ማርመድሕ ሚዲያ - Marmedh Media
4.73K subscribers
455 photos
10 videos
20 files
414 links
ገብተህ የማትወጣ ከሆነ ብቻ JOIN አድርግ! እርግጠኛ ነኝ ትወዱታላችኹ ተቀላቀሉን!
ጥቅሙን ተቀላቅላችኹ ዕዩት፥ በተለይ አጫጭር አነቃቂ ጽሑፎች ይ ማ ር ካ ሉ!
ወቅታዊ ጉዳይ አይታጣበትም... ከገባችኹ ትርፍ አላችኹ!

TIKTok
http://tiktok.com/@mekuriya19
ለሐሳብና አስተያየት
https://t.me/Proud24
Download Telegram
#ጸናጽል

" ድምፁ መልካም በሆነ
ጸናጽል አመስግኑት፤ እልልታ ባለው ጸናጽል አመስግኑት።"
         መዝ. ፻፶፥፭ /150፥5/

✝️
#ጸነጸለ፣ መታ ከሚለው ግስ የተገኘ ነው። ጸናጽል ማለት ትርገሙ "ሻኩራ፣ ቃጭል" ማለት ነው።
ጸናጽል የ"ሀ" አይነት ቅርጽ ያለው ሲሆን ከብር፣ ከነሃስና ከሌላም ማዕድን ሊሰራ የሚችል የዜማ መሳሪያ ነው።
ሲሰራም በ" ሀ" ቅርጽ መሀል ለመሀል ሁለት ዘንጎች እንዲኖሩት ይደረጋል። በዘንጎቹ ላይ ቅጠሎች (ሻኩራዎች) ይንጠለጠላሉ። ቁጥራቸውም የተወሰነ ነው።

✝️
#ጸናጽል ያማረ ድምፅ ያለው ሆኖ መልክና ልዩ ጌጥ አለው። መዝሙረኛው ቅዱስ ዳዊት እግዚአብሔርን አዘውትሮ ያመሰግንበት ነበር።

✝️ በቤተክርስቲያናችንም የምንገለገልበት
ጸናጽል ልዩ ቀስተ ደመና መምሰሉ "... ለዘለዓለም የማደርገው የቃልኪዳን ምልክት ይህ ነው" ዘፍ. 9፥12 ብሎ እግዚአብሔር ለኖኅ ያሳየው የምህረት ቃል ኪዳን መታሰቢያ መሆኑን አራቱ ዘንጎች የአራቱ ባህሪያተ ሥጋ ( መሬት፣ እሳት፣ ነፋስና ውሃ)
ቅጠሎቹ የፍጥረታት ምሳሌ መሆናቸውን ይኸውም ከአራቱ ባህሪያት የተፈጠሩትን ፍጥረታት ሁሉና ሰውንም አላጠፋም ብለህ ቃል ኪዳን ሰጥተሃልና ኪዳንህን አስብልን በኃጢአታችን አታጥፋን ብለው ማመስገናቸውን የሚያመለክት ነው።

✝️
#በጸናጽል ላይ የምናየው መሰላል ያዕቆብ በፍኖተ ሎዛ ተኝቶ ያየው መሰላል ምሳሌ ነው። ( "... ህልምም አለመ እነሆም መሰላል በምድር ላይ ተተክሎ፥ ራሱም ወደ ሰማይ ደርሶ፥ እነሆም የእግዚአብሔር መላእክት ይወጡበት ይወርዱበት ነበር።" ዘፍ. 28፥11-13) በግራና በቀኝ ባሉት ዓምዶች መካከል ያሉት ሁለት ቀጫጭን ዘንጎች ወይም ጋድሞች የመሰላል፣ የተንጠለጠሉት ቅጠሎች በመሰላሉ ላይ ይወጡና  ይወርዱ የነበሩት መላእክት ምሳሌ ናቸው።

✝️
ጸናጽል ስናወዛውዘው ድምጽ መስጠቱ ያዕቆብ ያያት መሰላል ላይ ሲወጡ ሲወርዱ ያመሰገኑት የመላእክት ምስጋና ድምፅ ምሳሌ ነው።

✝️ በግራና በቀኝ የቆሙት ዓምዶች የብሉይ ኪዳንና የሐዲስ ኪዳን ምሳሌ ናቸው። ጸናጽሉን የሚያፀኑት ሁለቱ ዓምዶች እንደሆኑ ሁሉ ሃይማኖትም የሚጸናው በብሉይና በሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት እንደሆኑ አባቶች ያመሰጥራሉ።

✝️ ሁለቱ ጋድሞች ደግሞ የፍቅረ እግዚአብሔር እና የፍቅረ ቢጽ ምሳሌ ናቸው። ሰውም ሁለቱን ገንዘብ አድርጎ ወደ መንግሥተ ሰማያት እንዲገባ ለማጠየቅ ጋድሞቹ ሁለት ሆነዋል።

✝️ በጋድሞቹ ላይ የሚገኙት ቅጠሎች የተለያየ ቁጥር ሊኖራቸው ይችላል።
⛪️ አምስት ከሆነ ቁጥራቸው የአምስቱ አዕማደ ምሥጢር ምሳሌ
⛪️ ስድስት ከሆኑ የስድስቱ ቃላተ ወንጌል ምሳሌ
⛪️ ሰባት ከሆኑ የሰባቱ ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን ምሳሌ እንደሆኑ አባቶች ያስተምራሉ።

ለአባቶቻችን እውነትንና እምነትን የገለጠ አምላክ እኛንም በፈለጋቸው እንጓዝ ዘንድ ይርዳን።🙏🏼

@MekuriyaM