ማርመድሕ ሚዲያ - Marmedh Media
6.93K subscribers
463 photos
10 videos
22 files
452 links
ገብተህ የማትወጣ ከሆነ ብቻ JOIN አድርግ! እርግጠኛ ነኝ ትወዱታላችኹ ተቀላቀሉን!
ጥቅሙን ተቀላቅላችኹ ዕዩት፥ በተለይ አጫጭር አነቃቂ ጽሑፎች ይ ማ ር ካ ሉ!
ወቅታዊ ጉዳይ አይታጣበትም... ከገባችኹ ትርፍ አላችኹ!

TIKTok
http://tiktok.com/@mekuriya19
ለሐሳብና አስተያየት
https://t.me/Proud24
Download Telegram
ማርመድሕ ሚዲያ - Marmedh Media
https://youtu.be/A0VxzHKYlfs?si=6-QbwQ8V67AVvfwD
እንተጋገዝ እንጂ ወገን SUBSCRIBE እያደረጋችኹ ከቻላችኹ ደግሞ እያስደረጋችኹ🙏
Forwarded from ማርመድሕ ሚዲያ - Marmedh Media (፩ Mekuriya Murashe)
👌 #ንነጽር_፺፱

ትሕትና ማለት ለካ ከልብ ዝቅ ማለት እንጂ ከላይ ከላይ ዝቅ ማለት አይደለም።
ጣዕም አለው ለካ ትሕትና! ለዚያ ነዋ አባቶቻችን ራሳቸውን ዝቅ እያደረጉ ከእግዚአብሔር የሚመጣውን ጸጋ የሚጎናጸፉት!

ይህንን ጽሑፍ ደርሷችኹ ማንበብ ከቻላችኹ በሕይወታችኹ ዛሬ አንድ ቁም ነገር ለመሥራት ብቁ እስኪ!
የእውነት ከልቤ ልምከራችኹ ያለምንም ማጉረምረምና መሳቀቅ ከልብ ዝቅ ማለትን ተለማመዱ።

ከልብ ዝቅ ማለትንና ትሕትናን ልትላበሱ ወስናችኹ እንደሆን አንድ መንገድ ልጠቁማችኹ ነው።

ወዲህ ወድያ እየተረማመሰ የምታዩት ሰው ላይ ምንም ሐሳብ አይኑራችኹ። ከላይ ከፍ የሚያደርግ አንድ እግዚአብሔር መኖሩን ብቻ ልብ በሉ። ክርስቶስን በልባችኹ አንግሡት!

እደግመዋለው!
   የምታውቃቸውም ሆነ የሚያውቁህ ሰዎች ሁሉንም ጠቅለል አድርግና የሆነ ቦታ ስጣቸው። አዕምሮህ ውስጥ የእግዚአብሔርን ሥጦታዎችና ሀብቶች ብዛት እንዲመላለሱ ፍቀድ። እነዚያ ጸጋዎች በሙሉ ከትሕትና ሥር መቀመጣቸውን አገናዝብ። እናማ ሰዎች የፈለገ ነገር ያድርጉልህ/ያድርጉልህ፤ አንተ ግን ኢየሱስን በልብህ ዙፋን አስቀምጠውና መሬት መሬቱን ውደድና ከመሬት ተቀመጥ ትልቅ ክብር አትፈላልግ።

ይኸውልህ
ሰዎች ያልክ እንደሆነ ስለ አንተ አይገዳቸውም። እመነኝ ብትራብም ሆነ ብትጠማ ከልቡ እኔን የሚልህ ልታገኝ አትችልም! ስለዚህ ከልብህ ዝቅ በልና በእግዚአብሔር ታመን እንጂ!

ያኔ ከልብ ዝቅ ማለትን ክብርን እንደሚሰጥ፤ ትሕትና ደግሞ የተለየ ደስታና ሰላም እንዳለው አይቶ መጓዝ ብቻ ነው!
'በጊዜው ከፍ ለማለት ለጊዜው ዝቅ ማለት'ን ይበጃልና ዝቅ በል ዝቅቅቅ!

