ በሰማዕትነት ዐረፉ፡፡ የዚህም ቅዱስ አባት የአቶር ንጉሥ የተቀረጹ ስማቸው ቤል አጵሎን የሚባሉ ጣዖታትን የሚያመልክ ነው እናቱ ግን ክርስቲያን ናት። ይህም ቅዱስ መርምህናም ወደ ዱር ሒዶ አራዊትን ያድን ዘንድ እንዲፈቅድለት አባቱን ለመነው በፈቀደለትም ጊዜ ወደ እናቱ ሒዶ "አራዊትን ለማደን ወደ በረሀ እሔዳለሁ" አላት እናቱም "የሰማይና የምድር አምላክ እግዚአብሔር በላይህ በረከትን ያሳድር" አለችው።

ከዚህም በኋላ ከአርባ ፈረሰኞች አገልጋዮቹ ጋር ወጥቶ ሔደ መቅሉብ ወደሚባል ተራራም ደርሶ በዚያ አደረ። በሌሊትም የእግዚአብሔር መልአክ ጠራው እንዲህም አለው "መርምህናም ሆይ ተነሥተህ ወደዚህ ተራራ ላይ ውጣ ስሙ ማቴዎስ የሚባል ቅዱስ ሰው ታገኛለህ እርሱም የሕይወትን ነገር ይነግርሃል" ሲነጋም ወደ ተራራው ወጣ እንደ በግ ጠጉር ለብሶ አባ ማቴዎስን አገኘው መርምህናም በአየው ጊዜ ፈራ ቅዱስ አባ ማቴዎስ "ልጄ ሆይ ወደ እኔ ቅረብ እኔም የእግዚአብሔር ፍጥረቱ የሆንኩ እንዳንተ ሰው ነኝ" አለው። መርምህናምም "ከአባቴ አማልክቶች በቀር አምላክ አለን?" አለው አባ ማቴዎስም የክርስትና ሃይማኖትን ከአባቱና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ክርስቶስን ህልውና በተለየ አካሉ ሰው መሆኑንና መከራ ተቀብሎ መሞቱን መነሣቱን ወደ ሰማይ ማረጉንም የፍርድ ቀንም እንዳ ለጻድቃን በጎ ዋጋ ለኃጢአተኞች ቅጣት እንዳለ አስተማረው። መርምህናምም "ከራስዋ እስከ እግርዋ ለምጽ የያዛት እኅት አለችኝ የአምላክህን ስም ጠርተህ በጸሎትህ ብታድናት እኔ አምንበታለሁ" አለው አባ ማቴዎስም "እኔ አድናታለሁ ና በአንድነት እንውረድ" አለው ከተራራው በወረዱ ጊዜ አባ ማቴዎስን በመንገድ ትቶ ቅዱስ መርምህናም ወደ እናቱ ሒዶ ሁሉን ነገራት እኅቱንም በሥውር ወደ አባ ማቴዎስ ወሰዳት አባ ማቴዎስም ወደ እግዚአብሔር ጸለየና ምድሪቱን አመሳቅሎ መታት በዚያን ጊዜ ውኃ መንጭቶ እንደ ባሕር ሆነ ወደ ባሕሩም አውርዶ እጁን በራሳቸው ላይ አድርጎ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠመቃቸው አሽከሮቹን አርባ ሰዎችንም ሥጋውንና ደሙንም አቀበላቸው ወዲያውኑ ሣራ ከለምጽዋ ነጻች።

ከዚህም በኋላ አባ ማቴዎስ ስለ ከበረ ስሙ በላያቸው የሚመጣውን መከራ በሚቀበሉ ጊዜ ክብር ይግባውና ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን በማመን እንዲጸኑ መከራቸው ከዚህም በኋላ በላያቸው ጸለየና በፍቅ አንድነት አሰናበታቸው። ቅዱስ መርምህናምም በመጣ ጊዜ ወደ እናቱ ቤት ገባ ወደ አባቱ ወይም ወደ አማልክቶቹ አልሔደም አባቱም ሰምቶ ተቆጣ ወደ አማልክቶቹ ቤትም እንዲጠሩት አዘዘ ቅዱስ መርምህናም ግን ከእኅቱና ከሠራዊቱ ጋር ስሟ ቅሳር ወደ ምትባል ተራራ ሒዶ ከላይ ወጥቶ በዚያ ተቀመጠ።

አባቱም በሰማ ጊዜ ከልብሰ መንግሥትና ከዘውድ ጋር መኳንንቱን "የመንግሥቴን ሥልጣን ተረከብ ብሎሃል" እንዲሉት ላካቸው እርሱ ግን በቊጣ ተመለከታቸውና "እኔ ክብር ይግባውና የጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስን ፈጽሞ የማይጠፋ መንግሥት እሻለሁ" አላቸው። የአቶር ንጉሥ አባቱም በዚያን ጊዜ ተቆጣ ልቡ ፈርቶ ይመለስ ዘንድ አገልጋዮቹን በፊቱ እንዲገድሏቸው ካልተመለሰ ግን እርሱንም እኅቱንም እንዲገድሉ አዘዘ። ቅዱስ መርምህናምም ሰምቶ የተመኘውን ይሰጠው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ "ጸሎትህን ሰማሁ ልብህ የወደደውንም ሰጠሁህ" የሚል ቃል ከሰማይ መጣ። ከዚህም በኋላ የቅዱሳኑን ራሳቸውን በሰይፍ ቆረጡና ከጒድጓድ ውስጥ ጣሏቸው ሥጋቸውንም ያቃጥሉ ዘንድ ብዙ ዕንጨቶችን ሰበሰቡ ግን አላገኙአቸውም እግዚአብሔር ሠውሮዋቸዋልና።

