#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጲያ
ንገሯት
ከጉያዋ አውጥታ
ረግጣው ስትሄድ ፣ ገፍታው የኔን ገላ
ትዝታ ደግፎ
በእንጉርጉሮ ዜማ ፣ ካቀናው በኋላ
ምናልባት አንድ ቀን
ትመጣ ይሆናል ፣ ወረቷ ሲላላ።
እናም የዚያን ጊዜ
ፍቅሯን ተከናንባ ፣ መውደዷን ተላብሳ
የመጣች እንደሆን ፣ በፀፀት ኮስሳ
(ንገሯት ለዛች ሴት)
ትዝታውን ጥሎ ፣ አንቺን የሚያነሳ
ሞኝ አይደለም በሏት ፣ ትሂድ ተመልሳ።
Mikiyas M Sheferaw
@kinchebchabi
@kinchebchabi
ንገሯት
ከጉያዋ አውጥታ
ረግጣው ስትሄድ ፣ ገፍታው የኔን ገላ
ትዝታ ደግፎ
በእንጉርጉሮ ዜማ ፣ ካቀናው በኋላ
ምናልባት አንድ ቀን
ትመጣ ይሆናል ፣ ወረቷ ሲላላ።
እናም የዚያን ጊዜ
ፍቅሯን ተከናንባ ፣ መውደዷን ተላብሳ
የመጣች እንደሆን ፣ በፀፀት ኮስሳ
(ንገሯት ለዛች ሴት)
ትዝታውን ጥሎ ፣ አንቺን የሚያነሳ
ሞኝ አይደለም በሏት ፣ ትሂድ ተመልሳ።
Mikiyas M Sheferaw
@kinchebchabi
@kinchebchabi
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጲያ
*ሴት*
የአዳም ፀጋ ንቃይ
የህይወት ጡዘት ስቃይ
የተፈጥሮ ህግጋት ቀንዲል
የአለም ኑረት ጠለል
ያለመኖር ስቃዥ ውጋት
የመኖር ቅኝት ፍካት
ሴት ማለት ........
የርህራሔ ጥጋት ቀለም
የበጎነት ምሳሌ ትልም
የመውደድ ደሴት ጥልም
በእንተ ፍቁረ ቅዥት
የኑረት ጅማሬ እንቅፋት
ሴት ልጅ ማለት ተስፋ
ሴት ልጅ ማለት ውድቀት
ሴት ልጅ ማለት ቅኔ
ሴት ልጅ ማለት ወረት
<<በናምሩድ>>
Join
@kinchebchabi
@kinchebchabi
*ሴት*
የአዳም ፀጋ ንቃይ
የህይወት ጡዘት ስቃይ
የተፈጥሮ ህግጋት ቀንዲል
የአለም ኑረት ጠለል
ያለመኖር ስቃዥ ውጋት
የመኖር ቅኝት ፍካት
ሴት ማለት ........
የርህራሔ ጥጋት ቀለም
የበጎነት ምሳሌ ትልም
የመውደድ ደሴት ጥልም
በእንተ ፍቁረ ቅዥት
የኑረት ጅማሬ እንቅፋት
ሴት ልጅ ማለት ተስፋ
ሴት ልጅ ማለት ውድቀት
ሴት ልጅ ማለት ቅኔ
ሴት ልጅ ማለት ወረት
<<በናምሩድ>>
Join
@kinchebchabi
@kinchebchabi
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጲያ
በሰለሞን ሳህለ
አንድ አፍቃሪ ወጣት
….የመጀመርያው ቀን….
ገና ስልኩን አንስቼ “ሄሎ” ከማለቴ
“ምን እንደጠየቀችኝ ታውቃለህ?” አለኝ
“ምን ጠየቀችህ?” አልኩት
“ደብዳቤ እንድፅፍላት”
“እና….?”
ስልኩን ዘጋው
እሱ አይደለም ስልኩን የዘጋው ቀልደኛው ቴሌ ነው….ምክንያቱም
ደግሞ ደወለልኝ
“ሄሎ”
“….ቀላል እፅፍላታለሁ እንደውም ስልክ ከመደወል ደብዳቤ
መፃፍ ይሻላል…ኔትወርኩ እንደዚህ እየተቆራረጠ ከእርሷ ጋርም
ከሚያቆራርጠኝ ደብዳቤ ብፅፍላት ነው የሚሻለው….ፖስታ
አገልግሎት ጉድ ፈላበት የኔን ደብዳቤ ብቻ ነው ሲያመላልስ
የሚከርመው….!”