◎●●Join us on telegram
      
@MekuriyaM
🛑 #ንነጽር_፻ |100|

#ሕጻናት_በነበርን_ጊዜ
የእግዚአብሔርን መኖር አናውቅም። ከእናትና ከአባታችን በቀር ማንም ጠባቂ እንደሌለን ነበር የምናውቀው። ከወላጆቻችን በላይ የምንቀርበውም ሆነ የምንወደው ማንም አልነበረም።

#ትንሽ_ከፍ_ስንል
ሰዎች "እግዚአብሔር፣ እግዚአብሔር' ሲሉ ስንሰማቸው 'እግዚአብሔር ማን ነው?' ብለን መጠየቅ ጀመርን። ከዚያም 'እግዚአብሔር አይታይም፥ ድምጹም አይሰማም እሱ ግን ለሁላችንም ያየናል። ጥሩም ሆነ መጥፎ ነገር ስናደርግ ይመለከተናል።' ተብሎ ስለሚመለስልን እግዚአብሔርን እንፈራው ነበር።

#ወደ_ወጣትነት_ስንሸጋገር
እግዚአብሔርን አወቅነው ግን መግለጥ ተሳነን። መኖሩንም አረጋገጥን ግን መፍራት ከበደን። ተቅበዘበዝን የምንይዘው፣ የምናየው ነገር በሙሉ እኛን አናስቆም አለ። ያኔ ልጅ እያለን እናትና አባታችንን እጅግ እንወድ የነበርነው መልካም ሕጻናቶች እዚህ ጋር ስንደርስ እነርሱን መሳደብና መምታት ጀመርን። ትንሽ ካደግን በኋላ እንፈራው የነበረውን እግዚአብሔር ወደ ጎን ገፍተር አደረግነው።

#ከዚያም_አለፍንና
አባት ወይም እናት ወደ መሆን በቃን። ልጅም ኖረን። "ለልጆቻችን ስለ እግዚአብሔር መናገር እያለብን፤ ለእግዚአብሔር ስለ ልጆቻችን መናገር ጀመርን።" እኛ ላይ ደርሶ ያየነው አላዋቂነት ለልጆቻችንም ለማትረፍ በቃን። ከመንግሥቱና ከጽድቁ ይልቅ ስለ ልጆቻችን ማሰብ ጀመርን። ከእግዚአብሔር ራቅን። ከልጅነት እስከ ሽምግልና ድረስ ያለውን ዘመናችን እግዚአብሔርን ከመፍራትና ከመታዘዝ ይልቅ፥ በዓለም ዲስኩር ታጅበን፣ በብልጭልጭታው ታጭቀን፣ በዘፈን በዳንኪራው ተመስጠን፣ በዲያቢሎስ ሐሳብ ተውጠን ይኸው ዛሬም እዚያው አለን።

❝አምላካችን ሆይ እንደ ቸርነትህ ነው እንጂ እንደ በደላችን አይኹን!❞

◍◍◍Join us on telegram
@MekuriyaM
እየተከታተላችኹን ነው?
Anonymous Poll
89%
አዎ!
11%
አይ!
አስታርቀን Dn Mekuriya Murashe MASTER
<unknown>
የገብርኤል ዝማሬ ተጋበዙልኝ
#ጸናጽል

" ድምፁ መልካም በሆነ ጸናጽል አመስግኑት፤ እልልታ ባለው ጸናጽል አመስግኑት።"
         መዝ. ፻፶፥፭ /150፥5/

✝️
#ጸነጸለ፣ መታ ከሚለው ግስ የተገኘ ነው። ጸናጽል ማለት ትርገሙ "ሻኩራ፣ ቃጭል" ማለት ነው።
ጸናጽል የ"ሀ" አይነት ቅርጽ ያለው ሲሆን ከብር፣ ከነሃስና ከሌላም ማዕድን ሊሰራ የሚችል የዜማ መሳሪያ ነው።
ሲሰራም በ" ሀ" ቅርጽ መሀል ለመሀል ሁለት ዘንጎች እንዲኖሩት ይደረጋል። በዘንጎቹ ላይ ቅጠሎች (ሻኩራዎች) ይንጠለጠላሉ። ቁጥራቸውም የተወሰነ ነው።

✝️
#ጸናጽል ያማረ ድምፅ ያለው ሆኖ መልክና ልዩ ጌጥ አለው። መዝሙረኛው ቅዱስ ዳዊት እግዚአብሔርን አዘውትሮ ያመሰግንበት ነበር።