ወዲያውኑ ንውጽውጽታ ሆነ ፀሐይም ጨለመ ወታደሮችም ፈርተው ሸሹ ሰይጣንም በአቶር ንጉሥ በሰናክሬም ላይ አድሮ አሳበደው እንደእሪያም ጮኸ የቅዱስ መርምህናምም እናት አይታ ወደ አባ ማቴዎስ ልካ አስመጣችውና የንጉሡን ነገር ነገረችው እርሱም በዘይት ላይ ጸልዮ ቀባው ሰይጣንም በእሪያ አምሳል ከርሱ ወጣ። በዚንም ጊዜ ንጉሥ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመነ ከቤተ ሰቦቹና በሚገዛው አገር ካሉ ሰዎች ሁሉ ጋር ተጠመቀ።

ከዚህም በኋላ አምላክን በወለደች በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ስም ቤተ ክርስቲያን እንዲሠሩ ገንዘብንም ለድኆችና ለችግረኞች እንዲበትኑ አዘዘ ሁሉንም እንዳዘዛቸው አደረጉ። የቅዱስ መርምህናምም እናት ከከበሩ ደንጊያዎች አርባ ሣጥኖችን አሠራች የልጅዋ ጭፍራ የነበሩ የእነዚያን አርባ ሰማዕታት አጥንቶቻቸውን አሰብስባ በየአንዳንዱ ሣጥን ጨመረቻቸው ለልጆቿም ብርሌ ከሚመስል ዕንቊ ሁለት ሣጥን አሠርታ በውስጣቸው አድርጋ በሠራችው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ አኖረቻቸው ከሥጋቸውም ታላላቅ የሆኑ ቊጥር የሌላቸው ተአምራት ተገለጡ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ስምዖን

ዳግመኛም በዚህች እለት መኑፍ ከሚባል አገር ቅዱስ ስምዖን በሰማዕትነት ዐረፈ፡፡ እርሱም በእስላሞች ዘመን ከመሳፍንቶቻቸው ከአንዱ ጋር ተከራከረና ቅዱስ ስምዖን ረትቶ አሳፈረው ያም እስላም ወደ መሳፍንቱ አለቃ ሒዶ "ይህ ስምዖን የእስላሞች ሃይማኖት ያቃልላል" ብሎ ወነጀለው ስለዚህም ይዘው በጽኑዕ ሥቃይ አሠቃዩት ከዚያም በኋላ ራሱን በሰይፍ ቆረጡት የሰማዕትነት አክሊል በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅድስት_ነሳሒት

በዚህች ዕለት የውሲም ኤጲስቆጶስ አባ ያዕቆብ ስርሷ የተናገረላት የሮሜ ንጉሥ ልጅ ቅድስት ነሳሒት ዐረፈች፡፡ እንዲህም አለ በአንዲት ዕለት አምላክን በወለደች በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እያለሁ የገዳሙን ደጅ ሰው ሲያንኳኳ ሰማሁ ተነሥቼም ወደ በሩ ሔድኩ ያረጀ ዓጽፍ የለበሰ ፊቱንም የተሸፋፈነ ሰው አየሁ "ከወዴት መጣህ? ወዴትስ ትሔዳለህ?" አልሁት። "ከአባ መቃርዮስ ገዳም መጣሁ በዚች ሌሊት ከዚህ ገዳም አድሬ ቊርባንን መቀበል እሻለሁ" አለኝ። ያን ጊዜ ቀዳሚት ሰንበት ነበረች እኔም "ፊትህን ካላሳየኸኝ አልከፋትልህም" አልሁት እርሱም "ፊቴን ማየት አትሻ ፊቴ በኃጢአቴ የጨለመ ነውና ፊቴንም ለሚያይ የከፋች ሥራዬ ትታየዋለች" አለኝ። በከለከልኩትም ጊዜ ወደ ዱር ሊመለስ ወደደ እኔም ተርቦ ወይም ተጠምቶ እንደሆነ ብዬ በልቤ አሰብኩ ስለዚህም ከፈትኩለትና ወደ ማደሪያዬ አስገባሁት መብልንም አመጣሁለት እርሱም "ከነገ ከቊርባን በኋላ በቀር እኔ አልበላም" በማለት እምቢ አለኝ።

ከዚህም በኋላ ወደ ቤተ ክርስቲያን ገባና በጨለማ ቦታ ቆመ ከዚያ ያሉ መነኰሳትም እስከ አደነቁ ድረስ የዳዊትን መዝሙር ሲያነብ ድምፁን እንደ መላእክት ድምፅ ሁኖ ሰማሁት በነጋም ጊዜ በእግሮቹ ላይ ተቀመጠ ምንም ምን ማንበብ አልሻም። እኛ ግን ይጸልይልን ዘንድ ልንለምነው ቀረብን እርሱም "አባቴቼ ሆይ በበደሌ ብዛት ፊቴን ያጨለምኩ ስሆን ስለ እናንተ እንዴት እጸልያለሁ" አለን። ቊርባንንም በምናሳርግ ጊዜ በእግሩ ቁሞ የቅዱስ ጳውሎስን መልእክት፣ የሐዋርያትንም መልእክትና የሐዋርያትን ሥራ ማንበብ ጀምረ በአራተኛም ጊዜ በመሠዊያው ፊት ቁሞ የቅዱስ ዮሐንስን ወንጌል ማንበብ ጀመረ በፊቱም ላይ የተከናነበውን ልብስ አስወግደ ከፊቱም
#መጋቢት_15

