ቅንጭብጭብ
7.18K subscribers
413 photos
9 videos
5 files
502 links
ካየሁት 👀 አስገራሚ
ከሠማሁት 👂 መሣጭ
ካነበብኩት 📖 አስተማሪ
ካሠብኩት ♀🅱 ልዩ ልዩ

እነሆ #ቅንጫቢ

ፅሁፎቻችሁን በ @bcrAzykid አካፍሉን።

ለማንኛውም አስተያየት ጥያቄ እና ጥቆማ @bcrAzykid ይጠቀሙ።
Download Telegram
#ተስፋ

ወዳጄ ሆይ ሰዎችን የፈለከዉን ያክል ብትወዳቸው እና ብታምናቸው ፈፅሞ ተስፋህ አታድርጋቸው።

ምክንያቱም የሠው ልጅ ከጎዶሎ የፀዳ አይደለምና ።
በመከራ እና በጎዶሎ ቀን ተስፋ ያደረከው ሰው ሲንሸራተት ቅስምህ ይሰበራል ፥ሰዉን እንዳታምን ያደርግሃል።

ስለዚህ ከጎደሎ የፀዳዉን ፈጣሪህን ተስፋ አድርግ !!!

በእርሱ ተስፋ ያደረጉ አያፍሩም

ለወዳጅዎ ያጋሩት
Join us
@kinchebchabi @kinchebchabi
#ቅንጭብጭብ
© #ተስፋ

ተስፋ በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ብርሃን አለ ብሎ ማመን ነው ፣
ተስፋ ማለት ወደ ባህር እየተወረወሩ በሆነ ተአምር እንደሚድኑ ማመን ነው ፣
ተስፋ ማለት በጠላት ተከቦ ወደ ሰማይ ለማረግ እንደማኮብኮብ ነው ።
ተስፋህ ያኖርህሃል

"መሆን ከተመኘህ ዛፍነትን ምረጥ
ቆርጠዉህ ሲሄዱ ሺህ ሆነህ አቆጥቁጥ"

Join us
@kinchebchabi @kinchebchabi
#ቅንጭብጭብ
© #ተስፋ

ሁሌም ማታ ወደ አልጋችን ስንሄድ ነገ እንደምንነሳ ምንም ማረጋገጫ የለንም!
ነገር ግን ነገ ብለን ሰዉ እንቀጥራለን! ነገ ላይ ብዙ ነገር ለማድረግ ብዙ ቦታ ልንሄድ እቅድ እናወጣለን። ያ ማለት #ተስፋ ነው። ሰዉ በተስፋ ይኖራል ተስፋን የሰጠ ፈጣሪ ደግሞ የታመነ ነዉ ነገን በመልካም ያኖረናል!

"ተስፋ እንዳለህ አምነህ ብዙ ነገር እያደረክ ተስፋ የለኝም የኔ ነገር አበቃ አትበል!"

Join us
@kinchebchabi @kinchebchabi

For any comment n suggestion @bcrAzykid
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጲያ
#ተስፋ

ተስፋ የመኖር ምክንያት ነው። ሰውን እንዲኖር የሚያደርገው ወይም የሚገፋው መለወጥ አለመለወጡ ሳይሆን የመለወጥ ተስፋው ነው። ቢሆንም ግን ህይወት ተከታታይ መሆኗን መገንዘብ ይጠቅማል።

ዛሬን የምንኖረው በትናንት ምክንያት ነው። እውነተኛ ለውጥ የማይኖረው ሰው ስላልጣረና ስላልሞከረ ሳይሆን፣ ለውጥ ሂደት እንጅ መድረሻ ባለመሆኑ ነው።

ሌሎች እንዲማሩበት መልእክቱን ያጋሩት

Join.us
@kinchebchabi @kinchebchabi
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጲያ
#ጠቃሚ_የህይወት_መርሆች

👉 ሶስት ነገሮችን እንጠብቅ

#እናትን #አገር #አይንን

👉 ለሶስት ዋና ዋና ነገሮች እንዘጋጅ

#ለሀላፊነት #ለእውቀት #ለትዳር

👉 ሶስት የማይረሱ ነገሮችን እናክብር

#ቃልኪዳንን #ጓደኛችንን #ትዳራችንን

👉 ሶስት ነገሮችን እንቆጣጠር

#ምላሳችንን #ቁጣችንን #ስሜታችንን

👉 ሶስት መጥፎ ነገሮችን እንጥላ

#ሀሜትን #ቅናትን #ተንኮልን

👉 ሶስት ነገሮችን ገንዘብ እናድርግ

#መልካም_ስነምግባርን #ትዕግስትን
#ማስተዋልን

👉 ሶስት መሠረታዊ ነገሮች ያስፈልጉናል

#እምነት #ተስፋ #ፍቅር

ስለዚህ በህይወት የመኖራችን ሚስጥሩና ትርጉም የምናረጋግጠው በማሰብ ብቻ ሳይሆን በመተግበር፣ በመናገር ብቻ ሳይሆን በመስራት፣ በመምሰል ብቻ ሳይሆን በመሆን ነው።

#ወዳጆቼ

ያለምንም ተንኮል በንፁህ ልቦና መንገዳችንን እናስተካክል ህይወታችንን እናቃና።

ለወዳጆቻችሁ አጋሩት

For any comment n suggestion 👉 @bcrazykid

Join.us
@kinchebchabi @kinchebchabi
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጲያ
#ተስፋ_አትቁረጡ

