መዝገበ ቅዱሳን
24.2K subscribers
1.97K photos
9 videos
6 files
26 links
የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው! መ/ሳ 1÷7
Bewust mesimer lemanegager
@Yesadkusitota
የሰማነውን እንናገራለን
ያየነውን እንመሰክራለን
Download Telegram
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

✞✞✞ እንኩዋን ለቅዱሳን ጻድቃን "እንድራኒቆስ ወአትናስያ" እና ለአቡነ "ፊልዾስ ዘደብረ ሊባኖስ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞

+*" ጻድቃን እንድራኒቆስ ወአትናስያ "*+

=>ሁለቱ ቅዱሳን ባል እና ሚስት (ባለትዳር) ናቸው:: የነበረበት ዘመን 4ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው:: እስኪ #እግዚአብሔር የቀደሰው ጋብቻ ምን እንደሚመስል እንመልከት::

+#እንድራኒቆስና_አትናስያ በዘመናቸው ከልጅነት ጀምረው ቃለ እግዚአብሔርን የሚሰሙ : ለወላጆቻቸው የሚታዘዙ ነበሩ:: ዘመኑ ደርሶ በሚገባው የተክሊል ሥርዓት ጋብቻቸውን ፈጸሙ:: 40 ቀን ከተፈጸመ በሁዋላ ከምንም ነገር በፊት 2ቱ ቁጭ ብለው ተወያዩ::

+የውይይታቸው ርዕስ ደግሞ "ፈጣሪያችን በምን እናስደስተው" የሚል ነበር:: ውይይታቸው የጠናቀቀው በእነዚህ ውሳኔዎች ነው::

1.ሁልጊዜም እንግዳ መቀበል አለብን::

2.ነዳያን ከቤታችን ሊጠፉ አይገባም::

3.ጸሎት : ጾምና ስግደት በቤት ውስጥ አይቁዋረጥም::

4.አብሮ ለመተኛት መቸኮል የለብንም::

+እነርሱ መልካምን አስበዋልና አምላክ የሰጣቸውን ሃብት ሲመጸውቱ ኖሩ:: ከዘመናት የቅድስና ጉዞ በሁዋላ በፈቃደ እግዚአብሔር 2 ልጆችን አከታትለው ወለዱ:: ወንዱን "#ዮሐንስ" : ሴቷን ደግሞ "#ማርያም" አሏት::

+እነርሱን ከወለዱ በሁዋላ እንደ ገና ሌላ ውሳኔ አሳለፉ:: "ይህንን ላደረገልን ጌታ ከዚህ በሁዋላ አልጋ እንለያለን" ብለው ለ12 ዓመታት በጾምና በጸሎት ተወሰኑ::

+ሕጻናቱ ዮሐንስና ማርያም በቅንነት አድገው እድሜአቸው 12 ሲሆን 2ቱም በአንድ ቀን ታመው ሞቱ:: ይህ ለአንድ ወላጅ የመጨረሻው አሰቃቂ ፈተና ነው:: ሁሉቱም (እንድራኒቆስና ሚስቱ አትናስያ) ልጆቻቸውን ታቅፈው ወስደው ቀበሩ::

+#እንድራኒቆስ ከቀብር በሁዋላ ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ ምርር ብሎ አለቀሰ:: ግን እንዲህ አለ:-
"አምላከ #ኢዮብ! አንተ ሰጠኸኝ:: አንተም ነሳኸኝ:: ስምህ ለዘለዓለም ይባረክ" ብሎ ሔደ:: እናት #አትናስያ ግን ከሐዘን ብዛት ልቡናዋ ሊሠወር ጥቂት ቀረው::

+የልጆቿ መቃብር ላይ ተደፍታ ስታለቅስ ቅዱስ መልአክ ልቡናዋን ወደ ሰማይ አሳረገው:: ልጆቿ ዮሐንስና ማርያም በገነት ውስጥ ከቅዱሳን ጋር ሐሴትን ሲያደርጉም ተመለከተች:: ወዲያው ወደ ቤት ተመልሳ ለባሏ እንድራኒቆስ ያየችውን ነገረችውና ደስ አላቸው::

+እዛው ላይ "ለዚህ ውለታው ከነፍሳችን ውጪ የምንሰጠው የለም" ብለው ሊመንኑ ተስማሙ:: እጅግ ሃብታሞች ነበሩና ነዳያንን ሰብስበው : ሃብት ንብረታቸውን : ቤት ርስታቸውን አካፍለው ወደ ገዳመ አስቄጥስ ሔዱ::

+እርሷ ከሴቶች ገዳም : እርሱ ደግሞ ከወንዶቹ ገቡ:: ለ12 ዓመታት በፍጹም ተጋድሎ ለፈጣሪያቸው ተገዙ:: በእነዚህ ዘመናት ተያይተው : አንዱ ስለ ሌላው ሰምቶ አያውቅም:: በጸሎት ግን ያለማቁዋረጥ ይተሣሠቡ ነበር::

+ከ12 ዓመታት በሁዋላ የፍቅር አምላክ በሁለቱም ልቡና በተመሳሳይ ሰዓት : ተመሳሳይ ሐሳብን አመጣ:: እርሱ ከአበ ምኔቱ (#ታላቁ_አባ_ዳንኤል) : እርሷም ከእመ ምኔቷ አስፈቅደው ወደ #ኢየሩሳሌም ከቅዱሳት መካናት ለመባረክ ጉዞ ጀመሩ:: በየፊናቸው ጥቂት እንደተጉዋዙ እርስ በርስ ተያዩ::

+እርሷ ለየችው:: እርሱ ግን ጭራሽ ሊለያት አልቻለም:: ይህም ጥበበ እግዚአብሔር ነው:: 2ቱም እየተጫወቱ : እየጸለዩ በሰላም ተባርከው ወደ ግብጽ ተመለሱ:: በእነዚህ ጊዜያት ቅድስት አትናስያን የሚለያት አልነበረም:: አካሏ በገድል ከመለወጡ ባሻገር የለበሰችው እንደ ወንድ መነኮሳት ነበር::

+ወደ #ገዳመ_አስቄጥስ ሲደርሱ ጸጋው ተሰጥቶታልና #አባ_ዳንኤል ባልና ሚስት መሆናቸውን አወቀ:: "ለምን አብራችሁ አትኖሩም?" አላቸው:: "እኛ ደስ ይለናል" አሉት:: ከዚያ እርሷ እያወቀችው: እርሱ ሳያውቃት ለ12 ዓመታት አብረው በቅድስና ኖሩ::