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም

መጋቢት ዐሥራ አምስት በዚች ቀን የከበረች ተጋዳይ መነኰሳዪት #ቅድስት_ሣራ አረፈች፣ #ቅዱስ_ሰለፍኮስ በሰማዕትነት አረፈ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#መነኰሳዪት_ቅድስት_ሣራ

መጋቢት ዐሥራ አምስት በዚች ቀን የከበረች ተጋዳይ መነኰሳዪት ሣራ አረፈች። ይቺም ቅድስት ከላይኛው ግብጽ ናት ወላጆቿም የክብር ባለቤት ክርስቶስን የሚያመልኩ ክርስቲያን ናቸው። እጅግም ባለጸጎች ነበሩ ነገር ግን ከእርስዋ በቀር ልጆች የሏቸውም በመልካም አስተዳደግም አሳደጓት ለክርስቲያን የሚገባ ትምህርትን ሁሉ አስተማሩዋት ደግሞም ጽሕፈትን አስተማሩዋት ሁልጊዜም የቤተ ክርስቲያንን መጻሕፍት ታነባለች ይልቁንም የመነኰሳትን ዜና ታነብ ነበር።

መጻሕፍትንም አዘውትራ ስለምታነብ የምንኲስና ልብስ ለመልበስ ፈለገች በላይኛው ግብጽ ከሚገኙ ገዳማትም ወደ አንዱ ገዳም ሒዳ ገባች ብዙ ዘመናትም ደናግልን እያገለገለች ኖረች።

ከዚህም በኋላ የምንኲስና ልብስን ለበሰች ሰይጣንን ድል እስከ አደረገችው ድረስ ሰይጣን የሚያመጣውን ሥጋዊ ፍትወት እየታገለች ዐሥራ ሦስት ዓመት ኖረች። ንጽሕናን ከመውደዷ ጽናት በተሸነፈ ጊዜ በትዕቢት ሊጥላት ወዶ በቤት መዛነቢያ ልትጸልይ ቁማ ሳለች ተገልጦ ሣራ ሆይ ሰይጣንን ድል አድርገሽዋልና ደስ ይበልሽ አላት እርሷም መልሳ እኔ ደካማ ሴት ነኝ ከክብር ባለቤት ከጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ድል አድርጌ ላበረው አልችልም አለችው።

ይህችም ቅድስት አብረዋት ላሉ ደናግል ጥቅም ያላቸውን ብዙ ትምህርቶችን ታስተምራቸው ነበር እንዲህም ትላቸዋለች ከቀን ብዛት ጠላት እንዳያስተኝ እኔ እንደምሞት አስቀድሜ ሳላስብ እግሬን ከአንዱ መወጣጫ ደረጃ ወደ ሁለተኛም አውጥቼ አላኖራትም።

ዳግመኛም ለሰው ርኅራኄ ማድረግ በተሻለው ነበር ይህንንም በሚያደርግ ጊዜ የኋላ ኋላ በእግዚአብሔር ፈቃድ ውስጥ ይኖራል በዜና አረጋውያን መነኰሳት መጽሐፍ ውስጥ የተጻፈ ሌሎች ብዙ ቃሎችንም ተናግራለች።

ታላቅ ተጋድሎም እየተጋደለች በዓቷም በባሕር ዳርቻ ሁኖ ሰባት ዓመት ኖረች አንዲት ቀን እንኳ ከሰው አንዱም አላያትም እርሷ ግን ሁሉን ታይ ነበር። ሸምግላ እስከ ሰማንያ ዓመት በደረሰች ጊዜ ከዚህ ዓለም የሕይወት ማሠሪያ ተፈትታ የዘላለም ተድላ ደስታ ወደሚገኝበት ሔደች።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ሰለፍኮስ

በዚችም ቀን ዳግመኛ የቅድስት አስጠራጦኒቃ እጮኛዋ ቅዱስ ሰለፍኮስ በሰማዕትነት አረፈ።

የዚህን ቅዱስ ዜና ክርስቲያን እንደሆነ ከሀዲ ንጉሥ በሰማ ጊዜ ያመጡት ዘንድ አዘዘ ወደርሱም ሲቀርብ የአስጠራጦኒቃ እጮኛዋ ሰለፍኮስ የተባልክ አንተ ነህን አለው አዎን ነኝ አለ። ዳግመኛም ማንን ታመልካለህ አለው እርሱም እኔ የክብር ባለቤት የሆነ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን አመልከዋለሁ ብሎ መለሰ። ንጉሡም መርዝ ያላቸው እባቦች ወዳሉበት እንዲጨምሩት አዘዘ እግዚአብሔርም አዳነው።

ከዚህም በኋላ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡት አዝዞ ቆረጡት በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለ።

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በከበሩ ቅዱሳን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ለዘለዓለሙ ይሁን አሜን፡፡

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_መጋቢት)
#ሚያዝያ_25

#ቅድስት_ሣራ

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም

ሚያዝያ ሃያ አምስት በዚች ቀን ቅድስት ሣራ ከሁለቱ ልጆቿ ጋራ በሰማዕትነት አረፈች፡፡ ይቺም ቅድስት ከአንጾኪያ አገር ናት እርስዋም ከዲዮቅልጥያኖስ መኳንንት ለአንዱ ስሙ ስቅራጥስ ለሚባል ሚስቱ ናት እርሱም በፊት ክርስቲያን ነበረ በኋላ ንጉሡን በመፍራት ካደ እርስዋ ግን በክርስትናዋ ጸንታ ኖረች።

