መድበል
1.21K subscribers
57 photos
1 video
3 files
154 links
በዚህ ቻናል 'መድበል'

፩. የአበው ቅኔዎች ፍቻቸውና ሙያቸው እንዲሁም ርቃቄያቸው በጽሑፍ

‎➙ ‎ይለቀቅበታል፤
‎➙ ‎ይቀጸልበታል፤
‎➙ ‎ይጠየቅበታል፤
‎➙ ‎ቅኔ ከነሙያው
‌‌‎➙ ነገረ ቅኔ ፤
‎➙‎ ነገረ አገባብ ፤
‌‎➙‎ የአእመረ ርባታ ፤
‌‎➙‎ የይቤ ርባታ ፤
‌‎➙‎ የግስ ርባታ ይታወቅበታል ።

፪. የግዕዝ ቋንቋ ይታወቅበታል

፫. አባቶቻችን በብራና ያስቀመጡትን ጥበብ ይለቀ
Download Telegram
🌹🥇🔥

🛑 ፫ኛ ዐቢይ እርባታ ወይም መሠርይ እርባታ ወይም ዝርዝር እርባታ ወይም የዋህ እርባታ
ማለት የግሱ ባለቤትና የግሱ ተሳቢን የሚያመለክት ዝርዝር ማለት ነው። ምሳሌ *አእመሮ* ብሎ አወቀው ሲል ባለቤቱ ያ ሰው ተሳቢው ያ ሰው መሆኑን ያመለክታል።

* 🥇 ዐቢይ እርባታ አንድ ግስ በ፲ ሠራዊት ወይም መራሕያን በ፹ አቅማር የሚረባበት መንገድ ነው። ፲ሩ መራሕያን የሚባሉ የሩቁ ወንድ ውእቱ፤ የቅርቡ ወንድ አንተ፤ የሩቆች ወንዶች ውእቶሙ፤ የቅርቦች ወንዶች አንትሙ፤ የሩቋ ሴት ይእቲ፤ የቅርቧ ሴት አንቲ፤ የሩቆች ሴቶች ውእቶን፤ የቅርቦች ሴቶች አንትን፤ የቅርብ ግሉል ጾታ (ለሴትም ለወንድም) እኔ የሚል አነ፤ የቅርቦች ግሉል ጾታ እኛ የሚሉ ንሕነ ናቸው።
* 🥈 ዐቢይ እርባታ በራሱ በለትና በበት አማርኛ ይፈታል። ማስረጃ *ትርከ ወቀሰታምከ እማንቱ ገሠጻኒ* ብሎ ቀጡኝ ቀጡልኝ ቀጡብኝ እን መዝ ፳፪፥፬። ሁሉንም የዘረዘረ አንቀጽ በ፫ በ፫ ፍታ። የሚጠብቀው ቀለም ከታቹ መስመር አለው። ተነሹንና ሰያፉን ወዳቂውንም ተጣዩንም ከጎኑ በተጻፈው አስተውል።

፩ኛ የሩቁ ወንድ በዝርዝር አንቀጽ ፲ሩ መራሕያንን ሲስብ
ውእቱ ብእሲ አእመሮ (ወዳቂ) ወይም አእመራሁ (ወዳቂ) ለውእቱ ብእሲ = ያ ሰውየ ያንን ሰውየ፤ አውቀው፣ አወቀለት፣ አወቀበት፤ አሳወቀው፤ አሳወቀበት፤ አሳወቀለት። (ሁሉን እንዲህ እያልህ አርባ።)
የአምሮ (ወዳቂ) የአምራሁ (ወዳቂ) = ያውቀዋል፤ ያሳውቀዋል።
ያእምሮ (ተነሽ) ያእምራሁ (ወዳቂ) = ያውቀው ዘንድ፤ ያሳውቀው ዘንድ።
ያእምሮ (ተነሽ) ያእምራሁ (ወዳቂ) = ይወቀው፤ ያሳውቀው።

፪ኛ የሩቁ ወንድ የቅርቡን ወንድ በዝርዝር ሲስበው በሁሉም ተነሽዎች ናቸው።
አንተ ብእሲ አእመረከ (ተነሽ) አእመራከ (ተነሽ) ውእቱ ብእሲ = አንተ ሰውየ ያ ሰውየ አወቀህ፤ አሳወቀህ።
የአምረከ (ተነሽ) የአምራከ (ተነሽ) = ያውቅሀል፤ ያሳውቅሀል።
ያእምርከ (ተነሽ) ያእምራከ (ተነሽ) = ያውቅህ ዘንድ፤ ያሳውቅህ ዘንድ።
ያእምርከ (ተነሽ) ያእምራከ (ተነሽ) = ይወቅህ፤ ያሳውቅህ።

፫ኛ የሩቁ ወንድ የሩቆቹን ወንዶች በዝርዝር ሲስባቸው በሁሉም ተነሽዎች ናቸው።
ውእቱ ብእሲ አእመሮሙ (ተነሽ) አእመራሆሙ (ተነሽ) ለውእቶሙ እደው = ያ ሰውየ እነዚያ ወንዶችን አወቃቸው አሳወቃቸው።
የአምሮሙ (ተነሽ) የአምራሆሙ (ተነሽ) = ያውቃቸዋል፤ ያሳውቃቸዋል።
ያእምሮሙ (ተነሽ) ያእምራሆሙ (ተነሽ) = ያውቃቸው ዘንድ፤ ያሳውቃቸው ዘንድ።
ያእምሮሙ (ተነሽ) ያእምራሆሙ (ተነሽ) = ይወቃቸው፤ ያሳውቃቸው።

፬ኛ የሩቁ ወንድ የቅርቦቹን ወንዶች በዝርዝር ሲስባቸው በሁሉም ተነሽዎች ናቸው።
አንትሙ እደው አእመረክሙ (ተነሽ) አእመራክሙ (ተነሽ) ለክሙ ውእቱ ብእሲ = እናንተ ወንዶች ያ ወንድ አወቃችሁ አሳወቃችሁ።
የአምረክሙ (ተነሽ) የአምራክሙ (ተነሽ) = ያውቃችኋል፤ ያሳውቃችኋል።
ያእምርክሙ (ተነሽ) ያእምራክሙ (ተነሽ) = ያውቃችሁ ዘንድ፤ ያሳውቃችሁ ዘንድ።
ያእምርክሙ (ተነሽ) ያእምራክሙ (ተነሽ) = ይወቃችሁ፤ ያሳውቃችሁ።

፭ኛ የሩቁ ወንድ የሩቂቱን ሴት በዝርዝር ሲስባት ያልደረበው በዘንድና በትእዛዝ ተነሽ በቀረው ወዳቂ ናቸው።
ውእቱ ብእሲ አእመራ (ወዳቂ) አእመራሃ (ወዳቂ) ለይእቲ ብእሲት = ያ ሰውየ ያቺን ሴትዮ አወቃት አሳወቃት።
የአምራ (ወዳቂ) የአምራሃ (ወዳቂ) = ያውቃታል፤ ያሳውቃታል።
ያእምራ (ተነሽ) ያእምራሃ (ወዳቂ) = ያውቃት ዘንድ፤ ያሳውቃት ዘንድ።
ያእምራ (ተነሽ) ያእምራሃ (ወዳቂ) = ይወቃት፤ ያሳውቃት።

፮ኛ ሩቁ ወንድ ቅርቢቱን ሴት በዝርዝር ሲስባት ሁሉም ተነሽዎች ናቸው።
አንቲ ብእሲ አእመረኪ (ተነሽ) አእመራኪ (ተነሽ) ለኪ ውእቱ ብእሲ = አንቺ ሴትዮ አንቺን ያ ሰውየ አወቀሽ አሳወቀሽ።
የአምረኪ (ተነሽ) የአምራኪ (ተነሽ) = ያውቅሻል፤ ያሳውቅሻል።
ያእምርኪ (ተነሽ) ያእምራኪ (ተነሽ) = ያውቅሽ ዘንድ፤ ያሳውቅሽ ዘንድ።
ያእምርኪ (ተነሽ) ያእምራኪ (ተነሽ) = ይወቅሽ፤ ያሳውቅሽ።

፯ኛ ሩቁ ወንድ ሩቆቹን ሴቶች በዝርዝር ሲስባቸው *ያእምሮን* ያለው ሰያፍ፤ የቀሩት ተጣይዎች ናቸው።
ውእቱ ብእሲ አእመሮን (ተጣይ) አእመራሆን (ተጣይ) ለውእቶን አእኑስ = ያ ሰውየ እነዚያ ሴቶችን አወቃቸው፤ አሳወቃቸው።
የአምሮን (ተጣይ) የአምራሆን (ተጣይ) = ያውቃቸዋል፤ ያሳውቃቸዋል።
ያእምሮን (ሰያፍ) ያእምራሆን (ተጣይ) = ያውቃቸው ዘንድ፤ ያሳውቃቸው ዘንድ።
ያእምሮን (ሰያፍ) ያእምራሆን (ተጣይ) = ይወቃቸው፤ ያሳውቃቸው።