+ከእነዚህ ዘመናት በሁዋላ ግን ሐምሌ 28 ቀን ቅድስት #አትናስያ ታመመች:: አባ ዳንኤል ሥጋውን ደሙን አቀብሏትም ዐረፈች:: ሊገንዟት ሲቀርቡ ቅዱስ #እንድራኒቆስ መልኩዋን ልብ ቢለው ሚስቱ ናት::

+በአንድ ጊዜ ሚስቱንና የሚወደውን ባልንጀራ በማጣቱ አለቀሰ:: እርሷን ቀብረው ወደ በዓቱ ተመልሶ "ጌታ ሆይ! ውሰደኝ?" አለ:: እርሱም ተከትሏት ዐረፈ:: አባ ዳንኤል እርሱንም ቀብሮ ጥዑም ዜናቸውን ጻፈ::

+*" አባ ፊልዾስ ዘደብረ ሊባኖስ "*+

=>ታላቁ ኢትዮዽያዊ ጻድቅ: ሐዋርያና ሰማዕት #አቡነ_ፊልዾስ የጻድቁ #አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት ደቀ መዝሙር ሲሆኑ የተወለዱት በምድረ ሽዋ በ1266 ዓ/ም ነው:: ከልጅነታቸው ጀምረው ምሥጢር ተመራማሪና መጻሕፍትን መርማሪ የነበሩት ጻድቁ የመነኑት ገና በ15 ዓመታቸው ነበር::

+#በደብረ_ሊባኖስ በአሞክሮ ለ3 ዓመታት ቆይተው መንኩሰዋል:: ለ22 ዓመታትም የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ደቀ መዝሙር ሆነው አገልግለዋል:: አቡነ ተክለ ሃይማኖት በ1306 ዓ/ም ነሐሴ 24 ቀን ሲያርፉ የተተኩት አባ ኤልሳዕ ቢሆኑም ለ3 ወራት ቆይተው ዐርፈዋል::

+በ1307 ዓ/ም አቡነ ፊልዾስ የደብረ ሊባኖስ አበ ምኔት (እጨጌ) ሁነዋል:: ገዳሙንም ለ28 ዓመታት መርተዋል:: ከዚያም በዘመነ አፄ ዓምደ ጽዮንና በአፄ ሰይፈ አርዕድ ብዙ ስደት: መከራ: እሥራትና ግርፋት ደርሶባቸዋል:: ምክንያቱ ደግሞ እውነትን መናገራቸውና ነገሥታቱን መገሰጻቸው ነበር:: በስደትም ለ6 ዓመታት ከ9 ወራት ቆይተዋል::

+ሃገሪቱን በስብከተ ወንጌል ካበሩ #12ቱ_ንቡራነ_እድ አንዱ የሆኑት #እጨጌ አባ ፊልዾስ በተወለዱ በ74 ዓመት ከ9 ወራቸው በ1341 ዓ/ም ዐርፈዋል:: የተቀበሩት #በደብረ_ዕንቁ ሲሆን ካረፉ በ140 ዓመት #አቡነ_መርሐ_ክርስቶስ ዐጽማቸውን አፍልሰዋል::

=>ከቅዱሳኑ እንድራኒቆስ ወአትናስያ እና ከጻድቁ አቡነ ፊልዾስ በረከትን ይክፈለን::

=>ሐምሌ 28 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱሳን ጻድቃን እንድራኒቆስና አትናስያ
2.አቡነ ፊልዾስ ጻድቅ (ዘደብረ ሊባኖስ)

=>ወርኀዊ በዓላት
1.አማኑኤል ቸር አምላካችን
2.ቅዱሳን አበው (አብርሃም : ይስሐቅና ያዕቆብ)
3.ቅድስት ዓመተ ክክርስቶስ
4.ቅዱስ ቴዎድሮስ ሮማዊ (ሰማዕት)

=>+"+ ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል:: ከሚስቱም ጋር ይተባበራል:: ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ:: ይህ ምሥጢር ታላቅ ነው:: እኔ ግን ይህን ስለ ክርስቶስና ስለ ቤተ ክርትስቲያን እላለሁ:: ሆኖም ከእናንተ ደግሞ እያንዳንዱ የገዛ ሚስቱን እንዲህ እንደ ራሱ አድርጐ ይውደዳት:: ሚስቱም ባሏን ትፍራ:: +"+ (ኤፌ. 5:31)

✞✞✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞✞✞
@petroswepawulos
#ታኅሣሥ_29_ልደታቸው_ከጌታችን_ልደት_ጋር_የተባበረላቸው_ቅዱሳን (በድጋሚ ) ፤ እንዲሁም #አቡነ_አብሳዲ_ዘደብረ_መጒና ልደታቸው ከጌታችን ልደት ጋር እንዲሁም የተባበረላቸው አባት
#አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ፤
#ቅዱስ ላሊበላ፤
#ቅዱስ ነዓኵቶ ለአብ፤
#አቡነ አብሳዲ ዘደብረ መጕናና የቆብ ልጃቸው #አቡነ መዝራዕተ ክርስቶስ፤
#ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ፤
#ቅዱሳን ነገሥታት አብርሃ ወአጽብሃ፤
#አቡነ አካለ ክርስቶስ፤
#መስፍኑ ኢያሱ፤
#አቡነ ዳንኤል ዘገርዓልታ፤
#ዳግማዊ ቂርቆስ ዘቡልጋና ሌሎችም ቅዱሳን አሉ፤ ነገር ግን ከቅዱሳን በዓል በላይ የጌታ በዓል መከበር ስለሚገባው የቅዱሳኑ ዋና በዓላቸው በሌላ ቀናት /በዕረፍታቸው…../ ቀን ይታሳባል፡፡