….ሁለተኛው ቀን….
ደወልኩለት
“ፃፍክላት?”
“መፃፉንማ ፅፌያለሁ ግን ትንሽ ቅር ያለኝ ነገር አለ….እወድሻለሁ
ብቻ ነው ያልኳት”
“በቂ እኮ ነው ታድያ!” አልኩት
“ባክህ በቂ አይደለም እሷን መውደድ ማለት ለብ ባለ ውሃ ሻወር
እንደመውሰድ ያለ ቀለል ያለ ስሜት እንደሚሰጠኝ መንገር
አልቻልኩም……. እርሷን መውደድ ማለት የመውደድ ትልቅ
ምሳሌ መሆኑን መንገር አልቻልኩም….እርሷን መውድድ ማለት
በእንቅልፍና በመንቃት መካከል ላይ ያለውን ቅስበት በምርምር
እንደማግኘት እንደሆነ መንገር አልቻልኩም…..እርሷን መውደድ
ማለት ሕይወትን እጅግ አድርጎ መውደድ መሆኑን መንገር
አልቻልኩም…….እና ሌላ ነገር ላስብ እስኪ………” አለኝ በረዥሙ
እየተነፈሰ…..
…ሶስተኛ ቀን…
“…የሰሜኑ ድብ ስለሚባለው ኮከብ ታውቃለህ?”
ስለ ስነ-ከዋክብት ሲነሳ ደስ ይለኛልና “አዎን አውቃለሁ” አልኩት
“ስለ መሪ ኮከብስ?...ስለ አንበሳው ምስልስ?... ስለንጋት
አብሳሪዋ ኮከብስ?... ስለኦርዮንስ ታውቃለህ?”
በፍጥነት ነው የሚያወራውና የሚጠይቀው ስለ ስነ-ከዋክብት
ሲፃፍና ሲነበብ ብቻ ሳይሆን ሲወራም ደስ ይለኛልና
“እህ…ስለነሱ ከዋክብት ምን ልታወራኝ ፈልገህ ነው?”
“በሚልኪዋይ ጋላክሲ ውስጥ በፀሃይ ዙርያ የሚሽከረከሩ የፀሃይ
አሽከሮች ናቸው….” ሲለኝ ሳቅ አመለጠኝ
“ምን ያስቅሃል?” ቆጣ ብሏል….
“ምን ያስቅሃል? እንደውም ልንገርህ አይደል ፀሃይዋ ደግሞ እሷ
እራሷ ናት!!!”
ስልኩን ማን እንደዘጋው አላውቅም እሱ እኔ ውይም ደግሞ ያ
ቀልደኛው ….
…አራተኛ ቀን…
“ትናንትና ስልኩ ተዘጋ አይደል እንኳንም ተዘጋ” አለኝ ሄሎ ከማለቱ
በፊት
“ለምን?” እየገረመኝ
“እንዴ ምን ማለትህ ነው ስለ ስነ-ከዋክብት ሳወራህ የነበያቱን
ትንቢት ረስቸው ነበር እኮ ይቅርታ አድርግልኝ እና እርሷን ፀሃይ ናት
ያልኩህ የነበያቱን ትንቢት ረስቸው ስለነበር ነው”
“የትኛው ትንቢት?” አሁንም እየገረመኝ
“ስለ ትንቢቱ አልሰማህም እንዴ?” አዲስ ነገር ለማውራት እየጓጓ
“አረ….አልሰማሁም ስለየትኛው ትንቢት ነው የምታወራው?”
“በምስራቅ ስለሚነሳው ንጉሥ…ሕዝብ የወደደው አምላክ
የመረጠው ንጉሥ….እርሷ ናት የምትወልደው……………..!
ሀገርን አንድ አድርጎ የሚያጸናውን…..የሰላም አባት የተባለውን
ንጉሥ እርሷናት የምትወልደው……..!! ለተረሱትና ለተበደሉት
ፍትህን…ለታመሙትና ለደከሙት ብርታትን…..ለተጨቆኑትና
ለታሰሩት ነፃነትን የሚያጎናጽፈውን ንጉሥ እግዜር የመረጠውን
ንጉሥ…….እርሷ ናት የምትወልደው…….!!!” አለኝ አፍቃሪው
ወጣት እርግጠኝነት በተሞላበት ስሜት…..