፰ኛ ሩቁ ወንድ ቅርቦቹን ሴቶች በዝርዝር ሲስባቸው ሁሉም ተጣይዎች ናቸው።
አንትን አእኑስ አእመርክን (ተጣይ) አእመራክን (ተጣይ) ለክን ውእቱ ብእሲ = እናንተ ሴቶች እናንተን ያ ሰውየ አወቃችሁ፤ አሳወቃችሁ።
የአምረክን (ተጣይ) የአምራክን (ተጣይ) = ያውቃችኋል፤ ያሳውቃችኋል።
ያእምርክን (ተጣይ) ያእምራክን (ተጣይ) = ያውቃችሁ ዘንድ፤ ያሳውቃችሁ ዘንድ።
ያእምርክን (ተጣይ) ያእምራክን (ተጣይ) = ይወቃችሁ፤ ያሳውቃችሁ።

፱ኛ ሩቁ ወንድ አነ ያለውን በዝርዝር ሲስበው ሁሉም ተነሽዎች ናቸው።
ውእቱ ብእሲ አእመረኒ (ተነሽ) አእመራኒ (ተነሽ) ሊተብእሲብእሲት = ያ ሰውየ እኔን ሰውየ እኔን ሴትዮ አወቀኝ፤ አሳወቀኝ። ሙያ፡ *ሊተ* ለ*ብእሲ* ያለው *ለ* ተጠቃሽ፤ *ተ* ዝርዝር፤ *ለ* አያያዥነቱ *ለብእሲ* የሚያሰኝ፤ *ብእሲ* የተጠቃሽ ባለቤት። *አእመረኒ* ለ*ብእሲ* ለ*ብእሲት* ካለ ግን *ለ* ተጠቃሽ፤ *ብእሲ* የተጠቃሽ ባለቤት። የመሰለው ሁሉ እንዲህ አድርገህ ሙያ ስጥ።
የአምረኒ (ተነሽ) የአምራኒ (ተነሽ) = ያውቀኛል፤ ያሳውቀኛል።
ያእምረኒ (ተነሽ) ያእምራኒ (ተነሽ) = ያውቀኝ ዘንድ፤ ያሳውቀኝ ዘንድ።
ያእምረኒ (ተነሽ) ያእምራኒ (ተነሽ) = ይወቀኝ፤ ያሳውቀኝ።

፲ኛ ሩቁ ወንድ ንሕነ እኛ ያሉትን በዝርዝር ሲስባቸው ሁሉም ተነሽዎች ናቸው።
➥ ውእቱ ብእሲ አእመረነ (ተነሽ) አእመራነ (ተነሽ) ለእደውአዕኑስ = ያ ሰውየ እኛ ወንዶችን እኛ እሴቶችን አወቀን፤ አሳወቀን።
➥ የአምረነ (ተነሽ) የአምራነ (ተነሽ) = ያውቀናል፤ ያሳውቀናል።
➥ ያእምረነ (ተነሽ) ያእምራነ (ተነሽ) = ያውቀን ዘንድ፤ ያሳውቀን ዘንድ።
ያእምረነ (ተነሽ) ያእምራነ (ተነሽ) = ይወቀን ፤ ያሳውቀን ።


🌹🥇🔥
3🔥2🥰1👏1
🌹🥇🔥

💐መልአከ-ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ 🥇

ሐምሌ ፳፬ ፲፱፻፷፪ ዓ.ም ፥ 🔥💥


የማዕረግ ስም እንደ ዛሬ ከመርከሱ በፊት ማዕረጉ ራሱ የተጨነቀላቸው ግብራቸው ከስማቸው የላቀባቸው እውነተኞች መምህራን ነበሩን ብለን የምንናገርላቸው መልአከ-ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ ዛሬ የዕረፍታቸው መታሰቢያ ነው ።

የታላቁ ሊቅ መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ የድርሰት ሥራዎች:-

➊ • መድሎተ አሚን
➋ • ኰኲሐ ሃይማኖት
➌ • አድስ ሕይወት
➍ • መጽሐፈ ቅኔ ዝክረ ሊቃወንት ቅፅ ፩
➎ • መጽሐፈ ቅኔ ዝክረ ሊቃውንት ቅፅ ፪
➏ • መጽሐፈ ግጻዌ ( ስማቸው ሳይጠቅሱ )
➐ • መጽሐፈ ተክሊል ( ስማቸውን ሳይጠቅሱ )
➑ • የበጋና መዝሙር

አማን በአማን መልአከ ብርሃን !!
የታላቁ ሊቅ መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ በረከት ይደረሰን ።

ከዚህ በታች አንድ የእርሳቸው ድንቅ መወድስ እጋብዛችኋለሁ !

🌹🥇🔥
4👏2🥰1
🌹🥇🔥

💐 የሊቁ መልአከ-ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ 🥇 💐
🌹መወድስ የቅኔው ንጉሥ 🔥


ኦ ጳውሎስ እመ-ትቤለነ ፥
አሐዱ አካል ብእሲ ወብእሲት

ቃለከ ዘንተ ነአምነከ በምንት
አኮኑ ብእሲት ምስለ ብእሲሃ ፥
ኢትመውት ነያ ጊዜ-በጽሐ ሞት
ወውስተ-መቃብር ኢትወርድ ፥
ዳእሙ ትነብር እስከ-ይበጽሓ መቅበርት

ቃለከሰ ታጠይቀነ ዘበላኤ-ሰብእ መርዓት
እምነ-ብእሲሃ ዘታፈቅሮ በሰዓተ-ሞታ ኢተፈልጠት
ወእመ-ብእሲሃ ወረደ ውስተ-መቃብር ጽንዕት
ምስለ-ብእሲሃ ዘታፈቅር መቃብረ ወረደት ።

ትርጉም በአማርኛ ፥👇💥


➥ ጳውሎስ ሆይ ! ባልና ሚስት አንድ አካል ናቸው ብትለን...
➥ ይህን ቃልህን በምን እንቀበለዋለን !? በምንስ እናምንሀለን ?!
➥ ሞት በደረሰ ጊዜ ሚስት ከባሏ ጋር አትሞትምና፤ እነሆ አትሞትም !
➥ ወደ መቃብርም አትወርድም፤ መቃብር እስኪ ደርሳት (የሷ ጊዜ እስኪደርስ) ድረስ ትቀመጣለች እንጂ ።
➥ ነገር ግን የበላዔ ሰብእ (የስምዖን) ሚስት ቃልህን ታስረዳንና ታብራራልን ዘንድ...
➥ በሞቷ ሰዓት ከምትወደው ባሏ ፈጽሞ አልተለየችም ።
➥ ባሏም ወደጸናችው መቃብር በወረደ ጊዜ...
➥ ከምትወደው ባሏ ጋር እርሷም አብራ ወደ መቃብር ወረደች ።

ወገን የሚገርመው እኮ 😎 የቅኔውን ውበት በስምዖን ሚስት አድርገው ያዳኑት ነው ‼️

ተመራመር ፥ ተመሳጠር ፥ ተራቀቅ ፥ ርቀቅ ፥ ምጠቅ ፥ ወደውስጥ ስረግ ፥ ወደሰማያት እደግ ፥ ከምስጢር ጋር ታገል ፥ ከመጻሕፍት ጋር ተዳበል ‼️

ተርጓሚሁ👇💥

የኔታ መጋቤ-ጥበባት መምህር ፍሬ-ሕይወት የደሜ
😎https://t.me/Gubaenikya

ከተመቻችሁ እንዲሁም ከወደዳችሁት ፥ 👇🤭
       ♡ ㅤ  ⎙ㅤ   ⌲          ✉️   
     ˡᶦᵏᵉ    ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃʳᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ
ʟɪᴋᴇ ɪᴛ ᴅᴏᴇsɴ'ᴛ ᴄᴏᴜɴᴛ ᴘʀᴇss & Share ɪᴛ ! ♡

https://t.me/medibeli😎

🌹🥇🔥
7🔥2🥰1👏1
🌹🥇🔥
ㅤㅤㅤㅤㅤㅤ
🌹መወድስ የቅኔው ንጉሥ ፥ 🌹
💐 ዘመልአከ-ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ
🔥


ጊዜ-ዕርገትከ ወልድ እመ-ተጋብኡ ፥
መላእክተ-ሰማይ አዝማድ አዝማደ ኢይምሰሉከ ፤
በሕማም ወሞት እስመ-ኢሞቱ ምስሌከ ፤
ሚካኤልሂ ዘታፈቅሮ ፥
በብዝኀ-አርምሞ ነጸረ ኪያከ
እንዘ-ሕዝበ-አይሁድ ይገፍዑከ ፥
ሚካኤል ፍቁር እስመ-ኢኮነ ሥጋከ ፤
ዘመድሰ ጰራቅሊጦስ ለእመ-ሰምዐ ሞተከ ፤
በለቢሰ-እሳት ተራወጸ መንገለ-ሀለዉ ዕድዋኒከ ፤
አምጣነ-ኀለየ ይሚጥ እንተ-ተክዕወ ደመከ ፤
እስከ-ፈርሁ ወደንገጹ ማኅበረ-አይሁድ ጸላዕትከ ።

🔥 አወይ ሊቅ ?! እኒህንም አፈር በላቸው !🙈🥹 🔥

🌹🥇🔥

ወአንሰ እብል በኅሊናየ ወበአርምሞ ሶበ-አነብብ ከመ-ዝ! 🔥

🤲 "ኢትሰደኒ በመንፈቀ-ዑቀትየ ቅድመ-እርአይ
        ገጸ-ጥበብቦሙ ለጠቢባን አበዊነ!
🔥🙏

💐 ትርጕም፦ ‎👇☝️


እኔም በዝምታ ውስጥ ኾኜ በሐሳብ ባሕር ጠልቄ "የጠቢባን አባቶቼን የጥበብ ፊት ሳልመለከት በግማሽ የዕውቀት ዘመኔ አትውስደኝ!" ብየ ተማፀንኹ! 🙏🤭

እንደ ነቢዩ ዳዊት ፥
መዝሙር ፻፩ ፥ ፳፭ / 101፥25
😎

ጸሓፊሁ

ግሩም ዘኒቅያ !

