ቅንጭብጭብ
7.25K subscribers
410 photos
9 videos
3 files
498 links
ካየሁት 👀 አስገራሚ
ከሠማሁት 👂 መሣጭ
ካነበብኩት 📖 አስተማሪ
ካሠብኩት ♀🅱 ልዩ ልዩ

እነሆ #ቅንጫቢ

ፅሁፎቻችሁን በ @bcrAzykid አካፍሉን።

ለማንኛውም አስተያየት ጥያቄ እና ጥቆማ @bcrAzykid ይጠቀሙ።
Download Telegram
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

#ፍቅር ማለት ውበት አይደለም፤ ጥቅም ፍለጋም አይደለም፤ ዝሙት ፍለጋ የስሜት መወጫም አይደለም፤ ፍቅር ማለት በደስታ ጊዜ መተቃቀፍም አይምሠልህ፤ ፍቅር አንዱ ስለወደደን መውደድ አይደለም፤ ፍቅር ማለት ስላከበረን ማክበር አይደለም፤ ፍቅር ማለት ስላገዘን አንተም ቀን ጠብቀህ ብድር መመለስ አይደለም!

#ፍቅር ማለት ከማንነት የፀዳ፤ ከማዳላት የራቀ ፣ከመፍረድ እጅን ያወጣ በመከራም፣ በሀዘንም፣ በጭንቀትም፣ በደስታም፣ መተሳሰብ፣ መተጋገዝ፣ መረዳዳት አንተ ያላገኘውን ነገር ሌሎች እንዲያገኙ መመኘት፣ ጠላትህን መውደድ፣ስለወንድምህ እራስህን አሳልፈህ መስጠት የወንድምህን በደል መሸከም ባንተ እንዲፈፀም የማትፈልገውን በሌላ አትፈፅም የአገሬ ሰው "በቆፈረው ጉድጓድ እራሱ ገባበት" እንዳለው ተመልሶ በራስህ መፈፀሙ አይቀርምና መልካም ሁን መልካም አድርግ... መልካምነት መልሶ ይከፍልሃል።

For any comment & suggestion @BcrAzykid

Join us
@kinchebchabi @kinchebchabi
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ
#ፍቅር

እውነተኛ ፍቅር ግዜውን ጠብቆ እራሱ ይመጣል
እውነተኛ ፍቅር ትእግስትኛ ነው
እውነተኛ ፍቅር ይቅር ባይ ነው
እውነተኛ ፍቅር በደልን አይቆጥርም፣
እውነተኛ ፍቅር ሩሩህ ነው፣
እውነተኛ ፍቅር በቀልን አያውቅም
እውነተኛ ፍቅር እግዚአብሔርን ያከብራል፣
እውነተኛ ፍቅር በግድ ተፈልጎ አይገኝም፣
እውነተኛ ፍቅር ዘርን አይቆጥርም
እውነተኛ ፍቅር መደበቅ አይቻልም፣
እውነተኛ ፍቅር ማንንም ከማንም ምንጠቅ አይችልም፣
እዉነተኛ ፍቅር የራሡን እውነት እንጂ የሌሎችን እውነት
አይከተልም፣
እውነተኛ ፍቅር ስራው ፍቅር ብቻ ነው፣
እውነተኛ ፍቅር በሰጠው ፍቅር ልክ ምላሽ አይጠብቅም፣
እውነተኛ ፍቅር ዘር ቀለም ሀይማኖት አይቆጥርም፣
እውነተኛ ፍቅር በውስጣዊ ማንነት እንጂ በፊት ገፅታ
አያምንም፣
እውነተኛ ፍቅር ክብሩን አሳልፎ ለሌሎች ይሰጣል፣
እንጂ ስለ ክብሩና ስለ ዝናው አይጨነቅም፣
እውነተኛ ፍቅር በማግኘት ውስጥ አይቀያየርም፣
እውነተኛ ፍቅር ከስር መሰረት አብሮ ያድጋል እንጂ ለጥቅም
አይጠጋም ፍፁም አይደለም ግን ፍቅሩ እውነተኛ ከሆነ የትኛውንም ፈተና ማለፍ ይችላል።