ባልዋ ስቅራጥስም እኔ የክርስቲያንን ሃይማኖት እወዳለሁ የንጉሡን ሥቃይ ከመፍራት በቀር ክርስቶስን በልቤ አልካድኩትም ይላት ነበር። እንደዚህም ስትኖር ሁለት ልጆችንም ወለደች በአንጾኪያም አገር የክርስትና ጥምቀትን ልታስጠምቃቸው አልተቻላትም። አብያተ ክርስቲያናት ተዘግተዋልና ጠፍተዋልምና ሰውን ወዳድ ክርስቶስን ብዙ ስለመውደዷ ልጆቿን ታስጠምቃቸው ዘንድ ታላቅ ተጋድሎ አደረገች ወደ እስክንድርያ ወደ ሊቀ ጳጳሳት አባ ጴጥሮስ ልትሔድ ወዳ አሽከሮቿን አስከትላ ሁለቱን ልጆቿን ይዛ በመርከብ ተሳፈረች።

የክብር ባለቤት ጌታችንም የሃይማኖቷን ልዕልና ለመጪው ትውልድ ሊገልጥ ወዶ ያቺ መርከብ ለመሥጠም እስከምትደርስ በባሕር መካከል ጥቅል ነፋስን አስነሣ። ይቺ ቅድስትም ልጆቿ ሳይጠመቁ እንዳይሞቱ ፈራች ተነሥታም ጸለየች ከዚያም ምላጭ አንሥታ ጡቷን የቀኙን በጣች ከደሟም ወስዳ ፊታቸውን በመስቀል ምልክት ቀባች በደረታቸውና በጀርባቸውም ላይ እንዲሁ አደረገች በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም በባሕሩ ውስጥ አጠመቀቻቸው ያን ጊዜም ታላቅ ጸጥታ ሆነ።

ወደ እስክንድርያ አገርም በደረሰች ጊዜ ከሀገር ልጆች ጋራ ያጠምቃቸው ዘንድ ወደ ሊቀ ጳጳሳት አባ ጴጥሮስ ልጆቿን አቀረበች በዚያን ጊዜም ከሀገር ልጆች አጠመቀ። ወደልጆቿም ደርሶ ሊአጠምቃቸው ወሰዳቸው ያን ጊዜ ውኃው ረጋ እነርሱን ትቶ ከአገር ልጆች አጠመቀ ውኃውም ተፈትቶ ወረደ ደግሞ ሊአጠምቃቸው ወደ ልጆቿ ተመለሰ አሁንም እንደቀድሞው ውኃው ረጋ እንዲሁም ሦስት ጊዜ አደረገ ውኃውም ይረጋል አደነቀ። እናታቸውንም አቅርቦ ጠየቃት እርሷም ፈርታ ተንቀጠቀጠች ከእርሷም የሆነውን በባሕር መካከል ዐውሎ ነፋስ እንደተነሣባት ጡቷን በጥታ ደሟን እንደ ቀባቻቸውና በባሕር ውስጥ እንዳጠመቀቻቸው ነገረችው ስለ አደረገችውም ድፍረት በፊቱ ሰግዳ ይቅር ይላት ዘንድ ለመነችው።

አባ ጴጥሮስም ሴትዮ አትፍሪ ሃይማኖትሽ ፍጹም ነው አንቺ በባሕር ውስጥ በአጠመቅሻቸው ጊዜ በመለኮታዊት እጁ ያጠመቃቸው ባለቤቱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነውና አይዞሽ አላት።ማጥመቁንም በፈጸመ ጊዜ ሥጋውን ደሙን አቀበላቸው ይቺም ቅድስት ወደ አንጾኪያ ቤቷ ተመለሰች።

ባሏም በአያት ጊዜ ይህን በማድረጓ ተቆጥቶ ወደ ንጉሡ ሒዶ ከሰሳት ያደረገችውንም ነገረው። ንጉሡም ወደርሱ ያቀርቧት ዘንድ አዘዘ ስትቀርብም ወደ እስክንድርያ ለምን ሔድሽ ከክርስቲያን ወገኖች ጋራ ልታመነዝሪ ነውን አላት። እርሷም እንዲህ ብላ መለሰችለት ክርስቲያኖች አያመነዝሩም እንደናንተ የረከሰ ጣዖትን አያመልኩም ከእንግዲህ ደግሞ ከእኔ ቃልን አትሰማም የወደድከውን አድርግ ሁለተኛም በእስክንድርያ ካንቺ የሆነውን ንገሪኝ ብሎ ጠየቃት ምንም ምን አልመለሰችለትም ።

ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስም እጆቿን የኋሊት አሥረው ሁለቱንም ልጆቿን በሆድዋ ላይ አድርገው ሦስቱንም በእሳት ያቃጥሉአቸው ዘንድ አዘዘ። ፊቷንም ወደ ምሥራቅ መልሳ ወደ ክብር ባለቤት ጌታችን ጸለየች ከዚያም ከልጆቿ ጋራ አቃጠሉዋት የድልና የሕይወት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለች።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቷ ለዘላለም ይማረን አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሚያዝያ)
††† እንኳን ለእናታችን ብጽዕት ሣራ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቅድስት ሣራ ብጽዕት †††