እርግጠኝነቱንና ተስፋውን ማሳነስ ስላልፈለኩ “አሜን ይሁን!” ብዬ
ተቀበልኩትና ተሰነባበትን….
….አምስተኛ ቀን….
ደወልኩለት…………………….ከብዙ ጥሪ በኋላ አነሳው……..
“እህሳ ፃፍከው?” የኔ ጥያቄ ነበር
“አልጻፍኩትም……..” ቁርጥ ያለ መልስ ሆነብኝ
“ለምን አልጻፍከውም ወይንስ ሌላ የተሸለ ሃሳብ መጣልህ?”
“እውነቱን ልንገርህና አልጽፍላትም….ልጽፍላትም አይገባኝም!”
“ለምን ሲባል ?” …….ልናደድ አምሮኛል
“እንዴት በፀሃይ የተመሰለች ሴት…..እናም ደግሞ በምስራቅ
የሚነሳውን ያን እግዜር የመረጠውን ንጉሥ የምትወልድ ሴት
ደብዳቤ እንዴት ይፃፍላታል…..? ይሄ የአህዛቦች ሥራ ነው……….
እኔ የእርሷ አገልጋይ ለእርሷ ስል በድፍረት ጦር እሰብቅላት
ይሆናል እንጂ በድፍረት ጦማር አልጦምርላትም…..!”
ሲያወራ ስሜታዊ ሆኖ ነው
“እና ምን አሰብክ…..ማለቴ ምን ወሰንክ?”
“ያለችበት ቦታ ሄጄ እጅ እነሳለሁ!!”
“በቃ.?” ግራ እየገባኝ
“በቃ ይሄው ነው!!!” በልበ ሙሉነት
“ይቅናህ!” አልኩት በፍቅሩ እና በእምነቱ እየቀናሁ
“አሜን ወዳጄ!!!” የመጨረሻ ቃሉ ነበር
…ስድስተኛ ቀን……
ስልኩን አያነሳም
…ሰባተኛ ቀን….
ስልኩ አይሰራም
(ንጉሡን ለምትወልደው ሴት እጅ ሊነሳ ሄዶ ይሆናል )
ይቅናው ወዳጄን…..!!!)

"መከራና ጉም እያደር ይቀላል"
ተራምደን ደራሽ ለመሆን ጀምሮ ጨራሽ መሆን ያሻናል!
እየለመለምን የምንረግፍ ሳይሆን እያበብን ፍሬ የምንሰጥ ዘሮች
እንሁን። ራሳችንን የራሳችን አረም ከማድረግ እናቅብ፡፡
የጣፈጠውን ለማጣጣም የመረረውን ቀምሶ ማለፍ አያስጠላን፡፡
ጠግቦ አዳሪ ለመሆን ለፍቶ ኗሪ መሆንን ግዳችን እናድርገው፡፡
አርብቶ አደር እንጂ አውርቶ አደር ጠግቦ አያድርም፡፡ በመሆንም
የሥንፍና ካባችንን ጥለን የሥራ ቱታችንን እንሸክፍ፡፡ የወደድነውን
እንዳናጣ ከሕሊናችን ተቃቅረን ሳይሆን ከሕሊናችን ተመካክረን
እንደር፡፡ በኩራት ለማምሸት በትጋት እንዋል፡፡ ያማረ ነገን
ለመፍጠር የተዋበ ዛሬን መኖር እንቻል። ገቢ በማንኪያ ወጪ
በማቡኪያ በሆነበት ዘመን ብዙ መሥራት እንጂ ብዙ ማውራት
አናብዛ፡፡ ተግባራችን ካልዘመነ አኗኗራችን አይሰለጥንም፡፡
በከፈለኝ ዘለለው (አሞዛ)

Yohannes T Degu