ፍቅር ያብዛልን ❤️ ለወዳጅ ሼር ይደረጋል

Join.us
@kinchebchabi @kinchebchabi
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ
🌹 #ፍቅር

ሰዎችን ሳይወዱን መውደዱ አናውቅበትም፤ ብናውቅበት
እንኳን ሞኝነት ይመስለናል።

ሰዎች ይቅር ሳይሉን ይቅር ማለቱን አንችልበትም፤ ብንችልበት እንኳን የተበለጥን ይመስለናል።

ሰዎች ሳያከብሩን ማክበሩን አንችልበትም፤ ብንችልበት እንኳን የተዋረድን ይመስለናል።

ሰዎች ካልረዱን መርዳት አንችልበትም፤ ብንችልበት እንኳን የዋህ የሆንን ይመስለናል።

ለምናደርገው ነገር ሁሉ ምላሽ
እንሻለን፤ ለፍቅራችን፤ ለደግነታችን፤ ለይቅርታችን፤ ለክብራችን ምላሽ ካልተሰጠን ደስተኞች አይደለንም።

ለዚህ ነው ኩርፊያ እና ቂም በትንሽ በትልቁ ብቅ የሚሉት። "እኔ እንዲህ አድርጌለት"
"እኔ ለሱ ጊዜ እንዲህ ነበርኩኝ?"
"ለእኔ የሚገባኝ ይህ ነው?" እያልን የገዛ ደስታችንን የምናጠፋው ያለምላሽ ማፍቀር፤ ያለ ምላሽ ማድረግ ስላለመድን ነው። ስንሰጥ ምላሽ ካልጠብቅን ሰዎች ክፉ ቢሆኑብን ግር አይለንም።
ስንወድ ለመወደድ ብለን ካልሆነ፤ ፍቅራችን ሲገፋ አይከፋንም። ስንረዳ ለክፉ ቀናችን ብለን ካልሆነ፤ ሰዎች እርዳታቸውን ሲነፍጉን አይደንቀንም። የምናደርገው ነገር ሁሉ ከልባችን ሲሆን፤ ደስታችን ሌሎች በሚሰጡን ምላሽ ላይ አይወሰንም።

#ፍሬ_ሃሳብ
ፍቅር ማለት መስጠት እንጂ መልስ ጠብቆ መስጠት አይደለም!

For any comment n suggestion @bcrazykid

Join.us
@kinchebchabi @kinchebchabi
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ
#ፍቅር

ማፍቀር እኮ ኀጥያት አይደለም። ነገር ግን በፍቅር ስም በሰው ስሜት ላይ መጫወት ትልቅ ኀጥያት ነው።

#ወዳጄ
እውነተኛ ፍቅር እኮ ለምትወደው ሰው ምንም ሳትሰስት እራስህን
አሳልፈህ መስጠት እንጂይ በማስመሰል ተጀምሮ በጥላቻ
የሚደመደም አይደለም ። ምክንያቱም እውነተኛ ፍቅር ስሜት
ሳይሆን ዘልአለማዊ መተሳሰብ ነው ።
የእውነት ፍቅር ነው!!
ቃላቶችን ሳይመርጥ ዝም ሲል አንደበት
በአይን እየተያዩ ፍቅርን በአይን ማውራት
በፍቅር መግባባት በአንድ ቋንቋ አውርቶ
ልብ ሲገጣጠም በፍቅር ተረቶ
በአካል ሲራራቁ በሀሳብ አንድ ሆነው
ከጎኑ ባይኖርም አንዱ አንዱን ሲያስበው
አይኖች ተጨፍነው ስእል እየሳሉ
ልብ የወደደውን ሲያዩ በስእሉ
አንዱ በሌላው ልብ ነግሶ ሲኖርበት
ያለውን ሲሰጠው ለፍቅሩ ሳይሰስት
ደስታና ሀዘኑን በማየት ሲረዳው
ከጎኑ ሳይጠፋ ደስታውን ሲያበዛው
አንደበቱን ሳይሆን ልቡን ሲሰጠው
በእውነት የተሞላ የእውነት ፍቅር ነው!!