ዘሩ ብቅ አላለም ብለህ ውሃ ማጠጣቱን አታቁም

የቻይና ባምቡ ዛፍ አስተዳደጉ ከሌሎች ዛፎች በጣም ይለያል። ሌሎች ዛፎች ከተተከሉ ጀምሮ ማቆጥቆጥ ሲጀምሩ ፤ ይህ የቻይና ባምቡ ዛፍ ግን ፤ በቀን በቀን ውሃ ቢጠጣም እስከ አምስተኛው አመት ድረስ አፈሩን በርቅሶ አይወጣም ። ያለማቋረጥ እለት ተእለት ውሃ መጠጣት አለበት ፤ ነገር ግን አራት አመት ሙሉ ምንም አይነት እድገት አያሳይም ።

በአምስተኛው አመት ግን በአምስት ሳምንት ወስጥ በአንዴ 90 ፊት ውይም 27 ሜትር ያድጋል። ታዲያ ይህ ዛፍ በአምስት ሳምንት ውስጥ ነው ያደገው ? ወይስ በአምስት አመት መልሱ በአምስት አመት ነው ። ጽናት የሌለው ሰው ግን ቶሎ ብቅ ለማይል ዘር አምስት አመት ሙሉ ውሃ ማጠጣቱ አይዋጥለትም እናም ዛፉን በእንጭጩ ይቀጨዋል ። የእኛም ነገር እንዲህ ነው ፤ ሃሳባችን ግቡን ባሰብነው ሰዓት ካልመታ ፤ አላማችን በአቀድነው ቀን ካልተሳካ ፤ ምኞታችን በእለቱ እውን ካልሆነ ፤ የማይሳካ ይመስለናል። ለዚህ ነው ብዙዎቻችን ጉዟችንን የምናቋርጠው ።

የእውነት አላማ በውስጥህ ካለ ፤ ውሃ ማጠጣትክን እንዳትተው ። ዛሬ ባይሳካ በጊዜው መሳካቱ አይቀርም ።
አንባቢ ባታገኝም መጻህፍህን አትተው ፤ የሚጎበኝልህ ብታጣም መሳልህን አትተው፤ የሚሰማህ ብታጣም መዝፈንህን አታቋርጥ ፤ አይዞህ የሚልህ ባታገኝ መማርህን አታቁም ።

የብዙዎቻችን አላማ ልክ እንደ ቻይናው ባምቡ ዛፍ ነው ፤ ሳናቋርጥ ውሃ ካጠጣነው እና ትዕግስት ካለን ፤ ማቆጥቆጡ ብሎም ማደጉ አይቀርም ።

ለሁሉም ጊዜ አለው ይል የለ መጽሃፉ በጊዜው የተከልነው ችግኝ ሰማይ ማከሉ አይቀርም ፤ እስከዛ ግን ማድረግ የሚገባህን ከማድረግ አትቆጠብ ፤ ነፍስህ በቀን በቀን ውሃ አጠጣት።

•፨፨፨• •፨፨፨• •፨፨፨• •፨፨፨•

አንዳንዴ ለፍተን ለፍተን ምንም ነገር ጠብ ሳይል ሲቀር ተስፋ መቁረጥ ፤ ከተፍ ማለቱ አይቀርም። የምንለፋው ለምንድን ነው? ያሰኘናል ። የምጓዘው ጨለማ መቼ ነው የሚነጋው? የልፋቴን ዋጋ መቼ ነው የማገኘው . . . ?
አንድ ነገር ሞክራችሁ ከማቋረጣችሁ ይህንን ታሪክ መልሳችሁ ለራሳችሁ ንገሩት።

አስተማሪ ስለሆነ ለወዳጀጅዎ ያጋሩት


Join.us
@kinchebchabi @kinchebchabi
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ
#ጆይስ_ማየር

#ተስፋ_አትቁረጡ
"አባቴ የወሲብ፣ የስነ-ልቦና የስሜት ጥቃት ያደርስብኝ ነበር ፣ ይህ ድርጊትም በ18 ዓመቴ ቤት ለቅቄ እስከምወጣ ድረስ ተባብሶ ቀጥሎ ነበር" ከ90 በላይ መፅሐፍት ደራሲ እና ከ1000 በላይ ትምህርቶችን ለአለም ያስተማረች ድንቅ ሴት 👉 @kinchebchabi
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ
#መውደቅ_ማለት_መሞት_አይደለም!

ውድቀት ሞት አይደለም ስትወድቅ የማትነሳ መስሎህ #ተስፋ_አትቁረጥ እንደውም ከነበርክበት ተሽለህ ልትነሳ ትችላለህ ምናልባትም የወደከው እኮ ሌላ መያዝ ያለብህን ነገር አንስተህ እንድትነሳ ሊሆንም ይችላል።

#እመነኝ
"መውደቅ ማለት የህይወት መጨረሻ (ሞት አይደለም!)"

የወደቀ ሁሉ አይሞትምና ዳግም ታብባለህ!

ወድደው 💜 ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉት

Join.us
@kinchebchabi @kinchebchabi
🌿❤️እንዴት አደርሽ🌿
Yohannes_Lawgaw ስለ እኔ @sleenee Yohannes Lawgaw sle enee
🌿ዛሬ ማለዳ በዛሬ ህይወት ሰላም በሆነች ንጋት.. እልፍ #ተስፋ ባለባት...🕊🌿ያንቺ እንደሆንኩ ነቅቻለሁ ♥️ እንዴት አደርሽ🌿
🌿#Morning_Queen #ጠዋት_ስትነቂ #ማለዳ #ፀሀይ
#ስጦታዬ #ፍቅር #ዕለተ_እሁድ

።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 t.me/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 t.me/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 t.me/sufafel 🦋🦋