መዝገበ ቅዱሳን
24.2K subscribers
1.97K photos
9 videos
6 files
26 links
የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው! መ/ሳ 1÷7
Bewust mesimer lemanegager
@Yesadkusitota
የሰማነውን እንናገራለን
ያየነውን እንመሰክራለን
Download Telegram
መስከረም ፪ በዚች ዕለት

#ነስሑ እስመ ቀርበት መንግሥተ ሰማያት እያለ የመጣ

#ቃለ ዓዋዲ ዘይሰብክ በገዳም በበረሐ የሚያስተምር አዋጅ ነጋሪ ተብሎ በኢሳይያስ የተነገረለት ኢሳ.፵፥፫ ማር ፩፥ ፫ ሉቃ ፫፥፬

#ጺሑአ ፎኖቶ ለእግዚአብሔር…. የእግዚአብሔርን መንገድ ጽረጉ እያለ ያስተማረ

#ምግቡ የበረሐ ማርና አንበጣ የሆነ

#ልብሱም ከግመል ፀጉር የሆነለት

#ጌታውን "አንተ ካህኑ ለዓለም በከመ ሲመቱ #ለመልከጸዴቅ ብሎ ያጠመቀ

#ከሴት ከተገኙት ሁሉ "አልቦ ዘይዐብዮ"ብሎ እግዚእነ ክርስቶስ የመሰከረለት የነባቤ ጽድቅ ዮሐንስ ምትረተ ክሳዱ ናት።

#ሄሮድስ አንቲጳስ የወንድሙን ሚስት ባገባ ጊዜ "ኢይደልወከ ታውስብ ለብእሲተ እሑከ ብሎ ቢገስፀው አሻፈረኝ ብሎ አሰረው አስሮትም አላበቃ ሌላ ስሕተት ሊደግም ሆነ…..

#ዮሐንስ በእስር በእንግልት ላይ እያለ የሄሮድስ አንቲጳስ ልደቱን ሊያከብር ባለስልጣናቱን መኳንንቱን ይዞ ተቀምጦ ግብዣን አደረገ

#በግብዣውም የሄሮድያዳ ልጅ "ሰሎሜ" ይላታል ዮሴፍ ወልደ ኮርዮን/ሊቁ ግን ወለተ ሄሮድያዳ ብሎ ያልፋታል/ ዘፋኝ ነበረችና ዘፈነችለትና ደስ አሰኘችው
"መጽኣት ወለተ ሄሮድያዳ ወዘፈነት ሎቱ ወአስመረቶ" እንዲል

#ከግብዣው ከጠጣው ወይን የተነሳ ዘፈኑም ተጨምሮበት ያልሆነ ቃል ገባ

"እስከ መንግሥቴ እኩሌታም ቢሆን እሰጥሻለሁ የወደድሽውን ጠይቂኝ" ብሎ አላት ለዘፋኝቱ ወለተ ሄሮድያዳ

#እሷም የተንኮለኛ ልጅ ተንኮለኛ ነበረችና ሂዳ እናቲቱን አማከረቻት። እናቲቱስ በዚህ ቅጽበት ማን "ጠላት" ነበረባትና ሌላ ታስብ? ንግሥትነትን ሽታ የባሏን ወንድም ብታገባ በጥብአት ተቃውሟታልና "የዮሐንስን ራስ በወጭት ስጠኝ በይው" አለቻታ።

#ዘፋኝቱ ልጇም እንደተመከረችው"ሀበኒ በጻሕል ርእሰ ዮሐንስ"ብላው ቁጭ

#ስካር ፈንጠዝያው ያልወጣለት ሄሮድስ አንቲጳስ ምን ይሁን ምን ይዋጠው?

አንዴ ምሎላታላ። መሐላውን ቢያፈርስ መኳንንቱ ምን ሊሉት እንደሚችሉ አሰበ።

አላወቀውም እንጂ ሊቁ "እምሔሶ ለሄሮድስ ይብላዕ መሐላሁ እምያምትር ርእሶ ለዮሐንስ" እንዳለው ክብርቲቱን ራስ ከሚያስቆርጣት መሐላውን ቢበላ ይሻለው ነበር።

#እሱቴ ምን ገዶት ተሳስቶ የማለውን መሐላ ሕግ አርጎት አረፈዋ እንዴት ይሻረው? በዚህ ላይ ሌላ ስሕተት አከለበት። ጋሻ ጃግሬዎቹን ጠርቶ "ቁረጡና ስጧት" ብሎ ለእሱ ቀጠን ያለች ነገር ግን የእግዚአብሔርን ነቢይ ዐርኩ ለመርዓዊ ክርስቶስ የሆነውን የውዱ ዮሐንስን ክብርት ራስ የምታሰይፍ ትእዛዙን ሰጠአ።

#ይህ ሁሉ የሆነው ግን መምህር ወመገስጽ ዘኢያደሉ ለገጽ እንዲሉ ይህ ንጉሥ፣ ይህ ባለጸጋ ፣ ይህ ድሃ እያለ ለሰው ሳያዳላ ማስተማር ያለበትን እያስተማረ መገሰጽ ያለበትን እየገሰጸ በመምጣቱ ነበር።

#ሄሮድስ አንቲጳስ እንደው "ተኮነን" ሲለው እንጂ ክብርት ርእሱስ ተቆርጣ ተሰይፋ አልቀረችም ለ፲፭ ዓመታት በዓለም ተዘዋውራ ወንጌል አስተማረች እንጂ

#ስለ እውነት የሞተ የእውነት ምስክር የሆነ የቅዱስ ዮሐንስ በረከት ረድኤቱ ኃያል የምትሆን ጸሎቱ በኛ በሁላችን ፀንታ ትኑር የሱን አርአያ ተከትለን ስለእውነት የምናወራ ስለእውነት የምንኖር ስለእውነት የምንመሰክር እንሆን ዘንድም ትርዳን አሜን+++