🌹🥇🔥
🔥72🥰1👏1🙏1
ብዙ የአእመረ ርባታዎችን ስጽፍ ፥ የተሰመረበትን እና
የደመቀውን እያጠፋው ስለኾነ በአጭር በአጭር ይኹን
🤝1
🌹🥇🔥

🛑 ፫ኛ ዐቢይ እርባታ ወይም መሠርይ እርባታ ወይም ዝርዝር እርባታ ወይም የዋህ እርባታ ማለት የግሱ ባለቤትና የግሱ ተሳቢን የሚያመለክት ዝርዝር ማለት ነው። ምሳሌ *አእመሮ* ብሎ አወቀው ሲል ባለቤቱ ያ ሰው ተሳቢው ያ ሰው መሆኑን ያመለክታል።

* 🥇 ዐቢይ እርባታ አንድ ግስ በ፲ ሠራዊት ወይም መራሕያን በ፹ አቅማር የሚረባበት መንገድ ነው። ፲ሩ መራሕያን የሚባሉ የሩቁ ወንድ ውእቱ፤ የቅርቡ ወንድ አንተ፤ የሩቆች ወንዶች ውእቶሙ፤ የቅርቦች ወንዶች አንትሙ፤ የሩቋ ሴት ይእቲ፤ የቅርቧ ሴት አንቲ፤ የሩቆች ሴቶች ውእቶን፤ የቅርቦች ሴቶች አንትን፤ የቅርብ ግሉል ጾታ (ለሴትም ለወንድም) እኔ የሚል አነ፤ የቅርቦች ግሉል ጾታ እኛ የሚሉ ንሕነ ናቸው።

* 🥈 ዐቢይ እርባታ በራሱ በለትና በበት አማርኛ ይፈታል። ማስረጃ *በትርከ ወቀሰታምከ እማንቱ ገሠጻኒ* ብሎ ቀጡኝ ቀጡልኝ ቀጡብኝ እን መዝ ፳፪፥፬። ሁሉንም የዘረዘረ አንቀጽ በ፫ በ፫ ፍታ። የሚጠብቀው ቀለም ከታቹ መስመር አለው። ተነሹንና ሰያፉን ወዳቂውንም ተጣዩንም ከጎኑ በተጻፈው አስተውል።

፩ኛ የሩቁ ወንድ በዝርዝር አንቀጽ ፲ሩ መራሕያንን ሲስብ
ውእቱ ብእሲ አእመሮ (ወዳቂ) ወይም አእመራሁ (ወዳቂ) ለውእቱ ብእሲ = ያ ሰውየ ያንን ሰውየ፤ አውቀው፣ አወቀለት፣ አወቀበት፤ አሳወቀው፤ አሳወቀበት፤ አሳወቀለት። (ሁሉን እንዲህ እያልህ አርባ።)
የአ (ወዳቂ) የአራሁ (ወዳቂ) = ያውቀዋል፤ ያሳውቀዋል።
➥ ያእምሮ (ተነሽ) ያእምራሁ (ወዳቂ) = ያውቀው ዘንድ፤ ያሳውቀው ዘንድ።
➥ ያእምሮ (ተነሽ) ያእምራሁ (ወዳቂ) = ይወቀው፤ ያሳውቀው።

፪ኛ የሩቁ ወንድ የቅርቡን ወንድ በዝርዝር ሲስበው በሁሉም ተነሽዎች ናቸው ።
➥ አንተ ብእሲ አእመረከ (ተነሽ) አእመራከ (ተነሽ) ውእቱ ብእሲ = አንተ ሰውየ ያ ሰውየ አወቀህ፤ አሳወቀህ።
የአምረ (ተነሽ) የአራከ (ተነሽ) = ያውቅሀል፤ ያሳውቅሀል።
ያእምርከ (ተነሽ) ያእምራከ (ተነሽ) = ያውቅህ ዘንድ፤ ያሳውቅህ ዘንድ።
ያእምርከ (ተነሽ) ያእምራከ (ተነሽ) = ይወቅህ፤ ያሳውቅህ።

፫ኛ የሩቁ ወንድ የሩቆቹን ወንዶች በዝርዝር ሲስባቸው በሁሉም ተነሽዎች ናቸው።
ውእቱ ብእሲ አእመሮሙ (ተነሽ) አእመራሆሙ (ተነሽ) ለውእቶሙ እደው = ያ ሰውየ እነዚያ ወንዶችን አወቃቸው አሳወቃቸው።
የአሮሙ (ተነሽ) የአራሆሙ (ተነሽ) = ያውቃቸዋል፤ ያሳውቃቸዋል።
ያእም (ተነሽ) ያእምራሆሙ (ተነሽ) = ያውቃቸው ዘንድ፤ ያሳውቃቸው ዘንድ።
ያእም (ተነሽ) ያእምራሆሙ (ተነሽ) = ይወቃቸው፤ ያሳውቃቸው።

፬ኛ የሩቁ ወንድ የቅርቦቹን ወንዶች በዝርዝር ሲስባቸው በሁሉም ተነሽዎች ናቸው ።
➥ አንትሙ እደው አእመረክሙ (ተነሽ) አእመራክሙ (ተነሽ) ለክሙ ውእቱ ብእሲ = እናንተ ወንዶች ያ ወንድ አወቃችሁ አሳወቃችሁ።
የአምረ (ተነሽ) የአምራክሙ (ተነሽ) = ያውቃችኋል፤ ያሳውቃችኋል።
ያእምርክሙ (ተነሽ) ያእምራክሙ (ተነሽ) = ያውቃችሁ ዘንድ፤ ያሳውቃችሁ ዘንድ።
ያእምርክሙ (ተነሽ) ያእምራክሙ (ተነሽ) = ይወቃችሁ፤ ያሳውቃችሁ።

፭ኛ የሩቁ ወንድ የሩቂቱን ሴት በዝርዝር ሲስባት ያልደረበው በዘንድና በትእዛዝ ተነሽ በቀረው ወዳቂ ናቸው ።
ውእቱ ብእሲ አእመራ (ወዳቂ) አእመራሃ (ወዳቂ) ለይእቲ ብእሲት = ያ ሰውየ ያቺን ሴትዮ አወቃት አሳወቃት።
የአ (ወዳቂ) የአምራሃ (ወዳቂ) = ያውቃታል፤ ያሳውቃታል።
ያእ (ተነሽ) ያእምራሃ (ወዳቂ) = ያውቃት ዘንድ፤ ያሳውቃት ዘንድ።
ያእ (ተነሽ) ያእምራሃ (ወዳቂ) = ይወቃት፤ ያሳውቃት።

🌹🥇🔥
🔥31
🌹🥇🔥

፮ኛ ሩቁ ወንድ ቅርቢቱን ሴት በዝርዝር ሲስባት ሁሉም ተነሽዎች ናቸው።
አንቲ ብእሲ አእመረ (ተነሽ) አእመራኪ (ተነሽ) ለኪ ውእቱ ብእሲ = አንቺ ሴትዮ አንቺን ያ ሰውየ አወቀሽ አሳወቀሽ።
የአምረ (ተነሽ) የአምራኪ (ተነሽ) = ያውቅሻል፤ ያሳውቅሻል።
ያእምርኪ (ተነሽ) ያእምራኪ (ተነሽ) = ያውቅሽ ዘንድ፤ ያሳውቅሽ ዘንድ።
ያእምርኪ (ተነሽ) ያእምራኪ (ተነሽ) = ይወቅሽ፤ ያሳውቅሽ።

፯ኛ ሩቁ ወንድ ሩቆቹን ሴቶች በዝርዝር ሲስባቸው *ያእምሮን* ያለው ሰያፍ፤ የቀሩት ተጣይዎች ናቸው።
ውእቱ ብእሲ አእመሮን (ተጣይ) አእመራሆን (ተጣይ) ለውእቶን አእኑስ = ያ ሰውየ እነዚያ ሴቶችን አወቃቸው፤ አሳወቃቸው።
የአምሮን (ተጣይ) የአምራሆን (ተጣይ) = ያውቃቸዋል፤ ያሳውቃቸዋል።
ያእም (ሰያፍ) ያእምራሆን (ተጣይ) = ያውቃቸው ዘንድ፤ ያሳውቃቸው ዘንድ።
ያእም (ሰያፍ) ያእምራሆን (ተጣይ) = ይወቃቸው፤ ያሳውቃቸው።

፰ኛ ሩቁ ወንድ ቅርቦቹን ሴቶች በዝርዝር ሲስባቸው ሁሉም ተጣይዎች ናቸው።
አንትን አእኑስ አእመረ (ተጣይ) አእመራክን (ተጣይ) ለክን ውእቱ ብእሲ = እናንተ ሴቶች እናንተን ያ ሰውየ አወቃችሁ፤ አሳወቃችሁ።
የአምረ (ተጣይ) የአምራክን (ተጣይ) = ያውቃችኋል፤ ያሳውቃችኋል።
ያእምርክን (ተጣይ) ያእምራክን (ተጣይ) = ያውቃችሁ ዘንድ፤ ያሳውቃችሁ ዘንድ።
ያእምርክን (ተጣይ) ያእምራክን (ተጣይ) = ይወቃችሁ፤ ያሳውቃችሁ።

