መዝገበ ቅዱሳን
24.2K subscribers
1.97K photos
9 videos
6 files
26 links
የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው! መ/ሳ 1÷7
Bewust mesimer lemanegager
@Yesadkusitota
የሰማነውን እንናገራለን
ያየነውን እንመሰክራለን
Download Telegram
መስከረም ፪ ዕረፍቱ #ለዮሐንስ_መጥምቅ

በዛቲ ዕለት ኮነ ሰምዐ ቅዱስ #ዮሐንስ መጥምቅ ወልደ ዘካርያሰስ ካህን በእዴሁ ለሄሮድስ ንጉሥ ዐላዊ ሕግ፡፡
#በዚህች_ቀን_የካህኑ_የዘካርያስ_ልጅ_የከበር_አጥማቂው_ዮሐንስ_ሕግን_አፍራሽ_በሆነ_በንጉሥ_ሄሮድስ_እጅ_ሰማዕት_ሆን፡፡#

ይህም እንዲህ ነው በፊልጶስ ሚስት በሄርድያዳ ምክንያት ነቢዩ ዮሐንስ በገሠጸው ጊዜ ፊልጶስ ወንድሙ ስለሆነ ቅዱስ #ዮሐንስም የወንድምህን ሚስት ልታገባ አይገባህም ይለው ነበርና፡፡#ቅዱስ_ዮሐንስም ሄሮድስን የወንድሙን የፊልጶስን ሚስት ሄሮድያዳን ስለማግባቱና ሌላም ያደርገው ስለነበረ ክፉ ሥራ ሁሉ ይገሥጸው ነበር ፡፡ደግሞም በተግሣጽ ላይ ተግሣጽን ጨመረ፡፡ስለዚህም ዮሐንስን ተቀየመውና በግዞት ቤት አኖረው፡፡

ሄሮድስም #ዮሐንስን ይፈራው ነበር ጻድቅ ቅዱስ ሰው እንደሆነ ያውቅ ነበርና ብዙ ይጠባበቀውም ነበር፡፡
ሄሮድስ የተወለደባት ቀን በዓል የሚከብርባት ዕለት ነበረች መኳንንቱን አለቆቹን መሣፍንቱን ሹሞቹን በገሊላ አገር ያሉትን ታላለቅ ሰዎች ግብር አገባ፡፡
የሄሮድያዳ ልጅም ወደ አዳራሹ ገብታ ዘፈነች ሄሮድስን ደስ አሰኝችው ከእርሱ ጋር በማዕድ የነበሩትንም ንጉሡም ያቺን ብላቴና የምትሺውን ለመኚኝ እስጥሻለሁ አላት ፡፡እስከ መንግሥቱ እኪሌታ ድረስም ቢሆን የለመነችውን ሊሰጣት ማለላት ፡፡
ወጥታም እናቷን ምን ልለምነው አለቻት እናቷም የመጥምቁ ዮሐንስን ራስ አለቻት ፡፡ያን ጊዜም እየሮጠች ወደ ንጉሡ ገብታ የመጥምቁ ዮሐንስን ራስ በወጭት አሁን እንትስጠጭ እሻለሁ ብለ ለመነችው፡፡
ንጉሡም ስለ መሐላው አብረውት ስለ ነበሩትም ሰዎች አዘነ እምቢ ሊላት ግን አልወደደም ፡፡

ያን ጊዜም ባለወጎችን ላከ በእሥር ቤትም ሳለ #የዮሐንስን ራስ ቆርጠው ራሱንም በወጭት አምጥተው ለዚያች ብላቴና ሰጡአት እርሷም ወስዳ ለእናቷ ሰጠች ፡፡
በዚያችም ቀን የቅዱስ ዮሐንስ ራስ ከሄሮድያድ እጆቿ ላይ ወደ አየር ስለ በረረ ታላቅ ድንጋጼ ሆነ፡፡ደግሞም ሄሮድስ ሆይ የወንድምህን ሚስት ልታገባ አይገባህም እያለች በመጮህ ዘልፋዋላችና ፡፡

#ደቀ_መዛሙርት ይህን በሰሙ ጊዜ መጥተው በድኑን ወስደው ቀበሩት ፡፡
ለእግዚአብሄር ምስጋና ይሁን እኛንም በከበረ #በአጥማቂው_ዮሐንስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር አሜን፡፡
@petroswepawulos