"የጥበብ መጀመሪያ ደነዝን 'ደደብ' ማለት ነው፡፡" እንዲህ ማውራት ይሻላል፡፡ አንደባበቅ፡፡ መደባበቁ አያዋጣም፡፡ አይናችን ይገለጥ፡፡ ጠቢብ መሆን አለብን፡፡ ዛሬ አልሰክስም፥ አልጠነቀቅም፥ አፈርጥልሃለሁ፡፡ ለእድፍህ ቅቤ የለኝም፡፡ ምርጫው ያንተ ነው፡፡ እድፍህን በልብስ መሸፈን፥ ወይም መታጠብ፡፡ ስትጨርስ ትፀዳለህ፡፡ ፅዳት እንደምትመርጥ ይጠበቃል፡፡
፩ . . . ሃሳብ
በኢትዮጵያ ሶስት ነገር አታገኝም፡፡ ሁለቱን እነግርሃለሁ፡፡ ምግብና ሃሳብ የለም፡፡ ስውር ነው፡፡ ሶስተኛውን አታስብ፡፡ ነብር ሳር እንዲግጥ መሞከር ነው፡፡ አታገኘውም፡፡ ምንድነው አትበለኝ፡፡ አልነግርህም፡፡ ጭንቄህ የተጋገረ ለምዷል፡፡ እየጠበከኝ ይሆናል፡፡ አትድከም፡፡ ስለሱ ማውራት አልፈልግም፡፡ ግዜውን ልጠቀመው፡፡
የሃበሻ ጭንቄ ሃሳብ ይፈራል፡፡ መቧደን፥ መንጋጋት፥ ማበር ይቀለዋል፡፡ ስነ - ልቦናው ፈሪ፥ ውሸታም፥ አስመሳይ ነው፡፡ አዲስ ሃሳብ ከምትነግረው ከሰውነቱ ስጋ ብትቆረጥ ይቀለዋል፡፡ ዝቅ ያለ መስሎ ክብሩን ሲጠብቅ ታገኘዋለህ፡፡ ከሃሳብ፥ ከእውቀት፥ ከስራ - ዝሪፊያ፥ ጦርነት፥ ሃሜት ይቀለዋል፡፡ አንድ ጭዌ ትዝ አለኝ፡፡ ተከተል፡፡
ፕሌቶ ደገሰ፡፡ ወዳጆቹን ጠራ፡፡ ዲዮጋን በወዳጁ ተጋበዘ፡፡ ፕሌቶ ቤት ሄደ፡፡ የፕሌቶ ቤት ምርጥ ነች፡፡ ምንጣፉ ውብ ነው፡፡ ዲዮጋን ደረሰ፥ ገባ፡፡ እንደገባ ቆመ፡፡ ምንጣፉ ላይ ቆሻሻውን በተነ፡፡ በእግሩ ረጋገጠ፡፡ ወደ ፕሌቶ ዞረ - "ራሱን በጌጥ ያስዋበውን፥ ፕሌቶን ናኩት" አለ፡፡ ፕሌቶ ወደ ዲዮጋን እያየ "ክብርን እየናቅክ፥ ራስህን ስታከብር አየሁ" አለ፡፡ የሐበሻ ንፁህ ቀለም ትመስላለች፡፡ ምናልባት በሆዱ ኢልማ ሃDhራው ብሎታል፡፡
፪ . . . ህዝብ
ፒፓው መሐይም ነው፡፡ እደግምልሃለሁ፡፡ እውቀት፥ ሃሳብ፥ ምክንያት የለውም፡፡ ከሱ ያልተሻለ ሰው ያስተምራል፥ ይመራል፥ ይናገራል፡፡ ቦርጭ፥ ልብስ፥ እድሜ፥ ወረቀት መለኪያ ነው፡፡ ድልብ ደደብ በቦርጭ ተከልሎ ይመጣል፡፡ ቢጤውን ይሰበስባል፥ መሐይሙን ይሰክሳል፥ ይነዳል፡፡
ጃዋር፥ ደሳለኝ ጫኔ፥ ደ/ፅዮን፥ አባዱላ፥ አየለ ጫሚሶ፥ ዳውድ ኢብሳ፥ በቀለ ገርባ፥ ክርስቲያን ታደለ፥ ሄኖክ የሺጥላ፥ ገዱ ወዘተ ምናምን ደነዝ ናቸው፡፡ የዳጃሚስት መንጋ ነው፡፡ ሃሳብ፥ እውቀት፥ ራዕይ የለውም፡፡ ለመንጋው ይመጥናል፡፡ እኩያው ነው፡፡ መረዳቱ ከመንጋው አይርቅም፡፡ መንጋው ይወደዋል፡፡ ለመንጋው ይጣፍጣል፡፡ አይጎረብጠውም፡፡ የመንጋው አቻ ነው፡፡ እኩል ለእኩል ናቸው፡፡ መሪ ከተመሪ ይቀድማል፡፡ ይሄ አይነገርህም፡፡ ባፋንኩሎ !