፱ኛ ሩቁ ወንድ አነ ያለውን በዝርዝር ሲስበው ሁሉም ተነሽዎች ናቸው።
➥ ውእቱ ብእሲ አእመረ (ተነሽ) አእመራኒ (ተነሽ) ሊተብእሲብእሲት = ያ ሰውየ እኔን ሰውየ እኔን ሴትዮ አወቀኝ፤ አሳወቀኝ። ሙያ፡ *ሊተ* ለ*ብእሲ* ያለው *ለ* ተጠቃሽ፤ *ተ* ዝርዝር፤ *ለ* አያያዥነቱ *ለብእሲ* የሚያሰኝ፤ *ብእሲ* የተጠቃሽ ባለቤት። *አእመረኒ* ለ*ብእሲ* ለ*ብእሲት* ካለ ግን *ለ* ተጠቃሽ፤ *ብእሲ* የተጠቃሽ ባለቤት። የመሰለው ሁሉ እንዲህ አድርገህ ሙያ ስጥ።
የአምረ (ተነሽ) የአምራኒ (ተነሽ) = ያውቀኛል፤ ያሳውቀኛል።
ያእምረ (ተነሽ) ያእምራኒ (ተነሽ) = ያውቀኝ ዘንድ፤ ያሳውቀኝ ዘንድ።
ያእምረ (ተነሽ) ያእምራኒ (ተነሽ) = ይወቀኝ፤ ያሳውቀኝ።

፲ኛ ሩቁ ወንድ ንሕነ እኛ ያሉትን በዝርዝር ሲስባቸው ሁሉም ተነሽዎች ናቸው።
ውእቱ ብእሲ አእመረ (ተነሽ) አእመራነ (ተነሽ) ለእደውአዕኑስ = ያ ሰውየ እኛ ወንዶችን እኛ እሴቶችን አወቀን፤ አሳወቀን።
የአምረ (ተነሽ) የአምራነ (ተነሽ) = ያውቀናል፤ ያሳውቀናል።
ያእምረ (ተነሽ) ያእምራነ (ተነሽ) = ያውቀን ዘንድ፤ ያሳውቀን ዘንድ።
ያእምረ (ተነሽ) ያእምራነ (ተነሽ) = ይወቀን ፤ ያሳውቀን ።



🌹🥇🔥
🔥4
🌹🥇🔥

፲፩ኛ ቅርቡ ወንድ ፮ቱን መራሕያን በዝርዝር ሲስባችው በሁሉም ይደርባል።

አንተ ብእሲ አእመርኮ (ወዳቂ) አእመርካሁ (ወዳቂ) ለውእቱ ብእሲ = አንተ ሰውየ ያንን ሰውየ አወቅኸው፤ አሳወቅኸው።
ተአምሮ (ወዳቂ) ተአምራሁ (ወዳቂ) = ታውቀዋለህ፤ ታሳውቀዋለህ።
ታእምሮ (ተነሽ) ታእምራሁ (ወዳቂ) = ታውቀው ዘንድ፤ ታሳውቅው ዘንድ።
አእምሮ (ተነሽ) አእምራሁ (ወዳቂ) = እወቀው፤ አሳውቀው።

፲፪ኛ ቅርቡ ወንድ ሩቆችን ወንዶች በዝርዝር ሲስባቸው ሁሉም ተነሽዎች ናቸው።
አንተ ብእሲ አእመርኮሙ (ተነሽ) አእመርካሆሙ (ተነሽ) ለውእቶሙ እደው = አንተ ሰውየ እነዚያ ወንዶችን አወቅሀቸው፤ አሳወቅሀቸው።
ተአምሮሙ (ተነሽ) ተአምራሆሙ (ተነሽ) = ታውቃቸዋለህ፤ ታሳውቃቸዋለህ።
ታእምሮሙ (ተነሽ) ታእምራሆሙ (ተነሽ) = ታውቃቸው ዘንድ፤ ታሳውቃቸው ዘንድ።
አእምሮሙ (ተነሽ) አእምራሆሙ (ተነሽ) = እወቃቸው፤ አሳውቃቸው።

፲፫ኛ ቅርቡ ወንድ ሩቂቱን ሴት በዝርዝር ሲስባት *ታእምራ*፤ *አእምራ* ተነሽ፤ የቀሩት ወዳቂዎች ናቸው።
አንተ ብእሲ አእመርካ (ወዳቂ) አእመርካሃ (ወዳቂ) ለይእቲ ብእሲት = አንተ ሰውየ ያቺን ሴትዮ አውቅኻት፤ አሳወቅሀት።
ተአምራ (ወዳቂ) ተአምራሃ (ወዳቂ) = ታውቃታለህ፤ ታሳውቃታለህ።
ታእምራ (ተነሽ) ታእምራሃ (ወዳቂ) = ታውቃት ዘንድ፤ ታሳውቃት ዘንድ።
አእምራ (ተነሽ) አእምራሃ (ወዳቂ) = እወቃት፤ አሳውቃት።

፲፬ኛ ቅርቡ ወንድ ሩቆቹን ሴቶች በዝርዝር ሲስባቸው *አእምሮን* ሰያፍ፤ የቀሩት ተጣይዎች ናቸው።
አንተ ብእሲ አእመርኮን (ተጣይ) አእመርካሆን (ተጣይ) ለውእቶን አእኑስ = አንተ ሰውየ እነዚያ ሴቶችን አወቅኻቸው፤ አሳውቅሀቸው።
ተአምሮን (ተጣይ) ተአምራሆን (ተጣይ) = ታውቃቸዋለኽ፤ ታሳውቃቸዋለህ።
ታእምሮን (ሰያፍ) ታእምራሆን (ተጣይ) = ታውቃቸው ዘንድ፤ ታሳውቃቸው ዘንድ።
አእምሮን (ሰያፍ) አእምራሆን (ተጣይ) = እወቃቸው፤ አሳውቃቸው።

፲፭ኛ ቅርቡ ወንድ አነ ያለውን በዝርዝር ሲስበው ሁሉም ተነሽዎች ናቸው።
አንተ ብእሲ አእመርከኒ (ተነሽ) አእመርካኒ (ተነሽ) ሊተብእሲብእሲት = አንተ ሰውየ እኔን ሰውየ እኔን ሴትዮ አወቅኸኝ፤ አሳወቀኝ።
ተአምረኒ (ተነሽ) ተአምራኒ (ተነሽ) = ታውቀኛለህ፤ ታሳውቀኛለሁ።
ታእምረኒ (ተነሽ) ታእምራኒ (ተነሽ) = ታውቀኝ ዘንድ፤ ታሳውቀኝ ዘንድ።
አእምረኒ (ተነሽ) አእምራኒ (ተነሽ) = እወቀኝ፤ አሳውቀኝ።

፲፮ኛ ቅርቡ ወንድ ንህነ እኛ ያሉትን በዝርዝር ሲስባቸው ሁሉም ተነሽዎች ናቸው።
አንተ ብእሲ አእመርከነ (ተነሽ) አእመርካነ (ተነሽ) ለእደውአዕኑስ = አንተ ሰውየ እኛ ወንዶችን እኛ ሴቶችን አወቅኸነ፤ አወቅኸን።
ተአምረነ (ተነሽ) ተአምራነ (ተነሽ) = ታውቀናለህ፤ ታሳውቀናለህ።
ታእምረነ (ተነሽ) ታእምራነ (ተነሽ) = ታውቀን ዘንድ፤ ታሳውቀን ዘንድ።
አእምረነ (ተነሽ) አእምራነ (ተነሽ) = እወቀን፤ አሳውቀን።

🌹🥇🔥
👏32🔥1
🌹🥇🔥

🛑 ፩ኛ ደቂቅ እርባታ ፥

ማለት በግሱ መዘርዝር ምክንያት የአንቀጹ ባለቤት እንጂ ተሳቢው የማይታወቅ ዝርዝር ማለት ነው። ምሳሌ *አእመሩ* ሲል ባለቤቱ ውእቶሙ መሆኑ ብቻ እንጂ ተሳቢው ማን እንደሆነ አይታወቅም።