✝️ በቤተክርስቲያናችንም የምንገለገልበት ጸናጽል ልዩ ቀስተ ደመና መምሰሉ "... ለዘለዓለም የማደርገው የቃልኪዳን ምልክት ይህ ነው" ዘፍ. 9፥12 ብሎ እግዚአብሔር ለኖኅ ያሳየው የምህረት ቃል ኪዳን መታሰቢያ መሆኑን አራቱ ዘንጎች የአራቱ ባህሪያተ ሥጋ ( መሬት፣ እሳት፣ ነፋስና ውሃ)
ቅጠሎቹ የፍጥረታት ምሳሌ መሆናቸውን ይኸውም ከአራቱ ባህሪያት የተፈጠሩትን ፍጥረታት ሁሉና ሰውንም አላጠፋም ብለህ ቃል ኪዳን ሰጥተሃልና ኪዳንህን አስብልን በኃጢአታችን አታጥፋን ብለው ማመስገናቸውን የሚያመለክት ነው።

✝️
#በጸናጽል ላይ የምናየው መሰላል ያዕቆብ በፍኖተ ሎዛ ተኝቶ ያየው መሰላል ምሳሌ ነው። ( "... ህልምም አለመ እነሆም መሰላል በምድር ላይ ተተክሎ፥ ራሱም ወደ ሰማይ ደርሶ፥ እነሆም የእግዚአብሔር መላእክት ይወጡበት ይወርዱበት ነበር።" ዘፍ. 28፥11-13) በግራና በቀኝ ባሉት ዓምዶች መካከል ያሉት ሁለት ቀጫጭን ዘንጎች ወይም ጋድሞች የመሰላል፣ የተንጠለጠሉት ቅጠሎች በመሰላሉ ላይ ይወጡና  ይወርዱ የነበሩት መላእክት ምሳሌ ናቸው።

✝️ ጸናጽል ስናወዛውዘው ድምጽ መስጠቱ ያዕቆብ ያያት መሰላል ላይ ሲወጡ ሲወርዱ ያመሰገኑት የመላእክት ምስጋና ድምፅ ምሳሌ ነው።

✝️ በግራና በቀኝ የቆሙት ዓምዶች የብሉይ ኪዳንና የሐዲስ ኪዳን ምሳሌ ናቸው። ጸናጽሉን የሚያፀኑት ሁለቱ ዓምዶች እንደሆኑ ሁሉ ሃይማኖትም የሚጸናው በብሉይና በሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት እንደሆኑ አባቶች ያመሰጥራሉ።

✝️ ሁለቱ ጋድሞች ደግሞ የፍቅረ እግዚአብሔር እና የፍቅረ ቢጽ ምሳሌ ናቸው። ሰውም ሁለቱን ገንዘብ አድርጎ ወደ መንግሥተ ሰማያት እንዲገባ ለማጠየቅ ጋድሞቹ ሁለት ሆነዋል።

✝️ በጋድሞቹ ላይ የሚገኙት ቅጠሎች የተለያየ ቁጥር ሊኖራቸው ይችላል።
⛪️ አምስት ከሆነ ቁጥራቸው የአምስቱ አዕማደ ምሥጢር ምሳሌ
⛪️ ስድስት ከሆኑ የስድስቱ ቃላተ ወንጌል ምሳሌ
⛪️ ሰባት ከሆኑ የሰባቱ ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን ምሳሌ እንደሆኑ አባቶች ያስተምራሉ።

ለአባቶቻችን እውነትንና እምነትን የገለጠ አምላክ እኛንም በፈለጋቸው እንጓዝ ዘንድ ይርዳን።🙏🏼

@MekuriyaM
#የአባቶች_ምክር

#ሀሜት :- ያለመሳሪያ ሰውን መግደል ነው።
#ማጉረምረም :- ባገኙት በቃኝ ብሎ አለማመስገን ነው።
#ቁጣ :-  ከስድብ የሚያደርስ የክፉ አድራጎት መሰረት ነው።
#ብስጭት :- የተበሳጨንበትን ነገር ሳይሆን ተመልሶ ራስን የሚጎዳ መርዝ ከክህደት የሚያደርስ የኃጢያት ምንጭ ጭንቀትን የሚያነድ ትንሽ ክብሪት ነው።

#መዋሸት :-  እውነተኛን ሰው ሳይታዩ የሚጎዱበት ረቂቅ የሰይጣን ጦር ነው።
#መርገም :- አቅም ሲያንስ ወደላይ የሚወረወር የደካማ ሰዎች ቀስት ነው።
#መሳደብ :- ህሌናን የሚያቆስል ቁስሉ ተሎ የማይድን አቅም የሌላቸው ሰዎች ዱላ ነው።
#ዋዛ_ፈዛዛ :- በስልት የሚቃኙት የስራ ፈቶች በገና ነው።