————-
#አቡነ_አብሳዲ_ዘደብረ_መጒና

#አቡነ_አብሳዲ_ዘደብረ_መጒና_#ታኅሣሥ 29 ልደታቸው ከጌታችን ልደት ጋር ከተባበረላቸው ቅዱሳን መካከል አንዱ ናቸው፡፡
#የበረሃው_ዕንቊ_ገዳም_መንበረ_ልዑል_ጽርሐ_አርያም_ደብረ_መጕናን_የመሠረቱ፡፡
፠ አብርሃም ቅድስት ሥላሴን እንዳስተናገደ፤ #አቡነ_አብሳዲ_ደግሞ_ጌታችንን_ተቀብለው_እግሩን_ያጠቡ_ናቸው፡፡ (ፎቶውን ይመልከቱ)
#ደቀ_መዛሙርቶቻቸው_በተሰየፉበት_አንገረብ_ወንዝ_ላይ_ #44ት #የፍል_ውኃ_ፈዋሽ_ጠበል_አንገረብ_የሚባል_ያላቸው፤ በሃገራችን ብዙሃን ሕዝብ ከሚጠመቅባቸው ጠበሎች ዋነኛው ከተጠማቂው ሕዝብ ብዛት የተነሣ #ቀንና_ሌሊት_ጥምቀት_የሚካሄድበት፡፡ (ፎቶውን ይመልከቱ)
፠ ከብቃታቸው የተነሣ ወደ ላይ ጽርሐ አርያምን ወደ ታች በርባሮስ ድረስ የሚደረገውን የሚመለከቱ፤
#ወላዴ_አእላፍ#ወላዴ_ቅዱሳን_ሊቃውንት#አበ_ብዙኃን#ወላዴ_ሰማዕታት የሆኑ፤
፠ በፀሐይ ሰረገላ፥ በብርሃን መንኰራኵር እየተጫኑ እንደ ሐዋርያት የሚያስተምሩት፤
፠ 470 ዓመታትን የኖሩት፡፡
፠ ታኅሣሥ 29 የጌታችንና,ን የጻድቁን የልደት በዓል፤ ሙሉ አርማጭሆ እንዲሁም የትክል ድንጋይ፣ የዳንሻና አካባቢው ምዕመናን በ10ሺዎች የሚቈጠር ሕዝብ የሚያከብርላቸው፡፡
* ምንኵስናን የተቀበሉት ከአቡነ ዮሐንስ ከማ ነው፡፡
* በማንዳባ ገዳም ከ7ቱ ከዋክብትና ከ7ቱ ከዋክብተ ጣና አንዱ ከኾኑትና ደንጊያን እንደ ጀልባ ከሚጠቀሙት ከአቡነ ያሳይ ጋር ብዙ የጽድቅ ሥራና የትሩፋት ተጋድሎን ፈጽመዋል፡፡
* ቀድሞ በኤርታ ደብረ ማርያም ነበር የሚኖሩት፤ ኋላ ታቦተ ማኅበረ በኵርንና ታቦተ ኪዳነ ምሕረትን ይዘው ብዙ ቅዱሳንን ወዳፈለቁበት መሥዋዕተ ኦሪት ይሠዋበት ወደነበረው ገዳመ መጕና መጡ፤ ገዳሙ የሚገኘውም በጎንደር ታች አርማጭሆ ነው፡፡
‹‹በሬ ሜዳ›› የሚባለው ቦታ ላይ የጌታችን ልደትና የጻድቁ ልደት ዝክር የሚዘከርበት ምርፋቅ ነው፡፡
ጻድቁ የተጓዙባቸው ምዕራፋት ከቁርባኔ ወንዝ እስከ መታጠቂያ በር 13ት ሲሆኑ የ13ቱ ሕማማት ምሳሌ ሲሆኑ፤ የመታጠቂያ በር ደግሞ የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነው፡፡
በ1407 ዓ.ም. በአፄ ይስሐቅ ዘመን ‹‹ዳሩ እሳት ፥ መሐሉ ገነት፡፡›› ተብሎ ተገድሟል፡፡
ወላዴ አእላፍ አበ ብዙኃን ዐምዳ ወብርሃና ለደብረ መጒና በቆብ የወለዷቸው በርካታ ቅዱሳን ቢኖርም፤
#ገዳማትን_የመሠረቱ_ለአብነት_ዋናዎቹ_
#አቡነ_ስነ_ኢየሱስ_ (ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ ገዳምን የመሠረቱ)
፠ አቡነ ሥልጣነ ክርስቶስ (አመራ ቊስቋም ገዳምን የመሠረቱ)
#አቡነ_ልብሰ_ክርስቶስ_ (ዳውጨና አማኑኤል ገዳምን የመሠረቱ)
፠ አቡነ ማቴዎስ (ያይራ ተክለ ሃይማኖት ገዳምን የመሠቱ)
#አቡነ_ዮሐንስ_ዘመረባ (ጊዮርጊስ ገዳምን የመሠረቱ)
፠ ሰማዕቱ አቡነ ጽጌ ድንግል (እንኮ ድብ ገዳምን የመሠረቱ)
#አቡነ_ዘወልደ_ዳዊት (ጐረፍ ተክለ ሃይማኖትን የመሠረቱ)
፠ አቡነ መቅደሰ ክርስቶስ (ሳይኮ ኪዳነ ምሕረትን የመሠረቱ)
#አቡነ_ህላዌ_ክርስቶስ (አምስትያ ገዳምን የመሠረቱ)
፠ አቡነ ተላዌ ክርስቶስ ( ገዳምን የመሠረቱ)
#አቡነ_ከናፍረ_ክርስቶስ (ገዳምን የመሠረቱ)
፠ አቡነ የማነ ክርስቶስ (ገው ጊዮርጊስን የመሠረቱ)
#አቡነ_ዕደ_ክርሰቶስ (የኢትዮጵያና የግብፅ ሐዋርያ ፥ የደብረ መጕና 3ኛ መምህር /አበምኔት/)
፠ አቡነ መዝራዕተ ክርስቶስ (በትግራይ ገዳምን የመሠረቱ፤ ልደታቸው ከአባታቸው ጋር በታኅሣሥ 29 የተባበረላቸው)
#ሰማዕቱና_በአባታቸው_ወንበር_የተተኩት_አቡነ_አምኀ_ጊዮርጊስ፡፡ (የደብረ መጕና 2ኛው መምህረ /አበምኔት/) ሲሆኑ፤
#ቅዱሳን_ደራስያን_ሊቃውንት_ከሆኑት_መካከል_ለአብነት_
#አባ_ገብረ_ኢየሱስ_ (የሰቈቃወ ድንግል ደራሲ)
#እጨጌ_በትረ_ጊዮርጊስ_ (በአፄ ፋሲል ዘመን የኢትዮጵያ ሊቃውንት አፈ ጕባኤ የነበሩና የቅባት ሃይማኖት መሪዎች እነ አልፎንሱ ሜንዴዝን የረቱ …. በዚህም ሊቃነታቸው በዐይኑ ያየ ባለቅኔ፤
‹‹ወረከብናሁ ለበትር ዘያደክማ ለሮሜ፤
ቅሩጸ በንባብ ወጽሩበ በትርጓሜ፡፡›› ብሎ የተቀኘላቸው የሊቃውንት ዋልታ፡፡
#አባ_ስብሐት_ለአብ_ (የመልክ ሥላሴ፣ ሰይፈ ሥላሴ፣ ዘይነግሥን የደረሱና 14ቱን ቅዳሴ ያመሠጠሩና በአንድምታ የተረጐሙ፣ በጎንደር ደብረ ብርሃን ሥላሴ ከብዙ ሊቃወንት ጋር በመሆን የቅኔና የመጻሕፍትን ምሥጢር ከነሙሉ አገባቡና እርባ ቅምሩን እንዲሁም የአቡሻኽርን ሁሉ የቀመሩ፤ የንጉሡ የአድያም ሰገድ ኢያሱ መምህረ ንስሐ የነበሩ)
#አባ_ዳንኤል_፤ (ብዙ መጻሕፍትን ያሰባሰቡና የጻፉ፤ ንዋያተ ቅድሳትን የሚሠርቅ ‹‹ቢዘራ ለበረድ ፥ ቢወልድ ልጁን ለጕጓድ፡፡›› ብለው ከ8000 በላይ ሊቃውንትን በማሰባሰብ እንዲወሰን ያደረጉ፡፡
#ከላይ_ያሉትን_ለአብነት_የጠቀስናቸውን_ቅሳንና_ሊቃውንት_አስተምረውና_ወልደው_
ለ90 ዓመታት ፍሬና ቅጠላ ቅጠል ተመግበው፤
ራቁታቸውን በጋ ከክረምት በበረሃው መንነው፤
ሳማ (አበርባራን) ለትሩፋትና ለተጋድሎ ለብሰው፤
በፀሐይ ሰረገላ፥ በብርሃን መንኰራኵር እየተጫኑ እንደ ሐዋርያት በማስተማራቸው፤ የጸጋና የቅብዐት ተካተዮችን እያስተማሩ ወደ እናት ቤ/ክ በመመለሳቸው፤
የሚያምረውን ሥጋዊ ደም ግባታቸውንና ሰውነታቸው እንደ ጻድቁ ቅዱስ ኢዮብና እንደ ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ወደ ቁስል በመቀየራቸውና ሥስቃዩንና መከራውን በመቻላቸው፤ ቁስላቸው ተልቶ ትሎቹን የገዳሙ አእዋፋት እስኪመገቡት ድረስ በመታገሣቸው፡፡
*
በርካታ ቃል ኪዳን አምላካችን ሰጥቷቸው በተወለዱ በ470 ዓመታቸው ዐርፈዋል፡፡
@petroswepawulos
#ኅዳር_14