ፒፓው ነጻነት፥ እውቀት፥ ድፍረት፥ ፈጠራ እንዲኖረው አይፈለግም፡፡ እንደታወረ መጋለብ ነው፡፡ ተመሪ በቢጤው ይመራል፡፡ መሪ አይጨነቅም፥ አያስብም፥ አይመረምርም፡፡ የያዛትን ያመነዥጋል፡፡ ያመሰኳል፡፡ አዲሰ አይጨምርም፡፡ ለመንጋው የተመቸ ነው፡፡ ሃሳብ፥ እውቀት፥ ምክንያት አይፈልግም፡፡ ወጪ ቆጣቢ ነው፡፡ ሚዲያ፥ ሰሚ፥ አስለቃሻ ካገኘ መበጥረቅ ነው፡፡ እየዬዬዬ ብቻ - ራዕይ አልባ ጩኸት፡፡
እውነቱን ልንገርህ፡፡ ቁስልህን እያደማ ነው፡፡ አይጠቅምህም፡፡ የሚያስፈልገህ እውነቱን የሚናገር ነው፡፡ ደሃ፥ ችጋራም፥ መሐይም እንደሆንክ፤ ወባ፥ ኤድስ፥ ረሃብ እንደሚጨርስህ፤ ትራኮማ፥ ግላኮማ፥ አተት እንደሚጠርግህ፤ ቤት፥ ልብስ፥ ምግብ እንደሌለህ፤ 40 ዓመት ስትሳቀቅ እንደምትኖር፤ ዓለም ላይ ከዓይጥ የበለጠ ድንግጡ፥ ለማኝ እንደሆንክ፥ ነፍስህ ከትል እንደማይበልጥ፤ ጥቅምህ ለቁጥር እንደሆነ፥ የተጸዳዳኽበት ዛፍ ስር እንደምትቀበር አይነገርህም፡፡
"ኦሮሞ ጀግና ነው፥ አማራ አይበገርም፥ ትግሬ ፅኑ ነው፥ ኣፋር ሃቅ አይነካም" ወዘተ ይልሃል፡፡ "እከካም" በለው፡፡ እያሰባህ ነው፡፡ ሊሸጥ ያሰበው ነገር አለ፡፡ እንዳትሰማው፡፡ እውነቱን ተቀበል፡፡ የህዝብ ጀግና፥ ፈሪ፥ ጠቢብ፥ አዋቂ የለም፡፡ ህዝብ የሰው ስብስብ ነው፡፡ ሰው ክፉና ደግ ነው፡፡ ብሄር ቅዠት ነው፡፡ አለቀ፡፡ አያንስም፥ አይጨምርም፡፡
፫ . . . ቄሮ፥ ፋኖ፥ ዘርማ፥ ኤጄቶ . . .