#የማይገባ_ሳቅ :- አላፊ አግዳሚውን የሚያጠምዱበት የአመንዝሮች ወጥመድ ነው።
#መሳለቅ :- በአካል ጉዳተኛ ሰው ላይ የሚዘብቱበት  የመርገም ስንቁ ወግ ነው።
#ዘፈን :- ለዝሙት የሚያነቃ ልብ የሚወጋ ክፉ ፈላጻ ነው።
#ድንፋታ :- የጀግኖች ባልትና የሰነፎች ጫጫታ ነው።

#መንፈግ :- የሚለምነውን ሰው የሚወጉበት የስስታሞች ፈላጻ ነው።
#በክፉ_መንሾካሾክ :- ቀስ ብለው ሰውን የሚገሉበት የአሳባቂዎች ጩቤ ነው።
#ነገር_ማመላለስ :- የሚዋደዱትን የሚለዩበት የዲያብሎስ የግብር ልጆች መሳሪያ ነው።

@MekuriyaM
⚠️ ማሳሰቢያ !!  ይድረስ ለቻናሉ አባላት በሙሉ

➲ በአዲሱ የቴሌግራም ፖሊሲ መሠረት ይህን  ከታች unmute ሚለው ላይ የሚያደርጉ አባላት ቻናሉ ላይ እንደሌሉ ይቆጠራሉ ፡፡ ይህንን ማድረግ የሚፖሰቱትን መረጃዎች #VIEW ይቀንሰዋል።

ምንም እንኳን የምንፖስተውን እየተመለከቱ ቢሆንም ቻናሉ ላይ እንዳሉም አይቆጠርም ፤ ስለዚህ...

➲ ከታች
#MUTE የሚለው ላይ ከሆነ ምንም አይንኩት ነገር ግን

#UNMUTE ላይ ከሆነ 1 ግዜ በመንካት MUTE የሚለው ላይ አድርጉት

🙏 ስለ ትብብርዎ እናመሰግናለን 🙏
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

              መንፈሳዊ የስብሰባ ጥሪ

ለአቶ/ለወ/ሮ _

#የእግዚአብሔርን_ቤት_ለመሥራት_ይወጡ_ዘንድ_እግዚአብሔር_መንፈሳቸውን_ያነሳሳ_ሁሉ_ተነሡ።❞
                    ዕዝራ 1:5

#በጉራጌ ሀገረ ስብከት በእዣ ወረዳ ቤተ-ክህነት #በቦዠባር ከተማ ከ8 ዓመት ብርቱ ጥረት በኋላ እግዚአብሔር ፈቅዶ በምዕመናኑ ጥያቄና በአባታችን በብጹዕ አቡነ መልከጼዴቅ መልካም ፈቃድ የቅዱስ አማኑኤል ቤተ-ክርስቲያን እንዲመሠረት(እንዲተከል) ተወስኗል።

ስለዚህ የቤተ-መቅደሱ የግንባታ ሥራውን ለማስጀመር እና ታቦተ ሕጉ በአጭር ጊዜ ለማስገባት ጅምር ላይ መሆናችንን እየገለጽን ይህንን የተቀደሰ ዓላማ ለማሳካት ይረዳን ዘንድ የወረዳው ቤተ-ክህነት ልዑካን እና የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት በዕለተ ሰንበት #ሰኔ 09/2016 ዓ.ም #ከቀኑ 07:00 ሰዓት በኮልፌ ገነት_አክሲዮን ማኅበር አዳራሽ መንፈሳዊ የምክክር ጉባኤ ስለተዘጋጀ፥

እርስዎ፣ ቤተሰቦችዎን እንዲሁም ወዳጅ ዘመድ ጨምረው በመገኘት የበረከቱ ተሳታፊ ይሆኑ ዘንድ በቅዱስ አሙኑኤል ስም ተጋብዘዋል።

           ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን
           የአዲስ አበባ ሕንጻ አሠሪ ኮሚቴ

ለበለጠ መረጃ፦
የስልክ ቍጥር
0911244047
                      0911450173
                      0911991632
                      0911451903