ኅዳር ዐሥራ አራት በዚህች ቀን #አባ_መርትያኖስ_ዘጠራክያ አረፈ፣ #የአባ_ዳንኤል_ገዳማዊ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አባ_መርትያኖስ_ዘጠራክያ

ኅዳር ዐሥራ አራት በዚህች ቀን የሀገረ ጠራክያ ኤጲስቆጶስ ቅዱስ አባት አባ መርትያኖስ አረፈ።

ይህም ቅዱስ ሶርያ ከምትባል አገር ነው ወላጆቹም ክርስቲያን ናቸው እርሱም በገድል የተጠመደ ተጋዳይ ነው አርዮሳውያንንም የሚቃወማቸው ከሀድያን የሚላቸው አውግዞም የሚያሳድዳቸው ሆነ። ስለዚህም በእርሱ ላይ ታላቅ መከራ ደረሰበት። በሚያልፍባትም ጎዳና ጠብቀው ይይዙታል አብዝተውም ገርፈው እግሩን ይዘው በሜዳ ውስጥ ይጎትቱታል እንዲህም ብዙ ጊዜ አደረጉበት። ከዚህም በኋላ ከእርሳቸው ሸሽቶ ወደ ሩቅ አገር ተጉዞ ከኤርትራ ባሕር ዳር ደረሰ ከምድር የሚበቅሉ ቅጠሎችን እየተመገበ በዚያ በዋሻ ውስጥ ብዙ ዓመታትን ኖረ።

ኤጲስቆጶስም ይሆን ዘንድ እግዚአብሔር መረጠው እነሆ የተጋድሎውና የትሩፋቱ ዜና በተሰማ ጊዜ ከዚያ ወስደው ጠራክያ በሚባል አገር ላይ ኤጲስቆጶስነት ሾሙት እንደ ሐዋርያት ሥርዓት በሹመቱ በጎ አካሔድን ተጓዘ በዘመኑም በብዙዎች ላይ ሰላም ፍቅር ቸርነት ሆነ።

እግዚአብሔርም በእጆቹ ታላላቅ ተአምራትን አደረገ በጎዳናም አልፎ ሲሔድ የሞተ ሰው አየ ሌላም ዓመፀኛ ልቡ የደነደነ በሐሰት ከእርሱ ላይ አራት መቶ የወርቅ ዲናር አለኝ ያንን ካልሰጡኝ አላስቀብርም ብሎ ዘመዶቹን ሲከለክል ነበር። ይህም ቅዱስ የሞተውን ይቅበሩት ተዋቸው ብሎ ብዙ ለመነው እርሱ ግን አልሰማውም። በዚያንም ጉዜ ይህ ቅዱስ ወደ እግዚአብሔር እየጸለየ ማለደ ያን ጊዜ የሞተው ሰው ተነሥቶ ምንም ምን ዕዳ እንደሌለበት ተናገረ።

ከዚህም በኋላ ቅዱስ መርትያኖስ ያንን ዓመፀኛ በሰው ፊት እንዲህ አለው ለምን በሐሰት ተናገርክ የተሠወረውን የሚያውቅ እግዚአብሔርን አትፈራውምን በዚያንም ጊዜ ያ ዓመፀኛ ሞተ ከሞት የተነሣው ግን በሰላም ወደ ቤቱ ገባ።

ከዚህም በኋላ ይህ ቅዱስ መርትያኖስ ብዙ ዘመናትን ኖረ መልካም አገልግሎቱንም ፈጽሞ እግዚአብሔርንም ደስ አሰኝቶ በሰላም አረፈ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አባ_ዳንኤል_ገዳማዊ

በዚህችም ቀን ለፋርስ ንጉሥ ተአምራት ያደረገና ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያሳመነው የአባ ዳንኤል የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው።

የእምነቱም ምክንያት እንዲህ ነው ይህ ንጉሥ ጽኑዕ የሆነ የሆድ በሽታ ታሞ ነበር፤ ባለ መድኃኒቶችም ሊአድኑት አልቻሉም። ንጉሡም ከማዕዱ የሚመግበው አብሮት የሚኖር ሥራየኛ ሰው ነበረው። ንጉሡም እንዲህ አለው "ያንተ ከእኔ ጋር መኖር ጥቅሙ ምንድን? ነው ከዚህ በሽታ ካልፈወስከኝ እገድልሃለሁ።"

