ቅንጭብጭብ
7.68K subscribers
408 photos
9 videos
1 file
497 links
ካየሁት 👀 አስገራሚ
ከሠማሁት 👂 መሣጭ
ካነበብኩት 📖 አስተማሪ
ካሠብኩት ♀🅱 ልዩ ልዩ

እነሆ #ቅንጫቢ

ፅሁፎቻችሁን በ @bcrAzykid አካፍሉን።

ለማንኛውም አስተያየት ጥያቄ እና ጥቆማ @bcrAzykid ይጠቀሙ።
Download Telegram
የደጋ በረከት
.
©ሲራክ ወንድሙ @siraaq
.
የተስፋ ሀገር ወዲያ ፥ የሀሳብ ሀገር ወዲህ ፣
ፋኖሱ ተሰዷል ፥ ሊመሽ ነው እንግዲህ ፤
ዶሮ ከቆጥ ሰፍሮ ፥ ሊኮኩል ሲቀጥር ፣
ይሄንን እያየ ፥ ልቤ ሲለኝ ጠርጥር ፣
በምናልባት መናጥ ፥ የቀን ድግግሞሽ ፣
እንዳሞራው ፍጥነት ፥ አክናፍ እሽክርክሮሽ ፤
ከቀየዋ ሳልሄድ ፥ በሯም ሳይዘጋ ፣
አድማስ ሲደማምን ፥ ምሽት ሲዘረጋ ፣
ባዶ እጄን ወጣለሁ ፥ ውብ አይኗን ፍለጋ።
__°°° _
የደጋ በረከት
መስከረም ፳፻፲፬ ዓ.ም
@kinchebchabi
@kinchebchabi
Sura
Untitled
አታውቅም

🌗የግማሽ አለም ጣኦት

አንባቢ ዘምሽ የአልግዬ
የጠቆረ ልብ

።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
የመኖር ትርጉሙና ጥፍጥናው በምን ይለካል

ንገሩኝ? በማርያም
አይጥ ወልዳ ወልዳ
ጅራቷ ሲቀር ሲጥ


የሙት መንፈስ መጡ ......

ነፍሷንም ከስጋዋ ነጠቋት


ጉዞ ወደ ጨለምተኝነት

😢 🌗የግማሽ አለም ጣኦት😢


@sufafel
@sufafel
****
@sufafel
መለዓከ ብርሀን


ብለፋ ብደክም፣ ባዶ ቢሆን እጄ
መሬቴን አረስኩት፣ መልዓክ ተጠምጄ፣

መቼም የኔ ነገር ፣ አልመጥንም ከሰው
ማልጄ ልነሳ ፣ መለዓኩን ልጥምደ፣

ቢቸግር ነው ፣ እንጂ አይጨከን ወዶ
ምን ይበቅል ይሆን? መልዓክ ተጠምዶ።


ገጣሚ መልዓከ ብርሀን
(ድብቅ አለም ቶ)

።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
ገላዬ....
ከመስኩ ላይ ቆሜ ፥ እምባን ባረገዘ
በናፍቆት ወይቦ ፥ በተድበዘበዘ
በዚያ መንታ አይኔ...
የመራቤን ጅራፍ ፥ የምኞቴን ጩኸት
ላንቀላፋው ጤዛ ፥ ለወፍ ጎጆው ምልዓት
ዘምሬ
ዘምሬ
ደስኩሬ
ደስኩሬ
ህቅ ባለው መንፈስ ፥ ምሬት ባየው ልሳን
ብናገር ለእነሱ ፥ የኔን እንዲህ መሆን
የአንቺ ወዲያ መቅረት ፥ የንጋት ሰቀቀን
በጉድ ወጣ እያሉ ፥ ለሰማይ ለምድሩ
ለሰው ላራዊቱ ፥ ለቀየው መንደሩ
መስቀሉ ናት ብለው ፥ ናፍቆት ወለፈንዴ
ተሸነፈ ብለው ፥ ያሙኝ ይሆን እንዴ?
.................. / / .....................
© ሲራክ ወንድሙ
@kinchebchabi
@kinchebchabi
የሀገሯ ~ ገመገም
ከጥርሶቿ ~ ግርግም፣
ሳቋ ~ ሲያፍገመግም
ሳልፍና ~ ሳገድም።


