Mella Tutorials
4.34K subscribers
89 photos
1 video
18 files
266 links
A hub of wisdom.

Subscribe on Youtube | www.youtube.com/@mella_tutorials

Buy ads https://telega.io/c/mella_tutorials
Download Telegram
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
#ExitExamResult

" የፈተናው ውጤት ተለቆ ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ተልኳል " - የትምህርት ሚኒስቴር አመራር

🔴" የፈተና ውጤት ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ጋር መጥቷል " -  የኢትዮጵያ ተማሪዎች ኅብረት

የሀገር አቀፍ መውጫ ፈተና ውጤት ለዩኒቨርሲቲዎች መላኩን የትምህርት ሚኒስቴር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት አጭር ቃል ፥ " ፈተናው ተለቆ ለዩኒቨርሲቲዎች ተልኳል " ብለዋል።

" በነገራችን ላይ ለዩኒቨርሲቲዎች ነው የሚላከው ሊንኩም ይላክላቸዋል። ውጤት ሁሉም ዩኒቨርሲቲ ጋር ደርሷል " ሲሉ ገልጸዋል።

ምን ያክል ተማሪ አለፈ ? ለሚለው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ " ውጤቱ አሁን ስለተለቀቀና ለተቋማት ስለተላከ አጠቃላይ ዳታውን የምናየው ነገ ነው " ብለዋል።

የኢትዮጵያ ተማሪዎች ኅብረት ቡኩሉ፣  " ውጤቱ ተለቋል። የሁሉም ዩኒቨርሲቲ መጥቷል " ሲል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

ውጤት መመልከቻ ሊንኩ ደርሷችኋል ? ስንል ላቀረብንለት ጥያቄ በሰጠን ምላሽ ደግሞ፣ " ዝም ብሎ ውጤቱ ነው የመጣው " የሚል አጭር ምላሽ ሰጥቷል።

ውጤሁ ለየዩኒቨርሲቲዎች ሬጅስትራር መላኩን የገለጸው ኅብረቱ ተፈታኞች ውጤታቸውን በየዩኒቨርሲቲያቸው / ካምፓሳቸው
#ከነገ ጀምሮ ማየት እንደሚችሉ ገልጿል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የፈተናው ውጤት በኦንላይ የሚታይበት መንገድ ካላ ጠይቆ ያቀርባል።

@tikvahethiopia
👍213
#ExitExamResult

“ ዳታውን አናላይዝ እያደረግን ነው ገና። ውጤት ግን ተለቋል ” - ኤባ መጂና (ዶ/ር)

በዘንድሮው መውጫ ፈተና ምን ያህል ተማሪዎች እንዳለፉና እንዳላለፉ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴርን ጠይቋል። 

የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ኤባ መጂና (ዶ/ር) በሰጡት ምላሽም “ ዳታውን አናላይዝ እያደረግን ነው ገና። ውጤት ግን ተለቋል ” ሲሉ ተናግረዋል።

ስንት ተማሪዎች አለፉ ? ስንት ተማሪዎች ወደቁ ? የሚለውን ጥያቄ በተመለከተ አናላይሲሱ እየተሰራ እንደሆነ፣ ነገ ማብራሪያ እንደሚሰጡን መሪ ሥራ አስፈጻሚው የገለጹ ሲሆን፣ ነገር ግን ውጤቱ ስለተለቀቀ ተማሪዎች ማየት እንደሚችሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል።

ከዚህ ቀደም ውጤት በሚለቀቅበት በተለመደው ድረ ገጽ ውጤት ማየት እንደሚቻል መሆኑን ጠቁመዋል። “ ውጤት የሚታየው ያው ከዚህ በፊት በነበረው ነው ” ሲሉ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ተማሪዎች ኀብረት በበኩሉ፣ ተማሪዎች እያዩ መሆኑን፣ ማለፊያው 50% መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድቷል። ምን ያህል ተማሪዎች እንዳለፉና እንዳላለፉ መረጃው እንደደረሰን የምናቀርብ ይሆናል።

https://result.ethernet.edu.et

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
31😁6🙏4🔥1