ሥራየኛውም ንጉሡን በተንኮል እንዲህ ብሎ ተናገረው "ንጉሥ ሆይ የምነግርህን ካደረግህ ከደዌህ ትድናለህ። አሁንም ለአባትና እናቱ አንድ ብቻ የሆነ ልጅ ይፈልጉልህ እናቱ አሥራ ትያዘው አባቱም ይረደው በእርሱም ደም ትድናለህ።" መሠርዩ ይህን ማለቱ ግን እንዲህ ያለ ሥራ መሥራትን ንጉሥ ይፈራል ወይም ልጁን የሚሰጥ አይገኝም ብሎ አስቦ ነው።

ንጉሥም በሚገዛው አገር ውስጥ ፈልገው በአንድ ሺህ የወርቅ ዲናር ሕፃን ልጅ ይገዙለት ዘንድ አሽከሮቹን አዘዘ። በዚያችም አገር አንድ ልጅ ያላቸው ድኆች የሆኑ ባልና ሚስት ነበሩ እነርሱም ይህን ነገር ሲሰሙ ልጃቸውን ወደ ንጉሥ ወሰዱ ልጁም በማልቀስ እኔ በፈጠረኝ እግዚአብሔር ላይ ተማምኛለሁና እርሱም ያድነኛል ይል ነበረ።

እናቱም አጥብቃ አሠረችው አባቱም ሊያርደው በንጉሡ ፊት ሾተሉን መዘዘ፤ በዚያንም ጊዜ ሕፃኑ አይኖቹን ወደ ሰማይ ቀና አድርጎ ወደ እግዚአብሔር በልቡ ሲጸልይ ከንፈሮቹን አንቀሳቀሰ። እግዚአብሔርም በንጉሡ ልብ ርኅራኄን አሳደረ ፈትታችሁ ልቀቁት ብሎ አዘዘ። ወደርሱም አቅርቦ "ዐይኖችህን ወደ ሰማይ በአቀናህ ጉዜ ምን አልክ?" አለው። "ጌታዬ ሆይ ልጅን የሚገፋው ቢኖር አባትና እናቱ ያድኑታል ከዚያም የጸና ሥራ ቢኖር ንጉሥ ዳኛ ያድነዋል እኔ ግን ከሁላችሁም ርዳታ በአጣሁ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ለመንኩ" አለው። ንጉሡም ሰምቶ ራራለት አንድ ሽህ የወርቅ ዲናርንም ሰጠው።

ስለዚህም እግዚአብሔር ይቅር ሊለው ወዶ መነኰስ ዳንኤልን ላከለት። እርሱም ወደ ንጉሡ በደረሰ ጊዜ በፊቱ ተአምራትን አድርጎ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አሳመነውደ ከበሽታውም ፈወሰው። ከቤተሰቦቹ ሁሉ ጋርም አጠመቀው። ከዚህም በኋላ ወደ በዓቱ ተመልሶ እየተጋደለ ኖረ። እግዚአብሔርንም አገልግሎ በሰላም አረፈ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን አባቶች ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ኅዳር)
#ታኅሣሥ_7

ታኅሣሥ ሰባት በዚችም ዕለት ከቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሚወለድ #በከበሩ_ነቢያት አፍ ለመሰበኩ መታሰቢያ ነው፣ በደብረ ሲሐት የሚኖር #አባ_ዳንኤል አረፈ፣ #ቅዱስ_አባት_አባ_ማቴዎስ አረፈ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ስብከተ_ነቢያት

ታኅሣሥ ሰባት በዚህችም ዕለት ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ እንደሚወለድ በከበሩ ነቢያት አፍ ለመሰበኩ መታሰቢያ ሆነ ።

ይህች ዕለት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት "ስብከት" ትባላለች። ስብከት ማለት በቁሙ "የምስራች፣ አዲስ ዜና መንገርን" የሚመለከት ሲሆን ዋናው ምሥጢር ግን ከነገረ ድኅነት (ከመዳን ትምሕርት) ጋር የተገናኘ ነው።

በዚህ ዕለት (ሳምንት) ሁሉም ነቢያት ከነ ትንቢታቸው ይታሰባሉ። ዘመነ ስብከትም ከታሕሳስ 7 እስከ 13 ያለውን ይይዛል። ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ፦ እግዚአብሔር አዳምን በ7 ሃብታት አክብሮ በገነት ቢያኖረው "አትብላ" የተባለውን ዕፀ በለስ በላ። በዚህም ከፈጣሪው ተጣልቶ በሞተ ሥጋ ሞተ ነፍስ፣ በርደተ መቃብር፣ ርደተ ገሃነም ተፈረደበት። በሁዋላ ግን ንስሃ ስለ ገባ "ከ5 ቀን ተኩል (5,500 ዘመን) በሁዋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ" የሚል ቃል ኪዳንን ሰጠው።

ከዚህ በሁዋላ ለ5,500 ዘመናት ጊዜ ወደ ታች ይቆጠር ጀመር። ስለ እግዚአብሔር ሰው መሆንና ዓለምን ማዳንም ትንቢት ይነገር፣ ሱባኤ ይቆጠር፣ ምሳሌም ይመሰል ገባ።

ከአዳም እስከ ሙሴ (ዘመነ አበው) ምሳሌያት ይበዛሉ። ከሙሴ እስከ ዳዊት (ዘመነ መሣፍንት) ምሳሌያቱ እየጐሉ መጥተዋል:: ከልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት እስከ ቅዱስ ሚልክያስ ድረስ (በዘመነ ነቢያት/ነገሥት) ግን ትንቢቶች ስለ ክርስቶስና ስለ ማደሪያ እናቱ እንደ ጐርፍ ፈሰዋል።

ነቢያትም የመሲህን መምጣት እየጠበቁ በጾም፣ በጸሎትና በትሕርምት ኑረዋል። እንባቸውንም አፍሰው ቅድመ እግዚአብሔር ደርሶላቸዋል። መድኅን ክርስቶስም ተወልዶ አድኗቸዋል።

