ማርመድሕ ሚዲያ - Marmedh Media
6.88K subscribers
463 photos
10 videos
22 files
453 links
ገብተህ የማትወጣ ከሆነ ብቻ JOIN አድርግ! እርግጠኛ ነኝ ትወዱታላችኹ ተቀላቀሉን!
ጥቅሙን ተቀላቅላችኹ ዕዩት፥ በተለይ አጫጭር አነቃቂ ጽሑፎች ይ ማ ር ካ ሉ!
ወቅታዊ ጉዳይ አይታጣበትም... ከገባችኹ ትርፍ አላችኹ!

TIKTok
http://tiktok.com/@mekuriya19
ለሐሳብና አስተያየት
https://t.me/Proud24
Download Telegram
   #ክፍል
▰ለአንዳንድ ጓደኞቼ በሰሞኑ ጉዳይ ምን ዓይነት ስሜት ተሰማችኹ ብዬ ለጥቂቶቹ ጠየቅኳቸው። እነርሱም እንዲህ አሉኝ...

➤ቤተ ክርስቲያን ፈተናዋ የጀመረው ዛሬ አይደለም። ገና ድሮ ስትመሠረት ፈተናዋም ተመሥርቶ ነበር። ብዙዎች ሊያጠፏት ተነሡ ነገር ግን እነርሱ ጠፉ እንጂ እርሷ ዛሬም አለች። እንደው ሌላው ቀርቶ በዮዲት ጉዲትና በአሕመድ ግራኝ ጊዜ ተጨፍጭፈንም ይኸው በዝተን አለን። እና ምንም ባላደረገችበት እንዲህ ስትደረግ በማየቴ እጅግ አዘንኩ።
...
●ፈተናዋን ፈተናቸው አድርገው የሚያሳልፉ ታላላቅ አባቶች እንዳሏት በማየቴ ደግሞ እጅግ ደስተኛ ነኝ። እነርሱን ስታይ ኃይል፣ጉልበት፣ደስታን... ታገኛለህ። ቅዱስ ሲኖዶስ የእውነት መንፈስ ቅዱስ የሚመራው መሆኑን በፍጹም ልብህ ታምናለህ።
ከዚህም በኋላ የባሰ ችግር ሊገጥማት ይችላል ግን እንደምናልፈው አልጠራጠርም።
...
ክርስቲያን ሲነካ ይበዛል እንጂ ከቶ አይቀንስም። ሆነም ቀረም ግን በክፉም በደጉም ማመስገን አለብንና የሆነው ኹሉ ለበጎ አድርገን ተመስገን ከማለት ልንቆጠብ አይገባም።
#ዲያቆን_ኃይለ_ሚካኤል_ዘርአብዛ /አ.አ❫

➤እኔ እንደዚህ ብዬ ልገለፅልህ ከምችለው በላይ
ነው የሆነብኝ ቲክታክ እንኳን ማየት
አልቻለኩም በእውነት አልቻልኩም። እንባ እየቀደመኝ ነው።
እግዚአብሔር ብቻ ለተዋሕዶ ቀን ያውጣላት። በተለይ የካህናት መደብደብ አላስቻለኝም በእውነት!
(
#ዘማሪ_ዮሐንስ_ፈዬ /ባሌሮቤ)

➤ኧረ በእመ ብርሃን! ምን አንደበት አለኝ ብለህ ነው እኔ ኃጢአተኛው? እጅጉን ከበደኝ! "ሰማዕታት በእውነት ይህቺን ዓለም በእውነት ናቁ  ደማቸውንም ሰለመንግሥተ ሰማያት አፈሰሱ"
(
#ዘማሪ_ኤርምያስ_በላይ/ዲላ)

➤ምን ያልተሰማኝ ነገር አለና ነው? ከምንም ጊዜ በላይ እሚያሳዝንና እሚያስለቅስ ልብን እሚሰብር ጊዜ ቢኖር አሁን ነው። ከምንም ጊዜ በላይ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶና የአባቶቼ ልጅ በመሆኔ ደስተኛ ነኝ።
...
ግን ደሞ የሕይወትን መንገድ ባወቅኩባት የአፍ ቋንቋ መፍቻዬ በሆነችኝ መጀመርያም መጨረሻዬም በሆነችው ስለ እሷ ለመግለፅ ቃላት የማይበቃኝ እውነትን ይዛ ለቆየች ድሃን ላሳደገች ቅድስት ሃይማኖቴና ቤተክርስትያኔ  በትንሽ የዲያቢሎስ ዕቃ በሆኑት ይህን ሁሉ መከራና ግፍ ሲደርስባት ለምን ብዬ አጅጉን አዘንኩኝ።
...
ምንም ቢሆንም እንኳ ኹሉንም የሆነው ለመልካም ነው ብዬ አምናለኹ። ሃይማኖቴ እውነተኛ አማኝና የቁርጥ ቀን ልጆች እንዳላትና ከምንም ጊዜ በላይ በመከራዋ ጊዜ ከጎና ሚሆን ልጅ እንዳላት አስመስክራለች።
...
ሲነካ ይበልጥ እሚጠነክር ሃይማኖታችን ከማን ለምን እንደተሰጠችን የምናውቅበት መንገድ ሆኖልናልና የሆነው ሁሉ ለበጎ ነው  እላለኹ።
#እኅት_ለምለም_ፈቀደ /አ.አ❵ የከተፋ ኖርቻ ጽዮን ማርያም ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ።

@MekuriyaM ይቀላቀሉን