ማርመድሕ ሚዲያ - Marmedh Media
6.9K subscribers
463 photos
10 videos
22 files
453 links
ገብተህ የማትወጣ ከሆነ ብቻ JOIN አድርግ! እርግጠኛ ነኝ ትወዱታላችኹ ተቀላቀሉን!
ጥቅሙን ተቀላቅላችኹ ዕዩት፥ በተለይ አጫጭር አነቃቂ ጽሑፎች ይ ማ ር ካ ሉ!
ወቅታዊ ጉዳይ አይታጣበትም... ከገባችኹ ትርፍ አላችኹ!

TIKTok
http://tiktok.com/@mekuriya19
ለሐሳብና አስተያየት
https://t.me/Proud24
Download Telegram
Forwarded from ፩ Mekuriya Murashe
🌎 #ንነጽር_፺፭

❝አባዬ ዓለም
#ለማን_ታዳላለች?❞

ልጄ ዓለም ለኹሉም እኩል ናት። ነገር ግን ለአንዳንድ ሰዎች የምታዳላ ይመስለኛል።

እነዚህም ሰዎች፦ በዚህ ዓለም ውስጥ ሲኖሩ ብዙ መከራን፣ ስቃይን፣ ዕንግልትን፣ ፈተናን፣ ውጣ ውረድን የመሳሰሉ ክፉ ነገሮች ደጋግመው ይገጥማቸዋል። ልጄ ዓለም የምታዳላው ለእነዚህ ሰዎች ይመስለኛል።

ምክንያቱም በዚህ ዓለም ውስጥ ስትኖር ብዙ ሕመም ካየህ፣ ብዙ ከቆሰልክ፣ ብዙ መከራ ከደረሰብህ ለማያልፈውና ዘለዓለማዊ ወደሆነው ዓለም መግቢያ ላይ ነህ ማለት ነው። ስለዚህ ዓለም ለእነዚህ ሰዎች
ታዳላለች

ይህች ዓለም ብልጭልጭታ ነገርን አጥብቃ ትወድዳለች፤ አንተ ግን የአንቺን ውዴታ አላሟላም ብለህ ከእሷ ከሸሽህና ፈተና ከደረሰብህ ዓለም እያዳላችልህ ነው ማለት ነው።

ይህቺ የምናያት ትርኪምርኪ የሆነች ምድር ከጠላሃት ያቺ የማታያትን ነገር ግን ተስፋ ወደምታደርጋት ዓለም ታስጠጋሃለች። ስለዚህ ዓለም እያዳላችልህ ነው።

ልጄ አትሳሳት ሰዎች ገፉኝ ብለህ መቼም እንዳትቆጭ፣ ፈተናው ማለፍ ተሳነኝ ብለህ መቼም ተስፋ እንዳትቆርጥ። ይህቺ አኹን ያለህባት ዓለም ስታሳድድህ ብቻ ነው ገነትን ልታገኛት የምትችል። ይህች ገነት ደግሞ በብዙ መከራና ጭንቅ እንጂ በብዙ ደስታና ጭፈራ አትገኝም።

መከራው ሲበዛብህ ነገን አሻግረህ ተመልከት። ፈተናው ሲደጋገምብህ ዓለም እያዳላችልህ እንደሆነ አስብ።

ለእውነተኞች ሰዎች ዓለም ሁሌም
ታዳላለች በመከራ እየገፋች ወደ ዘለዓለማዊ ክብር ታደርሳለች።

ለእኛም ዓለም ስቃዩን ታብዛብንና ወደ'ዛኛው ዓለም ትቀላቅለን🙏

   
   ይህ ጦማር በ ፲/፰/፪፻፲፮ ዓ.ም በዲ/ን መኩሪያ ሙራሼ ተከተበ
#እውነተኛ_ሰዎች ናቸው ብለው የምታምኗቸው ሰዎች ዘንድ አድርሱት።

◦◉◉Join us on telegram
@MekuriyaM