ነቢይ ማለት በቁሙ ኃላፍያትን (አልፎ የተሠወረውን ምሥጢር) መጻዕያትን (ለወደ ፊት የሚሆነውን) የሚያውቅ ሰው ማለት ነው። ሃብተ ትንቢት የእግዚአብሔር የባሕርይ ገንዘቡ ሲሆን እርሱ ለወደደው በጸጋ ይሰጠዋል:: እነዚህም ከጌታ ሃብተ ትንቢት የተሰጣቸው አባቶችና እናቶች "ቅዱሳን ነቢያት" በመባል ይታወቃሉ።

ዘመነ ነቢያት ተብሎ የሚታወቀው ብሉይ ኪዳን ቢሆንም እስከ ምጽዓት ድረስ ጸጋውን እግዚአብሔር ለፈቀደላቸው አይነሳቸውም። በሐዋርያት መካከልም ቅዱስ አጋቦስን የመሰሉ ነቢያት ነበሩ። (ሐዋ.11፥27) ቅዱሳን ነቢያት ከእግዚአብሔር እየተላኩ ሰውን ከፈጣሪው እንዲታረቅ ይመክራሉ: ይገስጻሉ።

ከበጐ ሃይማኖታቸውና ንጽሕናቸው የተነሳም እግዚአብሔርን በተለያየ አርአያና አምሳል አይተውታል፣ "እስመ በአንጽሖ መንፈስ ርዕይዎ ነቢያት ለእግዚአብሔር: ወተናጸሩ ገጸ በገጽ" እንዳለ አባ ሕርያቆስ። (ቅዳሴ ማርያም)

የብዙ ነቢያት ፍጻሜአቸው መከራን መቀበል ነው:: እውነትን ስለ ተናገሩ አንዳንዶቹም በእሳት፣ አንዳንዶቹም በሰይፍ፣ አንዳንዶቹም በመጋዝ ተፈትነዋል። ሌሎቹ ለአናብስት ሲጣሉ ቀሪዎቹ ደግሞ በድንጋይ ተወግረዋል።

ስለዚህም መከራቸው ለቤተ ክርስቲያን መሠረት ተብለዋል። ጌታም ለደቀ መዛሙርቱ "ሌሎች ደከሙ: እናንተ በድካማቸው ገባችሁ" ብሎ የነቢያቱን መከራ ተናግሯል። (ዮሐ.4፥36)

ነቢያት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እና ድንግል እናቱን ለማየት ብዙ ጥረዋል ሽተዋልም። "ብዙ ነቢያትና ጻድቃን እናንተ የምታዩትን ሊያዩ ሹ" እንዳለ ጌታ በወንጌል። (ማቴ. 13፥16፣ 1ዼጥ.1፥10) ዛሬ ግን በሰማያት ጸጋ በዝቶላቸው: ክብር ተሰጥቷቸው ሐሴትን ያደርጋሉ።

ቅዱሳን ነቢያት በዋነኝነት 15ቱ አበው ነቢያት: 4ቱ ዐበይት ነቢያት: 12ቱ ደቂቀ ነቢያት እና ካልአን ነቢያት ተብለው በ4 ይከፈላሉ::

#15ቱ_አበው_ነቢያት ማለት፦ ቅዱስ አዳም አባታችን፣ ሴት፣ ሔኖስ፣ ቃይናን፣ መላልኤል፣ ያሬድ፣ ኄኖክ፣ ማቱሳላ፣ ላሜሕ፣ ኖኅ፣ አብርሃም፣ ይስሐቅ፣ ያዕቆብ፣ ሙሴ እና ሳሙኤል ናቸው።

#4ቱ_ዐበይት_ነቢያት ቅዱስ ኢሳይያስ ልዑለ ቃል፣ ቅዱስ ኤርምያስ፣ ቅዱስ ሕዝቅኤልና፣ ቅዱስ ዳንኤል ናቸው።

#12ቱ_ደቂቀ_ነቢያት የሚባሉት ሆሴዕ፣ አሞጽ፣ ሚክያስ፣ ዮናስ፣ ናሆም፣ አብድዩ፣ ሶፎንያስ፣ ሐጌ፣ ኢዩኤል፣ ዕንባቆም፣ ዘካርያስ እና ሚልክያስ ናቸው።

#ካልአን_ነቢያት የሚባሉት ደግሞ፦ ኢያሱ፣ ሶምሶን፣ ዮፍታሔ፣ ጌዴዎን፣ ዳዊት፣ ሰሎሞን፣ ኤልያስ እና ኤልሳዕ ሌሎችም ናቸው::

ነቢያት በከተማም ይከፈላሉ፦
*የይሁዳ (ኢየሩሳሌም)፣ የሰማርያ (እሥራኤል) እና የባቢሎን (በምርኮ ጊዜ) ተብለው ይጠራሉ::

በዘመን አከፋፈል ደግሞ:-
* ከአዳም እስከ ዮሴፍ #የዘመነ_አበው_ነቢያት
* ከሊቀ ነቢያት ሙሴ እስከ ነቢዩ ሳሙኤል #የዘመ_መሳፍንት_ነቢያት
* ከቅዱስ ዳዊት እስከ ዘሩባቤል ያሉት #የዘመነ_ነገሥት_ነቢያት
* ከዘሩባቤል ዕረፍት እስከ መጥምቁ ዮሐንስ ያሉት ደግሞ #የዘመነ_ካህናት_ነቢያት ይባላሉ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አባ_ዳንኤል_ገዳማዊ

በዚህች ቀን በአባ መቃርስ ገዳም በደብረ ሲሐት የሚኖር አባ ዳንኤል አረፈ። ይህም አባ ዳንኤል ስሟን እንጣልዮስ አስኝያ የነበረች ንግሥት በጥሪቃን የገነዛት ነው እርሷም ከሞቷ በኋላ እንጂ ሴት እንደሆነች አልታወቀችም ነበር።

በአንዲት ቀንም ወደ እስክንድርያ አገር ከረድኡ ጋር ሲጓዝ ስሙ ምህርካ የሚባል እብድ አገኘ ብዙ እብዶችም ይከተሉታል ለአገር ሰዎችም በእውነት ያበደ ይመስላቸው ነበር አባ ዳንኤልም እጁን ይዞ ወደ ሊቀ ጳጳሳቱ ወስዶ ትሩፋቱን ተጋድሎውን ነገረው እንዲነግራቸውም በአማሉት ጊዜ ከዝሙት ጦር በመሸሽ ራሱን እብድ እንዳስመሰለ ነገራቸው ሰምተውም እግዚአብሔርን አመሰገኑት።