➥ በውእቱ ግሱ አይቀየርም። ያልተቀየረው ግስ የሚነገረው፤ ግስ የሚጻፈው በውእቱ ባለቤትነት ስለሆነ ነው። *አአመረ* ብሎ አወቀ፤ አሳወቀ ተብሎ በሁሉም መራሕያን በ፪ በ፪ እየዘለቀ ይፈታል አስተውል። ዋናው ግስ *አመረ* (መ ጠብቆ ይነበባል) *አመለከተ* *ተመለከተ* ያለው ነው። *አ* አመል ነው። በ*አ* አመል የፍች ለውጥ አምጥቶ ነው። በሁለት መፈታቱ *አ* የማስደረግ የማድርግ አመሉን ስለያዘለት ነው።
➥ በውእቶሙ ጊዜ ግሱ መድረሻውን ወደ ካዕብ መቀየር ነው። *አእመሩ* ብሎ አወቁ ይላል።
➥ በይእቲ ጊዜ ከግሱ ላይ *ት* ቀለምን መጨመር ነው። *አእመረት* ብሎ አወቀች ይላል።
➥ በውእቶን ጊዜ የግሱን መድረሻውን ወደ ራብዕ መቀየር ነው። *አእመራ* (ተነሽ) ብሎ አወቁ ይላል።
➥ በአንተ ጊዜ የግሱን መድረሻውን ወደ ሳድስ ቀለም ቀይሮ *ን* መጨመር ነው። *አእመርከ* ብሎ አወቅህ ይላል።
➥ በአንትሙ የግሱን መድረሻውን ወደ ሳድስ ቀይሮ *ክሙ* መጨመር ነው። *አእመርክሙ* ብሎ አወቃችሁ ይላል።
➥ በአንቲ የግሱን መድረሻውን ወደ ሳድስ ቀይሮ *ኪን* መጨመር ነው። *አእመርኪ* ብሎ አወቅሽ ይላል።
➥ በአንትን መድረሻውን ወደ ሳድስ ቀይሮ *ክንን* መጨመር ነው። *አእመርክን* (ተጣይ) ብሎ አወቃችሁ ይላል።
➥ በአነ መድረሻውን ወደ ሳድስ ቀይሮ *ኩን* መጨመር ነው። *አእመርኩ* ብሎ አወቅሁ ይላል።
➥ በንሕነ መደረሻውን ወደ ሳድስ ቀይሮ *ነን* መጨመር ነው። *አእመርነ* ብሎ አወቅነ ይላል።

😎 ገጸ ንባባቸውም ፦
ከአንትን አንቀጽ የቀረው ሁሉም ወይ ተነሽ ወይም ሰያፍ ነው። *አእመርክን* ያለው ግን ተጣይ ነው።

🛑 ፪ኛ ንዑስ እርባታ ፥
ማለት ከቀዳማይ አንቀጽ እስከ ትዕዛዝ አንቀጽ ዘልቆ ያለው እርባታ ነው።
* ቀዳማይ አንቀጽ ማለት የመጀመሪያ አንቀጽ ማለት ሲሆን ኀለፊ አንቀጽ ይባላል (*አእመረ* አወቀ አሳወቀ ያለው ነው።)
* ካልአይ ማለት ሁለተኛ አንቀጽ ማለት ሲሆን ትንቢት አንቀጽ ይባላል (*የአር* ያውቃል ያሳውቃል ያለው ነው።)
* ዘንድ አንቀጽ (*ያእምር* ያውቅ ዘንድ ያሳውቅ ዘንድ ያለው ነው።)
* ትእዛዝ አንቀጽ (*ያእምር* ይወቅ ያሳውቅ ያለው ነው።)

➥ የአእመረ ደቂቅና ንዑስ እርባታን ይመለከቷል ፥ አስተውል የሚጠብቀው ቀለም ከበታቹ ተሰምሮበታል። የንባብ ዓይነቱ ከጎኑ ተጽፎበታል።
ሥርወ ቀለም ማለት ተ፣ ነ፣ አ፣ የ ናቸው። ከትንቢት እስከ ትዕዛዝ ያሉ አናቅጽን ለመመስረት የሚረዱ ቀለማት ናቸው። በግዕዛቸው በራብዓቸው በሳድሳቸው ይገኛሉ። ግሱ በሀና በአ አመል ሲገኝ ግዕዝና ራብዕ ይሆናሉ። በቀረው ግን ሳድስ ናቸው አስተውል።

  ፩ኛ የሩቁ ወንድ ሲዘረዝር በቀዳማይ አንቀጽ ተነሽ በቀረው ሰያፍ ነው። ሥርወ ቀለሙ የ ነው።
   ➾ *አእመረ* (ተነሽ) = አወቀ፤ አሳወቀ።
   ➾ *የአር* (ሰያፍ) = ያውቃል፤ ያሳውቃል።
   ➾ *ያእምር* (ሰያፍ) = ያውቅ ዘንድ፤ ያሳውቅ ዘንድ።
   ➾ *ያእምር* (ሰያፍ) = ይወቅ፤ ያሳውቅ።
  ፪ኛ የቅርብ ወንድ ሲዘረዝር ንባቡ በቀዳማይ ተነሽ በቀረው ሰያፍ ነው። ሥርወ ቀለሙ ተ ነው።
   ➾ *አእመርከ* (ተነሽ) = አወቅህ፤ አሳወቅህ።
   ➾ *ተአር* (ሰያፍ) = ታውቃለህ፤ ታሳውቃለህ።
   ➾ *ታእምር* (ሰያፍ) = ታውቅ ዘንድ፤ ታሳውቅ ዘንድ።
   ➾ *አእምር* (ሰያፍ) = እወቅ፤ አሳውቅ።
  ፫ኛ የሩቅ ወንዶች ሲዘረዝሩ በሁሉም ተነሽዎች ናቸው። ሥርወ ቀለማቸው የ ነው።
   ➾ *አእመሩ* (ተነሽ) = አወቁ፤ አሳወቁ።
   ➾ *የአሩ* (ተነሽ) = ያውቃሉ፤ ያሳውቃሉ።
   ➾ *ያእምሩ* (ተነሽ) = ያውቁ ዘንድ፤ ያሳውቁ ዘንድ።
   ➾ *ያእምሩ* (ተነሽ) = ይወቁ፤ ያሳውቁ።
  ፬ኛ የቅርብ ወንዶች ሲዘረዝሩ በሁሉም ተነሽዎች ናቸው። ሥርወ ቀለሙ ተ ነው።
   ➾ *አእመርክሙ* (ተነሽ) = አወቃችሁ፤ አሳወቃችሁ።
   ➾ *ተአሩ* (ተነሽ) = ታውቃላችሁ፤ ታሳውቃላችሁ።
   ➾ *ታእምሩ* (ተነሽ) = ታውቁ ዘንድ፤ ታሳውቁ ዘንድ።
   ➾ *አእምሩ* (ተነሽ) = እውቁ፤ አሳውቁ። (ሥርወ ቀለሙ በትእዛዝ ለቅርብ መደብ ይጠፋል።)
  ፭ኛ የሩቅ ሴት ስትዘረዝር በሁሉም ሰያፍ ነው። ሥርወ ቀለሙ ተ ነው።
   ➾ *አእመረት* (ተነሽ) = አወቀች፤ አሳወቀች። በቀዳማይ ት ቀለምን መጨመር ነው።
   ➾ *ተአር* (ተነሽ) = ታውቃለች፤ ታሳውቃለች።
   ➾ *ታእምር* (ተነሽ) = ታውቅ ዘንድ፤ ታሳውቅ ዘንድ።
   ➾ *ታእምር* (ተነሽ) = ትወቅ፤ ታሳውቅ።
  ፮ኛ የቅርብ ሴት ስትዘረዝር በሁሉም ተነሽ ነው። ሥርወ ቀለሙ ተ ነው።
   ➾ *አእመርኪ* (ተነሽ) = አወቅሽ፤ አሳወቅሽ። በቀዳማይ የግሱን መድረሻ ወደ ሳድስ ቀይሮ ኪን መጨመር ነው።
   ➾ *ተአሪ* (ተነሽ) = ታውቂያለሽ፤ ታሳውቂያለሽ።
   ➾ *ታእምሪ* (ተነሽ) = ታውቂ ዘንድ፤ ታሳውቂ ዘንድ።
   ➾ *አእምሪ* (ተነሽ) = እወቂ፤ አሳውቂ።

፯ኛ የሩቅ ሴቶች ሲዘረዝሩ በሁሉም ተነሽዎች ናቸው። ሥርወ ቀለሙ የ ነው።
   ➾ *አእመራ* (ተነሽ) = አወቁ፤ አሳወቁ። መድረሻ ቀለሙን ወደ ራብዕ መቀየር ነው።
   ➾ *የአራ* (ተነሽ) = ያውቃሉ፤ ያሳውቃሉ።
   ➾ *ያእምራ* (ተነሽ) = ያውቁ ዘንድ፤ ያሳውቁ ዘንድ።
   ➾ *ያእምራ* (ተነሽ) = ይወቁ፤ ያሳውቁ።
  ፰ኛ የቅርብ ሴቶች ሲዘረዝሩ ቀዳማዩ ተጣይ የቀሩት ተነሽዎች ናቸው።
   ➾ *አእመርክን* (ተጣይ) = አወቃችሁ፤ አሳወቃችሁ። በቀዳማይ የግሱን መድረሻ ወደ ሳድስ ቀይሮ ክንን መጨመር።
   ➾ *ተአራ* (ተነሽ) = ታውቃላችሁ፤ ታሳውቃላችሁ።
   ➾ *ታእምራ* (ተነሽ) = ታውቁ ዘንድ፤ ታሳውቁ ዘንድ።
   ➾ *አእምራ* (ተነሽ) = እወቁ፤ አሳውቁ።
  ፱ኛ አነ ያለው ሲዘረዝር በሁሉም ተነሽ ነው። ሥርወ ቀለሙ አ ነው።
   ➾ *አእመርኩ* (ተነሽ) = አወቅሁ፤ተ አሳወቅሁ። የግሱን መድረሻ ወደ ሳድስ ቀይሮ ኩን መጨመር ነው።
   ➾ *አአር* (ሰያፍ) = አውቃለሁ፤ አሳውቃለሁ።
   ➾ *አእምር* (ሰያፍ) = አውቅ ዘንድ፤ አሳውቅ ዘንድ።
   ➾ *አእምር* (ሰያፍ) = ልወቅ፤ ላሳውቅ።
  ፲ኛ ንሕነ ያለው ሲዘረዝር በሁሉም ተነሽዎች ናቸው። ሥርወ ቀለሙ ነ ነው።
   ➾ *አእመርነ* (ተነሽ) = አወቅነ፤ አሳወቅን። በቀዳማይ የግሱን መድረሻ ወደ ሳድስ ቀይሮ ነን መጨመር ነው።
   ➾ *ነአር* (ተነሽ) = እናውቃለን፤ እናሳውቃለን።
➾ *ናእምር* (ተነሽ) = እናውቅ ዘንድ፤ እናሳውቅ ዘንድ።
   ➾ *ናእምር* (ተነሽ) = እንወቅ፤ እናሳውቅ።