Join.us
@kinchebchabi @kinchebchabi
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጲያ

ከዚህ ቀደም እንዳደረግነው ከሀምሌ 11.2010 ጀምሮ << #ፍቅር_እሽሩሩ >> የሚል አጭር የፍቅር ልቦለድ በተከታታይ ለእናንተ የምናደርስ ይሆናል፡፡

🙏🙏አብሮነታችሁ አይለየን🙏🙏

join us🙏

@kinchebchabi
@kinchebchabi
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጲያ

___ #ፍቅር_እሽሩሩ

<<< ክፍል_አንድ>>>

መቼም ታሪኬን ስነግራችሁ ጉደኛ ነሽ ሳትሉኝ አትቀሩም፡፡ አሊያም በየቤታችሁ የተለያየ ስም እያወጣችሁልኝ የቡና ማጣጫ ታደርጉኝ ይሆናል፡፡ ቢሆንስ ምን ቸገረኝ! እኔ እንደሆነ አልሰማው << ጆሮ ለባለቤቱ ባዳ ነው>>እንዲሉ፡፡ ለማንኛውም እስቲ አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ ለመሆኑ ሴት ልጅ የአንድን ሰው መልክና ቁመና ሳትገመግም ቢያንስ ቢያንስ ለአንድ ቀን እንኳ ከቅርብም ሆነ ከሩቅ አይታ ለማታውቀው ሰው በድምፁ ብቻ ፍቅር ይይዛታል? ያውም በስልክ ትውውቅ ብቻ? እኔንጃ! የምትሉኝን በሉኝ እንጂ እኔ ግን በድምፁ ብቻ ወድጄው ነብሴ ልትወጣለት ነበር፡፡

ዛሬን ሳስበው ጨርቄንም አለመጣሌ እኔ በመሆኔ ሳይሆን ይቀራል እላለው
እንዴት እንደተዋወቅንም ለካ አልነገርኳችሁም አቤት! የኔ ቀልብ እንግዲህ ይኸውላችሁ
ሁሌ ከትምህርት ቤት መልስ ሱቅ ነው ማመሸው <እርሶም ይሞክሩት> እንደሚባለው የግቢያችን አጥር ሸንቁረን የገነባናት አነስተኛ የትርኪሚኪ መሸጫ ሱቅ ናት፡፡ ለዕለት ፍጆታ የሚሆኑ እቃዋችን ከመሸጥ ሌላ የዋናውን ቤት ስልክም አስረዝመን እናከራያለን፡፡
አንድ ቀን ታድያ ከት/ቤት ተመልሼ ሱቅ ቁጭ ብዬ ሳለሁ ስልኩ አቃጨለ ከማንሳቴ በፊት ማን ሊደውል እንደሚችል ገመትኩ 'ማን ልትሆን ትችላለች?' እያልኩ ሳስብ ስልኩ ደጋግሞ ጥሪውን አሰማ 'እንደውም ፍቅርተ መሆን አለባት' አልኩ በርግጠኝነት ቅድም ተቀጣጥረን ስለነበር በ8 ሰዐት እመጣለሁ ብላኝ ስለነበር አሁን እንግዲህ የሆነ ሰበብ ፈጥራ "አይመቸኝም" ልትለኝ ነው አይደል ይቺ ሞዛዛ እውነትም እየሩስ አይደለሁም ጆሮዋ ላይ ባልዘጋባት በማለት ፎክሬ ስልኩን አነሳሁና
"ሄሎ" አልኩ ቆጣ ብዬ
መልስ የለም ትንሽ ጠበኩና ደግሜ "ሃሎ" ስል መልስ አገኘሁ፡፡
"እየሩስ ነሽ?" የሚል ቀጠን ያለ ወንድ ድምፅ በጆሮዬ ስንቅር አለብኝ.......