ጀግና አይደለም፡፡ ለውጥ አላመጣም፡፡ ተታለሃል፡፡ አንተ መንጋ ብቻ ነህ፡፡ አጀንዳ ይጋግራሉ፡፡ ኪስህ ይከታሉ፡፡ ይዘህ ትሮጣለህ፡፡ የታዘዝከውን ትፈፅማለህ፡፡ እነሱ ይሸቅላሉ፡፡ ለሌላ ባርነት እያሰቡህ ነው፡፡ መንጋነት በፊርማ አፅድቀኻል፡፡ ቂጥህን በካልቾ እያልክ፥ አጀንዳ ኪስህ ከተው፥ ቀን መርጠው፥ ይልኩኻል፡፡ እንደቁራ ትጮሃለህ፡፡
ትግል፥ ለውጥ፥ አቢዮት እንዲህ አይደለም፡፡ ትግል የሰውን ልጅ ያቅፋል፡፡ ለውጥ የአስተሳሰብ፥ የአኗኗር፥ የጣዕም ነው፡፡ አቢዮት ሁሉን ዓቀፍ ይመስላል፡፡ የአንተ መሪ አጠገብህ ካለው ጎረምሳ አይሻልም፡፡ የሃሳብ ልዕልና የለውም፡፡ ጠላት ፈልጎ ያናጭሃል፡፡ ትናጫለህ፡፡ ጀግና ጀግና ይሰራሃል፡፡ ባንተ ውስጥ ጀግንነት የለም፡፡ ተስፋ መቁረጥ እንዳየሁ ግን አልደብቅህም፡፡ ያልታጠቀ ላይ ዱላ፥ ክላሽ፥ ገጀራ መምዘዝ የፈሪ ባህሪ ነው፡፡ ገዳይ የምትጋፈጥ ተስፋ ስትቆርጥ ነው፡፡
የፈራና ተስፋ የቆረጠ መንጋ መንዳት ቀላል ነው፡፡ መንጃ ፍቃድ አይጠይቅም፡፡ መሪዎችህ ያረጉት ያንን ነው፡፡ ተስፋ፥ ሃይል፥ እውቀት፥ ድፍረት፥ ሰውነት አልሰጡህም፡፡ በጎደለህ ነገዱበት፡፡ ሰው የሚያረግ መሪ አላገኘህም፡፡ እሱን ጠብቅ፡፡ የሚመራህ እኩያህ ነው፡፡ አዲስ ነገር አይሰጥህም፡፡ ለራሱም የለው፡፡ የሱ ማርኬት አንተ ነህ፡፡
ሶስት፥ አራት ቋንቋ ያወራል፡፡ አንተን በአንድ ያጥራል፡፡ ደነዝ ሆነህ፥ በደደብ ሃገር እየኖርክ፥ ጭንቄህን ሳትቀየር ልጅ አትውልድ፡፡ በደነዝ አባት የሚያድግ ልጅ፥ አባቱን ይመስላል፡፡ የነገርኩህ እውነት ነው፡፡ ቢመርህም ዋጣው፡፡ በኢትዮጵያ ምድር በእርዳታ ስንዴ፥ በእርዳታ ማዳበሪያ፥ ዓለት ታቅፎ እየተጸዳዳ፥ እጁን ሳይታጠብ፥ በረባሶ ብርቅ ሆኖበት የሚኖር ፒፓ ነው፡፡ ሃብታም፥ ጀግና፥ ኩሩ፥ ፅኑ፥ ቸር የሚሉህ ሊቸበችቡህ ነው፡፡ እመነኝ - ያንተ ነፍስ ግድግዳ ላይ ካለ ሸረሪት አይልም፡፡ አያውቅህም፡፡

በመምህር ዘበና ለማ
"አይ ሰው መሆን! በሬውን አወፍረን በልተን፣በግና ፍየሉን አደልበን ስጋውን ቢሻን ቀቅለን ቢሻን ጠፍተን አጥንቱን ግጠን፤ መጥኔውን ሳይቀር መጥጠን፤ጥጃውን ከእናቱ ጡት ነጥለን፤ወተቱን ቀምተን ጠጥተን፤ትንሿ ዶሮ እንኳን ሳትቀር እንቁላሉዋን ከስክሰን፤አጥንቷን አድቅቀን፤ ስጋዎን እንክት አድርገን እየበላን ትንሽ እንኳ አለማዘናችን አሳዘነኝ።"

አንድ ላይ ስንሄድ
"እሷን ያየ ወዶ"
እኔን ሲያይ ተናዶ
"እሷን ያየ አፍቅሮ"
ለኔ ዱላ አዙሮ
እሷን ያየ ለብሶ
በ'ኔ ሆዱ ጭሶ
…አንድ ላይ ስንሄድ
እሷን ያያት ፈገግ
እኔን ያየ ጨፍገግ
ለ'ሷ መንገድ ለቀቅ
ለኔ እጁን ጠበቅ
ለ'ሷ ጥርስ በጥርስ
ለ'ኔ ኩስትር ኩምስስ