††† አበው እናታችን ሣራን " #ቡርክተ_ማሕጸን" ይሏታል:: (የቅዱሱ ዘር የይስሐቅ እናት ናትና) በዚያውም ላይ የደጉ ሰው የአብርሃም ሚስት ናት:: ልክ በዓለም ታሪክ "ከጠንካራና ስኬታማ ወንዶች ጀርባ ጠንካራ ሴቶች አሉ" እንደሚባለው ከአብርሃም አባታችን ስኬታማ የቅድስና ሕይወት ጀርባ ብጽዕት ሣራ አለች::

ለአብርሃም አባታችን መጽሐፍ የተናገረው ክብር ሁሉ ለቅድስት ሣራ ይገባታል:: አንድም ገንዘቧ ነው:: ቅድስቷ እናት ደጉ አብርሃምን ያገባችው ገና በከላውዴዎን (በ2ቱ ወንዞች መካከል) ሳለ ነው:: ገና ከልጅነቷ ጀምራ አብርሃምን "ጌታየ" እያለች ታገለግለው እንደ ነበር ቅዱስ መጽሐፍ ይናገራል:: (1ዼጥ. 3:5)

በዚህም ከብራበታለች: ገናበታለች እንጂ አልተጐዳችበትም:: አብርሃም ወደ ካራን ሲወጣ "ለምን?" አላላችም:: እንዲሁ ለፈቃደ እግዚአብሔር ታዘዘች እንጂ:: በካራን ታራን ቀብረው: በፈጣሪ ትዕዛዝ ወደ #ከነዓን ሲፈልሱም ቅድስት ሣራ አልተቃወመችም::

ለፈጣሪዋ ትዕዛዝና ለባሏ ስትል ርስቷን: ሃገሯን: ዘመዶቿን ሁሉ ትታ ሔዳለች:: ይሔውም በጐ ምናኔ ነው:: እናታችን ሳራ በከነዓን የተመቸ ነገር አልገጠማትም:: ከአንዴም ሁለቴ በረሃብና በድርቅ ምክንያት ወደ ግብጽ እና #ጌራራ ተሰደዋል::

በዚያም ፈርዖን "እነካለሁ" ቢል እግዚአብሔር ተቆጥቶ: ፈርኦንንና ግብጽን በደዌ መታ:: በዚህም ክብረ ሣራን ተመለከትን:: ከስደት መልስም በኬብሮን (በተመሳቀለ መንገድ ላይ) ድንኩዋን ሠርተው የወጣ የወረደውን ሲያበሉ: እንግዳ ሲቀበሉ ኑረዋል::
(ልብ በሉልኝ ይህን ትጋትና ደግነት ያሳየችውን ቅድስት ሣራን ልናከብራት ይገባል)

እድሜ ዘመኗን ያሳለፈችው እንግዳ በመቀበል: እግዚአብሔርን በማምለክ ነው:: ምንም እንኩዋ ማሕጸኗ ለጊዜው ቢዘጋ ተስፋ አልቆረጠችም:: ለአብርሃምም ከአጋር እንዲወልድ ፈቃድ ሰጥታለች::

ዕድሜዋ 89 ዓመት በሆነ ጊዜ ሰይጣን እንግዳ እንዳይመጣ ለ3 ቀናት ቢያስቀርባቸው እንደ ባሏ እርሷም 3 ቀናትን ያለ ምግብ አሣልፋለች:: በ3ኛው ቀን ሥላሴን በቤቷ አስተናግዳለች:: ስለ ክብሯም ከ3 መሥፈሪያ ዱቄት ለውሳ ያዘጋጀችውን እንጐቻ ሥላሴ በልተውላታል:: (ምንም ሥላሴ ምግብን ባይመገቡም)

የሥላሴ በዚያች ድንኩዋን ውስጥ መስተናገድ ታላቅ ምሥጢር አለው:: ከግብዣው በሁዋላም እግዚአብሔር አለ:- "አመ ከመ ዮም እገብእ ኀቤከ . . . እንዲሁ ከርሞ እመለሳለሁ: ሣራ ወንድ ልጅን ትወልድልሃለች" አለው::

ያን ጊዜ ሣራ በውሳጤ ሐይመት (በድኩዋኑ ውስጥ) ሆና ሰምታ ሣቀች:: ለምን ሳቀች ቢሉ:- እጅግ ደስ ቢላት! አንድም ቢገርማት:: ይሕስ በምን ይታወቃል ቢሉ:- ልጇ " #ይስሐቅ" የተባለው "ለእናቱ ሣቅን: ደስታን ያመጣ" ለማለት ነውና::

ሥላሴም:- "ምንት አስሐቃ ለሣራ በባሕቲታ: እንዘ ትብል ዓዲየኑ እስከ ይእዜ: ወእግዚእየኑ ልሕቀ: ቦኑ ነገር ዘይሰዓኖ ለእግዚአብሔር - ሣራን ምን አሳቃት? ለእግዚአብሔርስ የሚሳነው ነገር አለን" ብለዋል::

ቅድስት ሣራ በ90 ዓመቷ ይስሐቅን ወልዳ በቀሪ ዘመኖቿ በደስታ ኑራለች:: በዚህች ቀንም በመልካም ሽምግልና ዐርፋ: አባታችን #አብርሃም ከታላቅ ሐዘን ጋር ቀብሯታል:: ሐዋርያው #ቅዱስ_ዻውሎስ ብጽዕት ሣራን በበጐ ምሳሌ መስሏታል:: (ዕብ. 11:11)