🌹🥇🔥
4🔥1
🌹🥇🔥
ㅤㅤㅤㅤㅤㅤ

💐 ዋዜማ 💐


      🌹 ዘ-አበው 💐

ለኢዮስያስ በፋሲካሁ ፥
እለ-አልሕምተ ሦዑ ወአባግዐ ዘጠብሑ ፤
ኢያትረፉ ለሣኒታሁ ወበልዕዎ አሜሁ ፤
በግዐ-ፋሲካነሰ እንዘ-አሐዱ ለሊሁ ፤
ዮም ይትበላዕ ኵለንታሁ ፤
ወጌሠመ ይትረከብ ከማሁ ።


💐ትርጉም 💐


በኢዮስያስ ፋሲካ በሬዎችንና በጎችን ያረዱ ሰዎች ለማግስቱ አላተረፉም በዚያው ጊዜም በሉት ፤ የፋሲካችን በግ ግን አንድ ሲሆን ሁለንተናው ዛሬ ይበላል ፤ በነጋውም እንደዚያው ይገኛል ።

​▎ምስጢር🔥


➥ ሰም :-
💐

እስራኤላውያን በግብጽ ምድር ለብዙ መቶ ዓመታት በከባድ የባርነት ቀንበር ሥር ወድቀው ሲሰቃዩ እግዚአብሔር የሕዝቡን የሥቃይ ጩኸት ሰምቶ ነቢዩ ሙሴን ወደ ግብጹ ንጉሥ ፈርዖንላከው። ፈርዖን ሕዝቡን በነፃ ላለመልቀቅ ልቡን ባደነደነ ጊዜ፣ እግዚአብሔር በግብጽ ላይ አሥር ተከታታይ መቅሰፍቶችን  አወረደ።የመጨረሻውና አሥረኛው መቅሰፍት በግብጽ ያሉ የሰውም ሆነ የእንስሳት የበኩር (የመጀመሪያ) ልጆች በሙሉ መሞት ነበር። እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ከዚህ ሞት ለማዳን እያንዳንዱ ቤተሰብ ነውር የሌለበት ቀንዱ ያልከረከረ፣ ጥፍሩ ያልዘረዘረ፣ ጠጉሩ ያላረረ ዓመት የሆነው ጠቦት  አርዶ፣ ደሙን በቤታቸው የበር መቃን ላይ እንዲቀቡ አዘዛቸው። የታረደው በግም ተጠብሶ በዚያው ሌሊት ተበልቶ እንዲያልቅ ፣ እስከ ጠዋት ድረስም ምንም ዓይነት ሥጋ ማደር እንደሌለበት። በድንገት ሳይበላ ተርፎ እስከ ጠዋት የቆየ ሥጋ ካለ፣ በእሳት እንዲቃጠል እንጂ ለሌላ ቀን እንዳይቀመጥ እግዚአብሔር ስላዘዛቸው የዛን ዕለት ይበሉታል እንጂ ለቀጣዩ ቀን አያስቀምጡም

"ወኢታትርፉ እምኔሁ ለነግህ ወዓዕሞ ኢትስብሩ እምኔሁ፣ ወለእ መቦ ዘተርፈ እምኔሁ ለነግህ አውዕይዎ በእሳት፤''

​"እስከ ጥዋትም ከእርሱ አታስቀሩ፤ እስከ ጥዋትም ከእርሱ የቀረውን በእሳት አቃጥሉት።" (ዘጸአት 12፥10)  

ኢዮስያስምበነገሠ በ18ኛው ዓመት የፈረሰውን ቤተ መቅደስ እንዲታደስ አዘዞ እየተሰራ እያለ። በዚያን ጊዜ ሊቀ ካህናቱ ኬልቅያስ ለብዙ ዘመን ተረስቶና ተቀብሮ የቆየውን መጽሐፈ ኦሪት አገኝቶ መጽሐፉንለንጉሡ ሲነበብለት፣ ሕዝቡና አባቶቹ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ባለመጠበቃቸው ምን ያህል ከፈጣሪ እንደራቁ ተረድቶ ሕዝቡን በሙሉ ሰብስቦ ከአምልኮ-ጣዖት  እንዲመለሱና ከእግዚአብሔር ጋር የነበራቸውን ቃል ኪዳን እንዲያድሱ አደረገ። ፋሲካ ደግሞ የእስራኤል ሕዝብ ከእግዚአብሔር ጋር ያላቸው ግንኙነት መጀመሪያና መታሰቢያ ስለሆነ ይህን ቃል ኪዳን ለማጽናት ፋሲካን በ መጽሐፈ ኦሪት ላይ በተጻፈው ጥብቅ ሥርዓት መሠረት አመከናወነው ፣ የፋሲካቸውን ሥጋም እንደ ርዓታቸው በእለቱ  ጨረሱት እኛ ኦርቶዶክሶች ለፋሲካችን ገዝተን የምናርደው በግ ግን ከአረድነው በኋላ በነጋታውም፣ ከሳምንት በኋላም ቢሆን እስከፈለግነው ጊዜ ድረስ እያስቀመጥን መብላት እንችላለን ።

ወርቅ :- 💐

በግዕ የተባለው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ​የእኛ የፋሲካችን በግ እግዚአብሔር ወልድ አንድ ሲሆን፣ እርሱም የማይለወጥና የማይጠፋ  ሥጋው ዛሬም ነገም ለዘላለምም በሕያውነት የሚገኝ ነው ። በብሉይ ኪዳን የነበረው በግ ለጊዜው ታርዶ የሚበላና የሚያልቅ ነበረ፤ አማናዊው የፋሲካ በግ ክርስቶስ ግን በባሕርይው ሞት የሌለበትና የማይጎድል ሕያው መሥዋዕት ነው። አለም ሳይፈጠር በፊት ከአብ በባሕርይ የተወለደ የባሕርይ አምላክ  ከአለም መፈጠር በኋላም በዘመነ ሥጋዌ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በሥጋ የተወለደ ተቀዳሚና ተከታይ የሌለው አንድ ወልድ ክርስቶስ ። በሰማይ ከአብ ጋር በጌትነቱ እንዳለ፣ በምድርም ከእመቤታችን በሥጋ ተወልዶ ፍጹም ሰው ሁኖ ​ይህ አንድ ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ዛሬም በቤተክርስቲያን መሠዊያ ላይ ሥጋው በኅብስት፣ ደሙ በወይን ሲሰጥ ምንም ዓይነት ጉድለት የለበትም። በዓለም ዙሪያ በሚገኙ መሠዊያዎች ሁሉ ምእመናን ቢመገቡትም እርሱ አይከፈልም፣ አይጎድልምም፤ ይልቁንም ለሚቀበሉት ሁሉ የዘላለም ሕይወትን የሚሰጥ የሕይወት እንጀራ ነው። "ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው" (ዮሐ. 6፡54) እንዳለ፣ የእኛ ፋሲካ ክርስቶስ ዛሬም ነገም በሚቆረሰው ሥጋውና በሚፈስሰው ደሙ አማካኝነት ከእኛ ጋር አንድ ሆኖ ይኖራል ይላሉ ባለ ቅኔው ።

ከተመቻችሁ እንዲሁም ከወደዳችሁት ፥ 👇🤭
       ♡ ㅤ  ⎙ㅤ   ⌲          ✉️   
     ˡᶦᵏᵉ    ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃʳᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ
ʟɪᴋᴇ ɪᴛ ᴅᴏᴇsɴ'ᴛ ᴄᴏᴜɴᴛ ᴘʀᴇss & Share ɪᴛ ! ♡

https://t.me/medibeli😎

🌹🥇🔥
🔥6👏3
🌹🥇🔥
ㅤㅤㅤㅤㅤㅤ
💐 መወድስ የቅኔው ንጉሥ ፥ ስለ ተዋሕዶ ፥ 💐

🌹 ዘ-መምህር አካለ-ወልድ ዘቦሩ ሜዳ  💐

ለዳዊት ቃል ብሉየ-መዋዕል ፥
አስተማውቆቶ ኢክህለ ልብሱ ሥጋ-አደም ፤
እመኒ ተዐጽፈ ካዕበተ-ሥጋ ወዐፅም ፤
ባሕቱ ኀሠሡ ተዐግሦቱ ፥
ወኂሩተ-ልቡ ሕዝበ-ፍቅር ፍጹም ፤
አመ-አኀዞ ቍረ-ገዳም ፥
ዘታስተማውቆ ድንግል እስትንፋሰ-አድግ ወላሕም ፤
አንገሥዎሂ ለሰሎሞን ባሕርየ-ሥጋ ድኩም ፤
በግዮን ተዋሕዶ ፈለገ-ጣዕመ-ወይን ማርያም ፤
እንዘ-ይብሉ ሕዝብ መላእክተ-ስብሐት ጥዑም ፤
ሥጋ አበ-ነጋሢ ሕየው ለዓለም ።

💐ትርጉም 💐


የዕድሜ ባለ-ጸጋ የኾነ ዳዊት ቃልን ሥጋና አጥንት ደራርቦ ቢለብስም የአዳም ሥጋ ልብሱ ሊያሞቀው አልቻለም ፤ ነገር ግን የፍጹም ፍቅር ሕዝብ የኾኑ ትዕግሥቱና የልቡ ቸርነት የጫካ ብርድ በያዘው ጊዜ የምታሞቀው ድንግልን የአህያና የላም ትንፋሽ ፈለጉለት ፤ የጣፋጭ ምስጋና አለቆች ሕዝቦች << የነጋሽ አባት ሥጋ ለዘለዓለም ኑር ! >> ሲሉ ሰሎሞን የሥጋ ባሕርይንም የወይን ማርያም ጣዕም ወንዝ በምትኾን ተዋሕዶ ግዮን አነገሡት !