አማትሬ ~ ባየው:
ተሰትረው ~ ኑረው
የቅርብ ሩቅ ~ ሆነው።


ኩንስንስ አመሏ
ጵስጡቂስ ጠረኗ
ኑረት አኳኃኗ፣

ዘንጠፍጠፍ እያለ
ቀልብ እያዋለለ፣


የገዛ ጥላዋ
ብርቅርቅ ገላዋ፣


ውልብ ይልብኛል.....
የድምጿ ሲርሲርታ
ያቃጭልብኛል።


እናማ......

ምናብ ሀሳብ ሲምስ
ሲያወጣ ሲመልስ፣


ጣዕሙን ሊያጣጥም
ምላስ ሲፈረጥም፣


እፀበሉ ግርጌ
ነጠላ አደግድጌ፣

ስለቴን ላስገባ
በእግዜሩ ሙሀባ፣

መጣሁ ከአድባርሽ
እቤተስኪያን ቅጥርሽ፣


የኔ እንዲያ መዋተት
ደርሶ መንከራተት፣

የኔ እንዲያ መውተረተር
ካንቺ ለመሰተር።


እነሆ አካሏን ጎብኝቶ ጠረኗን በምናቡ ምጎ ካጣጣመ በኃላ በዕውኑ አለም ፍለጋውን ማነፍነፉን ቀጠለ።


አንቺ ሆዬ ወዴት አለሽ?


ቅዱስ አርዮስ
🌗
የግማሽ ዓለም ጣኦት🌗

።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
ከትቢያ ፥ ተጣብቆ ፥ እንዳል ፥ ነበር ክፉም : ደግም : ሀሳብ : በንፋስ : መልክ : ሽ'ው : ያለው። የቱማታው: ማርፊያውን : እንጃ እየተግተለተለ: ይላወሳል። መፃዕጉነቱ : ቢጠናበት ቀን ቆጥራ : ጅመረ። አዎ ቀኑ #19 ነው የአመቱ ገብርኤል ፥ የባለ : ቀኑን ስም ፍቺ መሰነጣጠቁን : ተያያዘው።

ገ ብ ር ኤ ል

አምላክ ሰው ሆነ
ሰው እምላክ ሆነ

በሚል ፥ ፍቺ ፥ ተዋህዶን ፥ እፀናት!

የዛር በቆሎ : እንደተጠናወተው : የግንባሩንም : ስጋ መሽሽግ አልፈለገም።የግማሽ ዓለም ጣኦትነቱን : አምኖ ከተቀበል : መክሩሙም አደል....

በገሚስ : ብርሀን :የሞላው : የእዕምሮው ክፍል : የባለ ቀኑን: ስም : ከነፍቺው መርምሮ : አወቀ : አውቆም ፣ ተደሰተ
ተደስቶም ፣ ከልቡ አመሰገነ።

የቀረው : ገሚሱ : ጨለምተኝነት ከእሱ ዘንድ : ተጣብቶት : ነበርና :ሀኔታው አልዋጥለት : ተብሎ : ነገር ይፈለፍል ፣ ይሰንጣጥቅ: ጀመር።

እንዴት ሰው አምላክ ሆን?

ጠየቀ......

ጥያቄውንም : በጥርጣሬ: አፀናው!!

በቀን : ከ 5 ግዜ በላይ :መርዛማ ፈሳሹን ልምትፋት እንደ ኮብራ : እባብ እንገት : የሚገትር: መቀንዘሪያው ልጓም : ሲበጥስ : ተመለከተው።

ጌታም : ሰው : በነበረበት : ግዜ ይህ ነገር : ገጥሞት : እንደነበር : አሰበ
:ባሰበበባት : ቅፅብትም : መብርቅ: ከምድረ: ገፅ መቶት አጠፋው።


ያኔም እግዜሩ ከላይ ሆኖ ከልቡ ሳቀ¡

የዛ መፃዕጉ ነፍስ የት ገብታ ይሆን?