በአንዲትም ዕለት ወደ አንዲት አገር ደረሰ በዚያም አውሎጊስ የሚባል ለድኆች የሚራራ እንግዳም የሚቀበል ደንጊያ በመውቀር የሚኖር ሰው አገኘ እርሱንም ተቀብሎ በደስታ አሳደረው መልካም ሥራውንም በአየ ጊዜ ድኆችን የሚረዳበት ገንዘብን ለአውሎጊስ ይሰጠው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ስለርሱ ለመነ ጌታችንም በሕፃን አምሳል ተገለጠለትና ገንዘብ ባገኘ ጊዜ ጠባዩን እንዳይለውጥ አንተ ትዋሰዋለህን አለው አባ ዳንኤልም አዎን እዋሰዋለሁ አለ።

ከዚህም በኋላ አውሎጊስ በድስት የመላ ወርቅን አግኝቶ ያንን ይዞ ወደ ንጉሥ ሒዶ የጭፍራ አለቃ ሆኖ ተሾመ ጠባዩንም ለወጠ። ጠባዩንም እንደለወጠ አባ ዳንኤል ሰምቶ ሊመክረውና ሊገሥጸው ሔደ የአውሎጊስ ወታደሮችም ለመሞት እስኪደርስ ድረስ ደበደቡት በዚህም እያዘነ ሳለ ያ ሕፃን በሕልም ታየው አባ ዳንኤልንም ለምን በሌላ ሰው ነገር ገባህ ብሎ እንዲሰቅሉት አዘዘ። ከዚህም በኋላ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም መጥታ ለሕፃኑ ሰገደች እግሮቹንም እየሳመች ስለ አባ ዳንኤል ለምና ከስቅለት አዳነችው።
#ግንቦት_8

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም

ግንቦት ስምንት በዚህች ዕለት የክብር ባለቤት #የጌታችንና_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ #በዓለ_ዕርገት ሆነ፣ ስንሑት ከሚባል አገር #ቅዱስ_ዮሐንስ በምስክርነት አረፈ፣ የአስቄጥስ ገዳም አበምኔት #አባ_ዳንኤል አረፈ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ዕርገተ_እግዚእ

ግንቦት ስምንት በዚህች ዕለት የክብር ባለቤት ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእኛ በነሣው ሥጋ ከአባቱና ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ ወደአለው የአንድነት አኗኗሩ ከሰማያት በላይ ያረገበት ሆነ።

እርሱም በረቀቀ ጥበቡ በመከራው በሞቱና በመነሣቱ ሥራውን ከፈጸመ በኋላ አርባው ቀን ሲፈጸም በነፋሳት ክንፍ ላይ ሆኖ ዐረገ።

ያን ጊዜ በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ ወጣ በነፋሳትም ክንፎች ላይ ሁኖ ወጣ ያለው የዳዊት ትንቢት ተፈጸመ። በዚህም ዕርገቱ ለሚያምኑበት በልዕልና ወደሚኖሩበት የሚዐርጉ መሆናቸው ተረዳ ተረጋገጠ ራስ በአለበት ሕዋሳት ሊኖሩ ይገባልና ።

አዳም አስቀድሞ በምድራዊ ርስቶች በሲኦልም እንደኖረ መኖርንም እንደ ቀደመ እንዲሁ ዳግማዊ አዳም ጌታ በመንግሥተ ሰማያት ርስት መኖርን ቀደመ። የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ዕርገቱን ከትንሣኤው አከታትሎ ወዲያውኑ አላደረገም መናፍቃን ዕርገቱ ምትሐት ናት ብለው እንዳያስቡ።

ጌታችንም በረቀቀ ጥበቡ የደቀ መዛሙርቱን ተሸብሮ የነበረ ልቡናቸውን እያጽናና መነሣቱንም እያስረዳቸው ከትንሣኤው በኋላ አርባ ቀን ኖረ። በጌታችንም ዕርገት የዳንኤል ትንቢት ተፈጸመ እንዲህ የሚል ሌሊት በራእይ አየሁ እነሆ ታላቅ እንደ ሰው ልጅ የሆነ መጣ ዘመናትን ወደሚያስረጃቸው ደረሰ ከፊቱም አቀረቡት።

የዘላለም አገዛዝ ጌትነት መንግሥት የዘላለም ሥልጣን ተሰጠው ሕዝቡና አሕዛቡ ሁሉ መንደር መንድረው የሚኖሩትና ነገዱም ነገሥታቱም ሁሉ ይገዙለታል አገዛዙም የዘላለም አገዛዝ ነው መንግሥቱም የማያልፍ የማይጠፋ ነዋሪ ነው።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ዮሐንስ_ሰማዕት

በዚህች ቀን ስንሑት ከሚባል አገር ቅዱስ ዮሐንስ በምስክርነት አረፈ። የዚህም ቅዱስ የአባቱ ስም መቃርስ የእናቱም ስም ሐና ነው። እርሱም የአባቱን በጎች ሲጠብቅ የእግዚአብሔር መልአክ ተገልጦ የብርሃን አክሊልን አሳየው። እነሆ ተጋድሎ ተዘርግቶ በክርስቶስ ስም ለሚጋደል አክሊላት ተዘጋጅተው ሳሉ አንተ ለምን ከዚህ ተቀመጥክ። አሁንም ወደ ሀገረ አትሪብ ሒድ የክብር ባለቤት ስለሆነ ስለ ክርስቶስ ስም ተጋደል አለው። ከዚያም ሰላምታ ሰጥቶት ከእርሱ ዘንድ ሔደ።

በዚያም ወቅት ቅዱስ ዮሐንስ ተነሣ እናቱንና አባቱንም ተሰናብቶ ወደ አትሪብ ከተማ ሔደ መኰንኑንም በውሽባ ቤት አገኘውና በወጣ ጊዜ በፊቱ በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ። መኰንኑም ለአንድ ወታደር ሰጥቶት ምናልባት ከምክሩ ተመልሶ ቢታዘዝለት አስቦ እንዲአባብለው ወታደሩን አዘዘው።

ከዚህ በኋላ መኰንኑ ወደ ሥራው ሔደ ወታደሩም ቅዱስ ዮሐንስን ወደ ቤቱ ወሰደው። ቅዱሱም ተአምራትን አደረገ ያ ወታደርም በክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመነ። መኰንኑም በተመለሰ ጊዜ ያ ወታደር በክብር ባለቤት በጌታችን በመኰንኑ ፊት ታመነ የሰማዕትነትንም አክሊል ተቀበለ።

ከዚህ በኋላም ቅዱስ ዮሐንስን እንዲአሠቃዮት መኰንኑ አዘዘ በየአይነቱ በሆነ ሥቃይም አሠቃዩት። እግዚአብሔርም ያጸናውና ያስታግሠው መልአኩንም ልኮ ቊስሎቹን አድኖ ያለ ጉዳት በደኀና ያነሣው ነበር።