††† ቅዱሳን ሞይስስና ሣራ †††

††† እነዚህ ቅዱሳን ግብጻውያን የአንድ እናት: የአንድ አባት ልጆች ሲሆኑ የነበሩትም በዘመነ ሰማዕታት ነው:: ከወላጆቻቸው ጋር በሥርዓተ ክርስትና አድገው ዕድሜአቸው ለአካለ መጠን ሲደርስ ወላጆቻቸው ሞቱባቸው::

ያን ጊዜ #ቅዱስ_ሞይስስ እህቱን ቅድስት ሣራን ጠርቶ "እህቴ! እኔ ወደ ገዳም መሔዴ ስለሆነ አንቺ ባል አግብተሽ: ሃብት ንብረቱን ወርሰሽ ኑሪ" አላት:: #ቅድስት_ሣራ ግን መልሳ "እንዴት እኔን በዚህ ዓለም ወጥመድ ውስጥ ትተወኛለህ? ሁለታችንም ከአንድ ማሕጸን ነን:: ስለዚህ ላንተ የምትፈልገው ሁሉ ለእኔም ያስፈልገኛልና እኔም መናኝ ነኝ" አለችው::

ቅዱስ ሞይስስ የልቡናዋን መጨከን ሲያይ ነዳያንን ሰበሰበ:: ገንዘቡን: ቤቱን: ሃብቱንና ንብረቱን ሁሉ በየስልቱ ለነዳያን አካፈለ:: ሳይዘገይም እህቱን ይዞ ወደ በርሃ ተጉዋዘ:: እርሷን ከደናግል ገዳም አስገብቶ እርሱ ከወንዶች ገዳም ውስጥ መነኮሰ::

ለ10 ዓመታት ሁለቱም ለፈጣሪያቸው በጾምና በጸሎት: ከስግደት ጋር ሲገዙ: ለአባቶችና እናቶች ደግሞ በትሕትና ሲታዘዙ ኖሩ:: በእነዚህ ሁሉ ዓመታት አንድም ቀን ተገናኝተው አያውቁም ነበር:: አንዱ ለሌላኛው ተግቶ መጸለይን ግን ቸል አላሉም::

ዘመኑ ዘመነ ዐጸባ (የመከራ) ነውና መከራው እየገፋ ሲመጣ ቅዱስ ሞይስስ አንድ ነገር አሰበ:: በክርስቶስ ስም ደሙን ለማፍሰስም ወሰነ:: ወደ ከተማ ከመውጣቱ በፊት ግን ለቅድስት ሣራ መልዕክት ላከባት:: "እኔ ወደ ምስክርነት እየሔድኩ ስለሆነ ቸር ሁኚ" የሚል ነበር መልእክቱ::

እርሱ ይህንን ብሎ ወደ ከተማ ሲሔድ ግን መንገድ ላይ እህቱን አገኛት:: ገርሞት የፍቅር ሰላምታን ከተለዋወጡ በሁዋላ "እንዴት መጣሽ?" ቢላት "ወንድሜ! ቀድሞም ነግሬሃለሁ:: ላንተ የምትፈልገው የድኅነት መንገድ ሁሉ ለእኔም ያስፈልገኛል" አለችው::

ሁለቱም ተያይዘው ወደ መከራ አደባባይ ደረሱ:: በዚያም ስመ ክርስቶስን ሰብከው: ብዙ መከራንም ተቀብለው በዚህች ቀን ሰማዕት ሆነዋል::

††† አምላከ ቅድስት ሣራ ደግነቷን: መታዘዟን ያሳድርብን:: ከበረከቷ: ከሌሎችም ቅዱሳን በረከትን ይክፈለን::

††† ነሐሴ 26 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ብጽዕት ሣራ (የአብርሃም ሚስት)
2.ቅዱሳን አባ ሞይስስና እህቱ ሣራ (ሰማዕታት)
3.ቅዱሳን አጋቦስና ቴክላ (ሰማዕታት)

††† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ
2.አቡነ ሐብተ ማርያም ጻድቅ
3.አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ
4.ቅዱሳን ሰማዕታተ ናግራን
5.ቅዱስ አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን

††† "እንዲህ በቀድሞ ዘመን በእግዚአብሔር ተስፋ ያደረጉት ቅዱሳት ሴቶች ደግሞ ለባሎቻቸው ሲገዙ ተሸልመው ነበርና:: እንዲሁም #ሣራ_ለአብርሃም:- #ጌታ ብላ እየጠራችው ታዘዘችለት:: እናንተም ከሚያስደግጥ ነገር አንዳች እንኩዋ ሳትፈሩ መልካም ብታደርጉ ልጆቿ ናችሁ::" †††
(1ዼጥ. 3:5)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
#ታኅሣሥ_14

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም

ታኅሣሥ ዐስራ አራት በዚህች እለት #ቅዱስ_መርምህናም እና እኅቱ #ቅድስት_ሣራ በሰማዕትነት ዐረፉ፣ መኑፍ ከሚባል አገር #ቅዱስ_ስምዖን በሰማዕትነት ዐረፈ፣ #የቅድስት_ነሳሒት ለዕረፍቷ ነው፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱሳን_መርምህናምና_እኅቱ_ሣራ