🦋 ቅዱስ አርዮስ
🌗የግማሽ ዓለም ጣኦት🌗

።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 t.me/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 t.me/sufafel 🦋🦋
.
.
ለተሻለ ጊዜ ተስፋ ማድረግ በአሁኑ ጊዜ ላይ የሆነ ነገር ማድረግ እንጂ ስሜት መሆን የለበትም።

✍️Vincent Van Gogh, The Letter of Vicent Van Gogh to Theo Van Gogh (1883)

join join join
👇👇👇👇👇👇👇
👉 t.me/YelbeDrset 👈
👉 t.me/YelbeDrset 👈
👉 t.me/YelbeDrset 👈


ከምንጭሽ ውሀ ስር
ለመቅዳት ስታትር፣

አንገቴ ሲል ዘንበል
በደጃፍሽ በኩል፣

ተጠምቼ ስግት
የተፈጥሮን ፍንክት፣


ሰው ሆኖ ሰው መስራት
ነፍሴን ከስጋዬ ነጥለሽ ሰወርሻት።


አወይ መታደልሽ!!

ቅዱስ አርዮስ
🌗የግማሽ ዓለም ጣኦት🌗

።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 t.me/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 t.me/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 t.me/sufafel 🦋🦋
ፍለጋ ዝምተኛው ሲርሎስ
<unknown>
#ፍለጋ

ገጣሚ ሮቤል አለማየው
ዝምተኛው_ሲርሎስ


#አንባቢ
🌗የግማሽ ዓለም ጣኦት🌗

።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋
t.me/sufafel 🦋🦋
🦋🦋
t.me/sufafel 🦋🦋
🦋🦋
t.me/sufafel 🦋🦋
ቆይ ግን አንተ ማን ነህ?


የማንነት ጥያቄው እየተመላለሰ ሲያቃጭልበት ለፌ ወለፌ ወመሆኑን ለመንገር በግድ ጆሮው ላይ ተለጥፈው ሲያንሾካሹን ግንርታቸው እያስተጋባ ሲሰማው ያስጨንቀዋል።

ወደዚች በከቻ አለም ፈልጎ እንዳልመጣ ሁሉ ተፈልጎ እንደሚሄድ ለማሳበቅ አፋቸውን ያሾሉ እልፍ የኢብሊስ ወዳጆች አሉ የሁካታቸው ማፍገምገም
የሲቃቸው ሲርሲርታ ለሱ ጥዑም የነፍስ ምግብ ሆኖታል

ነፍሳት ሲቃጠሉና ግግር በረዶ ሰርተው በቁማቸው ጋንድያ ሲሆኑ የሚደሰተው
ሰይጣን ሁሉንም ነፍሳት ተራ በተራ መቅጣቱን ተያይዞታል

እሱም ተራው ደርሶት ግግር በረዶ ውስጥ ነፍሱን ተጣለች

የሲኦልን ሙቀትና ቅዝቃዜ ጠንቅቆ ያውቅ ነበርና ስቃዩ ሲበዛበት ከሲኦል ለማምለጥ መላ ይዘይድ ጀመር

ከብዙ ጥረትና ልፋት በኃላ ልጁ ከሲኦል ታወጣኛለች ያላትን ሻማ ሰራ
በድቅድቁ ጨለማ በሻማይቱ ብርሀንነት ሶስት እርምጃዎችን ወደፊት ተራመደ
ነገር ግን ጨለማውን ተገን አድርገው የከበቡት ብዙ ነፍሳቶች አሰፍስፈው ነበር ሻማይቷን ሊቀሙት

የተጨነቀች ነፍስ .....

ሻማይቱን ለቀቃት...

ሻማዋንም ለመያዝ እልፍ ነፍሶች ተራኮቱ
ተሻሙባት

እሱግን ሊሻማባት ሊሻቀጥባት አልፈቅድምና አፈገፈገ...
ወደ መጨረሻው ጨለማ ወደሚባለው የሲኦል ክፍል ራሱን አሽቀንጥሮ ጣለ



ከወደቀበት ሲነሳም ሰይጣኑ ለእግዜር ፀሎት የሚያደርስበት የገነት መስኮት ታየችው ወደ መስኮቷ ተጠጋ

"እግዚአብሄር እረኛዬ ነው
በለመለመች መስክ ያሳድረኛል"