ከዚህም በኋላ ወደ እንዴናው ከተማ ላከው በዚያም ታላቅ ሥቃይን አሠቃዩት። መኰንኑም ማሠቃየቱን በሰለቸ ጊዜ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ የሰማዕትነትንም አክሊል ተቀበለ።

የአቅፍሐሲ ዮልዮስም ሥጋውን ወስዶ ገነዘው ወደ ሀገሩ ስንሑትም ላከው። የሀገሩ ሰዎች ሁሉም ወጥተው በፍጹም ደስታ ተቀበሉት ከማዕጠንት ጋራ እየዘመሩና እያመሰገኑ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አኖሩት ከሥጋውም ብዙዎች ድንቆች ተአምራት ተገለጡ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_አባ_ዳንኤል_ጻድቅ

በዚህችም ዕለት የአስቄጥስ ገዳም አበምኔት አባ ዳንኤል አረፈ። ይህም ቅዱስ ዕውነተኛ ንጹሕ ፍጹም ነው ዜናው በሁሉ ቦታ በተሰማ ጊዜ ሹመት ያላት አንስጣስያ የመኳንንቶችን ልብስ ለብሳ ወደርሱ መጥታ ከእርሱ መነኰሰች። በእርሱ አቅራቢያም ሃያ ስምንት ዓመት በበዓት ውስጥ ኖረች እርሷ ሴት እንደሆነችም ማንም አላወቀም።

ይህም ቅዱስ ስሙ አውሎጊስ የሚባለውን ሰው አየው ይህም አውሎጊስ የወፍጮ ድንጋይ እየወቀረ ለግርሽ እየሸጠ ሁል ጊዜ በመጠኑ እየተመገበ ድኆችንና ጦም አዳሪዎችን ይመግባቸዋል የተረፈውንም ፍርፋሪ ለውሾች ይጥላል ለነገ ብሎ ምንም አያሳድርም።

አባ ዳንኤልም ይህን መልካም ሥራውን አይቶ በርሱ ደስ አለው እጅግም አማረው ለአውሎጊስም የዚህን ዓለም ብልጽግና እንዲሰጠውና ለድኆች የሚመጸውተው እንዲጨመርለት ወደ እግዚአብሔር ለመነ።

ለአውሎጊስም ዋስ ሆነው የሚወቅረውንም ደንጊያ ሲፈነቅል በሸክላ ዕቃ የተደፈነ ወርቅን አገኘ ወደ ቊስጥንጥንያ ከተማ ሒዶ የንጉሥ የሠራዊት አለቃ ሆኖ ተሾመበት የሚሠራውንም የቀደመ በጎ ሥራውን ተወ። አባ ዳንኤልም ስለርሱ ሰምቶ ወደርሱ በሔደ ጊዜ የንጉሥ ሠራዊት አለቃ ሆኖ በፈረስ ላይም ተቀምጦ ብዙ ሠራዊት አጅቦት እርሱም በትዕቢት ተመልቶ የቀድሞ በጎ ሥራውንና ለድኃ መመጽወቱንም ትቶ አገኘው።

አባ ዳንኤልም አይቶ አዘነ ስለርሱ በመለመኑም ተጸጸተ። ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ለፍርድ እንደ መጣ አባ ዳንኤልንም እንዲሰቅሉት ሲያዝ የአውሎጊስንም ነፍስ ከእርሱ እንዲሹ በእርሱ ምክንያት ጠፍቷልና የከበረች ድንግል እመቤታችን ማርያምም የክብር ባለቤት ጌታችንን ልጅዋ ኢየሱስ ክርስቶስን ስለ አባ ዳንኤል እንደ ለመነችው በሌሊት ራእይ አባ ዳንኤል ራሱ አየ።

በነቃም ጊዜ ደነገጠ አውሎጊስንም ወደ ቀድሞ ሥራው ይመልሰው ዘንድ በጸሎትና በምሕላ በመትጋት ወደ እግዚአብሔር እየለመነ ግብር ገባ ሱባኤ ያዘ።

ከዚህ በኋላም ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ተገለጸለት በፍጥረቱ ላይ በሚያደርገው በእግዚአብሔር ፍርድ ውስጥ ለመግባት በመድፈሩ ገሠጸው። በዚያንም ወቅት አውሎጊስን የሾመው ንጉሥ ሞተ ሌላ ንጉሥም ነገሠ በአውሎጊስም ላይ ተነሥቶ ገንዘቡን ሁሉ ወረሰ። ደግሞም ሊገድለው ፈለገው አውሎጊስም ነፍሱን ለማዳን ከንጉሡ ሸሽቶ ወደ አገሩ ደረሰ እንደ ቀድሞውም ደንጊያ ይወቅር ጀመረ አባ ዳንኤልም ወደርሱ ተመልሶ ስለርሱ ያየውን ሁሉ ስለ ርሱም እንደሰቀሉትና ነፍሱንም ከእርሱ እንደፈለጉ ነገረው።

በዚህ በአባ ዳንኤልም የትንቢት መንፈስ አድሮበት ነበር ከእርሱም ብዙዎች ታላላቅ ታአምራት ተገለጡ። መናፍቃን አርዮሳውያንም ከቀናች ሃይማኖት ሊአወጡት በፈለጉ ጊዜ እንቢ አለ። ያቺንም የክህደት ደብዳቤ ተቀብሎ ቆራረጣት የአርዮሳዊ ንጉሥ ወታደርም ይዞ ብዙ ሥቃይን አሠቃየው። በአንዲት ዕለትም ቅዱሳት ደናግል ወደ ሚኖሩበት ወደ ሲሐት ገዳም አባ ዳንኤልን ተመስሎ ሽፍታ ገባ። ደናግሉም በደስታ ተቀብለው እግሮቹን አጠቡ። እነርሱም አባ ዳንኤል እንደሆነ አምነው የወንበዴውን የእግር እጣቢ ውኃ በረከቱን ለማግኘት በላያቸው ረጩት። በዚያም አንድ ዐይኗ የታወረ ነበረች ውኃው በነካት ጊዜ ዐይኗ በርቶላት አየች።
#ኅዳር_14

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ኅዳር ዐሥራ አራት በዚህች ቀን #ቅዱስ_መርትያኖስ_ዘጠራክያ አረፈ፣ #የአባ_ዳንኤል_ገዳማዊ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_መርትያኖስ_ዘጠራክያ