@MekuriyaM (JOIN)
የአሥርቱ ትዕዛዛት አከፋፈል

  የክርስቲያን ሕግ የፍቅር ሕግ ነው። ቅዱስ ጴጥሮስ ሌላውን የሚወድ ሕግን ፈጽሞታል ካለ በኋላ ከአሥርቱ ትዕዛዛት የተወሰኑትን በመጥቀስ ፍቅር የሕግ ሁሉ ፍጻሜ መሆኑን በግልጽ ይናገራል። /ሮሜ 13÷8-10/

  እንዲሁም ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳስተማረን ፍቅር በሁለት ይከፈላል። /ማቴ 22÷34-41/
1, ፍቅረ እግዚአብሔር (እግዚአብሔርን መውደድ)
2, ፍቅረ ቢጽ (ወንድምን መውደድ)

- በተጨማሪም ጌታችን ሕግም ነቢያትም በነዚህ በሁለቱ ትዕዛዛት ተጠቃለዋል ብሎ ስለተናገረ በዚህ መነሻነት አሥርቱን ትዕዛዛት በሁለት እንከፍላቸዋለን።

1,
#ፍቅረ_እግዚአብሔር ፦ ከ1ኛው ትዕዛዝ አስከ 3ተኛው ትዕዛዝ ድረስ ያሉት።
- ከኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁንልህ
- የእግዚአብሔር አምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ
- የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ

2,
#ፍቅረ_ቢጽ ፦ ከ4ተኛው ትዕዛዝ እሰከ 10ኛው ትዕዛዝ ያሉት።
- አባትና እናትህን አክብር 
- አትግደል
- አታመንዝር
- አትስረቅ
- በሐሰት አትመስክር
- የባልንጀራህን ቤት አትመኝ
- ባልንጀራህን እንደራስህ አድርገህ ውደድ

#ለሌሎች_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ!

JOIN
@MekuriyaM
ይገርማችኋል ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከ500 በላይ ቤተሰብ አግኝተን 2,000+ ደርሰናል።

Promotion👌

ደስ ብሎኛል😁
ይነበብ! ይነበብ!

ትብብር!
በኢ/ኦ/ተ/ቤተ-ክርስቲያን በጉራጌ ዞን ሀገረ ስብከት በእዣ ወረዳ በቦዥባር ለሚሠራው ቤተክርስቲያን፥ የቤተክርስቲያኑ ልጆቿ እሑድ ሰኔ 9/2016ዓ.ም ኮልፌ ገነት አዳራሽ የምክክር ጉባኤ አዘጋጅቷል።

በዚህ መርሐግብሩ በተለያየ ምክንያት መታደም ለምይችሉ ወይም ከአዲስ አበባ ውጪ ያሉ ይከታተሉ ዘንድ
Live ለማስተላለፍ ተፈልጓል።

በዚህም መሠረት ቀና የቤተክርስቲያን ልጆች ሙሉ ወይም በከፊል  መሳርያ ያላችሁ ዩቱዩበሮች በዚህ ቀን መርሐግብሩ እንድታስተላልፉ በቅዱስ አማኑኤል ስም እንጠይቃለን።

መስፈርት!
የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ሚዲያ መሆን አለበት!

በውስጥ አውሩኝ👇

t.me/Proud24
ተማሪዎች ከፈተና በፊት ምን ብለው ይጸልዩ?

ቅዱስ ቄርሎስ ሳድሳዊ ከሚታወቁባቸው በርካታ በጎ ነገሮች አንዱ ለተማሪዎች የነበራቸው ልዩ ፍቅርና ቅርበት ነበረ፡፡ አባ ሚናስ ተብለው ይጠሩ ከነበረበት የምንኩስናቸው ዘመን ጀምሮ አቡኑ በተማሪዎች የተከበቡ ነበሩ፡፡ ከልዩ ልዩ ክፍለ ሀገራት ካይሮ ዩኒቨርሲቲ ሊማሩ ለሚመጡ ተማሪዎች የማደሪያ አገልግሎት በቅዱስ ሚናስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ይሰጡ ነበር፡፡ ይህ አገልግሎታቸውም በግብፅ ለዘመናዊው ቤተ ክርስቲያንን የሚያካትት የማደሪያ አገልግሎት(church- affiliated dormitory) መወለድ ምክንያት ሆኗል፡፡ የዚህ የማደሪያ አገልግሎት ተጠቃሚዎች የነበሩ ተማሪዎችም ቀሳውስትና ጳጳሳት የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ለመሆን በቅተዋል፡፡(ሊቀ ጳጳሱ አቡነ ሳሙኤልና ቅዱስነታቸው አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊተጠቃሽ ናቸው፡፡) በወቅቱ መነኩሴ የነበሩት አባ ሚናስ (አቡነ ቄርሎስ) ለእያንዳንዱ የቤተ ክርስቲያኑ ካህን በተማሪዎቹ መኖሪያ ውስጥ የሥራ ድርሻ ሰጥተው ነበር፡፡ የእርሳቸውን የሥራ ድርሻ ምን እንደነበረ ግን ማንም ሰው አላወቀም ነበር፡፡ በሌሊት በድብቅ የሚሠሩት ሥራ ካህናቱና በቤተ ክርስቲያኑ የሚኖሩ ተማሪዎች የሚጠቀሙበትን መጸዳጃ ቤት ማጽዳት ነበር፡፡