የሚለው ፀሎት እውነት መሆኑን አመነ
ያመነውም ሲኦል ውስጥ ሆኖ ነው ያውም ሰይጣኑና እግዜሩ በሚገናኙበት በመስኮታቸው ቀዳዳ ተመልክቶ

ወቅቱ ፀደይ ነበርና የገነት ደጃፎች በአደይ አበባ ተንቆጥቁጠዋል

ወደ አበቦቹ አማተር
ከአበቦቹ መሀል ግን አይኑ ውስጥ የገቡት ስራቸው አንድ ቅርንጫፋቸው ለየቅል የሆኑትን ዕቡጦች ላይ አይኑ ተተክሎ ቀረ

ያለመታደል እጣ ፈንታዋ ሆነና አንድኛዋ መንታይቱ አበባ ከሰመች

በመክሰሟ ልጁ አዘነ

አንዷ አበባ አበበች
አንድኛዋ ከሰመች

እነሆ ርግብም በአክናፏ አየሩን ቀዝፋ መታ የቆረችጠውን አበባ በማንቁሯ ቀጠፈቻት ቀጥፋትም እሱ ሲኦል ውስጥ ሆኖ በሚያያት መስኮት በኩል በራ አረፈች። በማንቁሯ የያዘችውን አበባ እንዲቀበላት አንገቷን ወሱ ስክክ አድርጋ በተቀመለኝ አይነት ልምምጥ አይን አይኑን ታየዋለች

ይቀበላት ይሆን?

የኑሮን ውትፍትፍ ቀዳዳ መሙላት ባይችል እንኳን ሊሞላ የሚችል ደንዳና ጫንቃ እንዳለው ያወቀችው

ግን እሷ ማን ናት?

ሻማይቱ?
መንትያ አበቦቹ?
ወይስ ርግቢቱ?


✍️ቅዱስ አርዮስ✍️
🌗የግማሽ ዓለም ጣኦት🌗

🌗የግማሽ ዓለም ጣኦት🌗

።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 t.me/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 t.me/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 t.me/sufafel 🦋🦋
ደሞ እንኩ አጭሬ ግጥም!!!

ረድኤት

።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 t.me/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 t.me/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 t.me/sufafel 🦋🦋

እናት ስትረገም
በምጥ በሲቃ ደም፣


የርግማኗ ፍሬ
ከሷ ተፈጥሬ፣


ሌላ ዘር እሻለው...


ዘውትር መፀፀት
በዛች ባንዲቴ ቅፅበት
እናቴ የሳተች ለት።


ሳል'ፈለግ መጣሁ....


መንገድ ልያዝ ደሞ


ጉዞ በጨለማ
ከሱ እኔ ልስማማ።


እ ና ማ....







ሲጥ!!


✍️ ቅዱስ አርዮስ✍️
🌗የግማሽ ዓለም ጣኦት🌗

።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 t.me/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 t.me/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 t.me/sufafel 🦋🦋
ወፈፍታ


አንድም ወፍ አንድምታ
የአክናፍ ከፍታ፣
የቃል ሽሙንምታ
ሽልብ ሽልብታ፣
ቀልብን የሚሰውር
በጥበብ እርካታ፣

አካልን የሚሰልብ
ሰላቢ ወፈፍታ።

አንድም ወፍ
አንድምታ
እፍ'ታ ወፈፍታ።



✍️ቅዱስ አርዮስ✍️
🌗የግማሽ ዓለም ጣኦት🌗



👇👇👇👇
🦋🦋 @sufafel 🦋🦋
🦋🦋 @sufafel 🦋🦋
🦋🦋 @sufafel 🦋🦋
🌿❤️እንዴት አደርሽ🌿
Yohannes_Lawgaw ስለ እኔ @sleenee Yohannes Lawgaw sle enee
🌿ዛሬ ማለዳ በዛሬ ህይወት ሰላም በሆነች ንጋት.. እልፍ #ተስፋ ባለባት...🕊🌿ያንቺ እንደሆንኩ ነቅቻለሁ ♥️ እንዴት አደርሽ🌿
🌿#Morning_Queen #ጠዋት_ስትነቂ #ማለዳ #ፀሀይ
#ስጦታዬ #ፍቅር #ዕለተ_እሁድ