@kinchebchabi
@kinchebchabi
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

_ #ፍቅር_እሽሩሩ

<<ክፍል_ሁለት>>

ማን ይሆን ብዬ በመገረም "አቤት ማን ልበል?" አልኩ ለስለስ ባለ ድምፅ
"ይቅርታ እየሩስ አንቺ እንኳ ምታቂኝ አይመስለኝም መተዋወቁ አይከፋምና ጎሹ ጠና እባላለሁ" አለ ያው ድምፅ ቁርጥ ቁርጥ ባለ ትንፋሽ
ድምፁ ልብን ሰብሮ የሚገባ ስውር ሀይል ያለው ይመስላል
"አየሽ እየሩስ አንቺ ባታውቂኝም እኔ በደንብ አውቅሻለሁ ዘወትር አንቺን ለማየት በሱቃችሁ ሳልፍ ሳገድም ነው የምውለው እናም አንቺን ማወቅ ብቻ አይደለም አመልክብሻለሁ፡፡ እንደጓደኞቼ 'አባቴ ይሙት'ብዬ ሳይሆን 'እየሩስ ትሙት' ብዬ መማል ከጀመርኩ ሰነባብቻለሁ፡፡" አላስጨረስኩትም
"ለመሆኑ አንተ ማነህና ነው በኔ የምትምለው? ስልክ ቁጥሬንስ ማነው የሰጠህ!" አልኩት የምናገረው ቢጠፋኝ ለወጉ ያህል ስልክ ቁጥሬን ጠየኩት እንጂ ስልካችን እንደሆነ የህዝብ ከሆነ ቆይቷል
"እየሩስዬ ረጋ ብለሽ ብታዳምጪኝ እኮ ....."ብሎ የጀመረውን ሳይጨርስ አሁንም አቋረጥኩት
"እንድታቆላምጠኝ ደግሞ አልፈልግም" አልኩ ቆጣ ባለ ድምፅ
"ይቅርታ የኔ እመቤት ማቆላመጡም ቢሆን የመውደዴ ፅናት የሚገልፅ ይመስለኛል "አለ ቀዝቀዝ ባለ አነጋገር
እኔ ቆጣ ብዬ በተናገርኩ ቁጥር የሱ ረጋና ለስለስ ማለት ይበልጥ አበሸቀኝና
"እና ምን ይሁን ነው ምትለው?" አልኩት በለበጣ
"የሚሆነውን እንድነግርሽ መጀመሪያ ማቆላመጡን ፍቀጂልኛ"
"ማቆላመጡን ትተህ የደወልክበትን ምክንያት መናገር አትችልም?"
"ካላቆላመጥኩሽ ደስ ስለማይለኝ እኳ ነው የኔ እመቤት....."
"አዝናለሁ ስልኩን ልዘጋው ነው.."
"ምን ቦጣሽ ታዝኛለሽ ጠላትሽ ይዘን እንጂ" ካለ በኋላ
"ይልቅ ማቆላመጡን ብትፈቅጅልኝ ምናለ? ስትለመኚ አይገባሽም እንዴ" አለ በሚያባብል ድምፀት
"የኔ ወንድም ይቅርታ አድርግልኝና ስልኩን መዝጋቴ ነው"
"ምን አደከመሽ መልሼ መደወሌ አይቀር"
"ማን ላከብኝ ባካችሁ?" አልኩኝ የአግራሞት ሳቅ እየሳኩኝ
እያንዳንዱ ቃሎቹ የፍቅርን ሚስጥር አዝሎ ከደም ስር ጋር የሚቀላቀል ይመስላል፡፡ መለሳለሴ ገብቶኛል፡፡ መሸነፌንም ተረድቻለሁ፡፡ ጉደኛ ድምፁን ልቤ ቢፈቅደውም ቶሎ እጄን ለመስጠት ግን አልደፈርኩም ለትንሽ ጊዜም ቢሆን ማፈግፈጉን መረጥኩ፡፡
ለካ ልብና አንደበት ምስጥራዊ ግንኙነት አላቸው፡፡ ዘራፍ ሲል የነበረው አንደቤቴ መለሳለሱ ገርሞኝ ነው! ያ ሁሉ ቁጣ ቀረና
"ምናለ ማቆላመጡ ትተህ ብትነግረኝ" አልኩት
"ምናለ አንቺስ ብትፈቅጂልኝ"
"በስመዐብ እቴ ምን አይነቱ ደረቅ ነህ ባክህ?"
"አንቺስ ምን አይነቷ እምቢተኛ ነሽ ባክሽ?"
"አረ ባክህ"
"በቃ እያቆላመጥኩ ላጫውትሽ አይደል?" አለኝ ሙትት ብሎ
እንዴት ልቻለው ታድያ? የትኛው ልቤስ በአሻፈርኝነት ይፅና? እምቢታስ እንዴት ከአንደቤቴ እንዴት ላውጣው? ምን አለፋችሁ ባንዳፍታ በድምፁ ብቻ የልቤን ጓዳ አተረማመሳት፡፡
"እሺ በል ንገረኝ" በእንቢታ መልሴ ተከፍቶ ስልኩን እንዳይዘጋው ብዬ በመስጋት፡፡