​▎ምስጢር🔥


➥ ሰም :- 💐

ዳዊት ዕድሜው በገፋ ጊዜ ልብስ ቢደርቡለትም አይሞቀውም ነበር ፤ የምታሞቀው ድንግል ተፈልጋ ሱነማይቱ አቢሳ ከጎኑ ( ከብብቱ ) ኾነች ፤ ኾኖም ሊሞቀው አልቻለም ፥ በሩካቤም አያውቃትም ነበር ። ( ፩ ነገ ፩ ፥ ፲፬ ) እርሱ አልፎ ሰሎሞን በዓባይ ወንዝ ዳር ነገሠ ፤ ሕዝቡም " ንጉሥ ሆይ ፥ ዘለዓለም ንገሥ ! " አሉት ።

➥ ወርቅ :- 💐

በዘመናት ያረጀው የተባለው ቃል ሥጋን በመልበሱ ለራሱ ያገኘው ጥቅም የለም ፤ ሥጋም በማሕፀነ-ድንግል ከቃል በመዋሐዱ በተዋሕዶ ነገሠ ፤ በዚህም ዘመን የተቆጠረለት ሥጋ በተዋሕዶ ዘለዓለማዊ (ዘእንበለ-ጥንት ) በዘመናት ያረጀ ተባለ !

💥😯 አቤት ምስጢር ፥ አቤት ሊቅነት ! 🔥😎

ከተመቻችሁ እንዲሁም ከወደዳችሁት ፥ 👇🤭
       ♡ ㅤ  ⎙ㅤ   ⌲          ✉️   
     ˡᶦᵏᵉ    ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃʳᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ
ʟɪᴋᴇ ɪᴛ ᴅᴏᴇsɴ'ᴛ ᴄᴏᴜɴᴛ ᴘʀᴇss & Share ɪᴛ ! ♡

https://t.me/medibeli😎

🌹🥇🔥
3🔥3🤔2🥰1
🌹🥇🔥
ㅤㅤㅤㅤㅤㅤ
💐 መወድስ የቅኔው ንጉሥ ፥ ስለ ተዋሕዶ ፥ 💐

🌹 ዘ-አለቃ ዓለምአየሁ ዘአብማ ማርያም ፥ 💐

ረከበ ሳዖል እንተ-ኢኀለየ ፥
ቅብዐ-ዘይት ቅዱስ ወአክሊለ-መንግሥት ከመ-ይንግሥ ፤
አእዱጊሁ ዘጠፍዑ እንዘ-የኀሥሥ ፤
አምጣነ-ልማዱ ለአምላክነ ፥
ውሂብ ዘኢተኀለየ ውስቴታ ለከርሥ ፤
ኆሳዕናሁሰ ለጴጥሮስ ፥
ለኀሢሠ-ክልኤ አእዱግ እመ-ምድረ-ሳሌም ይገይሥ ፤
ረከበ በፈቃዱ ፈቃደ-ሥሉስ ቅዱስ ፤
ወሪቀ-ምራቅ ህየንተ-ቅብዕ ወህየንተ-አክሊል ተኰርዖ-ርእስ ፤
ወኢይጽሕቅ ቅብዐተ ለከዊነ-ንጉሥ ሐዲስ ፤
አምጣነ-ንጉሥ ቅድመ-ዓለም ወቅብዕ ዘይቄድስ ።

💐ትርጉም 💐


ሳኦል የጠፉ አህዮቹን ሲፈልግ ያላሰበውን ቅዱስ የዘይት ቅባትና የመንግሥት ዘውድ ይነግሥ ዘንድ አገኘ ፥ ለአምላካችን ያልታሰበን መስጠት ልማዱ ነውና ። የጴጥሮስ መድኃኒት (አዳኝ) ግን ኹለት አህዮችን ለመፈለግ ወደ ሳሌም ምድር ሲገሰግስ የሥሉስ ቅዱስ ፈቃድ የኾነን የምራቅ መተፋትን ስለ ቅብዓት ፈንታ ስለ ዘውድም የእሾኽ አክሊልን በፈቃዱ አገኘ ፤ አዲስ ለመኾንም ቅብዓትን አይሻም ፥ ከዓለም አስቀድሞ የሚያከብር ቅብዓት ነውና ።

​▎ምስጢር🔥


➥ ሰም :- 💐

ሳኦል የጠፉ አህዮቹን ሲፈልግ ባላሰበው መንገድ ፥ አስቀድሞ ሳይሻ ለቅብዐ-መንግሥት ተጠራ ። ( መጽ. ሳሙ ፱ ፥ ፫-፲፯ )

➥ ወርቅ :- 💐

በጠፉ አህዮች የተመሰሉ አዳምና ሔዋንን ለመፈለግ የመጣው ጌታ ግን በእርሱ ፥ በአባቱና በመንፈስቅዱስ ፈቃድ ሰው ኾኖ ፥ ምራቅ ተተፋበት ፥ የእሾኽ አክሊል ተደፋበት ፤ እርሱ አስቀድሞ ንጉሥ ነውና በራሱ የሚያከብር ቅብዕ ነውና ቅብዐት አያሻውም !

💥😯 አቤት ምስጢር ፥ አቤት ሊቅነት ! 🔥😎

ከተመቻችሁ እንዲሁም ከወደዳችሁት ፥ 👇🤭

       ♡ ㅤ  ⎙ㅤ   ⌲          ✉️   
     ˡᶦᵏᵉ    ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃʳᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ
ʟɪᴋᴇ ɪᴛ ᴅᴏᴇsɴ'ᴛ ᴄᴏᴜɴᴛ ᴘʀᴇss & Share ɪᴛ ! ♡

https://t.me/medibeli😎

🌹🥇🔥
🔥4🥰4👏1🙏1
ㅤㅤㅤㅤㅤㅤ
​«ይህ ጽሑፍ የሰው ደስታ ለሚያስደስታችሁ ነው፤ React እና Share ካደረጋችሁ እኔ እደሰታለሁ። እኔ ስደሰት እናንተ ትደሰታላችሁ፤ እናንተን ደስ ሲላችሁ ደግሞ እኔን ደስ ይለኛል። ድጋሚ እኔ ደስ ሲለኝ እናንተም ደስ ይላችኋል፤ ከዚህ በላይ ደስታ ምን አለ?! 😁»

''ምስለ ዘይትፌሣሕ ተፈሥሑ ወምስለ
ዘይበኪ ብክዩ
። "
​"ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ፤ ከሚያለቅሱም ጋር አልቅሱ።" ሮሜ 12፥15
5😁3🥰2👏1
🌹🥇🔥
ㅤㅤㅤㅤㅤㅤ
💐 መወድስ የቅኔው ንጉሥ ፥ ስለ ሕይወት ፥ 💐

🌹 ዘ-ክፍለ ዮሐንስ ዘጎንደር ፥ 💐

“ ጥቀ ኄር እግዚአብሔር ፥
ለሐዋርያ-ግብፅ ዮሴፍ ዘበ-ደዌ-ሞቅሕ ሐንካስ ፤
ወለዘ-ፈተኖ ዳንኤል በጾመ-ዕለታት ሠላስ፡፡
በጥቃ-መዓቱሰ እንዘ-ሀሎ ፥
ማዕረረ-ምንዳቤ ምሕረቱ ሐዲስ
እስመ-ያሜክረነ በተጽናስ ፥
ወአርዌ-ረኀብ ይነቁ ውስተ-ጸላዕትየ ከርሥ ፤
መብልዕየሂ ጼና-መብልዕ ዘያመጽኦ ነፋስ ፤
ወስቴ አንብዕየ ተረፈ-አንብዑ ለኤርምያስ ፤
ወልብስየኒ ምንንት መንጦላዕተ-ርሕቅት ነፍስ፡ ፤
እስመ-አነ ከመ-ዶርሆ ላዕለ-አብራክየ እለብስ ፡፡ ``

💐ትርጉም 💐


​▎ምስጢር🔥

➥ ሰም :- 💐

➥ ወርቅ :- 💐

💥😯 አቤት ምስጢር ፥ አቤት ሊቅነት ! 🔥😎

☝️ ከፈለጋችሁ ፥ 😎😉
➥ Comments መስጫው ላይ ጻፉልን !