።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 t.me/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 t.me/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 t.me/sufafel 🦋🦋
ሰላም ሰላም ወዳጆች በልዩ መልኩ በሚድያ ልንመጣ ዝግጅታችንን ጨርሰናል ሰብስክራይብ በማድረግ እንድትከተሉን ጋበዝን 😍🙏

https://youtube.com/channel/UCoYix1CBO2zTpdEbrF1D7Ow
ፀሎቴን ባሰማ ፥ እንደሰው ዝም አለኝ
እሱንም ዘመቻ ፥ ወሰዱት መሰለኝ
.......
የእቴሜቴ ጀምበር
©ሲራክ ወንድሙ
.
እረኛ አይዘምርም ፥ ዝም ነው አድባሩ
ፋኖስ ክሩን አጥቷል ፥ መሸ ደህና እደሩ
ቡሬ መንደር ራቃት ፥ የለችም ከቤቷ
በሌት አልዘመረች ፥ ከፍቷታል ወፊቷ
ማልዶ ሌት ሚያነቃኝ ፥ ዶሮ በጉድ ወጣ
የሌት ድምፁን ሸጦ ፥ መውዜር ይዞ መጣ
ወዲያም ወደ ሰማይ
ከጎጆዬ በላይ
ፀሎቴን ባሰማ እንደሰው ዝም አለኝ
እሱንም ዘመቻ ወሰዱት መሰለኝ
.
የዛች የእዝነት አርማ ፥ የህዋ ላይ ሰንደቅ
እንዴት ቀን ከፍቶባት ፥ ውብ ጀምበሯ ትጥለቅ
ከዛች ከገራገር ፥ ከደጊቱ ዳሴ
እንደምን ብርቅ ይሁን ፥ ሰላም ለእለት ጉርሴ
ኧረ እንደምን በምን
ኧረ እንደምን በምን
አምነን ያነገስነው ብራ ቀን ይዳምን
እኔን አፈር ይብላኝ ፥ ለእኔ ቀኑ ይክፋ
አንቺን ያሳጣችሽ ፥ ያች አለም ትደፋ
እስከ መች አስከ መች ፥ የአረር ሙዳይ ቋጥረን
እንደጃኖ ኩታ ፥ ዝናር ጥለት አርገን
ሀገር እያጠፋን ፥ ያልፋል እንላለን ?
እንዴት ነው መሰንበት ?
መውዜር እንደነዶ በሚመዘዝበት?
ኧረ እንደምን በምን
ኧረ እንደምን በምን
አምነን ያነገስነው ብራ ቀን ይዳምን?
.
ከጩኸትሽ ማዶ ፥ ካኮረፈው ሰማይ
ቄራ ከመሰለው ፥ ከአድማስሽ ሸራ ላይ
እብሪት ያጠላበት ፥ ምስል ድንገት ካየው
ለቸር አንመስለኝም ፥ ያን ጊዜ ፈራለሁ
አርብ አርቡን አመሻሽ
የሰማዩ ገላ ሲመስል የደም ሻሽ
ንትብ የለበሰ
ከወደ አንገቱ ዘሞ የተዘለሰ
ይሁዳሽን ባላይ ፥ ወድቆ ሲያንሰራራ
መስቀል ሆኗል ለሻጭ ፥ ገዢ ራሱን ያኩራ
ከክርስቶስ ይልቅ ፥ ይሁዳ ነውና ሚረከብ መከራ
ምክኒያቱም ......
ዘመን እያሰፉ
ትውልድ ለሚነቅፉ
ነገር ጠንቷል ዛሬ ፥ አውቀውት ይረፉ
ለሻጭ መስቀል ሊሆን ፥ ምሏልና ዛፉ
.
በኑረት ቀራንዮ ፥ በህይወት ጎለጎታ
ከገዳይሽ ቀዬ ፥ አንቺ ሆነሽ ጌታ
በሰማያ አኮርባጅ ፥ ወዲያ ስትላጊ
የመከራን መስቀል በሌት ተሸክመሽ ፥ መንገድ ስትፈልጊ
ጨረቃዋ ገባች ፥ ከደመና ጉያ
ከዋክቶች ሸሽተው ፥ እንደሰደድ ቋያ
ጠረንሽን ገፍተው ፥ ከገላሽ ሲርቁ
በንቄት ሸምቀው ፥ ሊጥሉሽ ዘለቁ
.
ዞር ብንል ወዲያ ፥ አራራይ መረዋ
ቀና ብንል ኦና ፥ የጠቆረ ህዋ
የፀሎትሽ ጩኸት ፥ ካልደረሰው ያ ' ቃል
እሱም እንደሰዉ ዘምቶልሽ ይሆናል።
..................... //// ..............
©ሲራክ ወንድሙ @siraaq
የእቴሜቴ ጀምበር
ህዳር ፳፻፲፬ ዓ.ም
http://t.me/kinchebchabi
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ
.
.
#ግዕዝ_ክብር_ይእቲ
#ዘዘዮሐንስ (አለቃ)