#___ይቀጥላል

@kinchebchabi
@kinchebchabi
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

#ፍቅር
ፍቅር የደስታ ሁሉ ንጉስ ነው፤
ፍቅር የህይወት መስረት ነው፤
ፍቅር የአዕምሮ ዕረፍት ነው፤
ፍቅር የደስታዎች ሁሉ ምንጭ ነው፤
ፍቅር የመንፈስ እርካታ ነው፡፡

💝💖❤️❤️💜❤️❤️💖💝

Join.us
@kinchebchabi @kinchebchabi
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ
.
"ፍቅር እዚህ ቦታ ፈገግ ብሎ ነበር"

(ኤፍሬም ስዩም)

ያሳለፍነዉ ሁሉ
አሁን ትዝታ እንጂ
ዉስጡ ህይወት የለም እያልሽ ላገሩ
ታወሪያለሽ አሉ
.
.
(እኔ ግን ልንገርሽ)
የሁለታችን ፍቅር
ምን እንደሚመስል. . .
እንዴት እንደነበር
በሶስት ምስክር
1
አሁን በቀደም ለት
የሆነ ቦታ ላይ
ድምጻችን ከፍ አርገን የሳቅንበት ቦታ
ፒያሳ አደባባይ
ድንገት
በቀደም ለት
በዛ ቦታ ስሄድ
ከሰባት ወር በፊት
ስቀሽ የነበረዉ
ያንቺ ሳቅ ተሰማኝ
መራመድ አቃተኝ
የሚገርምሽ ነገር
ያለፈ ነዉ ያልሺዉ
ትዝታ ነዉ ያልሽዉ
ፍቅርሽና ሳቅሽ
ከሰባት ወር ኋላ እንደ ወንዝ ፍሳሽ
ይሰማል ልንገርሽ
.
(ታዲያ ለምንድን ነዉ)
የወንዝ ዉሀ ሳቅሽ
ያለፈ ትዝታ ምናምን ነዉ ብሎ
ማንም ተራ ዘፋኝ የሚሸነግልሽ
(ይልቅ እኔን ስሚኝ)
.
ወደየትም ሳይሆን
ወዴትም ተመለሽ
የትም ሳትደርሺ
ጊዜን እንዳቆምነዉ
እንኳን ጊዜ ቀርቶ ሰዓት እንዳልሄደ
ደቂቃ እንዳልሄደ
አስረጂ ሊሆንሽ
ምስክር ሊሆንሽ
ከምንም አቅጣጫ. . . የትም ሳትመለሽ
አደባባይ መሀል
ከቡና ጠረን ጋር
እንደወንዝ የሚፈስ
ሳቅሽን ትሰሚያለሽ
.
2
ትዝ ይልሽ እንደሆን
ካንቺ መኖሪያ ቤት
(የመጣሁኝ ጊዜ)
የመራራቅ ናፍቆት
አስክሮን ቸኩለን
ሰማያት ለመዝለቅ
ከመሬት ላይ ወድቀን
ፍቅር ስንሰራ
ፍቅር ስንሰራ
ፍቅር ስንሰራ
ከሴት ወዝሽ ጋራ
የጡትሽ ስር ሽቶ
ሸሚዜ ላይ ቀርቶ
ሸሚዜ ላይ ቀርቶ
ምወደዉን ሸሚዝ
ለመልበስ እርም አልኩኝ
ለብሼዉ እንዳልሄድ
ከበደኝ ጨነቀኝ
ያንቺን ጠረን ማጠብ. . .
ነፍስ የማጥፋት ያህል
ሀጥያት መስሎ ታየኝ
(የሚገርምሽ ነገር)
እስከ ዛሬ ድረስ
በመስኮቱ ዘልቆ. . .በበሬ
የሚወጣዉ የማለዳዉ ነፋስ
በሽቶሽ ጠረን ነዉ መንደሩን የሚብስ
.