ታኅሣሥ ዐስራ አራት በዚህች እለት ቅዱሳን መርምህናምና እኅቱ ሣራ አርባ አገልጋዩቹ በሰማዕትነት ዐረፉ፡፡ የዚህም ቅዱስ አባት የአቶር ንጉሥ የተቀረጹ ስማቸው ቤል አጵሎን የሚባሉ ጣዖታትን የሚያመልክ ነው እናቱ ግን ክርስቲያን ናት። ይህም ቅዱስ መርምህናም ወደ ዱር ሒዶ አራዊትን ያድን ዘንድ እንዲፈቅድለት አባቱን ለመነው በፈቀደለትም ጊዜ ወደ እናቱ ሒዶ "አራዊትን ለማደን ወደ በረሀ እሔዳለሁ" አላት እናቱም "የሰማይና የምድር አምላክ እግዚአብሔር በላይህ በረከትን ያሳድር" አለችው።

ከዚህም በኋላ ከአርባ ፈረሰኞች አገልጋዮቹ ጋር ወጥቶ ሔደ መቅሉብ ወደሚባል ተራራም ደርሶ በዚያ አደረ። በሌሊትም የእግዚአብሔር መልአክ ጠራው እንዲህም አለው "መርምህናም ሆይ ተነሥተህ ወደዚህ ተራራ ላይ ውጣ ስሙ ማቴዎስ የሚባል ቅዱስ ሰው ታገኛለህ እርሱም የሕይወትን ነገር ይነግርሃል" ሲነጋም ወደ ተራራው ወጣ እንደ በግ ጠጉር ለብሶ አባ ማቴዎስን አገኘው መርምህናም በአየው ጊዜ ፈራ ቅዱስ አባ ማቴዎስ "ልጄ ሆይ ወደ እኔ ቅረብ እኔም የእግዚአብሔር ፍጥረቱ የሆንኩ እንዳንተ ሰው ነኝ" አለው። መርምህናምም "ከአባቴ አማልክቶች በቀር አምላክ አለን?" አለው አባ ማቴዎስም የክርስትና ሃይማኖትን ከአባቱና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ክርስቶስን ህልውና በተለየ አካሉ ሰው መሆኑንና መከራ ተቀብሎ መሞቱን መነሣቱን ወደ ሰማይ ማረጉንም የፍርድ ቀንም እንዳ ለጻድቃን በጎ ዋጋ ለኃጢአተኞች ቅጣት እንዳለ አስተማረው።

መርምህናምም "ከራስዋ እስከ እግርዋ ለምጽ የያዛት እኅት አለችኝ የአምላክህን ስም ጠርተህ በጸሎትህ ብታድናት እኔ አምንበታለሁ" አለው አባ ማቴዎስም "እኔ አድናታለሁ ና በአንድነት እንውረድ" አለው ከተራራው በወረዱ ጊዜ አባ ማቴዎስን በመንገድ ትቶ ቅዱስ መርምህናም ወደ እናቱ ሒዶ ሁሉን ነገራት እኅቱንም በሥውር ወደ አባ ማቴዎስ ወሰዳት አባ ማቴዎስም ወደ እግዚአብሔር ጸለየና ምድሪቱን አመሳቅሎ መታት በዚያን ጊዜ ውኃ መንጭቶ እንደ ባሕር ሆነ ወደ ባሕሩም አውርዶ እጁን በራሳቸው ላይ አድርጎ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠመቃቸው አሽከሮቹን አርባ ሰዎችንም ሥጋውንና ደሙንም አቀበላቸው ወዲያውኑ ሣራ ከለምጽዋ ነጻች።

ከዚህም በኋላ አባ ማቴዎስ ስለ ከበረ ስሙ በላያቸው የሚመጣውን መከራ በሚቀበሉ ጊዜ ክብር ይግባውና ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን በማመን እንዲጸኑ መከራቸው ከዚህም በኋላ በላያቸው ጸለየና በፍቅ አንድነት አሰናበታቸው። ቅዱስ መርምህናምም በመጣ ጊዜ ወደ እናቱ ቤት ገባ ወደ አባቱ ወይም ወደ አማልክቶቹ አልሔደም አባቱም ሰምቶ ተቆጣ ወደ አማልክቶቹ ቤትም እንዲጠሩት አዘዘ ቅዱስ መርምህናም ግን ከእኅቱና ከሠራዊቱ ጋር ስሟ ቅሳር ወደ ምትባል ተራራ ሒዶ ከላይ ወጥቶ በዚያ ተቀመጠ።

አባቱም በሰማ ጊዜ ከልብሰ መንግሥትና ከዘውድ ጋር መኳንንቱን "የመንግሥቴን ሥልጣን ተረከብ ብሎሃል" እንዲሉት ላካቸው እርሱ ግን በቊጣ ተመለከታቸውና "እኔ ክብር ይግባውና የጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስን ፈጽሞ የማይጠፋ መንግሥት እሻለሁ" አላቸው። የአቶር ንጉሥ አባቱም በዚያን ጊዜ ተቆጣ ልቡ ፈርቶ ይመለስ ዘንድ አገልጋዮቹን በፊቱ እንዲገድሏቸው ካልተመለሰ ግን እርሱንም እኅቱንም እንዲገድሉ አዘዘ። ቅዱስ መርምህናምም ሰምቶ የተመኘውን ይሰጠው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ "ጸሎትህን ሰማሁ ልብህ የወደደውንም ሰጠሁህ" የሚል ቃል ከሰማይ መጣ። ከዚህም በኋላ የቅዱሳኑን ራሳቸውን በሰይፍ ቆረጡና ከጒድጓድ ውስጥ ጣሏቸው ሥጋቸውንም ያቃጥሉ ዘንድ ብዙ ዕንጨቶችን ሰበሰቡ ግን አላገኙአቸውም እግዚአብሔር ሠውሮዋቸዋልና።