አንድ ላይ ስንሄድ
እሷን ሚለማመጥ
እኔን ገልመጥመጥ…
እንደው ባጠቃላይ
አንድ ላይ ስንታይ
"እሷ ከፊት ሁና፤ ለ'ሷ የሰገደ
እኔን ከኋላ ሲያይ፤
ጨርቁን ጥሎ አበደ"
እንደው ባጠቃላይ
አንድላይ ስንታይ
ባሏ መስያቸው
ወንዶቹ ከፋቸው
ይብላኝ ለ'ነሱ እንጂ
ለ'ኔስ እህቴ ናት
ያገባኋት ቀን ነው
ሚስቴ ነሽ የምላት።
፰-፮-፳፻፲፩
አብርሃም የሙሉ ልጅ(@yemulu_lij)
@kinchebchabi @kinchebchabi
አንድ ላይ ስንሄድ
"እሷን ያየ ወዶ"
እኔን ሲያይ ተናዶ
"እሷን ያየ አፍቅሮ"
ለኔ ዱላ አዙሮ
እሷን ያየ ለብሶ
በ'ኔ ሆዱ ጭሶ
…አንድ ላይ ስንሄድ
እሷን ያያት ፈገግ
እኔን ያየ ጨፍገግ
ለ'ሷ መንገድ ለቀቅ
ለኔ እጁን ጠበቅ
ለ'ሷ ጥርስ በጥርስ
ለ'ኔ ኩስትር ኩምስስ
አንድ ላይ ስንሄድ
እሷን ሚለማመጥ
እኔን ገልመጥመጥ…
እንደው ባጠቃላይ
አንድ ላይ ስንታይ
"እሷ ከፊት ሁና፤ ለ'ሷ የሰገደ
እኔን ከኋላ ሲያይ፤
ጨርቁን ጥሎ አበደ"
እንደው ባጠቃላይ
አንድላይ ስንታይ
ባሏ መስያቸው
ወንዶቹ ከፋቸው
ይብላኝ ለ'ነሱ እንጂ
ለ'ኔስ እህቴ ናት
ያገባኋት ቀን ነው
ሚስቴ ነሽ የምላት።
፰-፮-፳፻፲፩
አብርሃም የሙሉ ልጅ(@yemulu_lij)
@kinchebchabi @kinchebchabi
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጲያ
ሶት የወለደው ሰሞነኛ ጸሎት
።
።
መንግስታችን ሆይ ፣ በቤተ መንግስት የምትኖር
እንደምድር የምትዞር
ሀገርህ ውስት ችግር ሲኖር ፣ ቀድመህ ከሀገር ምትሰወር
ስምህ ዳግማዊ ሙሴ ፣ መንግስትህ የመወየን
ከእባብ እንቁላል ተፈልፍለህ ፣ እርግብ መስለህ ምትታየን
ፈቃድህ በመደመር እንደሆነ ፣ እንዲሁም በመቀነስ ትሁን
የእለት ገጀራ በቅቶናል
ለለት እንጀራ አታስብ ፣ የእለት ፍርድህን ስጥ አሁን
ከዘር ከመድሎ የነጣ
ሰው የሚነቅልን እየማርህ ፣ ችግኝ ነቃዩን አትቅጣ
ሀገር ውስጥ ብጥብጥ ሲኖር ፣ጠብቀህ ከሀገር አትውጣ
የበደሉንን እንድንረሳ ፣ በደሌ ቢራ ጋብዘን
እስከመቼ እንቃጠል ፣ እርቅ ሳይኖር አረቄ አዘን
አቤቱ ወደፈተና እንዳንገባ ፣ ትምህርት ሚኒስቴርን ዝጋ
አስጠኚ አስተኚ ይሁን ፣ ይቀነስ ያልጋ ቤት ዋጋ
መንግስት የአንተ ናትና
ሀይል ስልጣን ሙስና
በህዝብ እንባ በሸነና
ካገራችን ላይ ይጥፋ
ከቅኔ በቀር በምድሪቱ ፣ አይታይባት ዘረፋ
ስጋ ለብሶ ያሳየን ፣ ቃል የሆነ ያንተ ተስፋ
ለዘልአለሙ አሜን
ስበላ የኖርኩ አፈር ድሜን
ባታውቀውም አንተ ስሜን
እኔ ስምህን አውቃለሁ
ብጠራጠርም አምንሀለሁ።
።።።።
(በላይ በቀለ ወያ)
@kinchebchabi
@kinchebchabi
ሶት የወለደው ሰሞነኛ ጸሎት
።
።