ይህ ለተማሪዎች ያላቸው በጎ አመለካከት በፓትርያርክነት ዘመናቸው አልተለያቸውም፡፡ ተማሪዎች ፈተና ሲደርስባቸው ወደ እርሳቸው እየመጡ ጸልዩልን ይሉአቸው ነበር፡፡ አንዳንድ ተማሪዎች ደግሞ የሚያጠኑበትን መጽሐፍ ይዘው መጥተው ያስባርኩ ነበር፡፡ ቅዱስ አባ ቄርሎስ አንዳንዴ መጽሐፉን ገለጥ ያደርጉና ‹ይህንን አጥኑ› ብለው ይሠጡ ነበር፡፡ የፈተናውም አብዛኛው ጥያቄ ከዚያ ገጽ ይወጣ ነበር፡፡ እንዲሁም ለተማሪዎች ፈተና በሚፈተኑበት ጊዜ የሚገጥማቸውን የመንፈስ ጭንቀትና የአእምሮ ውጥረት በመረዳት የሚከተለውን ከፈተና በፊት የሚጸለይ ጸሎት አዘጋጅተውላቸዋል፡፡

+ ጸሎት +

‹‹ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ

‹‹በችግርህ ቀን ጥራኝ ፤ አድንሃለሁ አንተም ታከብረኛለህ›› ብለህ የአንተን መጠጊያነት መፈለግን ስላስተማርከኝ አመሰግንሃለሁ!

አሁንም ጌታ ሆይ! በዚህ የፈተና ሰዓት ጥበብና ማስተዋልን ትሰጠኝ ዘንድ እማጸንሃለሁ፡፡

ይህን ፈተና በሰላም አልፍ ዘንድ ጸጋን (ሞገስን) ስጠኝ፡፡ ፈተናውን በምሠራ ጊዜ ጥልቅ የሆነ ሰላምህንና በረከትህን ስጠኝ፡፡

ጌታዬ ኢየሱስ ውጤት በሚሰጡኝ ጊዜ በመምህራኖቼ ዓይን መወደድን ትሰጠኝና ልባቸውን ታለሰልስልኝ ዘንድ እለምንሃለሁ፡፡ የከበርከው ጌታእኔ ኃጢአተኛ ነኝ ፤ ዓመቱን ሙሉ አንተን ደስ አላሰኘሁህም ፤ ውስጤንም ጭምር ፤ ነገር ግን ከልቤ ደንዳናነትና ከኃጢአቶቼ የተነሣ ሳይሆን ከምሕረትህ እና ከርኅርኄህ የተነሣ እንደትረዳኝ እለምንሃለሁ፡

ጌታ ሆይ ‹‹ለምኑ ይሰጣችኋል፣ እሹ ታገኛላችሁ፤ አንኳኩ ይከፈትላችኋል›› ብለሃል፡፡ እናም እነሆኝ እየለመንኩ ነው፤ የምሕረትህንም ደጅ እያንኳኳሁ ነው፡፡  ‹‹ወደ እኔ የሚመጣውን ከቶ ከእኔ አላወጣውም›› ብለሃልና ጸሎቴን አትናቅ፡፡በቅድስት ድንግልና በመላእክትህ ሁሉ አማላጅነት መልስልኝ!! አሜን!"

ለዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪዎች እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን! የልባችሁን ዓይን ያብራላችሁ! ያጠናችሁትን ይባርክላችሁ

JOIN @MekuriyaM
Forwarded from ማርመድሕ ሚዲያ - Marmedh Media (፩ Mekuriya Murashe=M²)