ወዲያውኑ ንውጽውጽታ ሆነ ፀሐይም ጨለመ ወታደሮችም ፈርተው ሸሹ ሰይጣንም በአቶር ንጉሥ በሰናክሬም ላይ አድሮ አሳበደው እንደእሪያም ጮኸ የቅዱስ መርምህናምም እናት አይታ ወደ አባ ማቴዎስ ልካ አስመጣችውና የንጉሡን ነገር ነገረችው እርሱም በዘይት ላይ ጸልዮ ቀባው ሰይጣንም በእሪያ አምሳል ከርሱ ወጣ። በዚንም ጊዜ ንጉሥ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመነ ከቤተ ሰቦቹና በሚገዛው አገር ካሉ ሰዎች ሁሉ ጋር ተጠመቀ።

ከዚህም በኋላ አምላክን በወለደች በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ስም ቤተ ክርስቲያን እንዲሠሩ ገንዘብንም ለድኆችና ለችግረኞች እንዲበትኑ አዘዘ ሁሉንም እንዳዘዛቸው አደረጉ። የቅዱስ መርምህናምም እናት ከከበሩ ደንጊያዎች አርባ ሣጥኖችን አሠራች የልጅዋ ጭፍራ የነበሩ የእነዚያን አርባ ሰማዕታት አጥንቶቻቸውን አሰብስባ በየአንዳንዱ ሣጥን ጨመረቻቸው ለልጆቿም ብርሌ ከሚመስል ዕንቊ ሁለት ሣጥን አሠርታ በውስጣቸው አድርጋ በሠራችው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ አኖረቻቸው ከሥጋቸውም ታላላቅ የሆኑ ቊጥር የሌላቸው ተአምራት ተገለጡ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ስምዖን

ዳግመኛም በዚህች እለት መኑፍ ከሚባል አገር ቅዱስ ስምዖን በሰማዕትነት ዐረፈ፡፡ እርሱም በእስላሞች ዘመን ከመሳፍንቶቻቸው ከአንዱ ጋር ተከራከረና ቅዱስ ስምዖን ረትቶ አሳፈረው ያም እስላም ወደ መሳፍንቱ አለቃ ሒዶ "ይህ ስምዖን የእስላሞች ሃይማኖት ያቃልላል" ብሎ ወነጀለው ስለዚህም ይዘው በጽኑዕ ሥቃይ አሠቃዩት ከዚያም በኋላ ራሱን በሰይፍ ቆረጡት የሰማዕትነት አክሊል በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅድስት_ነሳሒት

በዚህች ዕለት የውሲም ኤጲስቆጶስ አባ ያዕቆብ ስርሷ የተናገረላት የሮሜ ንጉሥ ልጅ ቅድስት ነሳሒት ዐረፈች፡፡ እንዲህም አለ በአንዲት ዕለት አምላክን በወለደች በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እያለሁ የገዳሙን ደጅ ሰው ሲያንኳኳ ሰማሁ ተነሥቼም ወደ በሩ ሔድኩ ያረጀ ዓጽፍ የለበሰ ፊቱንም የተሸፋፈነ ሰው አየሁ "ከወዴት መጣህ? ወዴትስ ትሔዳለህ?" አልሁት። "ከአባ መቃርዮስ ገዳም መጣሁ በዚች ሌሊት ከዚህ ገዳም አድሬ ቊርባንን መቀበል እሻለሁ" አለኝ። ያን ጊዜ ቀዳሚት ሰንበት ነበረች እኔም "ፊትህን ካላሳየኸኝ አልከፋትልህም" አልሁት እርሱም "ፊቴን ማየት አትሻ ፊቴ በኃጢአቴ የጨለመ ነውና ፊቴንም ለሚያይ የከፋች ሥራዬ ትታየዋለች" አለኝ። በከለከልኩትም ጊዜ ወደ ዱር ሊመለስ ወደደ እኔም ተርቦ ወይም ተጠምቶ እንደሆነ ብዬ በልቤ አሰብኩ ስለዚህም ከፈትኩለትና ወደ ማደሪያዬ አስገባሁት መብልንም አመጣሁለት እርሱም "ከነገ ከቊርባን በኋላ በቀር እኔ አልበላም" በማለት እምቢ አለኝ።

ከዚህም በኋላ ወደ ቤተ ክርስቲያን ገባና በጨለማ ቦታ ቆመ ከዚያ ያሉ መነኰሳትም እስከ አደነቁ ድረስ የዳዊትን መዝሙር ሲያነብ ድምፁን እንደ መላእክት ድምፅ ሁኖ ሰማሁት በነጋም ጊዜ በእግሮቹ ላይ ተቀመጠ ምንም ምን ማንበብ አልሻም። እኛ ግን ይጸልይልን ዘንድ ልንለምነው ቀረብን እርሱም "አባቴቼ ሆይ በበደሌ ብዛት ፊቴን ያጨለምኩ ስሆን ስለ እናንተ እንዴት እጸልያለሁ" አለን። ቊርባንንም በምናሳርግ ጊዜ በእግሩ ቁሞ የቅዱስ ጳውሎስን መልእክት፣ የሐዋርያትንም መልእክትና የሐዋርያትን ሥራ ማንበብ ጀምረ በአራተኛም ጊዜ በመሠዊያው ፊት ቁሞ የቅዱስ ዮሐንስን ወንጌል ማንበብ ጀመረ በፊቱም ላይ የተከናነበውን ልብስ አስወግደ