3
ታስታዉሽ እንደሆን
የሆነ ቅዳሜ
የሆነ ዉብ ሆቴል
ደግሞም አትረሺዉም. . .ፍጻሜ ምሳ ነዉ
ይኼ እንኳን ትዝ ይላል
እና. . .
እኔና አንቺ ብቻ
የተቀመጥንበት ወንበር ጠረጴዛዉ
ከዘጠኝ ወር ኋላ. . .
እዛዉ ቤት ዳግመኛ ተመልሼ ባየዉ
የሚገርምሽ ነገር
ጻፊዉን ባላዉቅም
#ፍቅር_እዚህ_ቦታ_ፈገግ_ብሎ_ነበር
የሚል ጽሁፍ ሰቅለዉ
ከዘጠኝ ወር ኋላ
አንድ ለብቻዬ ካንድ አንቺ ናፍቆት ጋር
ነበር ለምትይዉ ለሁለታችን ፍቅር
(ምስክር ሊሆኑን)
ያኔ ሁለታችን የጠጣነዉ ወይን
ከወይንም. . . Two Ocean
እኔ የጨለጥኩት
አንቺ ያጋመስሽዉ
እኛ ያስተረፍነዉ
እስከዛሬ ድረስ
ያተረፍነዉ ማዕድ. . .
ጠርሙስና ጽዋዉ
በክብር ተቀምጧል
ማንም ሳያነሳዉ. . .ያኔ እንደነበረዉ
(ታዲያ ምን ማለት ነዉ)
.
.
.
ፒያሳ አደባባይ
የወንዝ ዉሃ ሳቅሽ
ከቡና ጠረን ጋ
ከኔ መኖሪያ ቤት. . .
የምወደዉ ሸሚዝ ላይ
የሽቶ መአዛሽ
ከሴት ላቦትሽ ጋር
ደግሞም
እዚያ ዉብ ሆቴል ስር
ያስተረፍነዉ . . .
ማዕድ ጠርሙስና ጽዋ
አንጀት ከሚበላ
ከቆንጆ ጥቅስ ጋር
‘’#ፍቅር_እዚህ_ቦታ_ፈገግ_ብሎ_ነበር::’’
.
ነበርን እስካሁን
በመሆን እያየሽ
ሳቅሽ ፈሶ ሳያልቅ
ከምወደዉ ሸሚዝ
የሽቶ መዓዛሽ ዉብ ጠረኑ ሳይለቅ
ማዕድ ሳይነሳ ጽዋዉ ሳይታጠብ
ሦሥቱን ምስክሮች በዓይንሽ ፊት እያየሽ
(ታዲያ ለምንድን ነዉ)
ያሳለፍነዉ ሁሉ
#አሁን_ትዝታ_እንጂ .....
#ዉስጡ_ህይወት_የለም
ብለሽ ለመንደሩ
ላገሩ ማዉራትሽ
እዉነት ለምንድን ነዉ?
.

@kinchebchabi @kinchebchabi
🌿❤️እንዴት አደርሽ🌿
Yohannes_Lawgaw ስለ እኔ @sleenee Yohannes Lawgaw sle enee
🌿ዛሬ ማለዳ በዛሬ ህይወት ሰላም በሆነች ንጋት.. እልፍ #ተስፋ ባለባት...🕊🌿ያንቺ እንደሆንኩ ነቅቻለሁ ♥️ እንዴት አደርሽ🌿
🌿#Morning_Queen #ጠዋት_ስትነቂ #ማለዳ #ፀሀይ
#ስጦታዬ #ፍቅር #ዕለተ_እሁድ

።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 t.me/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 t.me/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 t.me/sufafel 🦋🦋