መፈወስ ነፍስ ወይነ ለምንት ኢተኃሥሢ?
ዘታፈቅሪ ነፍስየጨቤተ መያሲ ትጊሢ
ወእንዘ ታነብቢ ዘልፈ ምዕዳነ ዳዊት ነጋሢ
እም እኩይ ግብር ለምንት ኢትትጋኀሢ?
.
.
.
ጠዋት በማለዳ
ወደ ጠጅ አደይ ቤት
የምትገሰግሺ አንቺ የኔ ነፍስ ሆይ!
ከጠጅ የተሻለ
ሕይወት የተሞላ ጥበብ የተሞላ
የሚፈዉስ ወይንን ለምን አትፈልጊም እሱ አይሻልም ወይ?
አዉቃለሁ ታዉቂያለሽ
የንጉስ ዳዊትን
ቅኔዉን ምክሩን ዞትር ታነቢያለሽ
ዞትር ትደግሚያለሽ።
ነገር ግን በተግባር
ወይንን ተጸይፈሽ እዛው ጠጅ ቤት ነሽ
ከማለዳ አንስቶ ጀንበር እስክትሸሽ።
ታዲያ!
ከቶ ምን ዋጋ አለው ቢያዉቁ ቢራቀቁ
ከመፅሐፍ ዉቂያኖስ ጫፍ ድረስ ቢጠልቁ
በሕይወት ካልታየ
የዕዉቀት ወሰኑ የዳዊት ድጋሙ
ጸሎትና ዕዉቀትሽ
ያለ'ካል የሚታይ ረጅም ጥላን ነው ሚሆነው ትርጉሙ
እባክሽ ነፍሴ ሆይ?

✍️ዉርስ ትርጉም
#በኤፍሬም_ሥዩም_ተሰማ

📚ምንጭ #ተዋነይ_ብሉይ_የግዕዝ_ቅኔያት_ፍልስፍና_ከቀደምት_የኢትዮጵያ_ነገሥታት_እና_ሊቃዉንት

join join join join
👇👇👇👇👇
@YelbeDrset
@YelbeDrset
@YelbeDrset
👆👆👆👆👆
📚📚📚📚📚📚📚📚
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ
.
.
"..አመታት ከሚመስሉ ወር ከማይሞሉ ቀናት በኋላ አየኋት፣ ቀረብኳት፣ የምትተነፍሰዉን አየር እኩል ተነፈስኩኝ፣ ደግሞ እጆቿን ያዝኩ በስስት ተሳለምኩ አክየም አቀፍኳት ትንፋሽ እስከሚያጥራት ከንፈሯን ጎረስኩኝ አንገቷ ስር ገባሁ ጠረኗ አወደኝ! ሰከርኩ! ሰከርኩ! ሰከረኩ! ይባስ ናፈቀችኝ!..ከጎኔ እንዳትርቅ ካይኔ ሰር እንድትኖር ቃልኪዳን አሰብኩኝ..አስቤ አልቀርም..!!

✍️Aman😑 YTZ
@amanYTZ23

join join join join
👇👇👇👇👇
@YelbeDrset
@YelbeDrset
@YelbeDrset
👆👆👆👆👆
📚📚📚📚📚📚📚📚