መንግስታችን ሆይ ፣ በቤተ መንግስት የምትኖር
እንደምድር የምትዞር
ሀገርህ ውስት ችግር ሲኖር ፣ ቀድመህ ከሀገር ምትሰወር
ስምህ ዳግማዊ ሙሴ ፣ መንግስትህ የመወየን
ከእባብ እንቁላል ተፈልፍለህ ፣ እርግብ መስለህ ምትታየን
ፈቃድህ በመደመር እንደሆነ ፣ እንዲሁም በመቀነስ ትሁን
የእለት ገጀራ በቅቶናል
ለለት እንጀራ አታስብ ፣ የእለት ፍርድህን ስጥ አሁን
ከዘር ከመድሎ የነጣ
ሰው የሚነቅልን እየማርህ ፣ ችግኝ ነቃዩን አትቅጣ
ሀገር ውስጥ ብጥብጥ ሲኖር ፣ጠብቀህ ከሀገር አትውጣ
የበደሉንን እንድንረሳ ፣ በደሌ ቢራ ጋብዘን
እስከመቼ እንቃጠል ፣ እርቅ ሳይኖር አረቄ አዘን
አቤቱ ወደፈተና እንዳንገባ ፣ ትምህርት ሚኒስቴርን ዝጋ
አስጠኚ አስተኚ ይሁን ፣ ይቀነስ ያልጋ ቤት ዋጋ
መንግስት የአንተ ናትና
ሀይል ስልጣን ሙስና
በህዝብ እንባ በሸነና
ካገራችን ላይ ይጥፋ
ከቅኔ በቀር በምድሪቱ ፣ አይታይባት ዘረፋ
ስጋ ለብሶ ያሳየን ፣ ቃል የሆነ ያንተ ተስፋ
ለዘልአለሙ አሜን
ስበላ የኖርኩ አፈር ድሜን
ባታውቀውም አንተ ስሜን
እኔ ስምህን አውቃለሁ
ብጠራጠርም አምንሀለሁ።
።።።።
(በላይ በቀለ ወያ)
@kinchebchabi
@kinchebchabi
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጲያ
ባል የማይረጋልሽ ሆኖብሽ ስራይ
የአምና ፍቅረኛሽ ለከርሞ አይታይ
ከነግልሙትናሽ 40 ዓመት ሰቀቀን
40 ዓመት ስቃይ
እምዬ ኢትዮጲያ አንቺ ሀገሬ ሆይ
አንቺንም እንደ ሰው
መጋኛ ዓይነ ጥላ ያጠቃሻል ወይ?
አበባው መላኩ
@kinchebchabi
@kinchebchabi
ባል የማይረጋልሽ ሆኖብሽ ስራይ
የአምና ፍቅረኛሽ ለከርሞ አይታይ
ከነግልሙትናሽ 40 ዓመት ሰቀቀን
40 ዓመት ስቃይ
እምዬ ኢትዮጲያ አንቺ ሀገሬ ሆይ
አንቺንም እንደ ሰው
መጋኛ ዓይነ ጥላ ያጠቃሻል ወይ?
አበባው መላኩ
@kinchebchabi
@kinchebchabi
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጲያ
ታክሲ ውስጥ ገብታ ልትቀመጥ ስትል ከወደኋላ ድምፅ ሰማሁ
"ጡ..ጥ"
ከሷ ፊት ስለተቀመጥኩ በመገረም ዞር ስል በሀፍረት ጥሬ አክላ አገኛታለሁ ያልኳት ባለድምፅ እኔ ላይ አፍጣ
"ምነው? ስምህ ነው እንዴ?"
"ስም ያለው ሞኝ ነው ደገመቸኝ።"
@kinchebchabi
@kinchebchabi
ታክሲ ውስጥ ገብታ ልትቀመጥ ስትል ከወደኋላ ድምፅ ሰማሁ
"ጡ..ጥ"
ከሷ ፊት ስለተቀመጥኩ በመገረም ዞር ስል በሀፍረት ጥሬ አክላ አገኛታለሁ ያልኳት ባለድምፅ እኔ ላይ አፍጣ
"ምነው? ስምህ ነው እንዴ?"
"ስም ያለው ሞኝ ነው ደገመቸኝ።"
@kinchebchabi
@kinchebchabi