ከተመቻችሁ እንዲሁም ከወደዳችሁት ፥ 👇🤭

       ♡ ㅤ  ⎙ㅤ   ⌲          ✉️   
     ˡᶦᵏᵉ    ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃʳᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ
ʟɪᴋᴇ ɪᴛ ᴅᴏᴇsɴ'ᴛ ᴄᴏᴜɴᴛ ᴘʀᴇss & Share ɪᴛ ! ♡

https://t.me/medibeli😎

🌹🥇🔥
4🔥2🥰1👏1
🌹🥇🔥

💐 የሊቁ መምህር ሐዲስ ኪዳናት
/የእማሆይ ገላነሽ ወላጅ አባት/
💐

🌹መወድስ የቅኔው ንጉሥ 🔥


➟ ቅኔ ዘበዓለ-ደብረ-ታቦር

ሰረቅተ-ጣእዋ ምስጢር ዘደብረ-ታቦር ፥
‎መስተገብራን ጴጥሮስ ያዕቆብ ወዮሐንስ ፤
‎ሶበ-ምጽአተከ ርእዩ ለባሴ-ጸዓዳ ክርስቶስ ፤
‎ምድር ጸበበቶሙ ፥
ወተኀብዑ ውሳጤ-ደመና ዘኢዮር ተሥላስ
‎አምጣነ-ጥዩቀ አፍርሆሙ ፥
‎ቃሉ ለአብ እንተ-ሰማያት ንጉሥ ፤
‎በታቦርሂ አመ-ቀነጸ መለኮትከ ፈረስ ፤ (አባት)
‎ኢክህሉ ስሒቦቶ ሙሴ ወኤልያስ ፤ (ልጃቸው ‎ገላነሽ)
‎ወእንዘ-ትትናገሪ አንቲ በአልዕሎ-ክሳድ ወርእስ ፤ (‎አባት)
‎ከመ-አነ ሰማዕኩኪ ኢይስማዕኪ ጳውሎስ ።

በማለት በዚህ የመወድስ ቅኔ ላይ አባትና ልጅ ጥበባዊ አሻራቸውን አሳርፈውበታል ።

💥 መወድሱን እንደ ዳዊት አስተዛዝለውታል !

🌹የቅኔው ፍቺ እና ሙያ ፥ 💐

🥇የቅኔው ስምና ወርቅ ርቃቂ ፥ 🌹

☝️ ከፈለጋችሁ Comments መስጫው ላይ ጻፉልን !

ከተመቻችሁ እንዲሁም ከወደዳችሁት ፥ 👇🤭
       ♡ ㅤ  ⎙ㅤ   ⌲          ✉️   
     ˡᶦᵏᵉ    ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃʳᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ
ʟɪᴋᴇ ɪᴛ ᴅᴏᴇsɴ'ᴛ ᴄᴏᴜɴᴛ ᴘʀᴇss & Share ɪᴛ ! ♡

https://t.me/medibeli😎

🌹🥇🔥
🥰62👏2🔥1
🌹🥇🔥

💐 የሊቁ አለቃ ዶሪ የቅኔ ፈጣሪ ፥ ዘጎንጅ ፥ 💐
🌹መወድስ የቅኔው ንጉሥ 🔥


እም-ሀልዎትየ ሊተ በዓለመ-ሀጕል ፥
ይኄይስ ወትረ ንብረተ-ሙሴ ውስተ-መሬት ፤
ወእም-ሀልዎትየ ካዕበ ውስተ-ቤተ-ሐሳር ጽንንት ፤
ትኄይስ ነያ በአንጻር ቅርብት ፤
ሀልዎተ-ዓሣ ውስተ-ልጎት ፥
አምጣነ-ይሰቲ ማየ ዘኢይሠፍሮ በዐለ-ቤት ፤
ነቢረሰ ይነብሩ በዘዚኣየ ትምህርት ፤
ቈናጽል ውስተ-ግበብ ወአዕዋፍ ውስተ-ጾላዕት ፤
ባሕቱ ፥ ለኵሉ ዓለም እንተ-ከመ-ዝ ሥርዐት ፤
ሀልዎ በኢሀልዎ ወመዊት እም-ቅድመ-መዊት ።

🌹🥇🔥

🌹የቅኔው ፍቺ እና ሙያ ፥ 💐

🥇የቅኔው ስምና ወርቅ ርቃቂ ፥ 🌹


☝️ ከፈለጋችሁ Comments መስጫው ላይ ጻፉልን !

ከተመቻችሁ እንዲሁም ከወደዳችሁት ፥ 👇🤭
       ♡ ㅤ  ⎙ㅤ   ⌲          ✉️   
     ˡᶦᵏᵉ    ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃʳᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ
ʟɪᴋᴇ ɪᴛ ᴅᴏᴇsɴ'ᴛ ᴄᴏᴜɴᴛ ᴘʀᴇss & Share ɪᴛ ! ♡

https://t.me/medibeli😎

🌹🥇🔥
3🔥1🥰1👏1
🌹🥇🔥

💐 የሊቁ መምህር ሐዲስ ኪዳናት
/የእማሆይ ገላነሽ ወላጅ አባት/
💐

🌹መወድስ የቅኔው ንጉሥ 🔥


➟ ቅኔ ዘበዓለ-ደብረ-ታቦር

ሰረቅተ-ጣእዋ ምስጢር ዘደብረ-ታቦር ፥
‎መስተገብራን ጴጥሮስ ያዕቆብ ወዮሐንስ ፤
‎ሶበ-ምጽአተከ ርእዩ ለባሴ-ጸዓዳ ክርስቶስ ፤
‎ምድር ጸበበቶሙ ፥
ወተኀብዑ ውሳጤ-ደመና ዘኢዮር ተሥላስ
‎አምጣነ-ጥዩቀ አፍርሆሙ ፥
‎ቃሉ ለአብ እንተ-ሰማያት ንጉሥ ፤
‎በታቦርሂ አመ-ቀነጸ መለኮትከ ፈረስ ፤ (አባት)
‎ኢክህሉ ስሒቦቶ ሙሴ ወኤልያስ ፤ (ልጃቸው ‎ገላነሽ)
‎ወእንዘ-ትትናገሪ አንቲ በአልዕሎ-ክሳድ ወርእስ ፤ (‎አባት)
‎ከመ-አነ ሰማዕኩኪ ኢይስማዕኪ ጳውሎስ ።

በማለት በዚህ የመወድስ ቅኔ ላይ አባትና ልጅ ጥበባዊ አሻራቸውን አሳርፈውበታል ።

💥 መወድሱን እንደ ዳዊት አስተዛዝለውታል !

🌹የቅኔው ፍቺ ፥ 💐


ነጭ ለባሽ ክርስቶስ ሆይ ! የደብረ-ታቦር ምሥጢር ጥጃን የሰረቁ ምንደኞች ያዕቆብ ዮሐንስ እና ጴጥሮስ መምጣትህን ባዩ ግዜ ምድር ጠበበቻቸው (ሚገቡበት ጨነቃቸው) ፤ በሰማይ ሰገነት ደመናም ተሸሸጉ ፡፡ የሰማያት ንጉሥ አብ ድምፅ በጣም አስደንግጧቸዋልና ፡፡

◉ መለኮትህ ፈረስ በደብረ-ታቦር በጋለበ ግዜም
➦ ሲሉ በሴቶች መቆምያ በኩል “የነበረች “ 1 ሕፃን ቀበል አረገችና
ሙሴ እና ኤልያስ መሳቡን አልቻሉም !
ብላ እርፍ… 😳ምን ቢልዋት ጥሩ ነው አሞካሽ ተው ሲያበቁ
አንገትሽን ና ራስሽን ከፍ በማድረግ ይህንን ስትናገሪ እኔ እንደሰማሁሽ ጳውሎስ አይስማሽ ፡፡

በማለት መወድሱን ሞሉት ፥ እማሆይ ገላነሽ ሐዲስ ባገራችን ከነበሩ እውቅ የቅኔ መምህራን አንዷ ናቸው ፡፡በ1898ዓ.ም በቀድሞ ባሕር ዳር አውራጃ ይልማና ዴንሳ ወረዳ ተወልደው በ50 ዓመታት የማስተማር ዕድሜያው ከ 54000 በላይ ተሰምተው የማይጠገቡ ቅኔያት ለዚች ዓለም አበርክው በ1978ዓ.ም አረፉ......💥

🥇የቅኔው ስምና ወርቅ ርቃቂ ፥ 🌹


ይህ ምኑ ይራቀቃል ፤ ተራቀቁበት እንጂ ! 💥🔥

☝️ ከፈለጋችሁ Comments መስጫው ላይ ጻፉልን !

ከተመቻችሁ እንዲሁም ከወደዳችሁት ፥ 👇🤭
       ♡ ㅤ  ⎙ㅤ   ⌲          ✉️   
     ˡᶦᵏᵉ    ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃʳᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ
ʟɪᴋᴇ ɪᴛ ᴅᴏᴇsɴ'ᴛ ᴄᴏᴜɴᴛ ᴘʀᴇss & Share ɪᴛ ! ♡

https://t.me/medibeli😎

🌹🥇🔥
🔥4😁31